No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 36ዐ13 ታህሣሥ 21 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ዘምዘም ኑሩ - ጠ/በረከት በርሓ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የኢት/ልማት ባንክ - አልቀረቡም።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የመያዣ መብት ያለውን ባለገንዘብ የቀዲሚነት መብት የሚመለከት ነው።
በምዕ/ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ባቀረቡት ክስ፤ በባሕር ዲር ከተማ ዐ4 የቤት ቁጥር 151 የሆነውን ቤት በአፈፃፀም ከሣሽ ባሕር ዲር ልዩ ዞን አገር ውስጥ ገቢ መ/ቤትና በአፈፃፀም ተከሣሽ ሐጂ ኑር ሁሴን ምትኩ መካከል በነበረው የአፈፃፀም ክርክር በወጣው ጨረታ ተሣትፈው በማሸነፍ ቤቱን የገዙ መሆኑን፣ የቤቱን የባለቤትነት ስም በስማቸው ለማዛወር ሲሞክሩ የማዘጋጃ ቤቱ በመያዣነት ተይዟል በማለት የከለከላቸው መሆኑን፣ በዚህ ሂደት ላይ ተጠሪ ቤቱ ያለአግባብ የተሸጠ ስለሆነ ጨረታው ይፍረስ በማለት አመልክቶ ጥያቄው ውድቅ መደረጉን፣ ከዚህ በኋላ የቤቱ ባለቤትነት ስም በስማቸው መዛወሩን በስማቸው ካርታና ፔላን ተሰርቶ የተሰጣቸው መሆኑን፣ ቤቱን በይዞታቸው ሥር አድርገው እየተገለገለበት እያለ ተጠሪ ቤቱን ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱን ገልፀው በንብረታቸው ላይ የፈጠረው ሁከት እንዱወገድላቸው ጠይቀዋል።
ተጠሪ ለቀረበት ክስ በሰጠው መልስም ጉዲዩ በልላ መዝገብ ክርክር ቀርቦበት ውሣኔ ያገኘ በመሆኑ በድጋሚ ላታይ አይገባም፣ ተጠሪ ቀደም ሲል በነበረው ክርክር ጣልቃ በመግባት ንብረቱ ላይ ያለው መብት እንዱከበርለት ጠይቆ ፍ/ቤቱ በንብረቱ ላይ ያለውን መያዣ መብት ንብረቱን በመከተል መጠቀም የሚችል መሆኑን በመግለጽ ብይን የሰጠ በመሆኑና ቤቱን ለአቶ ኑር ሁሴን ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘው በመሆኑ የመያዣ መብቱን ንብረቱን ከገዛው ሰው ላይም መጠቀም ይችላል፤ በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም አከራካሪ በሆነው ቤት ላይ ተጠሪ የመያዣ መብት ያለው መሆኑን አመልካች አልካደም በመያዣ የያዘውን ቤት ደግሞ በአ/ቁ. 97/9ዐ መሰረት የጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት መሸጥ ይችላል፣ ስለሆነም በጨረታ የያዘውን ንብረት ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ሁከት ፈጥሯል የሚያሰኝ አይደለም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኛቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ፤ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ የሰጠው ተገቢውን ጭብጥ ሣይዝ ነው፣ ተጠሪ ንብረቱን የመከተል መብት የሚኖረው ንብረቱን በዋስትና ካስያዘው ሰው ላይ ገዝቼው ቢሆን ነበር ንብረቱ በላልች ገንዘብ ጠያቂዎች ከተያዘ በኋላ የተጠሪ መብት ከንብረቱ ሽያጭ ገንዘብ ውስጥ በቅድሚያ ዕዲው እንዱከፈለው መጠየቅ ነው በመያዣ የተያዘው ንብረት በሃራጅ ተሸጦ ገንዘቡ በባለገንዘቦች ከተከፊፈለ በኋላ የመያዣ መብቱ ቀሪ ይሆናል፣ ተጠሪ ከመንግሥት ግብር በፉት ቅድሚያ መብት የለውም እንጂ አለው ቢባል እንኳን መብት ያለው መሆኑ በማሣወቅ ያቀረበው ጥያቄ የለም፣ በመሆኑም የገዛሁትን ንብረት በሃራጅ በድጋሚ የመሸጥ መብት የለውም የሚል ነው።
