No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 332ዐ1 ጥቅምት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ አመልካች፡- የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ የሺጥላ ተሾመ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሼል ኢትዮጵያ - ጠበቃ አጥናፈ ቦጋለ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጉዲት ካሣን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ አመልካች ንብረትነቱ የተጠሪ በሆነው የነዲጅ ማደያ ላይ በደረሰው የቃጠል አደጋ መንስኤነት አመልካች የሚያስተዲድረው አድራሻው ወረዲ 18 ቀበላ 27 የቤት ቁጥር 3ዐ3 የሆነው ቤት ተቃጥል ጉዲት የደረሰበትን ቤት ተጠሪ በማደስ ለአመልካች ቢያስረክብም በእድሣቱ ምክንያት ቤቱ በመዘጋቱ አመልካች የኪራይ ገቢ ማጣቱን በመግለጽ አመልካች ከኪራይ ገቢ ያጣውን ብር 6375.ዐዐ /ስድስት ሺህ ሦስት መቶ ሰባ አምስት ብር/ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር እንዱከፍለው ይወሰንለት ዘንድ በአሁኑ ተጠሪ ላይ ነሐሴ 26 ቀን 1997 ዓ.ም በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረተው ክስ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በፍ/ቤቱ ጥሪ መሰረት ቀርቦ የአመልካችን ቤት ያሣደሰው የነዲጅ ማደያው ስራ እንዲይቆም እንጂ አላፉነትን በመቀበል አለመሆኑን፣ ለጉዲት አላፉነት ያለበት አካልም በወቅቱ የነዲጁ አጓጓዥ የነበረው ኢነርት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የወከለው ቴዱ ኃላፉነቱ የተወሰነ ኩባንያ ሹፋር መሆኑን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም ተጠሪ ለደረሰው ጉዲት አላፉ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ሲል የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው የሚልበትን ምክንያቶች በ15/ዐ1/2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ዘርዝሯል። ይዘቱም በአጭሩ የተቃጠለው የነዲጅ ማደያም ሆነ ለቃጠልው መንስኤ የሆነው በወቅቱ በመራገፍ ላይ የነበረው ነዲጅ ባለቤት ሼል ኢትዮጵያ ሉሚትድ እንጂ ላላ ባለመሆኑ ከአላፉነት ነፃ መባለ ያላግባብ ስለሆነ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ሉሻር ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪን ያስቀርባል ተብል ተጠሪ የካቲት 11 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል። ይዘቱም በአጭሩ አመልካች በሰበር ባላነሣው የሕግ ነጥብ የበታች ፍ/ቤቶች ስህተት ፈጽመዋል ልባል ስለማይገባ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ሆኖ ይወሰንልኝ በማለት መከራከሩን የሚያሣይ ነው። አመልካች በበኩለ በበታች ፍ/ቤት የሕግ ድንጋጌ ተጠቅሶ ክርክር አለመቅረቡ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ በመለየት ውሣኔ መስጠት የፍ/ቤት የስራ ድርሻ ከመሆኑ አኳያ በስር ያልተነሣ የክርክር ነጥብ ልባል አይችልም በማለትና የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር መጋቢት ዐ1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል እንደመረመረውም ለአመልካች የተቋረጠ የኪራይ ገቢ ይከፈለኝ ጥያቄ ተጠሪ አላፉነት የለበትም ተብል ውድቅ መደረጉ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን? በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
በክርክሩ ሂደት ተጠሪ የቃጠል አደጋ የደረሰበት ነዲጅ ማደያ ባለቤት መሆኑ ቃጠልውን ያስነሣው መኪና ባለቤት ከተጠሪ ጋር የአጓጓዥነት ስራ የተዋዋለ ሰው መሆኑ፣ በቃጠልው የአመልካች ቤት መጎዲቱና ተጠሪ ይህንኑ በቃጠልው የተጎዲውን ቤት በማሣደስ ለአመልካች ማስረከቡ የተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች ናቸው። የአሁኑ ተጠሪ የተቋረጠውን የኪራይ ገቢ እንዱከፍል በአመልካች በኩል የቀረበበት ክስ ውድቅ የሆነው ቃጠልውን ያስነሣው መኪና ሹፋር በፈፀመው ስለሆነ እና ሹፋሩ የተጠሪ ተቀጣሪ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በሚል ምክንያት ነው።
ይሁን እንጂ ነዲጁ ሲራገፍ የነበረው ተጠሪ ስራውን በሚያከናውንበት የነዲጅ ማደያ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ የተጠሪ አላፉነት የሚመነጨው ከሚያከናውነው ስራ አደገኝነት አኳያ ታይቶ ነው። ማንም ሰው ስራው በሚያደርሰው ጉዲት ምክንያት ጥፊት ባይኖርበትም ከውል ውጪ አላፉነት ሉከተልበት እንደሚችል ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ66 - 2ዐ89 ድረስ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ያስረዲለ።
በእጃችን ላለው ጉዲይ አግባብነት የሚኖረው ድንጋጌም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ69/1/ ሲሆን ተጠሪ በሚያከናውነው የነዲጅ ማደያ ስራ ለሚከሰተው አደጋ አላፉነቱን ሉወስድ እንደሚገባ ያስገነዝባል። ምክንያቱም የነዲጅ ማደያ ስራ ጥንቃቄ የሚያስፈልገውና በቀላለም የመቀጣጠል ወይም የመፈንዲት ባህርይ ስላለው የአደገኛ ስራ ባህርይነት ኑሮት አጥፉ ሣይሆን አላፉ መሆንን የሚያስከትል ነው። ተጠሪ በዚህ ድንጋጌ መሰረት አላፉነት የለብኝም የሚል ክርክር ሣያቀርብ በስር ፍ/ቤት ተነስቶ ክርክር ያልተደረገበት ነው በሚል ምክንያት ብቻ በዚህ ችልት በሰጠው መልስ ተከራክሯል። ይሁን እንጂ ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ መጥቀስ የፍ/ቤት የስራ ድርሻ ከመሆኑ አኳያ የተጠሪ ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 329/1/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ባገናዘበ መልኩ ያልቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በልላ በኩል ተጠሪ የአመልካች ቤት በቃጠልው ከወደመ በኋላ አድሶ ማስረከቡን ሣይክድ ይኸው ተግባሩ አላፉነቱን መቀበለን አያሣይም የሚል ክርክር ማቅረቡ አሣማኝነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም የአሁኑ ተጠሪ ከአላፉነት ነፃ የተደረገው የግራ ቀኙን ክርክር እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2ዐ69/1/ ድንጋጌን ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት የሚከተለውን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ 1/ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57875 ጥቅምት ዐ6 ቀን 1999 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 51136