No summary available.
ጥቅምት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አብልሃሚድ የሱፍ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የምሥራቅ ቀጠና ጉምሩክ ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ አጥለ ሀብታሙ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የንብረት ግምት ጥያቄ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ አመልካች ጥር ዐ5 ቀን 1997 ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ በአወዲይ ከተማ ውስጥ የንግድ ስራ በሕጋዊ መንገድ እያካሄደ ባለበት ሁኔታ ተጠሪ የጉምሩክ ፕሉስ እና ላላ የፕሉስ ኃይል በማስተባበር የሱቁን ቁልፍ በመስበር በሱቁ ውስጥ የነበረውን የንግድ ዕቃ በሙለ አውጥተው በጭነት መኪና ጭነው በመውሰድ በተጠሪ መጋዘን ማስገባቱን፤ የተወሰደ ንብረቶችን ተጠሪ ይመልስላቸው ዘንድ ጥያቄ ቢያቀርቡም ተጠሪ ፈቃደኛ ሆኖ አለመገኘቱን፤ የተወሰደባቸው በሱቁ ውስጥ የነበሩት ንብረቶች ዓይነታቸውና ብዛታቸው እንዱሁም ግምታቸው ምን ያሕል እንደሆነ በመዘርዝር ግምቱ ብር 5ዐዐ,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ የሆነ ንብረት እንዱመለስላቸው፣ ንብረቶቹ ተሸጠው ይገኝ የነበረውን ትርፍ እንዱከፍለ፣ ንብረቶቹን ካልመለሱ ግምቱን እንዱከፍለ እና የተለያዩ ወጪዎችንም ጭምር እንዱከፍለ ይወስንላቸው ዘንድ የአሁኑን ተጠሪ አንደኛ ተከሣሽ ላልች ሁለት የፕሉስ አባላትን ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተከሣሽ በማድረግ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በአመልካች በኩል ተዘርዝረው የቀረቡትን የንብረት ዓይነቶች በፍ/ቤት የብርበራ ትዕዛዝና በሕብረተሰቡ ትብብር የኮንትሮባንድ ንግድን ለመቆጣጠር እና ለመያዝ በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የወሰደ መሆኑን በመግለጽ ተጠያቂነት እንደላለበት፤ በአመልካች በኩል የቀረቡት ማስረጃዎችም ተቀባይነት የላላቸው መሆኑንና ላልች የመከራከሪያ ነጥቦችን በማንሣት ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት በ27/ዐ7/97 ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ የተጠሪን መከራከሪያ ነጥቦች ውድቅ በማድረግ ተጠሪንና በስር ሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩትን የጉምሩክ ፕሉስ የወንጀል ምርመራ ኃላፉን ለድርጊቱ አላፉ አድርጎ የአመልካችን ንብረት በክሱ በቀረበው ዝርዝር መሰረት በእራሣቸው ወጪ ከወሰደበት ቦታ ከአመልካች ሱቅ እንዱመልሱ ይህን ካልፈፀሙ ግምቱን ብር 5ዐዐ,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ፣ ወጪና ኪሣራ ዝርዝር የማቅረብ መብት ለአመልካች በመጠበቅ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኙን ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የተለያዩ ምክንያቶችን ከዘረዘረ በኋላ በአሁኑ አመልካች በኩል የቀረቡት ማስረጃዎች ንብረቶቹ የአመልካቹ ለመሆናቸው ለማስረዲትና ለማረጋገጥ የማይችለ አጥጋቢና አሣማኝ አይደለም ወደሚል ድምዲሜ በመድረስ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር ተጠሪን በነፃ በማሰናበት ወስኗል።
ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ያለባቸውን ምክንያቶች ሰኔ ዐ3 ቀን 1999 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ዘርዝረዋል። አቤቱታውም ተመርምሮ ለሰበር ችልቱ ቀርቦ ላታይ ይገባል በመባለ ተጠሪ ጥር ዐ1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ መልሱን አቅርቧል። አመልካችም በተጠሪው መልስ ላይ የካቲት ዐ6 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርነውም የዚህ ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው ጭብጥ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ንብረቶች ተጠሪ የወሰዲቸው ከአመልካች ሱቅ ነው እየተባለ ንብረቶቹ የአመልካች መሆናቸው አልተረጋገጠም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ሆኖ ተገኝቷል።
