No summary available.
ሰ/መ/ቁ. 317ዐ4 ጥር 29 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ አሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አማረ መጃ - ቀርበዋል ተጠሪ፡- የድሬዲዋ ለጋር ጉምሩክ - ነ/ፈጅ አቶ ታደሰ ጎለንዳ ቀርበዋል ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል።
ይህ የሰበር ክርክር ላቀርብ የቻለው አመልካች ሐምል ዐ2 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታቸው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግንቦት 1ዐ ቀን 1999 ዓ.ም በፍ/ይ/መ/ቁ. 24665 የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይሻርልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የድሬዲዋ ምድብ ችልት ሲሆን የአሁን አመልካች ከሣሽ የአሁኑ ተጠሪ ደግሞ ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። ስር ከሣሹ ሐምል 21 ቀን 1997 ዓ.ም የተፃፈ ክስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም የሰላዲ ቁጥሯ 3-ዐ5884 የሆነች ኢሮቶዮታ መኪናዬ ኮንትሮባንድ ጭናለች በሚል ምክንያት ታህሣሥ ዐ9 ቀን 1996 ዓ.ም ተከሣሹ በድሬዲዋ ከተማ በቁጥጥር ስር አውሎት ስትፈተሽ አንድ ቦንዲና 1ዐ ሜትር ብትን የመጋረጃ ጨርቅ ጭና ስለተገኘች መኪናዋ ልትለቀቅልኝ ባለመቻሎ ባቀረብኩት አቤቱታ መነሻነት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን በየደረጃው ያለት ኃላፉዎች ለተያዘው ዕቃ ሉከፈል የሚገባው 36.83 ብር የጉምሩክ ቀረጥ ተመን ተከፍል መኪናዋ እንዱለቅ በተደጋጋሚ ደብዲቤ ለተከሣሹ ቢጽፍለትም ሉለቅልኝ አልቻለም፤በመሆኑም ከመኪናዋ አገኝ የነበረው በቀን ብር 1ዐዐዐ /አንድ ሺህ ብር/ ሂሣብ ሆኖ ከታህሣሥ ዐ9 ቀን 1996 ዓ.ም እስከ ሰኔ 16 ቀን 1997 ዓ.ም ድረስ ያለውን የተቋረጠ ገቢ ብር 6ዐ8,000 /ስድስት መቶ ስምንት ሺህ ብር/ ከነወለደ ይከፈለኝ የሚል ነው።
ስር ተከሣሹ በ23/ዐ2/1998 ዓ.ም በተፃፈ መልሱ መኪናው መስከረም ዐ4 ቀን 1998 ዓ.ም ተለቋል፤ መኪናዋን የያዝኩት በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 ዓንቀጽ 6 በተሰጠኝ ስልጣን መሰረት ነው። በመኪናዋ ከተጫነው 19ዐ ጣቃ ጨርቅ 1ዐ ሜትር የመጋረጃ ጨርቅ አደባልቆ በራሱ እየነዲ ነው በቁጥጥር ስር የዋለችው፤ የመጨረሻ ውሣኔ እስኪያገኝ ድረስ መኪናዋን በቁጥጥር ስር አውል ማቆየት ሕግ ይፈቅድልኛል፤ በተለይም የጉምሩክ ባለሥልጣን ባወጣው መመሪያ ሲያሽከረክር የተገኘው የመኪናው ባለቤት ከሆነ የመጨረሻ የፍ/ቤት ውሣኔ ይጠብቃል ይላል፤ ስለሆነም መኪናው በሕግ አግባብ የተያዘ ነው ብሎል።
የስር ፍ/ቤቱም በመ/ቁ. ዐ1735 መጋቢት 2ዐ ቀን 1998 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ተከሣሹ መኪናዋን እንዱለቅ በተደጋጋሚ ከበላይ የመዋቅሩ አካላት ደብዲቤ በተደጋጋሚ እየተፃፈለት እምቢተኛ ሆኖ ከሣሽን ለኪሣራ የዲረገ በመሆኑ ከ11/ዐ6/96 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምል 21 ቀን 1997 ዓ.ም ድረስ ያለውን የመኪናዋን የተቋረጠ ገቢ ከሣሹ ለመንግሥት ሪፕርት ባደረጉት ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ሂሣብ ብር 36,111.11 /ሰላሣ ስድስት ሺህ አንድ መቶ አስራ አንድ ብር ከአስራ አንድ ሣንቲም/ ሉከፍላቸው ይገባል ብሎል።
ክርክሩ በይግባኝ ወደ ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍ/ቤቱ በፍ/ይ/መ/ቁ. 24665 ግንቦት 1ዐ/1999 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ አዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 ዓንቀጽ 6 እና 58 መሰረት ጉዲዩ የመጨረሻ እልባት እስከሚያገኝ ድረስ ኮንትሮባንድ ጭኖ የተያዘን መኪና ይ/ባይ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ የማቆየት ስልጣን ስላለው ካሣ ክፈል ልባል አይገባም በማለት ከላይ የተጠቀሰውን የከፍተኛ ፍ/ቤቱ ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/መሰረት ሽሮታል።
