No summary available.
ሰኔ 2 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ መንገድች ባለስልጣን - ነ/ፈጅ ቀረበ።
ተጠሪ፡- ተመኘሁ እንደሻው - አልቀረበም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በመኪና አደጋ ደረሰ የተባለውን ጉዲት መሰረት በማድረግ የተጠየቀውን የካሣ ክፍያ ጥያቄ /ክርክር/ የሚመለከት ነው። ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው በአመልካች ሹፋር ሲሽከረከር በነበረው መኪናው ተሳፍሬ ስጓዝ በነበረበት ጊዜ መኪናው በመገልበጡ በእግሬ ላይ ጉዲት ደርሶአል። ስለዚህ ካሣ ይከፍለኝ ዘንድ ይወሰንልኝ በማለት ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ መኪናው ለመንግስት ሥራ የተሰማራ እንጂ ሰዎችን ለማጓጓዝ የተዘጋጀ የንግድ መኪና አይደለም። ከሣሽ በመኪናው ላይ የተሳፈረው ያለአግባብ እና ለከሣሽ ጥቅም በማይሰጥ ሁኔታ ስለሆነ በሕግ ረገድ ኃላፉነት የለብኝም በማለት የተከራከረ ሲሆን፣ ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም አመልካች ለደረሰው ጉዲት ሃላፉነት አለበት በማለት ካሣ እንዱከፍል ወስኖአል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔውን አፅንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ሰኔ 9 ቀን 2000 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው በተጠሪው ላይ ለደረሰው ጉዲት አመልካች ኃላፉ ነው የተባለበትን አግባብ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2089(1) አንፃር ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው ሉመረመር እና ትርጉም ሉሰጠው የተፈለገው ሕግ የፍ/ብ/ሕግ ቁ 2089(1) የሚገኘው ከውል ውጪ ስለሚደርስ አላፉነትና ያለአግባብ ስለመበልፀግ በሚለው በፍትሐብሕር ሕጉ በአንቀጽ 13 ሥር ነው። ተጠሪ አመልካችን የከሰሰውም ከውል ውጪ ደረሰ የሚለውን ኃላፉነት መሰረት በማድረግ ነው። በስር ፍ/ቤቶች በተደረገው ክርክር በፍሬ ነገር ረገድ እንደተረጋገጠው ተጠሪ የተባለውን ጉዲት የደረሰበት በአመልካች መኪና በመገጨቱ ሳይሆን፣ በመኪናው ላይ ተሳፍሮ ሲሄድ መኪናው በመገልበጡ ምክንያት ነው። በእርግጥ መኪናው የአመልካች ንብረት ነው።
ሆኖም ለመንግስት ሥራ የተሰማራ እንጂ ገንዘብ በማስከፈል ሰዎችን የሚያጓጉዝ የንግድ መኪና አይደለም። ተጠሪ በመኪናው ስለመሳፈሩ እንኳን አመልካች አያውቅም። ተጠሪን በማሳፈር ያገኘው ጥቅምም የለም። በፍሬ ነገር ረገድ እነዚህን ሁኔታዎች ከተረጋገጡ ቀጥል መታየት ያለበት አመልካች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ የሚሆንበት የሕግ አግባብ አለ ወይስ የለም የሚለው ነው።
በፍ/ብ/ሕግ ቁ 2081(1) እንደተደነገገው የመኪናው ባለቤት መኪናው በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው ጉዲት ኃላፉ የሚሆንበት አግባብ አለ። ይህ እንግዱህ በአጠቃላይ የተቀመጠ የኃላፉነት መርህ ሲሆን፣ በቁጥር 2089 ደግሞ ልዩ ሁኔታ ማለትም የመኪናው ባለቤት ኃላፉ የማይሆንበትን ሁኔታ ተደንግጎአል። ከድንጋጌው ርእስ መገንዘብ እንደሚቻለው ጉዲቱ የደረሰው ጥቅም በላለው ግንኙነት ጊዜ ሲሆን፣ የመኪናው ወይም ጉዲቱን ያደረሰው ንብረት ባለቤት ኃላፉነት አይኖርበትም። ከላይ እንዲመለከትነው ተጠሪ በአመልካች መኪና የተገለገለው ለአመልካች ጥቅም በማያስገኝ ሁኔታ ነው።
ከሁለ በላይ ደግሞ አመልካች በዚህ ረገድ ጥፊት ፈጽሞአል አልተባለም። በመሆኑም አመልካች ኃላፉ የሚሆንበት የሕግ አግባብ የለም። የስር ፍ/ቤቶችም በዚህ አግባብ ሕጉን ባለመተርጏማቸው የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ብ/ክ/መ የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ህዲር 12 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ሚያዝያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በተጠሪ ላይ ደረሰ ለተባለው ጉዲት ኃላፉነት የለበትም ብለናል። ስለዚህም በሥር ፍ/ቤቶች የተወሰነውን ካሣ አይከፍልም በማለት ወስነናል።
ወጪና ኪሣራ በሚመለከት ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.