No summary available.
ታህሳስ 21 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- በላይ አበበ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የተጀመረው በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች በስር ከሣሽ ተጠሪዎች ደግሞ የስር ተከሣሽ ነበሩ አመልካች ባቀረቡት ክስ አንደኛ ተጠሪ የእንጀራ እናቴ ሁለተኛ ተጠሪ አባቴ ናቸው። በወረዲ 11 ቀበላ 15 ክልል በቤት ቁ. 433 ግቢ በራሴ ወጪ ቤት ሰርቼ እንድጠቀም ፈቅደውልኝ 40,000(አርባ ሺህ ብር) አውጥቼ ሰርቼ ይህንንም በህዲር 6 ቀን 1976 በጽሁፍ አረጋግጦልኝ ለ19 ዓመት እየኖርኩበት በሚያዝያ 11 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ መብራትና ውሐ በመቁረጥ ሁከት በመፍጠር ለቅቄ እንድወጣ አድርገውኛል።
ስለዚህ የስራሁትን ቤት እንዱያስረክቡኝ ፍቃደኛ ካለሆኑ ያወጣውትን 40,000 ብር (አርባ ሺህ ብር ) እና የደረሰብኝን ኪሣራ ይከፈለኝ ሲል ጠይቋል።
ፍ/ቤቱም ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ በማዘዝ በመልሳቸውም ተፈረመ የተባለው የስጦታ ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
2443 መሰረት ያልተፈፀመ ነው ስለዚህ ፈራሽ ነው። ስጦታ ተቀባዩ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2436 መሰረት መቀበለን አላረጋገጠም፣ውል ይፈጸምልኝ ለማለት በ1845 መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው። የቤቱ መለያ ያልታወቀ ነው። የመክሰስ መብት የለውም 40,000 ብር (አርባ ሺህ) አውጥቶ አልሰራም በኛ ገንዘብ ነው ቤቱ የተሰራው የውሃና የመብራት አልከፍልም በማለት ነው ሁከት ተፈጠረ የሚለው በማለት መልስ ሰጥቷል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አግባብነት ካለው ሕግ በማገናዘብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1179/1/ መሰረት ባለመሬቱ ሣይቃወም በልላ ሰው መሬት ሕንፃ የሰራ ሰው የዚሁ ሕንፃ ባለሐብት ነው ይላል። በዚህም ጉዲይ አመልካች በተጠሪዎች መሬት ቤት ሲሰሩ አልተቃወሙም ይልቁንስ መፍቀዲቸውን በጽሐፍ አረጋግጠዋል። ስለዚህ ጉዲይ መታየት ያለበት በስጦታ ውል መስፈርት ሣይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1179/1/ መሰረት ነው ስለሆነም አመልካች በቤቱ ውስጥ ሲኖሩ እንደነበር የተረጋገጠ ስለሆነ አመልካች የቤቱ ባለሐበት ናቸው የተፈጠረው ሁከት ይወገድ አመልካች ወደ ቤቱ ይመለሱ።
ተጠሪዎች ይህን የማይፈልጉ ከሆነ ግምቱን ያልተቃወሙ ስለሆነ 40,000 ብር (አርባ ሺህ ብር) ከፍለው ቤቱን የማስቀረት መብት አላቸው ሲል ውሳኔ።
ይግባኝ ባይም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለፋደራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታቸውን አቅርበው ፍ/ቤቱም ጉዲዩን በማከራከር ካዩ በኋላ የግራ ቀኙ ክርክር የሁከት ይወገድልኝ ጥያቄ ነው አንድ ሁከት ይወገድልኝ የሚል ወገን ሁከት የተፈጠረበትን ነገር በእጁ አድርጏ በእውነት የሚያዝበት ሆኖ መገኘት እንዲለበት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1140 በግልጽ ተደንግጓል አመልካች ሁከት ተፈጥሮብኛል ሉል የቻለበት በኀዲር 6 ቀን 1976 ዓ.ም የተፃፈ ውል ቤት ሰርቶ እንዱኖር የተሰማሙበትን ነው። እንደዚህ አይነት የስጦታ ውል ደግሞ በግልጽ በመደረጉ የጉዛዜ ስርአት መደረግ እንዲለበት ሕጉ ያዛል ከዚህ ስርአት ውጪ የሆኑት ስጦታ ፈራሽ ናቸው ሲል የፍ/ሕጉ /ቁ. 2443 ያዛል በመሆኑም የስጦታው ውለ ፍርማሉትን ያላሟላ ስለሆነ ፈራሽ ነው የተፈጠረ ሁከት የለም በማለት በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ሽሮታል።
አመልካችም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኙን ቢያቀርብም የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ዘግቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው በዚሁ ውሣኔ ባለመስማማት ነው።