ከላይ የተጠቀሰውን የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ይግባኝ ችልት ውሣኔ በመቃወም አመልካች ሐምል ዐ2 ቀን 1999 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ወደዚህ ሰበር ችልት ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም መኪናዋ በክሱ የተመለከተውን ሕጋዊ ያልሆነ እቃ ጭና የተያዘችው የመኪናው ባለቤት የሆንኩት እያሽከረከርኩ እያለሁ አይደለም፤ ላላ ሹፋር ነበር ሲያሽከረክራት የነበረው፤ ሕጋዊ ያልሆነ ወይም ኮንትሮባንድ ነው የሚባል እቃ የተጫነበት መኪና ተይዞ እንዱቆም የሚደረገው አሽከርካሪው የመኪናው ባለንብረት ሲሆን ነው፤ ለዚህም የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን በቁጥር 1ዐ/መ352/2ዐ1/18/123 በ18/ዐ8/1996 ዓ.ም ግልጽ መመሪያ ያስተላለፈበት ነው፤ መኪናው እንዱለቅ ተደጋጋሚ ትእዛዝ ተጽፍለት እያለ ተጠሪ መኪናዋ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ገቢዬ አላግባብ እንዱቋረጥ አድርጓል፤ይሁን እና ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ከዚህ ነጥብ አኳያ እንደማጤን ተጠሪው በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 ዓንቀጽ 6 እና 58 መሰረት የመኪናዋን በቁጥጥር ስር የማዋልና ችግሩ እልባት እስኪያገኝ ድረስ በቁጥጥር ስር አድርጎ ማቆየት ይችላል ብል ፍርድ መሰጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ሉሻርልኝ ይገባል የሚል ነው።
No topics extracted.
ተጠሪም ጥቅምት 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም አመልካች መኪናው በልላ ሹፋር ይሽከረከር ነበር ከማለት ውጭ የዛ ሹፋር ማንነት በስር ፍ/ቤትም ሆነ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አልጠቀሱም መኪናው ሲያሽከረክሩ የነበሩት ራሣቸው አመልካች ናቸው፤ ኮንትሮባንድ ጭኖ የተገኘን መኪና ችግሩ እልባት እስኪያገኝ ድረስ በቁጥጥር ስር አድርጌ ማቆየት እንደምችል አዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 ዓንቀጽ 6/5/፣ 58/1/ለ/፣61 እና 78 ይፈቅድልኛል፤
መኪናዋ ኮንትሮባንድ ጭና መገኘቷ አያከራክርም፤ ስለሆነም የጠቅላይ ፍ/ቤት የፈፀመው የሕግ ስህተት ስለላለ ፍርደ ይጽናልኝ የሚል ነው።
የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጥ ከላይ እየተገለፀ እንደመጣው ሆኖ ይህ ፍርድ ቤትም ተጠሪው የአመልካችን መኪና ይዞ በማቆየቱ የተቋረጠ ገቢ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም? የሚል መሰረታዊ ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክር አመጣጥ መረዲት የሚቻለው የአመልካቹ መኪና በሕጋዊ መንገድ ጭናው ከነበር 19ዐ ጣቃ ጨርቅ ውስጥ አንድ ቦንዲና 1ዐ ሜትር ብትን የመጋረጃ ጨርቅ ሕግን ባልተከተለ መንገድ ተደብቆ እንደተገኘና በዚህ ምክንያም መኪናዋ በተጠሪ በቁጥጥር ስር እንደዋለች ነው በወቅቱ መኪናዋ በአመልካች ሣይሆን በልላ ሾፋር ትሽከረከር እንደነበር ነው። በግራና ቀኙ ክርክር ጉዲይ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለውሣኔያቸው መሰረት ያደረጉት ጭብጥ ልዩነት ያለው ይመስላል የኸውም የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ አስተሳሰብ በኮንትሮባንድ ጭና የተገኘት መኪና በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 መሰረት በቁጥጥር ማዋልና ችግሩ መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ ይዞ ማቆየት አይቻልም የሚል አይደለም። ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በውሣኔው ያሰመረበት መሰረታዊ ነገር መኪናዋ በልላ ሾፋር ስትሽከረከር ከላይ የተጠቀሱት ንብረቶች ይዛ መገኘቷ ታውቆ መኪናዋ መለቀቅ እንዲለባት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን የበላይ አመራሮች ወደ ተጠሪው በተደጋጋሚ ደብዲቤዎች ጽፈው እያለ /በቁ.ዘ4ዐ/ቀ64/64ዐ/ዐ5/15 መጋቢት ዐ9/1996፣ በቁ.ዘ3ዐ/ቀ64-16/ዐ6 መስከረም 28/1997 ዓ.ም፣ በቁጥር ዘ4ዐ/ቀ 64-6/ዐ3 ነሐሴ 27/1997 ዓ.ም/ ተጠሪው ይህንን ትእዛዝ ወደጎን በመተው የአመልካችን መኪና ጉዲዩን ለማጣራት ከሚገባው ጊዜ በላይ በቁጥጥር ስር አውል አመልካችን ለተጨማሪ ወጪ ዲርጓል የሚል ሲሆን፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሣኔ ደግሞ ከላይ የተመለከተውን የደብዲቤዎች ልውውጥ ግምት ውስጥ ባለማስገባት በአጠቃላይ በኮንትሮባንድ የተጠረጠረች መኪና በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ የማቆየት ስልጣን በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 መሰረት ያለው መሆኑን ነው። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጠቀሰው አሰራር በሕጉ የተመለከተ ሃቅ ቢሆንም ሁኔታውን በሚባ ተገንዝቦና የጉምሩክ መመሪያን መሰረት በማድረግ የባለስልጣኑ የበላይ አመራሮች መኪናዋ በወቅቱ ትሽከረከር የነበረው በልላ ሹፋር እንጂ የመኪናዋ ባለቤት በሆኑት በአመልካች ባለመሆኗ በአስቸኳይ እንድትለቀቅ በተደጋጋሚ እያዘዙት ተጠሪው መኪናዋን በወቅቱ ወይም ተገቢ በሆነ ጊዜ ውስጥ ሣይለቅ በቀረበት ሁኔታ ከላይ የተጠቀሰው አዋጅ የያዘው ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ ነው ማለቱ ተገቢነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በተጠሪው ጥፊት ምክንያት በአመልካቹ ላይ የገቢ መቋረጥ ሲደርስ አዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 ሽፊን በማድረግ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተጠሪው ያቀረበው ክርክር መሰረት ያለው አይደለም፤ አዋጁ የጉምሩክ ባለስልጣን ሰራተኞች ወይም ቅርንጫፍቻቸው በጥፊታቸው ምክንያት በባለንብረቶች ላይ ለሚያደርሱት ጉዲት ተጠያቂ እንዲይሆኑ ሽፊን የመስጠት ዓላማ የለውም፤
ስለሆነም በአሁኑ ጉዲይ መኪናዋ ስትሽከረከር የነበረው በሹፋር እንጂ በአመልካቹ አለመሆኗ ተገልፆለትና እንዱህ በሆነ ጊዜም መኪናዋ በቁጥጥር ስር አድርጎ ለረጅም ጊዜ ማቆየት በጉምሩክ መመሪያ መሰረት እንደማይፈቀድ ተጠሪው በግልጽ እያወቀ ሆን ብል መኪናዋን አለቅም በማለት በአመልካቹ ላይ ጉዲት ማድረሱ የተረጋገጠ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
2ዐ28፣2ዐ31/1/ መሰረት ለደረሰው የገቢ መቋረጥ ጉዲት ኃላፉነት አለበት ብለናል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ፍርድ ተጠሪው በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት መኪናዋን በቁጥጥር ሥር አውል የማቆየት ስልጣን ስላለው ሉጠየቅ አይገባም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል፤ ሥለሆነም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 24665፣ ግንቦት 1ዐ/1999 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል፤ ይፃፍ።
2/ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የድሬዲዋ ምድብ ችልት በመ.ቁ. ዐ1735፣ መጋቢት 2ዐ ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል፤ ይፃፍ።
3/ ተጠሪው ጥፊት መፈፀሙ ስለተረጋገጠ በአመልካቹ ላይ ለደረሰው የገቢ መቋረጥ ኃላፉነት አለበት፤ ሥለሆነም ብር 36,111.11 /ሰላሣ ስድስት ሺህ አንድ መቶ አስራ አንድ ብር ከአስራ አንድ ሣንቲም/ ለአመልካቹ ይክፈል ብለናል።
4/ ግራ ቀኙ ወገኖች በዚህ ችልት ላካሄደት ክርክር ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
ጉዲዩ በውሣኔ የተቋጨ በመሆኑ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።