No summary available.
ታህሳስ 2 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ በላቸው አንሺሶ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነገረፈጅ አቶ በላይነህ አለማየሁ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አለምነሽ ዋቅጅራ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ወለጋ ዞን ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሳስ 17 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ የካቲት 27 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ሚያዚያ 10 ቀን 2000 ዓ.ም ባቀረበው የሰበር አቤቱታ ስለጠየቀ ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች በነቀምቴ ከተማ ቀበላ 02 ቁጥሩ 964 የሆነውን የመኖሪያ ቤት በመያዥያነት በመያዝ ብድር ያበደረ ሲሆን ተጠሪ ይኸ ቤት የአቶ ይማሙ ባቲና የእሷ የጋራ ንብረት መሆኑንና የመያዥያ ውለ እሷ ሣታውቅና ሳትፈቅድ የተፈፀመ በመሆኑ በእሷ ድርሻ ላይ ውጤት እንደላለው እንዱወሰንላት ክስ አቅርባ አመልካች በመያዥነት የያዘው ቤት የተጠሪ የጋራ ሐብት እንደሆነና የመያዥያ ውለም የተጠሪን ድርሻ ውጤት የላለው መሆኑን በፍርድ አስወስናለች አመልካች ቤቱን ለመሸጥ፣የቤቱን ግምት 28,092/ሃያ ስምንት ሺ ዘጠና ሁለት ብር/ መሆኑን በመግለጽ የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል። ተጠሪ አመልካች የጋራ ንብረቷን ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ በመቃወም የቤቱ ግማሽ ባሐብት መሆኔና መያዥያው የእኔን ድርሻ የማይመለከት መሆኑ በፍርድ የተረጋገጠ ስለሆነ በዚህ መሰረት ይፈፀምልኝ በማለት አመልክታለች። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ የቤቱ ግምት ግማሽ ዋጋ ለአመልካች ከፍላ ቤቱን የግሎ ታድርግ በማለት የአፈፃፀም ትእዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኙን ሰርዞታል። አመልካች ይኸ ትእዛዝ በግማሽ የመያዥያ መብት ያለን መሆኑ የተረጋገጠውን ቤት፣በገበያ ዋጋ በመሸጥ በተሻለ ሁኔታ መብታችንን የማስከበርና እዲችንን የመሰብሰብ መብታችን የሚያሳጣና የቤቱን የመሐዱስ ግምት ግማሽ ዋጋ በመክፈል ተጠሪ ቤቱን እንድትረከብ የሚያደርግ፣ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ይታረምልን በማለት ያመለከተ ሲሆን ተጠሪ በበኩሎ አመልካች የእኔን ድርሻ ጨምሮ ለመሸጥ የሚፈቀድለት ሕግ የለም። ስለዚህ የስር ፍርድ ቤቶች የቅድሚያ የመግዛት መብቴን በመጠበቅ የሰጡት ትእዛዝ የሕግ ስህተት የላለበት በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ሐምል 8 ቀን 2000 ዓ.ም ባቀረበችው መልስ ተከራክራለች።
አመልካች የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል። የክርክሩ መሰረታዊ ጉዲይ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። ጉዲዩን እንዲየነው አመልካች ክርክር በተነሳበት ቤት ላይ ከፉል የመያዥያ መብት ያለው መሆኑና ተጠሪዋ በበኩሎ የንብረቱ የጋራ ባለሐብት መሆኗ አያከራክርም። የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የጋራ ሐብቷ የሆነውንና በከፉል የአመልካች ባለመብት የሆነበትን ቤት ቅድሚያ የመግዛት መብት ያላት መሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1261/1/ ተደንግጓል። ስለዚህ ተጠሪ ቤቱን የመግዛት መብት አላት በማለት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ትእዛዝ የሕግ ስህተት የለበትም።
ሆኖም ተጠሪ ቤቱን በቅድሚያ የመግዛት መብቷን ተጠቅማ የምትገዛውና ለአመልካች ገቢ የምታደርገው የቤቱን የመሐድስ ግምት ዋጋ መሰረት ነው ወይስ ቤቱ በገበያ የሚያወጣውን እርግጠኛ ዋጋ የሚለው ነጥብ የስር ፍርድ ቤቶች በትኩረት አላዩትም። ተጠሪ ቤቱን የመግዛት የቅድሚያ መብት ያላት ቢሆንም ቤቱን የምትገዛው በመሐድስ ግምትና መነሻ ዋጋ ግማሹን በመክፈል ሣይሆን ቤቱ ለግልጽ ጨረታ ቀርቦ ያወጣውን እርግጠኛ ዋጋ ግማሹን በመክፈል ነው።
ስለሆነም የስር ፍርድ በቶች ተጠሪ የቤቱን የመሐዱስ ግምት ግማሽ ዋጋ በመክፈል ቤቱን የግሎ ታድርግ በማለት የሰጡት ትእዛዝ የአመልካችን ንብረቱን በዋጋው የመሸጥ መብት የሚጋፈት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ወለጋ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ትእዛዝ ተሻሽሎል ይፃፍ።
በነቀምቴ ከተማ ቀበላ 02 የሚገኘውና ቁጥሩ 964 የሆነው መኖሪያ ቤት ለግልጽ ጨረታ ከወጣ በኋላ ተጠሪ ቤቱ ያወጣውን ከፍተኛ ዋጋ ግማሹን ለአመልካች ገቢ በማድረግ የጋራ ንብረቷን በቅድሚያ የመግዛት መብቷን ትጠቀም ብለናል።
No topics extracted.
ተጠሪ ቤቱ በግልጽ ጨረታ የሚያወጣውን ዋጋ ግማሹን ለአመልካች ገቢ ማድረግ ካልቻለ ቤቱ ለጨረታ አሸናፉው ተሸጦ የቤቱ ግማሽ ዋጋ ለተጠሪ ይከፈላት ብለናል። ግማሹ ለአመልካች ይከፈለው ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡት ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ራሳቸውን ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር ሰሚ ችልት ታህሣስ 2 ቀን 2001 ዓ.ም በመለ ድምጽ ተሰጠ።