በክርክሩ ሂደት ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ንብረቶች ተጠሪ የወሰዲቸው ከአመልካች ሱቅ መሆኑ፣ የአመልካች ሱቅ ቁጥር የለውም ቢባልም በብር 1ዐ,ዐዐዐ.00 /አስር ሺህ/ ካፑታል ልዩ ልዩ ዕቃዎችንና ሸቀጦችን ለመነገድ ከተገቢው አካል ፈቃድ አውጥተው የሚሰሩበት መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪ ከአመልካች ሱቅ ንብረቶቹን መወሰደን ሣይክድ ተግባሩን የፈፀመው በሕጉ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሆኑንና ንብረቶቹ የአመልካች ስለመሆናቸው ተቀባይነት ያለው ማስረጃ አለመቅረቡን በመጥቀስ የሚከራከር መሆኑን ተገንዝበናል። የተጠሪ መ/ቤት ስልጣንና ተግባር በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 በአንቀጽ 6 እና 58 ስር ተዘርዝሯል። እነዚህ የአዋጁ ድንጋጌዎች የሚያሣዩት የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የጉምሩክ ባለስልጣንና ሹም የተሰጣቸው ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር መቀመጣቸውን ነው። የጉምሩክ ባለስልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 368/1995 ደግሞ ኮንትሮባንድ ማለት ሕጎችንና በሕግ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን በመተላለፍ ወደ ጉምሩክ ክልል ዕቃዎችን በማስገባት ወይም ከጉምሩክ ክልል በማስወጣት፣ በሕጋዊ መንገድ የመጡትን በሕገ ወጥ መንገድ መልሶ ማስባት፣ መያዝ፣ ማከማቸት፣ ማዘዋወር ማስተላለፍ እንዱገቡ ወይም እንዱወጡ ለማድረግ መሞከር እና ከእንደዚህ ያለ ድርጊቶች መተባበርን እንደሚጨምር በአንቀጽ 2/28/ ትርጓሜ ሰጥቶበታል።
ከላይ እንደተጠቀሰው ተጠሪ ተግባሩን ሕጋዊ ነው ብል ሲከራከር በተለይ መሰረት ያደረጋቸው የአዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 አንቀጽ 6/5/ እና 58/1/ለ/ ድንጋጌዎችን ነው። አንቀጽ 6/5/ ሙለ ይዘቱ ሲታይ ባለስልጣኑ “በኮንትሮባንድ ወደ አገር የሚገቡትን ወይም ከአገር የሚወጡትን ዕቃዎች እንቅስቀሴ ይቆጣጠራል፣ ይከላከላል፣ በዚሁ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ ዕቃዎችንና ማጓጓዣዎችን ይይዛል፣ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ይወስዲል” በማለት ሲደነግግ አንቀጽ 58/1/ለ/ ደግሞ ወደ አገር እንዲይገቡ ወይም ከአገር እንይወጡ የተከለከለ ገደብ የተደረገባቸው ወይም ቀረጥ እንዲይከፈልባቸው በማሰብ የተደበቁ ዕቃዎች በፍተሻ ሲገኙ ዕቃዎችን የመያዝ እንዱሁም እንደሁኔታው ማጓጓዣውን የማጓጓዣውን ኃላፉ ወይም የዕቃውን ባለቤት ይዞ ለምርመራ በጥበቃ ሥር የማቆየት ስልጣንና ኃላፉነት የጉምሩክ ሹም ያለው መሆኑን ይደነግጋል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለው የጉምሩክ ባለስልጣን በኮንትሮባንድ ወደ አገር የሚገቡትን ወይም ከአገር የሚወጡትን ዕቃዎች እንቅስቃሴ የመቆጣጠር፣ የሚንቀሳቀሱ ዕቃዎችንና ማጓጓዣዎችን የመያዝና አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ፣ በሕገ ወጥ መንገድ መገልገያ የሆኑ መጓጓዣዎችን ጭምር ይዞ ለምርመራ በጥበቃ ስር የማቆየት ስልጣን በሕጉ የተሰጠው መሆኑን ነው። እነዚህን ተግባራት የሚያከናውነው ግን ኮንትሮባንድ ተብል በሕግ የተሰጠው ትርጓሜ ተሟልቶ ሲገኝ ነው። ማንኛውም የዕቃ እንቅስቃሴ ኮንትሮባንድ ስለመሆኑ አሣማኝ እና በቂ ምክንያት ሣይኖረው ባለስልጣኑ መ/ቤት እንዱይዝና እንዱቆጣጠር ሕጉ ስልጣን ሰጥቶታል ተብል አይታሰብም። የአንድን ሰው መኖሪያ ቤት ወይም የንግድ ቤት የኮንትሮባንድ ዕቃ የተደበቀበት ስለመሆኑም ባስልጣኑ ጥርጣሬ ሲኖረው ሰብሮ በመግባት ዕቃዎችን እንዱይዝ ሕጉ ይፈቅድለታል ወደሚለው ድምዲሜ መድረስ በኢ/ፋ/ዱ/ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 26/1/ ስር ጥበቃ የተደረገለትን የግል ሕይወት የመከበርና የመጠበቅ መብት ዋስትና የሚያሣጣ ነው። በመሆኑም የጉምሩክ ባለስልጣን ተግባር ሕጋዊ ነው ልባል የሚችለው በሕጉ መሰረት ሉሟለ የሚችለትን ሁኔታዎች አሟልቶ ሲገኝ ብቻ እንጂ በማንኛውም ጥርጣሬና ምክንያት ሁለ የግለሰብን ንብረት በመያዝ ላሆን አይችልም።
