No summary available.
ታህሣሥ 7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ሐጂ መሐመድ አወል ረጃ - ጠ/ደሣለኝ አለሙ ክብረት ተጠሪ፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው የሁከትን ጉዲይ የሚመለከትን ነው።
የአሁኑ አመልካች በሥር ፍ/ቤት ከሣሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሣሾች ነበሩ። አመልካች ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በሰበታ ወረዲ ካራብህርቡ ቀበላ ገ/ማኀበር ውስጥ ሁለገብ የአረብኛ እና የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል አቋቁው እየሰሩ ባለበት ወቅት ተጠሪዎች ድንበሩን ለመከላከል የተቆፈረው አፈር በመሙላት፣ የጥበቃውን ቤት በማፍረስና የተማሪዎቹን መኖሪያ በቁፊሮ በማናጋት ሁከት እየፈጠሩ በመሆኑ ሁከቱ ተወግድ በሁከቱ ምክንያት ለደረሰው ጉዲት ካሣ እንዱከፍለ በማለት ጠይቀዋል። ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ሁከት ተፈጠረበት የተባለው ቦታ በአመልካች ይዞታ ስር መሆኑና በዚሁ ቦታ ላይ ተጠሪዎች ሁከት መፍጠራቸው በማስረጃ ስለተረጋገጠ ሁከቱ እንዱወገድ፣ በሁከቱ ምክንያት ለደረሰው ተጠሪዎች ብር 45ዐዐ.00 /አራት ሺህ አምስት መቶ/ ይክፈለ በማለት ወስኗል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን አከራከሮ ይዞታ የሚረጋገጠው በፍ/ሕ/ቁ. 1195 መሰረት ከሚመለከተው አስተዲደር መ/ቤት በተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ወይም ካርታ ነው፣ አመልካች ይዞታው የራሣቸው መሆኑን ለማስረዲት ይህን መሰል የሰነድ ማስረጃ አላቀረቡም፣ ስለሆነም ባለይዞታ መሆናቸውን ሳያስረደ ተጠሪዎች ሁከት ፈጥረዋል ተብል የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈጠረበት ነው በማለት ውሣኔውን ሽሯል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ላይ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም የሁከትን ጉዲይ ለመወሰን አመልካች በፍ/ሕ/ቁ. 1195 መሰረት ከአስተዲደር መ/ቤት የተሰጠ የባለይዞታነት ማረጋገጫ መቅረብ አለበት በማለት የሰጠውን ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ አድርጓል። ተጠሪዎችም ለቀረበው የሰበር አቤቱታ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ከላይ እንደተመለከተው አመልካች ስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ በይዞታቸው ላይ ተጠሪዎች ሁከት እየፈጠሩ በመሆኑ ሁከቱ ተወግድ በሁከቱ ምክንያት ለደሰረሰው ጉዲት ኪሣራውን ተጠሪዎች እንዱከፍለ ነው። በይዞታው የተወሰደበት ወይም በይዞታው ላይ ሁከት የተነሣበት ሰው የተወሰደበት ነገር እንዱመለስለት ወይም የተነሣው ሁከት እንዱወገድለት እንዱሁም ስለደረሰበት ጉዲት ኪሣራ እንዱሰጠው መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 1149/1/ ሥር ጠ/ አምሃ ነጋሽ ቀረቡ።
ተመልክቷል። ይዞታ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በፍ/ሕ/ቁ. 114ዐ ሥር ትርጓሜ ተሰጥቶታል። ይዞታ ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር በእጁ አድርጎ በእውነት የሚያዝበት ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ ከዚህ ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። በመሆኑም በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ ሰው ባለይዞታ ነው ለማለት በግድ በይዞታው ላይ ባለሃብት መሆን እንደላለበት መገንዘብ ይቻላል። በዚህም ምክንያት አንድን ነገር በእጁ አድርጎ በእውነት ያዝበት የነበረ መሆኑን ካስረዲ ባለይዞታ መሆኑ ይረጋገጣል ወደ ፍ/ሕ/ቁ. 1195 ስንመለስ ግን ይህ ድንጋጌ የሚገናረው ስለባለሃብትነት /ownership/ ነው። በመሆኑም አንድ ሰው የማይንቀሣቀስ ንብርት ባለሀብት መሆኑ ከሚመለከተው አስተዲደር ክፍል የሚሰጠውን የባለሃብትነት የምስክር ወረቀት በማቅረብ ማስረዲት ይችላል። በእርግጥ መሬት የማይንቀሳቀስ ንብረት ቢሆንም የመሬት ባለሀብት መሆን ባይችልም የመሬቱ የይዞታ ባለሀብት መሆኑን በማረጋገጥ ግን ተመሣሣይ ማስረጃ ማቅረብ ይገባል። በመሆኑም በፍ/ሕ/ቁ. 114ዐ እና 1195 መሃከል የሰፊ ልዩነት አለ። የመጀመሪያው አንድን ነገር ይዞ መገልገል ባለይዞታ የሚያደርግ መሆኑን የሚልጽ ሲሆን ሁለተኛው ግን አንድን ነገር ይዞ መገልገልን ብቻ ሣይሆን ከዛ ባለፈ የዚሁ ነገር ባለቤት መሆንን ለማረጋገጥ የሚያገለግል ድንጋጌው ነው። ስለሆነም የሁከትን ክስ ለማቅረብ ከሣሽ ማስረዲት ያለበት ሁከት ተፈጠረ የተባለበትን ነገር በእጁ አድርጎ በውነት ያዝበት የነበረ መሆኑን ብቻ እንጂ የዚሁ ነገር ባለሃብት መሆኑን አይደለም።
No topics extracted.
ስለሆነም የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካች ባቀረቡት የሁከት ይወገድልኝ ክስ የፍ/ሕ/ቁ. 1195 መሰረት አድርጎ መወሰኑ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ተገንዝበናል። በልላ በኩል ግን አመልካች ሁከት ተፈጠረ የተባለበትን በእጃቸው አድርገው ያዙበት የነበረ ለመሆኑ እና ተጠሪዎችም ሁከት የፈጠሩ መሆኑ በሥር ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት አለበት ለማለት አይቻልም።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 58254 በ16/ዐ4/2ዐዐዐ የሰጠው ውሣኔ እና በፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 3585ዐ በ12/ዐ7/2ዐዐዐ የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 19195 በዐ4/11/99 የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ተጠሪዎች በአመልካች ቦታ ላይ የፈጠሩት ሁከት ሉወገድ ይገባል። በሁከቱ ምክንያት በደረሰው ጉዲትም ብር 45ዐዐ.00 /አራት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ሉከፍለ ይገባል ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።