No summary available.
ኀዲር 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ግምጃ ጎበና - ጠበቃ እንዲልካቸው ይላቅ ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
አቶ ወንድወሰን ወልዳ - በላለበት
ወ/ሮ ላይላ አህመድ- ወኪል አብደልቃድር ቀረቡ።
አቶ ተስፊዬ ተሾመ - በላለበት
አቶ ደረሰ ለገሰ - በላለበት
አቶ ጋሪሣ ድረራ - በላለበት
ናይስ ኢንሹራንስ ኩባንያ - አልቀረበም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከውል ውጪ አላፉነትን መሰረት አድርጎ የቀረበ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች ሟች ልጃቸው አደኛ ደበላ ዕድሜው 3ዐ /ሰላሣ/ ዓመት የሆነው መጋቢት 14 ቀን 1995 ዓ.ም. ከቀኑ በግምት 1፡ዐዐ በሚሆንበት ጊዜ የአሁኑ አንደኛ ተጠሪ ንብረት የሆነውና በአሁኑ ሦስተኛ ተጠሪ ይሽከረከር የነበረው መኪና እና የአሁኗ ሁለተኛ ተጠሪ ንብረት የሆነውና በአሁኑ አራተኛ ተጠሪ ይሽከረከር የነበረው፣ በአሁኑ 6ኛ ተጠሪ የመድን ሽፊን የተሰጠው መኪና ባደረሱት ግጭት ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን፤ በሕይወት እያለም በግብርና ስራ ተሰማርቶ በዓመት የተለያዩ ሰብልችን በማምረት ገቢ ያገኝ እንደነበር፤ በዚህ ገቢውም አመልካችን ይረዲቸውና ያስተዲድራቸው የነበረ መሆኑን ዘርዝረው የመኪናዎቹ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ለሟች መሞት አላፉ ተብለው ሟች ወደፉት ለ1ዐ /አስር/ ዓመታት ቢኖር ያገኝ ነበር ብለው ያሰለትን ብር 1ዐ4ዐዐዐ.00 /አንድ መቶ አራት ሺህ ብር/ የተቋረጠ ጥቅም፣ ከዲኝነትና ጠበቃ አበል ጋር እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ጥቅምት ዐ2 ቀን 1996 ዓ.ም. በተፃፈ የክስ ማመልከቻ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። በፍ/ቤቱ ጥሪ መሰረት ተከሣሾች ቀርበውም አለን ያለትን የመከራከሪያ ነጥብ አቅርበዋል። ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ የተጠየቁ ተከራካሪዎችም ቀርበው ተከራክረዋል።
የሥር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር በአላፉነትና በጉዲት ካሣ መጠን ክርክር ላይ በተለያዩ የክርክር ደረጃዎች ተገቢ ነው ያለውን ውሣኔ ሰጥቷል። አላፉነትን በተመለከተ ውሣኔ የተሰጠው መጋቢት 2ዐ ቀን 1998 ዓ.ም.
ሲሆን በዚህ ጊዜም የአሁኑ አንደኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ለጉዲቱ አላፉነት የላለባቸው መሆኑ ተገልፆ በነፃ ሲሰናበቱ የአሁኑ አንደኛ እና አራተኛ ተጠሪዎች ግን ለጉዲቱ አላፉነት አለባቸው ተብለው የጉዲት ካሣ መጠኑን በተመለከተ የአመልካች ምስክሮች ተሰምተዋል። ከዚህም በኋላ የአመልካች ምስክሮች ቃል በጉዲዩ ላይ ከቀረበው ክርክር አንጻር መመርመሩ ተገልፆ አመልካች ሟች ልጃቸው ምን ያሕል ይረዲቸው እንደነበረ ያላስረደና ወደፉት ሉኖሩ የሚችለት ዕድሜም ምን ያሕል እንደሆነ አልገለፁም የሚል ምክንያት መሰረት ተደርጎ የካሣ ጥያቄውን የስር ፍ/ቤት ውድቅ አድርጎ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኗ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ይኸው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ጥቅምት 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ አመልካች ከሟች ልጃቸው ጋር እየኖሩ ይጦሩ እንደነበር ተረጋግጦ እያለ አመልካች ምን ያሕል ዓመት ወደፉት እንደሚኖሩ ዕድሜአቸውን ገልፀው አልቀረቡም ተብል የካሣ ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ተቀባይነት የላለው ምክንያት መሆኑንና ሟች