No summary available.
ጥቅምት 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን- ነገረ ፈጅ አቶ መስፍን ሃብቴ ይመር - ቀረበ መልስ ሰጭ፡- ወ/ሮ ፊጤ ዓሉ - በላለበት የሚታይ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር መዝገብ ተከፍቶ የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ጉዲይ በይግባኝ ተመልክቶ በኮ.መ.ቁ. 48755 ታህሳስ 07 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ ላይ የአሁን አመልካች ቅር ተሰኝቶ የሰበር አቤቱታውን በማቅረቡ ነው።
ጉዲዩ ባጭሩ እንደሚከተለው ነው። የአሁን መልስ ሰጭ በጋምቤላ ህዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት በጋምቤላ ከተማ ዙሪያ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሳሽ በመሆን በባለቤቷ ሞት ምክንያት በእራሷ እና የሞግዚትነት ሥልጣን ባገኘችባቸው ልጆቿ ስም ደረሰ ያለችውን ጉዲት አስልታ የጉዲት ካሣ ገንዘብ በአሁን አመልካች ላይ ከውል ውጭ በሚደርስ ኃላፉነት የተነሳ የክስ አቤቱታ አቅርባለች።
የአሁን አመልካችም በዚህ አኳኋን ለቀረበበት ክስ ጉዲቱ ደርሷል ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ድረስ ያለው ጊዜ ሲታሰብ ሁለት ዓመት ያለፈው በመሆኑ ክሱ በይርጋ ይቋረጣል የሚለውን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ካቀረበ በኋላ ስለ ፍሬ ጉዲዩም ያለውን የመከራከሪያ ነጥቦች በመዘርዘር ተከራክሯል።
ክሱ በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበለት ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር አገናዝቦ ከመረመረ በኋላ ክሱ ለጉዲቱ ምክንያት የሆነው ድርጊት ከተፈፀመ ሁለት ዓመት ካለፈው በኋላ የቀረበ መሆኑ ቢታወቅም ጉዲቱ ሞት ነው፤ የደረሰው ጉዲት ሞት በሆነ ጊዜ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2143 የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ ላሆን አይችልም የሚለውን ምክንያት አስፍሮ ክሱ በይርጋ ሉቋረጥ አይችልም የሚል ዲኝነት ሰጥቶ በአሁን አመልካች ላይ ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ጠቅሶ የካሣ ገንዘቡን በሚመለከት ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በርትእ እንዱከፈል ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ የአሁን አመልካች ቅር ተሰኝቶ የይግባኝ አቤቱታ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረቡ ይኸው ፍ/ቤት በይግባኝ ደረጃ ሙለ ክርክር ካደረገ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ውሳኔውን አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውንም ሆነ የኃላፉነቱን ነጥብ በሚመለከት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በሚል ነው።
መልስ ሰጭ በዚሁ የሰበር አቤቱታው መነሻነት ቀርባ መልስ እንድትሰጥበት ቢታዘዝም ጥሪ ደርሷት ያልቀረበች በመሆኑ ጉዲዩ በላለችበት ታይቷል።
እኛም ጉዲዩን አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። በዚህ ጉዲይ አከራካሪ ነጥብ ሆኖ የተገኘው ይርጋን አስመልክቶ ለቀረበው ክርክር የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ትርጉም የሕግ መሰረት አለው ወይስ የለውም? የሚለው ነው።
ምንም እንኳ ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍ/ቤት ይህንኑ ነጥብ በሚመለከት ዲኝነት ያልሰጠበት ስለመሆኑ የውሳኔው ግልባጭ ቢያስረዲም የአሁን አመልካች ለዚሁ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ያቀረበውን የይግባኝ ማመልከቻ ቅጅ እንዲየነው የይርጋ ጉዲይ በመቃወሚያነት በመጀመሪያ ደረጃው ፍ/ቤት እንስቶ የተከራከረበት መሆኑን ገልፆ ክሱ በመቃወሚያው ክርክር መቋረጥ የሚገባው ሆኖ እያለ ያለአግባብ መታለፈ ቅሬታ የፈጠረበት መሆኑን ጠቅሶ በይግባኝ የተከራከረበት ስለመሆኑ ተገንዝበናል። ስለሆነም ከክርክር አቀራረብ ሥርዓት አንፃር ይህ የሰበር አቤቱታ ደረጃውን ሳይጠብቅ የቀረበ ነው ማለት አይቻልም።
ወደ ተያዘው አከራካሪ ነጥብ ስንመለስ ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ክስ ጉዲቱ ደረሰ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ የቀረበ ለመሆኑ አከራካሪ ነጥብ ሆኖ አልተገኘም። የክሱም ምክንያት ከውል ውጭ በሚደርስ ኃላፉነት ላይ የተመረኮዘ ነው። ይህም ከሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2143 እንደተደነገገው ማናቸውም የጉዲት ካሣ ክስ ካሣ የሚጠየቅበት ጉዲት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ካልቀረበ በቀር ክሱ በይርጋ የሚቋረጥ ነው።
ካሣ የሚጠየቅበት ጉዲት ሲባል ደግሞ ሞትንም እንደሚያካትት ይኸው ሕግ በማያሻማ አኳኋን ደንግጏ እያለ፤ ክሱ የቀረበለት የጋምቤላ ከተማ ዙሪያ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከዚህ በግልጽ ከተደነገገው ሕግ በመራቅ የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ ጉዲት ሞት ሆኖ በተገኘ ጊዜ ተፈፃሚ ላሆን የሚችል አይደለም በማለት የይርጋውን ክርክር ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን ተገንዝበናል። ስለሆነም ቀድሞውንም ቢሆን ስለኃላፉነቱ ከማከራከሩ በፉት ክሱ በይርጋ ይቋረጣል በማለት መዝገቡን መዝጋት ሲገባው በተሳሳተ የሕግ አተረጓጏም የተነሣ የተሟላ የክስ መስማት ሂደት ማከናወኑ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
የጋምቤላ ከተማ ዙሪያ ከፍተኛው ፍ/ቤት በፍት/መ/ቁ. 6/95 ግንቦት 06 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 48755 ታህሳስ 07 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
የአሁን መልስ ሰጭ በአመልካች ላይ ያቀረበችው የጉዲት ካሣ ክስ ከውል ውጭ በሚደርሰው ኃላፉነት ሕግ እንደተመለከተው በሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ የተቋረጠ ነው ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተመልሷል።