No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 35ዐ34 ጥቅም ዐ6 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው አሉ መሐመድ አመልካ‡ች፡- እነ ወ/ሮ ጥሩቀለም ደሴ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- እነ ወ/ሮ ጽጌ ከፍያለው - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ክርክሩ ከውል ውጪ አላፉነትን መሰረት ያደረገ ነው። የስር ከሣሾች የነበሩት የአሁኑ አመልካ‡ች ሲሆኑ መጋቢት 28 ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ ክስ ንብረትነቱ የአንደኛ ተጠሪ የሆነ ታክሲ በሁለተኛ ተጠሪ ሲሽከረከር ተማሪ እየሩሣላም ስሙር የተባለች የአስራ አንድ ዓመት እድሜ ያላት ሕፃን ልጃቸውን በመግጨት በቀኝ ታፊዋ ላይ ጉዲት በማድረስ አጥንቷ ተሰብሮ እያነከሰች እንደምትገኝ እና በጉዲቱ ምክንያትም ወደፉት ተምራ ልትጦራቸው በማትችልበት ሁኔታ እንደምትገኝ በመጥቀስ ለአካል ጉዲትና ለሞራል ካሣ በድምሩ ብር 1ዐዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የአሁኑ ተጠሪዎች እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁኑ ተጠሪዎችም ሰኔ 27 ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ የመከላከያ መልስ ማመልከቻ ለአደጋው ኃላፉነት የላለባቸው መሆኑንና የተቋረጠ ጥቅምም አለመኖሩን በመግለጽ ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ ተገቢ ናቸው ያላቸውን ጭብጦችን በመመስረት ተከሣሾች አደጋው የደረሰው በክሱ ላይ በተጠቀሰው ተሽከርካሪ መሆኑን አምነው መከራከራቸውንና የከሣሾች ማስረጃም ጥፊቱ የአሽከርካሪው መሆኑን ማረጋገጡን ገልፆ ለጉዲቱ ተከሣሾች አላፉ ናቸው ካለ በኋላ የጉዲት መጠኑን በተመለከተ ግን ተጎጂዋ ትምህርቷን በመከታተል ላይ እንደምትገኝ መረጋገጡን፣ የህክምና ማስረጃውም መካከለኛ የሆነ ማነከስ ቢኖርባትም መራመድ እንደምትችል መግለፁን ጠቅሶ ተጎጂዋ ከሣሾችን ወደፉት ልትረዲ የማትችል እና ራሷም ሉቀርባት የሚችል ጥቅም ስለመኖሩ አጠራጣሪ ነው በማለት የአካል ጉዲት ካሣ ጥያቄን ውድቅ አድርጎ የህሉና ጉዲትን በተመለከተ ግን ብር 8ዐዐ.ዐዐ /ስምንት መቶ/ ሁለተኛ ተጠሪ ከወጪና ኪሣራ ጋር እንዱከፍል ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም አመልካ‡ች በእርግጠኝነት በአደጋው ምክንያት በልጅቷ ላይ የደረሰውን የአሁንና የወደፉት ቁሣዊ ጉዲት አላስረደም ሲል ይግባኙን ሣይቀበል ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ በመቃወም ሲሆን አመልካ‡ች ጥር ዐ8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የቅሬታ ነጥቦችን ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮም የስር ፍ/ቤት ጉዲት የደረሰባት ልጅ መካከለኛ ማነከስ ያለባት እንደሆነ በህክምና ተረጋግጧል እያለ በልላ በኩል ወደፉት ተጎጂዋ ሉቀርባት የሚችል ጥቅም ስለመኖሩ አጠራጣሪ ነው በማለት የጉዲት ካሣ ክፍያ አይገባትም በሚል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪዎች መጋቢት 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን ሲያቀርቡ አመልካ‡ች በበኩላቸው ሚያዝያ 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን አቅርበዋል።
እኛም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር፣ ለሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደመረመርነውም ተጠሪዎች የአካል ጉዲት ካሣ ለመክፈል ይገደዲለ ወይስ አይገደደም? የሚለው ነጥብ የችልቱ ምላሽ የሚያስፈልገው ሆኖ ተገኝቷል።