አመልካች መጋቢት 17 ቀን 2000 ዓ.ም በቀረበው ማመልካቻ በፋደራል ከፍ/ቤት እና በፋ/ጠ/ፍ/ቤት የተሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ሲል አመልክቷል።
እኛም በዚሁም መሰረት አቤቱታ የቀረበበትን የስር ውሣኔ እና የአመልካች አቤቱታን አግባብ ካለው ሕግ ለማገናዘብ ተጠሪዎችን በማስጠራት ሰምተናል በመሆኑም ጉዲዩ ለሰበር ይቅረብ የተባለው አመልካች በስጦታ ውል አገኘሁት የሚለት ቤት ለመስራት ያወጡት ወጪ ሣይከፈላቸው የስር ፍ/ቤቶች የስጦታ ውለ ፈርሶ አመልካች ቤቱን ያስረክቡ መባለ በአግባቡ መሆኑን ለመመርመር ነው።፡ ጉዲዩን እንደመረመርነው የአመልካች ጥያቄ የነበረው በተጠሪዎች ይዞታ ላይ ባገኘው ፍቃድ ቤት ሰርቶ ለ”19” አመት የኖረበት እና ለግንባታውም 40,000 ብር (አርባ ሺህ ብር)እንዲወጣበት እና ተጠሪዎች በ1975 በተፃፈ ጽሁፍ ተስማምተው እንደሰጡት በመጥቀስና ከግዜ በኋላ መብራትና ውሐ አልከፈልክም በማለት ተጠሪዎች ከቤት እንዲስለቀቁት በመጥቀስ ሁከት ተወግድ ወደ ቤቱ እንዱመለስ ተጠሪ ካለፈቀደ አመልካች ለቤቱ ግንባታ ያወጣውን 40,000 ብር(አርባ ሺህ ብር) እንዱከፍለት ጠይቋል። የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤትም አመልካች በተጠሪዎች ፈቃድ ቤት ገንብተው ለ19 ዓመታት የኖሩበት መሆኑን በመረዲት ጉዲዩ መታየት ያለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1979/1/2/ መሰረት የሚታይ እንጂ በስጦታ ውለ መሰረት መታየት የለበትም ብል ሁከት ይወገድ አመልካች ወደ ቤቱ ይመለስ ተጠሪዎች ካልፈቀደ ለአመልካች 40,000 ብር(አርባ ሺህ ብር) ይክፈለ ሲል ሲወስን የከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዲዩ የሚታየው በስጦታው ውል መሰረት ነው በማለት የስር ውሣኔን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ሲሽር የፋ/ጠ/ፍ/ቤትም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ዘግቶታል።
No topics extracted.
በመሰረቱ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ የሚነቀፍ አልነበረም። ምክንያቱም ፍ/ቤቱ ለውሳኔው መሰረት ያደረገው የሕጉን አንቀጽ 1179/1/2/ ነው ይህ አንቀጽ ባለመሬቱ ሣይቃወም በልላ ሰው መሬት ላይ ህንፃ የሰራ የዚሁ ሕንፃ ባለሐብት ይሆናል በዚህም ጉዲይ አመልካች በቤቱ ውስጥ ለ19 አመት መኖሩ በተጠሪ አልተካደም መብራትና ውሐ ስላልከፈለ ነው የወጣው(የለቀቀው) ሲለ ተከራክረዋል ይህ ደግሞ ከመጀመሪያውኑ ፍቃድ(ስምምነት) እንደነበረ የሚያመለክት ነው አመልካችም ይህንኑ በግምት በማስገባት ቤቱን ይገነባል ተብል ይታመናል በልላ በኩል ፍ/ቤቱም አመልካች በራሱ ወጪ ቤት ለመስራቱም አረጋግጧል። የከፍተኛው ፍ/ቤትም የስጦታ ውለን ቢያልፈው (ፈራሽ) ነው ቢል እንኳ አመልካች ያለ ምንም ተቃውሞ ለ19 አመት የኔ ነው በሚል እምነት የኖረበትን እግምት ማስገባት ሲገባው የአመልካች አባት (ወላጅ) ሁለተኛ ተጠሪ አመልካች ቤቱን ሰርቶ መኖር ከጀመረ በኋላ ቤቴን ለልጄ ሰጥቻለሁ ብለው ጽፈው ለሽማግላዎች ያስፈረሙትን ጽሐፍ መሰረት በማድረግ ሁከት የለም በማለት የስር ውሣኔን መሻሩና የፋ/ጠ/ፍ/ቤትም ይህንን ማረም ሲገባው መዝገቡን ጉድለት የለበትም ብል መዝጋቱ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመዝገቡ ቁ.44725 በጥር 7 ቀን 2000 ዓ.ም እና በጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 35834 በ8/7/2000 የተሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 02183 ጥር 4 ቀን 1998 የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ተጠሪ አመልካች ወደ ቤቱ እንዱመለሱ ካልፈቀደ አመልካች ያወጣውን 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ይክፈለ ብለናል። ይፃፍ።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።