ይህ ችልትም አከራካሪው ንብረት በአገር ውስጥ ገቢ ግብር ክፍያ በሃራጅ ከተሸጠ በኋላ በድጋሚ ተጠሪ በሃራጅ ሉሸጠው የሚችል መሆን አለመሆኑን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ስለተባለ ተጠሪ መልሱን አቅርቧል።
ተጠሪ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ በሰጠው መልስ፣ በአ/ቁ. 97/9ዐ እና 98/9ዐ በተሰጠኝ መብት በመያዣ የያዝኩትን ንብረት ለመሸጥ ማስታወቂያ ማውጣቴ ሁከት አይደለም፣ መያዣው በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመና የተመዘገበ በመሆኑ ንብረቱን የመከተል መብት አለኝ፣ ንብረቱ በግብር እዲ ተሸጦ ባለቤትነቱ ለላላ ሰው የተላለፈ ቢሆን እንኳን ንብረቱን የመከተል መብቴን አያስቀርም፣ ቀደም ሲል በነበረው ክርክር ፍ/ቤቱ ንብረቱን የመከተል መብት ያለኝ መሆኑን አረጋግጧል፣ በመያዣ ውለ ምክንያት የሆነው እዲ የተሰጠው ለአመልካች አባት ነው ቤቱን ሲገዙ እዲ ያለበት መሆኑን ያውቃለ፤ በማለት የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ እንዱፀና ጠይቋል።
ከዚህ በተጨማሪ ችልቱ ኀዲር 2/2ዐዐ1 በነበረው ችልት የግራ ቀኙን የቃል ክርክር አድምጧል። ከላይ የተመለከተው የግራ ቀኙ ክርክርና የፍ/ቤቶች ውሣኔ ሲሆን ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔና አግባብነት ካላቸው የሕጉ ድንጋጌዎች አኳያ መርምሯል።
ከላይ እንደተመለከተው በዚህ መዝገብ መሰረታዊ የሆነው ጭብጥ ተጠሪ በመያዣነት የያዘው ንብረት በልላ ገንዘብ ጠያቂ ዕዲ ምክንያት በሃራጅ ከተሸጠ በኋላ የተጠሪ መብት ምንድነው? የሚለው ነው። በመሆኑም ይህንን ጭብጥ አግባብነት ካላቸው የፍ/ብ/ሕጉ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት መያዝ ከተደነገጉት ሕጎች አንፃር መመርመሩ ተገቢ ይሆናል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ከክርክሩ ሂደት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በሐጅ ኑር ሁሴን ምትኩ እና በባሕር ዲር ከተማ ልዩ ዞን አገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት በሃከል በነበረው የአፈፃፀም ክርክር ንብረቱ ከመሸጡ በፉት ተጠሪ ለሐጂ ኑር ሁሴን ምትኩ ለሰጠው ብድር በመያዣ የተሰጠው መሆኑን ተረድተናል። አንድ ባለገንዘብ በአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በሕጉ መሰረት የተቋቋመ የመያዣ ውል ካለው ውለ ሁለት ዓይነት መሰረታዊ መብቶችን ያጎናጽፈዋል። እነዚህም መብቶች በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3ዐ59/1/ እና /2/ ሥር የተመለከቱት ናቸው። ለውሣኔ ያመች ዘንድ ሕጎቹን በዝርዝር ማስቀመጡ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3ዐ59
3ዐ84/1/ እና /2/ መረዲት ይቻላል። በመሆኑም ምንም እንኳን አንድ ንብረት በመያዣ የተሰጠ ቢሆንም አስያዠ ንብረቱን ለላላ ሰው ለመሸጥ ለመለወጥ ወይም በስጦታ ለማስተላለፍ ይችላል። ዋናው ባለዕዲም ግዳታውን መፈፀም እስከቻለ ድረስ ባለገንዘቡ መያዣ በተሰጠው ንብረት ላይ መብት አይኖረውም። ነገር ግን ባለዕዲው ግዳታውን መፈፀም ሲያቅተው ንብረቱ ለልች 3ኛ ወገኖች ተላልፍ እንኳን ቢሆን በማስያዝ የመሸጥ መብት አለው። ይህ ንብረቱን የመከተል መብት ተፈፃሚም የሚሆነው ንብረቱ ለላልች ገንዘብ ጠያቂዎች ጥያቄ መሰረት ከመያዙ በፉት ነው።
ንብረቱ በላልች ገንዘብ ጠያቂዎች ከተያዘ በኋላስ መያዣ የተሰጠው ባለገንዘብ መብት ምንድነው ይህ ጥያቄ ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3ዐ59/1/ ሥር ወደተመለከተው የቀዲሚነት መብት ይወስደናል። የቀዲሚነት መብት /right of preference/ የሚነሣው በመያዣ የተያዘው ንብረት በላልች ገንዘብ ጠያቂዎች እዲ ተይዞ ንብረቱ በሃራጅ ከተሸጠ በኋላ የሚገኘው ገንዘብ በሁላችንም ገንዘብ ጠያቂዎች ዕዲ ለመሸፈን የማይበቃ ሲሆን ነው። አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣ የተሰጠ ቢሆንም መያዣ በልላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ዕዲም ተይዞ ሉሸጥ እንደሚችል ድንጋጌው ራሱ የሚናገር ሲሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1988/1/ ሥር በባለዕዲው ግዳታ አፈፃፀም በሕግ ሉያዙ አይገባውም ተብል ክልከላ ካልተደረገባቸው ንብረቶች በቀር ላልች የባለዕዲው ንብረቶች ሁለ ሉያዙ መሆኑ መደንገጉ በፍ/ሕ/ጠ 3ዐ59/1/ ሥር የተቀመጠውን ሃሣብ የሚያጠናክር ነው። ከዚህ በተጨማሪም አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከአንድ ለበለጠ ዕዲ በመያዣ ላሰጥ የሚችል መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3ዐ88/1/ ተመልክቷል። በመሆኑም በባለዕዲው ላይ መያዣ ያላቸውም ሆነ የላላቸው ባለገንዘቦች በመያዣ የተያዘውን ንብረት በማስያዝ ለማሸጥ መብት አላቸው። ይህ በሆነ ጊዜ መያዣ ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች የመያዣ መብታቸውን ባስመዘገቡበት ቅደም ተከተል ከሽያጩ ገንዘብ ላይ በቅድሚያ ገንዘባቸውን የማግኘት መብት ያላቸው በመሆኑ ንብረቱ በማንኛውም ገንዘብ ጠያቂ ተይዞ ከተሸጠ በኋላ የመያዣ መብት ያለው ገንዘብ ጠያቂ የሚኖረው ብቸኛ መብት ከሽያጩ ገንዘብ ላይ በቅድሚያ ዕዲቸውን መሰብሰብ ነው። ከዚህ በቀር ንብረቱ ተይዞ ከተሸጠና ከሽያጩ ገንዘብ በቅድሚያ እንዱከፈለው ሣይጠይቅ ቀርቶ ገንዘቡ በላልች ባለገንዘቦች መሃከል ከተከፊፈለ በኋላ ንብረቱን የመከተል መብት አለኝ በማለት የሚያነሣው መብት የለም። ምክንያቱም በመያዣ የተያዘው ንብረት በላልች ገንዘብ ጠያቂዎች ዕዲ ምክንያት ተይዞና በሐራጅ ተሸጦ ዋጋው ለባለመብቶቹ ከተከፊፈለ በኋላ መያዣው ቀሪ እንደሚሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
311ዐ/ሐ/ መገንዘብ ይቻላል። መያዣው ቀሪ ከሆነ ደግሞ መያዣውን መሰረት በማድረግ የሚያነሣው የመብት ጥያቄ አይኖርም ማለት ነው። ስለሆነም በንብረቱ ላይ የመያዣ መብት ያለው ባለገንዘብ ንብረቱን የመከተል መብት የሚኖረው ንብረቱ በማንኛውም ገንዘብ ጠያቂ ዕዲ ከመያዙና ከመሸጡ በፉት ነው።
