No summary available.
ሐምል 9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ - ነ/ፈጅ ታምራት አባተ ተጠሪ፡- ባላንባራስ ተስፊዬ ገ/እየሱስ - ጠበቃ ገ/እግዚአብሄር ተስፊዬ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን አመልካች በተጠሪ ላይ በትግራይ ብ/ክ/መ/በመቀላ ዞን ማዕከላዊ ፍ/ቤት ባቀረበው አቤቱታ ለአቶ ተስፊዬ ፍትዊ ለሰጠው ብድር መያዣ የሆነ በመቀላ ከተማ ደቡብ ወረዲ ኩሃ ቀበላ የሚገኝ በ35259 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሰፈረ መጋዘንን ዕዲው ሳይከፈል በመቅረቱ ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ፣ 98/9ዐ እና 216/92 መሰረት አመልካች ከተበዲሪው ላይ ተረክቦ በማስተዲደር ላይ እያለ ተከሣሽ ከዚሁ ባለዕዲ ላይ ለሚፈልጉት ገንዘብ ይሄው ንብረት እንዱሸጥ ጠይቀው በሐራጅ ባለመሸጡ ምክንያት ንብረቱን እንዱረከቡ በፍ/ቤት ትዕዛዝ በመስጠቱ ንብረቱን መረከባቸው ተገቢ እንዲልሆነ በመጥቀስ ይመለስልኝ በማለት ጠይቋል።
ተከሳሽም ቀርበው በሰጡት መልስ ንብረቱን የተረከቡት ዕዲው ሳይከፈል በመቅረቱ ምክንያት የተጠቀሰው መሬትና መጋዘን ባለዕዲው በባለይዞታነት የሚጠቀምበት መሆኑን በመግለጽ ይሄው ንብረት እንዱሸጥ ተጠይቆ ሁለት ጊዜ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ወጥቶ ገዢ ባለመገኘቱ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/428/2/ መሰረት የፍርድ ባለመብቱ እንዱረከበው ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ በዚሁ መሰረት የተረከብኩት ስለሆነ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሣሽ የብድር ዕዲው ሳይከፈለው በመቅረቱ ምክንያት ንብረቱን ተረክቤያለሁ ቢልም ንብረቱን ስለመረከቡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1723/1/ መሰረት ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ያልተደረገ ከመሆኑም በላይ ተከሣሽ ንብረቱን በሐራጅ የሚገዛ በመጥፊቱ የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/428/1/ በሚፈቅደው መሰረት የተረከበ ስለሆነ ንብረቱን ሉመልስ አይገባም በማለት የከሣሽን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል።
ከሣሽ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለትግራይ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የላለው ነው ሲል በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/337 መሰረት ይግባኙን ሰርዟል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ሲሆን ይህ ሰበር ችልትም አቤቱታውን መርምሮ አመልካች በመያዣ ይዞት የነበረውን ንብረት አግባብ ባለው አካል ከማስመዝገብ አልፍ በስሙ በርስት መዝገብ አላስመዘገበም ተብል በመያዣ የያዘውን የተረከበውን ንብረት ለተጠሪ እንዱያስረክብ መባለ ለሰበር ቀርቦ ሉመረመር እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ አመጣጥና ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን በበኩላችንም አቤቱታው ለሰበር ይቅረብ ከተባለበት ነጥብ አኳያ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
አመልካች አቶ ተስፊዬ ፍትዊ የተባለ ግለሰብ የተበደሩትን ገንዘብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በመያዣ የያዘውንና ለዚህ ክርክር ምክንያት የሆነውን መሬትና መጋዘን አዋጅ ቁጥር 97/9ዐ፣ 98/90 እና 216/92 በሚፈቅደው መሰረት ገዢ በመጥፊቱ ምክንያት ተረክቦት እንደነበር መረጋገጡን ተገንዝበናል በልላ በኩልም የአሁን ተጠሪ በዚሁ ባለዕዲ በአቶ ተስፊዬ ፍትዊ ላይ አስፈርደው አመልካች በመያዣ ይዞት የነበረውና በኋላም የተረከበው መጋዘን በሐራጅ እንደሸጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሲሰጥ አመልካች ንብረቱን በመያዣ ይዞት እንደነበረና ዕዲው ባለመከፈለ ምክንያትም ንብረቱ በሐራጅ ለመሸጥ ተሞክሮ ገዢ በመጥፊቱ ምክንያት ከፍ ብል በተጠቀሱት አዋጆች መሰረት ንብረቱን እንደተረከበ በመግለጽና በንብረቱም ላይ መብት እንዲለው በመጥቀስ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/444 መሰረት ሽያጩን በመቃወም አመልካች አቤቱታ አቅርቦ እንደነበረና ፍ/ቤቱም አቤቱታው የቀረበው ዘግይቶ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ ማድረጉንም ከመዝገቡ ተረድተናል።
በዚህ መልኩ አቤቱታው ተቀባይነት ሳያገኝ ከቀረ አመልካች በዚህ ጉዲይ ላይ ክስ ከማቅረብ እንደማይታገድ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/421 እና 455 ላይ ተመልክቷል።
አመልካች በዚሁ መሰረት አቤቱታውን ሲያቀርብ የከፍተኛው ፍ/ቤት አቤቱታውን ሳይቀበለው የቀረው ከፍ ብል እንደተጠቀሰው ንብረቱን ስለመረከቡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1723/1/ መሰረት ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ስላልተደረገ ተቀባይነት የለውም በማለት ነው።
No topics extracted.