ከናዝሬት ወደ አዱስ አበባ ተሣፍሮ ይጓዝበት የነበረው የአንደኛ ተጠሪ መኪና በሆነው በሦስተኛ ተጠሪ ይሽከረከር በነበረው ሆኖ እያለ ተገቢው ውሣኔ ሣይሰጥ መታለፈ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ተሽሮ በስር ፍ/ቤት የተጠየቀውን የመተዲደሪያና የመጦሪያ ካሣ ገንዘብ ተጠሪዎች ባልተነጣጠለ አላፉነት እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል በመባለ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጓል። በዚህም መሰረት አንደኛ፣ ሦስተኛ እና አምስተኛ ተጠሪዎች በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን 4ኛ ተጠሪም የፍ/ቤቱን መጥሪያ ተቀብለው ያልቀረቡ መሆኑ ሰለተረጋገጠ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል። 2ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች ግን ቀርበው ጥር 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ የሟች ሕይወት ያለፈው በሁለተኛ ተጠሪ መኪና ተሣፍሮ ሲሄድ ባለመሆኑ አላፉነቱ የአጓጓዥ እንጂ የሁለተኛ ተጠሪ ባለመሆኑ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ላሆን እንደሚገባ፣ ይህ የሚታለፍ ከሆነም አመልካች በስር ፍ/ቤት በልጃቸው ሞት ምክንያት የተቋረጠባቸው ገቢ መኖሩን ገልፀው ያላቀረቡና በሰውም ማስረጃ አስደግፈው ያላቀረቡ በመሆኑ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ የሚነቀፍበት ምክንያት ስለላለ ውሣኔው ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው መጋቢት ዐ3 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈት ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን አቅርበዋል።
No topics extracted.
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ ይዘትና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች በልጃቸው ሞት ምክንያት ተቋርጧል ያለትን ጥቅም ሉያገኙ አይገባም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
በክርክሩ ሂደት ለሟች ሕይወት ማለፍ አላፉነት አለባቸው ተብል ውሣኔ ያረፈባቸው ወገኖች የአሁኑ ሁለተኛ እና አራተኛ ተጠሪዎች ናቸው። የአሁኑ አንደኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ለጉዲቱ አላፉነት የለባቸውም ተብል መጋቢት 2ዐ ቀን 1998 ዓ.ም. ውሣኔ መስጠቱን የስር ፍ/ቤት የውሣኔ ግልባጭ ያስረዲል። በመሆኑም በአመልካች የሰበር አቤቱታ በአንደኛ እና በሦስተኛ ተጠሪዎች ላይ የስር ፍ/ቤት ተገቢውን ውሣኔ ሣይሰጥ አልፎል ተብል የቀረበው ቅሬታ እውነትነት የላለው ከመሆኑም በላይ ሥነ ሥርዓቱን ጠብቆ ያልቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት የላለው ነው ብለናል።
በልላ በኩል የአሁኑ ስድስተኛ ተጠሪ ለሟች ሕይወት ማለፍ አላፉነት ያለበት አጓጓዡ እንጂ ሁለተኛ ተጠሪ ናቸው ልባል አይገባም በማለት ያቀረበው የሰበር መከራከሪያ ነጥብ የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን ከውል ውጪ አላፉነትን በሚመለከት ሕግ ተመልክቶ ለአደጋው አላፉነት የሚወስደት የአሁኑ ሁለተኛ እና አራተኛ ተጠሪዎች ናቸው በማለት ውሣኔ የሰጠበት እና በበላይ ፍ/ቤትም የተለወጠ ካለመሆኑም በላይ በይዘቱ የማስረጃ ምዘና ጉዲይ በመሆኑ የስድስተኛ ተጠሪ ክርክር በሰበር ችልቱ የሚስተናገድበት ሥርዓት አልተገኘም።
በመቀጠል የስር ፍ/ቤት ሁለተኛ እና አራተኛ ተጠሪዎች ለሟች ሕይወት ማለፍ አላፉ ናቸው ካለ በኋላ፤