እጃችን ወዲለው ጉዲይ ስንመለስ በተጠሪ ተወሰደ የተባለ ንብረቶች በአመልካች ይዞታ ስር የነበሩ መሆኑ ተረጋግጧል። እንዱህ ከሆነ ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1193/1/ ሥር በተደነገገው አኳኋን አመልካች የንብረቶቹ ባለሀብት መሆናቸውን ሕጉ ግምት ይወስዲል። ይህ ሕጋዊ ግምት ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ ሉፈርስ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1193/2/ ድንጋጌ ያስረዲል። በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለይዞታነት የሰው ወይም የጽሁፍ ማስረጃ በማቅረብ ካልፈረሰ በቀር ባለይዞታው የንብረቱ ሕጋዊ ባለሀብት ስለመሆኑ ግምት የሚወሰድበት እና ባለሀብትነትን የማስረዲት /proof of ownership/ አንደ ዘዳ ነው።
ተጠሪ ንብረቶቹ የአመልካች አለመሆናቸውንና በኮንትሮባንድ ስራ ወደ አመልካች እጅ የገቡ ናቸው በማለት የሚከራከረው በአመልካች በኩል የቀረቡትን ደረሰኞች፣ የንግድ ፈቃድ ካፑታል መጠንና የንግድ ዓይነትን መሰረት በማድረግ እንጂ ያላግባብ ወደ አገር ውስጥ ገብቶ የተገኘ መሆኑን በማስረዲት አይደለም። በተለይም ተጠሪ የአመልካችን ንብረቶች ያዝኩ የሚለው በፍ/ቤት የብርበራ ትዕዛዝ ቢሆንም ይኸንኑ ትዕዛዝ ብርበራው ከተፈፀመ በኋላ ፍ/ቤቱ ማንሣቱ መረጋገጡ የተጠሪን ተግባር ሕጋዊነት ቀሪ ማድረጉን ከሚጠቁም በስተቀር አመልካች የንብረቶቹ ሕጋዊ ባለቤት አለመሆናቸውን የማያሣይ ነው። በመሆኑም ተጠሪ የአመልካች ንብረቶች ኮንትሮባንድ ስለመሆናቸው አላስረዲም።
በአንፃሩ ንብረቶቹን በይዞታቸው በማድረግ ይጠቀሙባቸው የነበረ ስለመሆኑ አመልካች ያረጋገጡ በመሆኑ በማስረጃ ምዘና መርህ ረገድ ሲታይ የተሻለ ማስረጃ ያቀረቡትም አመልካች ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ያቀረቡትን ማስረጃዎች የመዘነበት መንገድ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1193 /1/እና /2/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ባላገናዘበ ሁኔታ ነው።
ስለሆነም የአመልካች ዕቃዎች ከአመልካች ሱቅ መወሰዲቸው ተረጋግጦ እያለና ንብረቶቹ በኮንትሮባንድ ተግባር ወደ አመልካች ዕጅ የገቡ መሆናቸውን ተጠሪ ባላስረዲበት ሁኔታ ተጠሪ ተጠያቂነት የለበትም መባለ ባግባቡ ሆኖ ስላልተገኘ ውሣኔው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1193፣ የአዋጅ ቁ. 6ዐ/1989 አንቀጽ 6/5/ እና 58/1/ለ/ እንዱሁም የአዋጅ ቁጥር 368/1995 አንቀጽ 2/28/ ድንጋጌዎችን መንፈስ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። በዚህም ምክንያት ተጠሪ በሕገ-ወጥ መንገድ የአመልካችን ንብረቶች መወሰደ በበቂ ሁኔታ ስለተረጋገጠ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ27፣ 2ዐ35 እና 2ዐ54 ስር በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት አላፉ ልባል የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
የካሣውን መጠን በተመለከተም አመልካች ከጠየቁት ዲኝነትና ካቀረቡት ማስረጃ እንዱሁም ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2118 አኳያ ሲታይ ተጠሪ ተዘርዝረው የቀረቡትን ንብረቶች በዓይነት እንዱመልስ ወይም ግምታቸውን እንዱከፍል መወሰኑ ፍትሐዊነት ያለው ሆኖ ተገኝቷል። ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 32974 ሰኔ ዐ8 ቀን 1998 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 26383 መጋቢት 19 ቀን 1999 ዓ.ም. በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ2282 ሐምል ዐ7 ቀን 1997 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል። ይፃፍ።
ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ንብረቶች ከአመልካች ይዞታ ያላግባብ የወሰዲቸው መሆኑ ስለተረጋገጠ ንብረቶቹን በዓይነት እንዱመልስ ወይም ግምታቸውን ብር 5ዐዐ,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ሉከፍል ይገባል ብለናል።
በዚህ የሰበር ችልት በተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.