No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 12 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ - ነ.ፈ. ሂሩት አስራት ተጠሪ፡- የወ/ሮ ንጋቷ ዘለቀ ወራሽ አቶ እሸቱ ቦጋለ - ቀርቧል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች የሥር ከሣሽ ተጠሪ የሥር ተከሣሽ ነበሩ አመልካች ባቀረቡት ክስ በወረዲ 17 ቀበላ 24 ቁጥር 360 የሆነውን ቤት ወ/ሮ ንጋቷ ዘለቀ ከ1973 ጀምሮ በመያዝ ክራይ ሣይከፍለና የኪራይ ውል ሣይሞለ እስከ የካቲት 1990 ድረስ ሲገለገልበት ከቆየ በኋላ ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው የተጠሪ ወራሽ የሟች ወራሽነኝ በማለት ቤቱን በመያዝ ክራይ ሣይከፍለ ይገለገለበታል የሥር ሁለተኛ ተከሣሽም የሟች ዘመድነኝ በማለት ቤቱን እየተገለገለበት ስለሆነ ሁለቱም ተከሣሽ ኪራይ ሣይከፍለ ከውል ውጭ በሕገ ወጥ መንገድ ቤቱን በመያዛቸው አመልካች አከራይቶ ሉያገኝ የሚገባውን ጥቅም አጥቷል። ስለዚህ ያለ አግባብ የበለፀጉበትን እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 1994 የቤቱን ኪራይ በወር 54 እያከራየ ሉያገኝ የሚገባውን ብር 14,193.76(አስራ አራት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሦስት ብር ከሰባ ስድስት ሣንቲም) ከወለድ ጋር 150,628.55 በአጠቃላይ(አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከሃምሣ አምስት ሣንቲም) ብር 164,817.41 (አንድ መቶ ስልሳ አራት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ሰባት ብር ከአርባ አንድ ምንቲም) በአንድነትና በነጠላ ከፍለው ቤቱን ለቀው እንዱወጡ ሲል ጠይቋል።
(ተጠሪ) ተከሣሽ ለቀረበበት ክስ መልሱን ሲሰጥ አመልካች የጠቀሰው የኪራይ ግምት የተጋነነ ነው። አመልካች በቤቱ ላይ ያለውን መብትና ጥቅም ባለማረጋገጡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33(2)(3) መሰረት ክስ ማቅረብ አይችልም ፍ/ቤቱ ሥልጣን የለውም። በይርጋ ይታገዲል ካለ በኋላ በአማራጭም መልሳቸውን ሲሰጡ አውራሻችን ወ/ሮ ንጋቷ እና እኔ በአንድነት ስንኖርበት ቆይተናል ቤቱ የተሰጠን በቀድሞ የደርግ መንግሥት የከተማ ልማት ቤት ምንስተር ትዕዛዝ መሰረት የቤተ መንግሥት አካባቢ በራሳችን ወጪ ሰርተን ስንጠቀምበት ለነበረው ቤታችን በልዋጭነት ነው። አመልካች በራሱ ተምኖ ያቀረበው ገንዘብ መጠን ሕጋዊ አይደለም ስለዚህ አመልካች ያቀረበው ክስ ውድቅ ላሆን ይገባዋል ሲል መልሱን ሰጥቷል።
ጉዲዩ የቀረበለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የቀረበውን ክስ ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ ውሣኔ ሰጥቷል በውሣኔውም የቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ውስጥ በፍ/ሥ/ሥ/ቁ 33(2)(3) መሰረት አመልካች መብትና ጥቅም ስለላለው ሉከሰን አይገባም ያለትን ነጥብ ብቻ መርምረዋል። በመሆኑም አመልካች ተጠሪ ቤቱን ያስረክቡኝ የሚል ነው ይሁን እንጂ አመልካች ለተጠሪም ሆነ ለላላ ሰው እያከራየ የሚያስተዲድር መሆኑን ወይም ቤቱ መወረሱን የሚያሳይ ማስረጃ አልቀረበም በቤቱ ላይ አለኝ የሚለውን መብት ወይም ጥቅም ምን እንደሆነ አላረጋገጠም ስለዚህ መቃወሚያውን በመቀበል ክሱን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33(2)(3) መሰረት ክሱን ውድቅ አድርጓል።
ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በማከራከር አመልካች ይህን ቤት በሥሩ ይዞ የሚያስተዲድረው የገነባው ወይንም በመንግሥት የተወረሰ ለመሆኑ አላስረዲም በተጨማሪም የቀረበው ማስረጃም ቤቱን እንዱያስተዲድር መብት ሉሰጡ የሚችለ አይደለም ከቤተ መንግሥት ተፅፎል የተባለው ደብዲቤም ቢሆን ቤቱ የቤተ መንግሥት መሆኑን አያረጋግጥም። ስለዚህ አመልካች ክስ በቀረበበት ቤት ላይ መብት የለውም ሲል የሥር ውሣኔን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 348(1) አፅንቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው በዚሁ ውሣኔ ላይ ነው።
አመልካች በ29/9/2000 ፅፍ ባቀረበው ማመልከቻ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ነው። ሲል እንዱታረምለት ጠይቋል። ይህ የሰበር ችልትም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪውን አስቀርቦ ክርክራቸውን ሰምቷል። ጉዲዩ በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች መብት ወይም ጥቅም የለውም በማለት የተሰጠውን ውሣኔ ለመመርመር ነው።
በዚህም መሰረት ይህንን ነጥብ ግራቀኙ ካቀረቡት ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እና የክርክሩን አመጣጥ ባጭሩ ስናይ አመልካች ለክርክሩ መንስኤ የሆነውን ቤት ተጠሪ ወራሽ ነኝ በማለት ብቻ መብት ሣይኖራቸው ክራይ ሣይከፍለ በሕገ ወጥ መንገድ እየተገለገለበት ነው በማለት ውዝፍ ኪራይ ከፍለው ቤቱን እንዱለቁ በመጠየቁና ተጠሪም በበኩለ ቤቱ የአመልካች እንዲልሆነና ቤቱን በደርግ ትዕዛዝ የከተማ ልማት በራሱ ወጪ ለሰራሁበት ቤት በልዋጭ ያገኘሁት ነው። ሉከሰኝ አይችልም ሲል በመከራከሩ የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች በቤቱ ላይ መብት ወይም ጥቅም እንዲለው አላስረዲም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጓል።
No topics extracted.
እኛም አመልካች በተጠቀሰው ቤት ላይ ክስ የማቅረብ መብት ወይም ጥቅም የለህም የተባለው አስመልክቶ በመዝገቡ ውስጥ ያለትን የተለያዩ ፅሐፍ (ደብዲቤ) ሆነ የግራ ቀኙ በሰበር ችልት ያካሄደትን የቃል ክርክር በጥልቀት እንደመረመርነው የተጠሪ አውራሽ (ሟች) የቤተ መንግሥት አገልጋይ የነበሩና የቤተ መንግሥት አስተዲደር በሰጣቸው ቤት ውስጥ ሲኖሩ የነበረ በመሆኑ ከግራ ቀኙ ክርክር ለመረዲት ተችሎል። በመሆኑም ይህ ክርክር የተነሳበት ቤት በጏርፍ ምክንያት በመፍረሱ ለቤተ መንግሥት አስተዲደር ቤቱን በጊዜያዊነት የተጠሪ አውራሽ በሕይወት እስካለ እንዱገለገለበት የተፈቀደላቸው እንጂ በልዋጭ የተሰጣቸው እንዲልሆነ ፍ/ቤቱ ተረድቷል ቤቱም በወቅቱ በነበረው የከተማ ልማትና የቤት ሚንስተር ትዕዛዝ ነው እንዱኖሩበት የተደረገው ይህ ማለት ደግሞ ቤቱ የመንግሥት መሆኑን ያስረዲል። ቤቱ የመንግሥት ከሆነ ስለ ቤቱ የመከራከር መብቱ መንግሥትን የወከለው ተቋም ነው እሱም አመልካች (የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ) ነው ወደሚለው ድምዲሜ ያደርሰናል።
ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቶች ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ሳያገናዝቡ አመልካች ለመክሰስ መብት ወይም ጥቅም የለውም ሲለ የሰጡት ውሣኔ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.33(2) መንፈስ ውጪ በመሆኑ አግባብነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. በቀን 20/1/98 እና የፋ.ከ/ፍ/ቤት መጋቢት 2/2000 የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች የመክሰስ መብት አለው ብለናል።
የፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍሬ ነገሩ ላይ በማከራከር ሕጋዊ ውሣኔ ይስጥበት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
341 መሰረት መዝገቡን መልሰናል።