No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ ስአማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ አበባ አስተዲደር ግብርና ቢሮ - ነ/ፈጁ ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ አቶ አበበ ዓባይ ዘጠኝ ሰዎች - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ሁከት ይወገድልንን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ ተጠሪዎች በቂላንጦ ቀበላ ገበሬ ማህበር ክልል ከ26 ዓመታት በላይ ግብር እየገበሩ በቦታው ከ6000(ስድስት ሺህ) ዛፍች በላይ ተክለው ከብቶቻቸውንም የሚያቆሙበትን ቦታ የአሁኑ አመልካችና ሦስት ሰራተኞቹ በኃይል ያስለቀቋቸውና ሁከት የፈጠሩባቸው መሆኑን ገልጸው ሁከቱ ተወግድ ይዞታቸው እንዱመለስላቸው ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ አመልካችና ሰራተኞቹ ላይ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ መሬቱ የመንግስት እንጅ የተጠሪዎች አለመሆኑን፣ቦታው ለምለም ቦታ የተከለለ መሆኑን ገልፆ የተጠሪዎች ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረና ተጨማሪ ማስረጃም ተገቢ ነው ካለው አካል ከጠየቀ በኋላ ቦታው ለደን ቦታ ተብል የተተከለ ቢሆንም ባለይዞታነቱ ግን የተጠሪዎች መሆኑ መረጋገጡ፣ የደን ክልልም በመንግስት ብቻ የሚከለል ሣይሆን በቀበላ ማህበረሰብና በግለሰብ ሉከናወን እንደሚችል ከደን አዋጅ መረዲት የሚቻል መሆኑን በምክንያትነት ይዞ አመልካች ከሰራተኞቹ ጋር ሁኖ የፈጠረው ሁከት አለ በማለት ሁከቱ እንዱወገድ፣በቁጥር ብር 1000.00(አንድ ሺህ) ለተጠሪዎች እንዱከፍል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አቅርቦ ይኸው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል። ከዚህ በኋላም አመልካች ለዚሁ ፍ/ቤት የሰበር አቤቱታው አቅርቦ ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ባለመስማማት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነ/ፈጅ ሐምል 23 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት 4/አራት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚልባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪዎች ለክርክሩ መነሻ በሆነው ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ያላቀረቡ መሆኑን፣ቦታው የመንግስት ስለመሆኑ ሕገ-መንግስቱና አግባብነት ያላቸው አዋጆች እየደነገጉ ከእነዚህ ህግ ጋር አኳያ ጉዲዩ አለመታየቱን፣ደን በቦታው ላይ ለማልማት ስልጣንና ኃላፉነቱ የተሰጠው ለአመልካች ሆኖ በአዱስ አበባ ማስተር ፔላን ላይ በጸደቀው መሰረት የደን ልማት ስራ ማከናወን የሚችል መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ አለመግባቱን ዘርዝሮ ሁከት ይወገድ ተብል የተሰጠው ውሣኔ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ተጠሪዎች እንዱቀርቡ ተደርጏ መጋቢት 24 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ 4/አራት/ ገጽ ማመልከቻ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ቅሬታ ነጥቦች እውነት የላላቸው፤የፈራጅን ህሉና ሉያሣምን በሚችል መልኩ ተቀነባብረው መቅረባቸውን፣ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቦታ ከ35 