ይሁንና የንብረት ባለሀብትነት ከሕግ ወይም ከውል የሚያመነጭ ሲሆን አመልካች በዚህ ንብረት ላይ ባለሀብትነትን አቋቁሜያለሁ የሚለው ከውል ሳይሆን ከሕግ ነው። ይሄውም አመልካች በመያዣ የያዘው ንብረት ዕዲው ባለመከፈለ ምክንያት በሐራጅ መሸጥ ካልቻለ ንብረቱን መረከብ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ እና 98/9ዐ ሥልጣን ተሰጥቶታል። በዚሁ መሰረትም ይህንኑ ንብረት የተረከበው ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደመሆኑ መጠን አመልካች የንብረቱ ባለሀብት መሆን የቻለው ከሕግ በመነጨ መብት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የፍ/ብ/ሕ/ቁ/1723 ተፈፃሚነቱ የማይንቀሣቀስ ንብረት ባለሀብትነት በውል ማስተላለፍ በተፈለገ ጊዜ ስለሆነ የከፍተኛው ፍ/ቤት ይህንኑ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ለጉዲዩ ዕልባት መስጠቱ አግባብነት በላለው ሁኔታ እንደሆነ ተገንዝበናል።
አመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መሬትና መጋዘን በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት መረከቡ ከተረጋገጠ ይህንኑ ንብረት በልላ ዕዲ ምክንያት ተጠሪ እንዱረከቡት ትዕዛዝ ሲሰጥ የተረከበውን ንብረት በአመቺው መንገድ በመሸጥ ገንዘቡን ገቢ የማድረግ መብቱን የሚጋፊ ነው።
ስለሆነም ተጠሪ የፍርድ ባለመብት የሆኑበት ጉዲይ አመልካች በሕግ አግባብነት የንብረቱ ባለቤት በሆነበትና ለዚህ ክርክር ምክንያት በሆነው መሬትና መጋዘን ላይ አፈፃፀም ሉቀጥል የማይገባው ሆኖ ሳለ የመቀላ ዞን ማዕከላዊ ፍ/ቤት ከጉዲዩ ጋር ግንኙነት የላለውን ድንጋጌ በመጥቀስ የአመልካችን ክስ ውድቅ ማድረጉ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የመቀላ ዞን ማዕከላዊ ፍ/ቤት በመ.ቁ. ዐ5134 በ24/6/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እንደዚሁም የክልለ ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 24ዐ88 በ8/9/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በመቀላ ከተማ ደቡብ ወረዲ ኩሃ ቀበላ ካ.ሜትር ቦታ ላይ የሰፈረውን መጋዘን አመልካች በሕግ አግባብነት የተረከበው ስለሆነ ተጠሪ መልሰው ለአመልካች እንዱያስረክቡ ብለናል።
በዚህ ፍርድ መሰረትም እንዱፈጽም የፍርደ ግልባጭ ለመቀላ ዞን ማዕከላዊ ፍ/ቤት ይተላለፍ ብለናል።
የግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ ብለን መዝገቡን ዘግተናል።