No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3994ዐ ግንቦት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋይ አስማማው በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ አመልካች፡- ወ/ሮ ነጂባ ነጋሽ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዚያዲ ዳታሞ - ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ሁከት ይወገድልኝን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኗ ተጠሪ ነሐሴ 15 ቀን 1998 ዓ.ም.
በፃፈት ማመልከቻ ሟች አቶ አብድ ናስር ሼህ ጀቤር ከተባለት ባለቤታቸው ጋር በአዱስ አበባ ከተማ አራዲ ክፍለ ከተማ ቀበላ 11/12 የቤት ቁጥር 1638 የሆነውን ከመንግሥት ተከራይተው ሲኖሩ እንደነበር፣ ተጠሪ ያላግባብ የቤቱን ኪራይ ቀበላው በስማቸው አድርጎላቸው ቤቱን መያዛቸውን በመዘርዘር ተጠሪ የፈጠሩት ሁከት እንዱወገድ ይወስንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኗ አመልካችም የቤቱ ኪራይ በስማቸው የዞረላቸው የሟቹ ሚስት በመሆናቸው መሆኑን፣ ተጠሪ በወቅቱ በቤቱ ያልነበሩ መሆኑን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የቀበላው አስተዲደር ተጠሪ በቤቱ ላይ ከአመልካች ጋር አኩል መብት ያላቸው መሆኑን እያወቀ ተጠሪን በማስታወቂያ ሣይጠራና የቤት ኪራይ ስም ዝውውሩን መፈፀሙና ከአመልካች ኪራይ መቀበለ በተጠሪ ላይ ሁከት መፍጠር ነው በማለት አመልካችና ተጠሪ በቤቱ ላይ በጋራ እንዱገለገለበትና በጋራ ኪራይ እንዱከፍለ እንዱደረግ ሲል ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የከተማው ይግባኝ ሰሚ ችልትም ይግባኙን ሣይቀበለው ቀርቷል። የከተማው የሰበር ሰሚ ችልትም በጉዲዩ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተገኘም ሲል የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ነሐሴ ዐ9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈት 2 /ሁለት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚልባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- የተጠሪ የሁከት ይወገድልኝ ጥያቄ በጊዜ ያልቀረበና የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1149 ድንጋጌን ያላገናዘበ ሆኖ እያለ በተከራይነት ባገኘሁት የይዞታ መብትን እንዲካፍል መወሰኑ ሕጋዊነት የላለው በመሆኑ ሉሻር ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው ኀዲር ዐ3 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ የአመልካችን ቅሬታ ለመንቀፍ፣ የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ተገቢነት በመዘርዘር ውሣኔው ሉፀና ይገባል ሲለ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች ሁከት ፈጥረዋል መባለ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ነጥብ ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የቀበላው አስተዲደር የሚያስተዲድረው የመንግሥት ንብረት መሆኑን፣ ቤቱን ሟቹ ተከራይተውት ይኖሩበት እንደነበር፣ ከሟች ሕይወት ማለፍ በኋላ በወቅቱ ይዘውት በነበረው የሚስትነት ማስረጃ መሰረት አመልካች የቤቱን የተከራይነት መብት ቀበላው ያስተላለፈላቸው መሆኑን፣ በዚህ ጊዜ ተጠሪ ከቤት ያልነበሩና ሕጋዊ ጠባቂም ያልነበራቸው መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ይዞታው ለመንጠቅ ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ለመፍጠር የሚፈፀምን ማንኛውንም ድርጊት እንዱቆም ወይም ተገቢው መብት እንዱመለስለት ሕጉ ከዘረጋላቸው መንገድች አንደ የይዞታ ክስ /Possessory action/ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1149/1/ ድንጋጌ ያስገነዝባል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የሚቻለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ንብረት ላይ በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ ሲኖረውና ይህንኑ ሁኔታ በኃይል ሲነጠቅ ነው። እንዱሁም የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም ዓይነት መብት የላለው ሰው ሲይዝ ስለመሆኑም ተጠቃሹ ድንጋጌ ያሣያል። በመሆኑም የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ አቅራቢ ማረጋገጥ ያለበት ንብረቱ በሕግ አግባብ በይዞታው የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጢር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ነው። ይህ የድንጋጌው መንፈስ የሚያስረዲው የሁከት ተግባር የሚኖረው ባለይዞታ የሆነው ሰው በይዞታው ሥር በሚገኘው ንብረት እንዲይገለገልበት ላላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ሲፈጥርበት ወይም ረብሻ ሲፈጥርበት መሆኑን ነው። የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 114ዐ እና 1149 ድንጋጌዎች ይዘት የሚያሣዩትም ይህንኑ ነው። እነዚህ ድንጋጌዎች ከላይ ከተገለፀው ነጥብ በተጨማሪ የሚያስገነዝቡት ነጥብ የሁከት ይወገድልኝ ክስ አቅራቢ የተሻለ የይዞታ መብት ያለው ስለመሆኑ ማረጋገጥ ያለበት መሆኑን ነው። ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ በቤቱ ላይ ከአመልካች የተሻለ መብት የላላቸው መሆኑ፣ አመልካች ቤቱን የያዙት በቀበላው ስምምነት የተከራይነት መብት አግኝተው እንጂ በኃይል አለመሆኑ የተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች ናቸው። እንዱህ ከሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 114ዐ እና 1149 ድንጋጌዎች የተመለከቱት ሕጋዊ መሥፈርቶች አለመሟላታቸውን በቀላለ ለመገንዘብ አያዲግትም። በመሆኑም የአመልካች ተግባር ሁከት ልባል የሚችልበትን ሕጋዊ ምክንያት ስላላገኘን የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ው ሣ ኔ 1/ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ. አራ-ዐ3ዐ95 ጥቅምት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ፣ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ5585 መጋቢት 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ እንዱሁም የዚሁ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. ዐ6753 ሐምል 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
2/ አመልካች በተጠሪ ላይ የፈጠሩት ሁከት የለም ብለናል። ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት በጋራ የሚገለገለበት ወይም እኩል ተካፍለው የሚከራዩበት ሕጋዊ ምክንያትም የለም ብለናል።
3/ ለክርክሩ የተደረገውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።