የአመልካችን የጉዲት ካሣ ጥያቄ ውድቅ የማድረጉን አግባብነት መመልከቱ የግድ ይሎል። ከመዝገቡ መገንዘብ የተቻለው በአመልካች በኩል የቀረቡት ሁለት ምስክሮች ሟች የአመልካች ልጅ መሆኑን፣ በግብርና ሥራ ይተዲደር እንደነበር፣ በዓመት ከአርባ እስከ ሃምሣ ኩንታል እህል ያመርት እንደነበር፣ አትክልት በማልማት ደግሞ በዓመት እስከ ብር 1ዐ,ዐዐዐ.00 /አስር ሺህ ብር/ ያገኝ እንደነበር፣ ልጅና ሚስት ያልነበረውና 6/ስድስት/ ቤተሰብ ያስተዲድር የነበረ ስለመሆኑ መመስከራቸውን ነው። ከዚህም በላይ የአመልካች ልጅ የሆነው ሟች አመልካችን በቤቱ ውስጥ ይዞአቸው ይጦራቸው እንደነበር በአመልካች በኩል የቀረበው የጽሁፍ ማስረጃ ይጠቁማል። ይህንኑ የአመልካችን ማስረጃ ተጠሪዎች ለማስተባበል ያቀረቡት ማስረጃ የለም። በመሆኑም አመልካች በሟች ልጃቸው እርዲታ ይጦሩ የነበሩ ስለመሆኑ ከተጠሪዎች በተሻለ ሁኔታ አስረድተዋል። ጉዲዩ የፍትሐብሕር እንደመሆኑ መጠንም የማስረጃ ምዘናው የትኛው ተከራካሪ ወገን የተሻለ ማስረጃ አቅርቧል? የሚለው መመዘኛ መሰረት ተደርጎ የሚስተናገድ መሆኑ ይታወቃል። የስር ፍ/ቤት የማስረጃ ምዘናም መርሁን ያላገናዘበ ነው።
አመልካች በሟች ልጃቸው ስር ይተዲደሩ የነበሩና ሟች ልጃቸውም ገቢ የነበረው ስለመሆኑ ካስረደ ደግሞ የራሣቸውን የወደፉት ዕድሜ በማመልከቻቸው አለመጥቀሣቸውና ሟች በትክክል ይሰጣቸው የነበረው የመጦሪያ ገንዘብ መጠን አለመታወቁ የጉዲት ካሣ ጥያቄአቸውን ሙለ በሙለ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል የሕግ መሰረት የላለው ምክንያት ነው። ይልቁንም አመልካች ልጃቸው ገቢ የነበረውና በስሩ አድርጎ ያስተዲድራቸው የነበረ መሆኑን ማስረዲታቸው የጉዲት ካሣ መጠኑን በርትዕ ለመወሰን መነሻ ላሆን የሚችል ነው። የጉዲት ካሣ መጠኑን በተመለከተ በርትዕ መተመን የሚቻልበት ሁኔታ ስለመኖሩም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 21ዐ2 ድንጋጌ ያሣያል። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የጉዲት ካሣ መጠኑን በሕጉ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት መተመን እየቻለ አመልካች በማስረጃ አላስረደም በማለት ጥያቄአቸውን ሙለ በሙለ ውድቅ ማድረጉ ከውል ውጪ አላፉነቱን በተመለከተ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች አጠቃላይ ዓላማም ሆነ የካሣ አተማመኑን በተመለከተ በሕጉ የተቀረጹትን ሥርዓቶች ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 33149 መስከረም 29 ቀን 1999 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 49878 ጥቅምት ዐ8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፀናው ውሣኔ የአመልካችን የጉዲት ካሣ ጥያቄ ውድቅ ያደረገው የውሣኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ሁለተኛ ተጠሪ በተሽከርካሪ ባለቤትነታቸው፣ አራተኛ ተጠሪ በአሽከርካሪነታቸው፣ ስድስተኛ ተጠሪ ደግሞ ለተሽከርካሪው በሰጠው የመድን ሽፊን ዋስትና መሰረት በአመልካች ላይ በልጃቸው መሞት ምክንያት ለተቋረጠው የመተዲደሪያ ገቢ ባልተነጣጠለ ሁኔታ አላፉነት አለባቸው ብለናል።
የስድስተኛ ተጠሪ የአላፉነት መጠን በመድን ዋስትና ውለ የተመለከተውን ያሕል ነው ብለናል።
አንደኛ፣ ሦስተኛ እና አምስተኛ ተጠሪዎችን በተመለከተ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
በአመልካች ላይ የደረሰው የጉዲት ካሣ መጠን በርትዕ ሉወሰን የሚገባው ሆኖ ስለተገኘ ብር 25,ዐዐዐ.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ሁለተኛ፣ አራተኛ እና ስድስትኛ ተጠሪዎች ለአመልካች በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ብለናል።
በዚህ ጉዲይ ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መ/ቤት ይመለስ።