ዓመታት በላይ ይዘው የሚጠቀሙት ስለመሆኑና የአመልካች እርምጃ ከሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40/4/ ስር ጥበቃ ከተደረገው መብት ጋር ተቃራኒ መሆኑን ዘርዝረው የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ የሕግ ስህተት የለውም ተብል ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። የአመልካች ነ/ፈጅም ሚያዝያ 07 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት 2/ሁለት/ ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም አመልካች ሁከት ፈጥሯል ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቦታ ተጠሪዎች ለበርካታ ዓመታት በይዞታችን ስር አድርገን እየተጠቀምንበት የሚገኝ ነው በማለት የሚከራከሩ መሆኑን፣ፍ/ቤቱ ባደረገው ማጣራትም መሬቱ ለተጠሪዎች በ1991 ዓ.ም ለግጦሽ መሬት ተብል የተሰጠ መሆኑን ቀበላው ያረጋገጠው መሆኑን፣በ1991 ዓ.ም ቦታው የደን ቦታ ተብል የተከለለ መሆኑን የስር ፍ/ቤት አረጋግጦ የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረገው ደን በመንግስት ብቻ የሚከለል አይደለም በማለት ስለመሆኑ ነው።
በመሰረቱ የአመልካች ክርክር ዋቢ ያደረገው የአዱስ አበባ ከተማ መሪ ፔላን ማጽደቂና የአፈፃፀም አዋጅ ቁጥር 7/1986 “ን” ነው። ይህ አዋጅ በአንቀጽ 2/5/ ስር የመሪ ፔላን ትርጉምንና የሚያዛቸውን ካርታዎች ዓይነት አስቀምጧል። ለዚህ ክርክር አግባብነት ያለው የካርታ ዓይነትም የለምለም ክልል ካርታ ሲሆን አዋጁ በአንቀጽ 2/5/ሸ/ ስር የተደነገገው ነው። የአዋጁ አንቀጽ 21 ስለለምለም ክልል ካርታ ይዘት፣አንቀጽ 22 የለምለም ክልል ማለት ጥበቃና እንክብካቤ፣አንቀጽ 23 ደግሞ የዛፍችና እጽዋቶች ልማትና እንክብካቤ ከደነገጉ በኋላ በአንቀጽ 24 የክልል መስተደደሩ በለምለም ክልል ካርታው ላይ የተመለከቱትን ክልልች የመጠበቅ፣ የመንከባከብ፣ ወይም እንዱጠበቁ የማድረግ፣ እንዱለሙ የታቀደትን የለምለም ክልልች ስለሚለሙበት፣ ስለሚጠበቁት ሁኔታ አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ ተመልክቷል። አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቦታ ለደን የተከለለ ስለመሆኑ ማረጋገጡን፣ሰራተኞች ጉድጓድ አስቆፍረው በቦታው ላይ ችግኝ ያስተከለትም ከቢሮው በተሰጠው መመሪያ ስለመሆኑ አረጋግጧል። በመሆኑም አዋጁ አመልካች ተግባርና ኃላፉነት ያለው ስለመሆኑ ያሣያል።
ተጠሪዎች ላቀረቡት ክርክር የማስረዲት ብቃት ያለው ማስረጃ ያላቀረቡ ስለመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ያሣያል።
ፍ/ቤቱ ተጠሪዎች ያቀረቡት ማስረጃ የማስረዲት ብቃት የላለው መሆኑን አምኖም ተገቢ ነው ካለው አካል ተጨማሪ ማስረጃ እንዱያቀርብ አድርጓል። ይሁን እንጂ ተጠሪዎች ቦታው ላይ የተደረገውን የአመልካች እንቅስቃሴ ሁከት ነው ለማለት የቻለት በ1991 ዓ.ም በተደረገው የግጦሽ መሬት ክፍፍል ተሰጥቷቸዋል የሚል ማረጋገጫ ከቀበላ ገብሬ ማህበር ስለተላከላቸው እንጂ በህጉ አግባብ የይዞታ ማረጋገጫ በማቅረብ አይደለም። ከሁለም በላይ የተጠሪዎች ህጋዊ የሆነ የይዞታ መብት ያላቸው መሆኑ ከተረጋገጠም ከፍ/ቤት የሚጠይቁት ዲኝነት የሁከት ይወገድልኝ ሣይሆን የካሣ ጥያቄ ስለመሆኑ የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40/8/ እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/1997 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝበን ነው። እንደሚታወቀው የአንድ ንብረት ባለ ይዞታ የሆነ ሰው ይዞታውን ለመንጠቅ ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ለመፍጠር የሚፈጸምን ማንኛውንም ድርጊት እንዱቆም ወይም ንብረቱ እንዱመለስለት ሕጉ ከአስቀመጣቸው መንገድች አንደ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1149/1/2/ ስር የተመለከተው ነው። በዚህ አንቀጽ መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ መቅረብ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ነገር በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ ሲኖረው ነው። እንዱሁም የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም ዓይነት መብት በላለው ሰው ስለመሆኑም የተጠቃሹ ድንጋጌ መንፈስ ያስገነዝባል። በልላ አገላለጽ የሁከት ይወገድልኝ ክስ አቅራቢ ከተከሣሹ የተሻለ የይዞታ መብት ያለው ስለመሆኑ ማሣየት ይጠበቅበታል። ሆኖም ይህንኑ ያስረዲ ከሣሽ ጥያቄው ተቀባይነት የሚያገኘው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1140 እና 1149 ድንጋጌዎች የተመለከቱትን መብቶች የሚገድብ ላላ ሕግ በላለበት ሁኔታ ነው። የይዞታ መብት ፍጹም አይደለም። በሕጉ አግባብ ላላ መፍትሓ ላሰጥበት የሚችል ነው። ከእነዚህ መፍትሓዎች መካከልም ይዞታው ለሕዝብ ጥቅም ተብል ሲወሰድ ካሣ የሚከፈልበት ስለመሆኑ አንደ ነው።
የአመልካች ጥያቄም ተጠሪዎች በቦታው ላይ ህጋዊ የባለይዞታነት የላቸውም ከሚል በተጨማሪ በአዱስ አበባ ከተማ መሪ ፔላን ማጽደቂያና አፈፃፀም አዋጅ ቁጥር 7/1986 መሰረት ድርጊቱ ሁከት ልባል የሚገባ አይደለም የሚል ነው። ተጠሪዎች በቦታው በዚህ አዋጅ መሰረት የደን ተብል አለመከለለን አላረጋገጡም። ይልቁንም ቦታው ለደን ተብል የተከለለ ስለመሆኑ የስር ፍ/ቤትም አረጋግጧል።
እንግዱህ የአዋጅ ቁጥር 7/1986 አንደ ዓላማ በአዱስ አበባ መስተዲድር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መሰረት የከተማው እድገት ስርአት እንዱይዝና እንዱፊጠን ማድረግ ስለመሆኑ በመግቢያው ላይ ተመልክቷል።
እንዱሁም የክልል መስተዲደሩ በለምለም ክልል ካርታው ላይ የተመለከቱትን ክልልች እንደሚጠብቅ እንደሚንከባከብ፣ወይም እንዱጠበቁ የማድረግና እንዱለሙ የታቀደበትን የለምለም ክልልች ስለሚለሙበት፣ስለሚጠበቁበት ሁኔታ አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ ኃላፉነት ያለው ስለመሆኑ ተጠቃሹ አዋጅ በአንቀጽ 24 ስር በግልጽ አስፍሯል።
በተያዘው ጉዲይም ቦታው በደን የተከለለ መሆኑ ከተረጋገጠ አመልካችና ሰራተኞቹ ጉድጓድ በማስቆፈር ችግኝ ማስተከላቸው በሕጉ የተፈቀደ ተግባር ነው ከሚባል በስተቀር ሁከት ልባል የሚቻልበት የሕግ አግባብ የለም። ተጠሪዎች ቦታውን በሕጉ አግባብ የያዙትና ያለሙት ዛፍ ካለም በሕጉ አግባብ ካሣ የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል እንጂ ይዞታውን ልንለቅ አይገባም፣ሁከቱ ሉወገድ ይገባል በማለት ሉከራከሩ የሚችለ አይደለም። አመልካች ሁከት ፈጥሯል በማለት በማስተር ፔላኑ መሰረት ቦታውን ለአረንጓዳ ክልል በማዋል እንዲይንከባከብና እንዲይጠበቅ ማድረግ ነው ከሚባል በስተቀር ላላ ሕጋዊ ምክንያት የሚሰጠው ሆኖ አልተገኘም።
በአጠቃላይ የአመልካች አድራጏት ሁከት ነው ተብል በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1140 እና 1149 ድንጋጌዎችን ከአዱስ አበባ ከተማ መሪ ፔላን ማጽደቂና የአፈፃፀም አዋጅ ቁጥር 7/1986 አንቀጽ 2/5/፣21፣22፣23 እና 24 ድንጋጌዎች ጋር ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.