የተያዘውን ጉዲይ ከፍ ሲል ከተዘረዘሩት የሕጉ ድንጋጌዎች አኳያ ስንመረምርም ተጠሪ ለክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት በመያዣ የያዘው መሆኑ አላከራከም። ነገር ግን የዚሁ ቤት ባለቤት በባሕር ዲር ልዩ ዞን አገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ላይ ባለባቸው የግብር ዕዲ ምክንያት ቤቱ ተይዞ በፍ/ቤት በኩል በሐራጅ በአሁኑ አመልካች ተሸጧል። ቤቱ ከተሸጠ በኋላ ተጠሪ በንብረቱ ላይ የመያዣ መብት ያለው መሆኑን በመግለጽ ሽያጩን ተቃውሟል። ፍ/ቤቱም ተጠሪ በቤቱ ላይ ባለው የመያዣ መብት መሰረት ንብረቱን ከሚከተል በቀር ሽያጩን ሉቃወም እንደማይችል ገልፆ ጥያቄውን ሣይቀበለው ቀርቷል። በእርግጥ በመያዣ የተያዘ ንብረት በልላ በማንኛውም ባለገንዘብ ዕዲ ተይዞ ሉሸጥ የሚችል በመሆኑ ፍ/ቤቱ ተጠሪ ሽያጩን በመቃወም ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ አግባብ ነበር። ሆኖም ንብረቱ በልላ ሰው ዕዲ ተይዞ በሐራጅ ሲሸጥ ተጠሪ የሚኖረው መብት ከሽያጩ ገንዘብ በቅድሚያ እንዱከፈለው መጠየቅ እንጂ ንብረቱን የመከተል መብት እንዲልሆነ ከላይ ከተመለከትናቸው የመያዣ ሕግ ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል። በመሆኑም ተጠሪ ንብረቱ በአገር ውስጥ ገቢ እዲ በሐራጅ ሲሸጥ ሽያጩን መቃወም ሣይሆን ከሽያጩ ገንዘብ ቅድሚያ እንዱከፈለው ሉጠይቅ ይገባ ነበር። ፍ/ቤቱም ንብረቱን የመከተል መብቱን ጠብቆ ሲያሰናብተው በዚሁ ላይ ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኙን አቅርቦ የቀዲሚነት መብቱ እንዱጠበቅለት ማድረግ ሲገባው ይህንን አላደረገም። በመሆኑም በክርክር ላይ ያለው ንብረት በባህር ዲር ልዩ ዞን አገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ዕዲ ተይዞ በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡ ለባለገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ተጠሪ ንብረቱን የመከተል መብት ስላለኝ በሃራጅ ሽያጩ ላይ ተወደድረው ከገዙት የአሁኗ አመልካች ላይ ይዤ መሸጥ እችላለሁ በማለት ያቀረበው ክርክርና ፍ/ቤቶችም ይህንኑ ክርክር ተቀብለው የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የምዕ/ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 17ዐ72 በ3ዐ/ዐ1/2ዐዐዐ የሰጠው ውሣኔ እና የአማራ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 14659 በ19/ዐ5/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ ተሽረዋል።
በባሕር ዲር ከተማ ቀበላ ዐ4 የቤት ቁጥር ዱ 151 የሆነውን ቤት በባሕር ዲር ልዩ ዞን አገር ውስጥ ገቢ እዲ ምክንያት ተይዞ በሐራጅ የተሸጠ ስለሆነ ንብረቱን የመከተል መብት ስለላለው ንብረቱን በጨረታ ለመሸጥ አይችልም ሁከቱ ይወገድ ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።