በክርክሩ ሂደት አንደኛ ተጠሪ የታክሲው ባለቤት ሁለተኛ ተጠሪ ደግሞ በተጎጂዋ ጉዲት አደረሰ የተባለውን ታክሲ በወቅቱ ሲያሽከረክሩ የነበሩ መሆኑ እና ለጉዲቱ መድረስ አንደኛ ተጠሪ የታክሲው ባለቤት በመሆናቸው ብቻ ያለጥፊት ሁለተኛው ተጠሪ ደግሞ በጥፊቱ አላፉነት ያለባቸው መሆኑ ተረጋግጧል። የስር ፍ/ቤት የአመልካ‡ችን የአካል ጉዲት ካሣ ጥያቄ ያለፈው ተጎጂዋ ወደፉት ሉቀርባት የሚችል ጥቅም ስለመኖሩ እና አመልካ‡ችንም ልትረዲ የማትችልበት ሁኔታ መኖሩ አጠራጣሪ ሆኖ ተገኝቷል በሚል ምክንያት ነው። ይሁን እንጂ ተጎጂዋ መካከለኛ የሆነ ማነከስ ያለባት መሆኑ በሐኪም ከመረጋገጡ አኳያ እና የካሣ አከፊፈልና ልክ ከሚደነግጉት የፍትሐብሕር ሕጋችን ድንጋጌዎች አንፃር ሲታይ የስር ፍ/ቤት ድምዲሜ ሕጋዊ መሰረት ያለው አይደለም።
በመሰረቱ በፍትሐብሕር ሕጋችን ከውል ውጪ አላፉነትን በሚመለከት የተቀመጡ ድንጋጌዎች ጉዲት የደረሰበት ሰው የሚካስበትን ሥርዓት የዘረጉ ናቸው። የእነዚህ ድንጋጌዎች ዓይነተኛ ግባቸውም ጉዲትን የመካስና የጥፊት ባህርይን የመግታት ስለመሆኑ በድንጋጌዎቹ ላይ ማብራሪያ ጽሐፍ ያበረከቱት በቀድሞ ቀዲማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ክፍል አስተማሪ የነበሩት ቺቺኖቪች ገልፀውታል።
ከውል ውጪ አላፉነትን በተመለከተ የሚገዙት የፍትሐብሕር ሕጋችን ድንጋጌዎች መንፈስ የጉዲትን ጠቅላላ ባህርይና የካሣ ልክ አተማመን ሁኔታዎችን ያስገነዝቡናል። በዚህም መሰረት ጉዲት በሰው ጥቅም ላይ ችግር ማድረስ መሆኑን፣ ይህም ጥቅም ማቴሪያላዊ /በሰው አካል ወይም ንብረት የደረሰ/ ወይም ሞራላዊ ላሆን እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል። የተጎዲ ሰው ደግሞ መካስ እንዲለበት ያስረዲለ። የካሣውን አተማመን በተመለከተም መጠኑ በተበዲዩ ላይ ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ መመዘን ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ91 ድንጋጌ ያሣያል። የጉዲት ካሣ ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ ሲመዘንም በተጎጂው ላይ በእርግጠኝነት መድረሱ የታወቀ /actual damage/ ወይም ወደፉት ሉደርስ የሚችል /future damage/ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት የግድ የሚል መሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ9ዐ/1/ አና 2ዐ92 ድንጋጌዎች መንፈስ ያስረዲል። ለእነዚህ ጉዲዮች ካሣ ሉተመን የሚገባ መሆኑን ሕጉ በግልጽ ከማስቀመጡም በተጨማሪ የአተማመኑ ሥርዓትም እንደጉዲቱ ዓይነትና ማስረጃ አቀራረብ ውስብስብና ሉለያይ የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ በሕጉ ተመልክቷል። በዚህም መሰረት የጉዲት ካሣ መጠን አጥጋቢና በቂ ማስረጃን ወይም ርትዕን መሰረት በማድረግ ሉወሰን የሚገባው መሆኑን የካሣ አከፊፈልን ልክ በሚደነግገው የሕጉ ክፍል የተቀመጡ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። በልላ በኩል የካሣ አተማመን ሥርዓት ጠቅላላ የመሥራት አቅም /General utility/ ሣይሆን ልዩ ጠቀሜታ/specific utility/ መርህን ቢከተል ፍትሐዊነት ያለው አሰራር መሆኑ ይታመናል። ይህም አሰራር በተጨባጭ የደረሰው ጉዲት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ የካሣውን ልክ ያላግባብ ከማጋነንና ከመቀነስ የራሱ የሆነ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብል ይታሰባል። በመሆኑም ጉዲት መድረሱ በማስረጃ ከተረጋገጠና ጉዲቱም በተጎጂው የወደፉት ሕይወት ላይ አለታዊ ተጽእኖ ማሣደሩ እንደማይቀር ምክንያታዊ እርግጠኝነት ያለ መሆኑ ከተረጋገጠ ካሣ መወሰን ከአጠቃላይ የሕጉ ዓላማና ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ91 እና 2ዐ92 ድንጋጌዎች መንፈስ አኳያ አግባብነት ያለው ነው። መጠኑን በተመለከተ በሕጉ ለዳኞች በተሰጠው ሥልጣን ወይም በጉዲዩ ላይ በቀረበው ማስረጃ መሰረት በመተመን ለተጎጂው መፍረድ የሚቻልበት ሁኔታ መኖሩን ከላይ ተመልክተናል። ከዚህ ውጪ ጉዲቱ መድረሱ እየታወቀ የአሁንና የወደፉት ቁሣዊ ጉዲት /material damage/ ስለመኖሩ ተጎጂው አላስረዲም ተብል የመካስ መብት ማጣት ከአጠቃላይ የሕጉ ዓላማ ያፈነገጠ ነው።
No topics extracted.
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስም የአመልካ‡ች ልጅ በደረሰባት የመኪና አደጋ በቀኝ እግሯ ላይ መካከለኛ ማነከስ የደረሰባት መሆኑ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ጉዲቱ ወደፉት ሉጠፊ የሚችል ስለመሆኑም የተገለፀ ነገር የለም።
ተጠሪዎች ጉዲት የደረሰባት ሕፃን ትምህርት እየተማረች ትገኛለች በማለት ከመከራከራቸው ውጪ ከጉዲቱ ሙለ በሙለ ስለመዲኗ ያስረደት ነገር የለም። ስለሆነም በተጎጂዋ ላይ የደረሰው ጉዲት በወደፉት ሕይወቷ አለታዊ ተጽእኖ ማሣደሩ የማይቀር ስለመሆኑ የነባራዊው ዓለም ሁኔታዎች ያስገነዝቡናል። በእርግጥ በተጎጂዋ ላይ የወደፉት ሕይወት ጉዲቱ የሚያደርሰውን የካሣ መጠን በትክክል መገመት አስቸጋሪ ይሆናል። ይሁን እንጂ የጉዲት ካሣ መጠኑን በተመለከተ በሕጉ ለዳኞች በተሰጠው ስልጣን መሰረት መተመን የሚቻልበት ሁኔታ ስለመኖሩ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 21ዐ2 ድንጋጌ ያሣያል።
በመሆኑም አመልካ‡ች በልጃቸው ላይ ጉዲት መድረሱን በሚገባ አስረድተው እያለና ይህ ጉዲትም በተጎጂዋ የወደፉት ሕይወት አለታዊ ተጽእኖ ማሣደሩ የማይቀር መሆኑን በምክንያታዊ እርግጠኝነት ከነባራዊው ዓለም መገንዘብ እየተቻለ፤
እንደዚሁም የካሣ አተማመኑም ርትዕን መሰረት ሉያደርግ የሚገባ በመሆኑ የበታች ፍ/ቤቶች የአመል‡ችን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው ከውል ውጪ አላፉነቱን በተመለከተ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች አጠቃላይ ዓላማም ሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
2ዐ9ዐ፣2ዐ91፣2ዐ92 እና 21ዐ2 ስር የተመለከቱትን መርሆዎች ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1/ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 33351 ግንቦት ዐ3 ቀን 1999 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57181 ታህሣሥ 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
2/ አመልካ‡ች በልጃቸው ላይ ጉዲት የደረሰባት ስለመሆኑ በማስረጃ ያረጋገጡ ከመሆኑም በላይ ጉዲቱም በወደፉት ህይወቷ ላይ አለታዊ ተፅዕኖ (Negative impact) ማሣደሩ እንደማይቀር ምክንያታዊ እርግጠኛነት ያለው ስለመሆኑ ስለተረጋገጠ የካሣ አተማመኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 21ዐ2 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ በርትዕ ሉወሰን የሚገባው ነው ብለናል።
3/ የካሣ መጠኑን በተመለከተ የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን ከርትዕ አኳያ በመመልከት እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343/1/ መሰረት መልሰናል።
4/ በዚህ ችልት ትእዛዝ መሰረት ተጠሪዎች ለጉዲት ካሣው በአንድነትና በነጠላ አላፉነት ያለባቸው መሆኑን ተገንዝቦ መጠኑን በመተለከተ ይወስን ዘንድ የውሣኔው ግልባጭ ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ይተላለፍ ብለናል።
5/ በዚህ ችልት ለተደገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
የማይነበብ የአመስት ዳኞች ፊርማ አለበት