No summary available.
ጥቅምት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ብዙነሽ ኃ/ዮሐንስ - ጠበቃ መድሕን መሐሪ ቀረበ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ስንታየሁ እሸቱ - በላለችበት መዝገቡን መረምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ ከውል ውጪ የደረሰ ኃላፉነትን መሰረት አድርጎ የቀረበ የካሣ ክፍያ ጥያቄን /ክርክር/ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በሶማላ ብ/ክ/መ/ በጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። ከሣሽ የነበረችው የአሁንዋ ተጠሪ ስትሆን በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተችውም የምትወልደው ልጅዋ ሦስት ሕፃናት ልጆቼን አርድ ስለገደለብኝ በእናትነትዋ ካሣ ልትከፍለኝ ይገባል በማለት ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠችው መልስ ጉዲዩ በፈጸመው ድርጊት ኃላፉ የምሆንበት የሕግ ምክንያት የለም፤ መከሰሴም ያለአግባብ ነው፡፤ በማለት ስለመከራከርዋ ከመዝገቡ ለመገንዘብ ችለናል። ክሱን ያስተናገደው ፍ/ቤትም የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ከሰማ በኋላ ተከሣሽ ላደረሰው ጉዲት ኃላፉ ናት በመሆኑም በጠቅላላው ብር 35ዐዐዐ(ሰላሳ አምስት ሺህ) ካሣ ለከሣሽ ትክፈል በማለት ወስኗል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ይህን ውሣኔ በመቃወም ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማለትዋ በዚህ ይግባኝ ደረጃም ክርክሩ ተሰምቶአል።
በመቀጠልም ፍ/ቤቱ በከፍተኛው ፍ/ቤት ተሰጥቶ የነበረውን ውሣኔ በማሻሻል አመልካች ብር 78ዐዐዐ(ሰባት ሺህ ስምንት መቶ) ካሣ እንድትከፍል ወስኖአል። በጨረሻም የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ከአመልካች በቀረበለት አቤቱታ መነሻነት ክርክሩን ከሰማ በኋላ በጠ/ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ አጽንቶአል። የአሁኑ አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ሐምል 6 ቀን 1999 ዓ.ም. በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። ተጠሪ በተደረገላት ጥሪ መሰረት ባለመቅረብዋ ክርክሩ የተሰማው እሷዋ በላለችበት ነው።
አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች ደረሰ ለተባለው ጉዲት ኃላፉ የምትሆንበትና ካሣ የምትከፍልበት የሕግ ምክንያት አለ ወይ? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ ባጭሩ እንደተመለከተው አመልካች የተከሰሰችው እና በመጨረሻም ኃላፉ ነሽ የተባለችው እርስዋ በፈጸመችው ድርጊት ጉዲቱን አድርሳለች በሚል አይደለም። ጉዲቱን አድርሷል የተባለው የእሷ ልጅ የሆነው ሰው ነው።
እርሱም ልጆቹን ከገደለ በኋላ ራሱንም እንዲጠፊ በተጠሪ ክስ ተገልጾአል። ከዚህም በተጨማሪ ሰውየው አካለ መጠን የደረሰና ዕድሜውም ከ4ዐ ዓመት በላይ እንደነበረ በክርክሩ ተመልክቶአል። ተጠሪ ክሱን የመሰረተችው በፍ/ብ/ሕግ ቁ.
2125 የተመለከተውን ድንጋጌ በመጥቀስ ሲሆን ይህ ድንጋጌ የሚያመለክተው በአባት አላፉነት ምትክ ሆነው ስለሚጠየቁት ሰዎች ነው። ድንጋጌው የሚገኘው “ለላላ ሰው ተግባር አላፉ ስለመሆን” በፍትሐብሕር ሕጉ በአንቀጽ 13 በምዕራፍ 1 /ከውል ውጪ ስለሚደርስ አላፉነት/ በሚለው በክፍል 4 ስር ነው። ከቁጥር 2125 በፉት ያለው ቁ. 2124 አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ አላፉነትን የሚያስከትል ሥራ የሰራ እንደሆነ በፍትሐብሕር በኩል ለተሰራው ሥራ አላፉ የሚሆነው አባት እንደሆነ ያመለክታል። ቁጥር 2125 ደግሞ አባት በላለ ጊዜ በሱ ምትክ ኃላፉ የሚሆኑትን በተመለከተ የሚደነግግ ነው። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዶ የልጁ እናት እንደሆነችም በዚሁ ቁጥር 2125/ሀ/ ተመልክቶአል።
እንግዱህ እንደተጠሪ ክስ አመልካች ኃላፉ ልትሆን ትችል የነበረው ጉዲቱን አድርሷል /የተጠሪን ልጆች ገድልአል/ የተባለው ሰው አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ቢሆን ነበር። ይህ ግን በተጠሪ በኩል አልተረጋገጠም። ጉዲት አድራሹ አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ነው የሚል በተጠሪ ክስም ሆነ ክርክር አልተነሳም። የሥር ፍ/ቤቶችም ቢሆኑ ጉዲት አድራሹ ሰው ዕድሜው ከ4ዐ ዓመት በላይ የነበረ እና በኔም ስር የሚተዲደር ያልነበረ ነው የሚለውን የአመልካችን ክርክር ከመመዝገብ አልፈው በእርግጥ አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ነበር አላለም። ይህም የሚያመለክተው ፍ/ቤቶቹ አመልካችን ኃላፉ ያደረጉዋት ኃላፉ የምትሆንበት የሕግ ምክንያት ሳይኖር እንደሆነ ነው። ከዚህ የተነሣም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
አቤቱታ የቀረበበት በሶማላ ብ/ክ/መ/ በጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ እና በዚህ ውሣኔ ላይ በቀረበው ይግባኝ እና አቤቱታ ማስረጃነት በክልለ ጠ/ፍ/ቤት እና ሰበር ችልት በመ/ቁ. GM181/98 ሰኔ 28 ቀን 98 ዓ.ም. እና በመ/ቁ. 09/99 ሚያዝያ 13 ቀን 1999 ዓ.ም. የተሰጡት ውሣኔዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች ደረሰ ለተባለው ጉዲት ኃላፉ የምትሆንበትም ሆነ ካሣ የምትከፍልበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት ወስነናል።
መዝገቡ ይመለስ።