No summary available.
ታህሣሥ ዐ2 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ በላቸው አንሺሶ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ - ነ/ፈጅ በላይነህ ዓለማየሁ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ እታለም ተስፊ - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኗ ተጠሪ በነቀምቴ ከተማ ቀበላ ዐ7 ክልል ውስጥ የሚገኘውን በቁጥር 864 የተመዘገበውን የመኖሪያ ቤት ባለቤታቸው አቶ አብሽሩ ብልሃት ከአመልካች ድርጅት ገንዘብ ሲበደሩ ተጠቃሹን ቤት ከተጠሪ እውቅና ውጪ ለብድሩ በዋስትና ያስያዙ ሁኖ አግኝተው በቤቱ ላይ ያላቸው ድርሻ እንዱጠበቅላቸው ዘንድ በፍ/ቤት ክስ መስርተው ክርክር ከተካሄደ በኋላ ፍ/ቤቱ ተጠሪ በቤቱ ላይ ያላቸውን ግማሽ መብት በመጠበቅ ውሣኔ ሰጥቶ ይህ ውሣኔ በበላይ ፍ/ቤት አለመለወጡን፣ በቤቱ ላይ ያላቸው መብት በፍ/ቤት ውሣኔ ተጠብቆላቸው እያለ ግን አመልካች በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ መሰረት ተጠቃሹን ቤት በሐራጅ ለመሸጥ በጋዜጣ ማስታወቂያ አውጥቶ በዝግጅት ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው በቀድሞ ውሣኔ መሰረት እንዱፈፀምላቸው ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ አመልካች በምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመሰረቱት የአፈፃፀም ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካችም በፉት በተሰጠው ውሣኔ መሰረት በንብረቱ ላይ የመያዝ መብት እንዲለው መረጋጉጡን፣ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቱን በሐራጅ በመሸጥ ለተጠሪዋ በፍ/ቤቱ ውሣኔ መሰረት ለመፈፀም በዝግጅት ላይ ባለበት ጊዜ የቀረበ ጥያቄ መሆኑን በመግለጽ የተጠሪዋ የአፈፃፀም ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ ክርክር የተነሣበት ንብረት ላይ ተጠሪዋ መብት እንዲላቸው ከዚህ በፉት በተሰጠው ውሣኔ የተረጋገጠ ስለሆነ የተጠሪዋን መብት ወደ ጎን በመተው ንብረቱን በሐራጅ ለመሸጥ ማስታወቂያ ማውጣቱ የሕግ አግባብነት የለውም የሚለውን ነጥብ በምክንያትነት በመያዝ ንብረቱ በሐራጅ የቀረበበትን ዋጋ .50 /አስራ ስድስት ሺህ ሦስት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከሃምሣ ሣንቲም/ ግማሽ ብር 8174.75/ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ሰባ አራት ብር ከሰባ አምስት ሳንቲም/ ተጠሪዋ ለአመልካች ከከፈለ በኋላ የንብረቱ ስም ወደ ተጠሪዋ እንዱዞር በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ላይ ቅር በመሰኘት ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ይኸው ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ትዕዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነ/ፈጅ ሚያዝያ 1ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ አመልካች በንብረቱ ግማሽ ላይ የፍርድ ባለመብት ሁኖ እያለ የበታች ፍ/ቤቶች ትዕዛዝ ይህንኑ ሁኔታ ያላገናዘበ መሆኑን፣ እንዱሁም በቤተሰብ ሕጉ ላይ የተመለከተውን የጋብቻ የጋራ ንብረት ክፍፍል አፈፃፀምን መሰረት ያላደረገ መሆኑን፣ የመሐንዱስ ግምት የገበያ ዋጋ የማይወክል መሆኑን፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ላይ አመልካች በግማሽ መብቱ በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ መሰረት ማስፈፀም እንደሚችል ተረጋግጦ እያለ በአፈፃፀም ወቅት መሻሩ ያለአግባብ መሆኑን መበዘርዘር የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ተሽሮ ክርክር ያስነሳው ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ መሰረት በሀራጅ ተሸጦ አመልካችና ተጠሪ እኩል እንዱካፈለ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ሐምል ዐ8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የመልሣቸው ይዘትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ነጥቦችን ያላግባበነት፣ የበታች ፍ/ቤቶችን ትዕዛዝ ደግሞ ሕጋዊ መሰረት ያለው መሆኑን የሚያሣይ ነው። አመልካችም ሐምል 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሱን አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ተጠሪ በመያዣ ንብረት ላይ ያላቸው የድርሻ መብት የሚታሰበው ከሐራጅ የሽያጭ ገንዘብ ሣይሆን በሐራጅ መነሻ ዋጋ መሰረት ነው ተብል ተጠሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ግማሹን ለአመልካች እንዱከፍለ መወሰኑ ባግባቡ መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
No topics extracted.
በክርክሩ ሂደት አመልካች ለክርክሩ መነሻ በሆነው ንብረት የመያዣ መብት እንዲለውና በግማሽ የፍርድ ባለመብት መሆኑ፣ ንብረቱ በዓይነት ሉከፊፈል የማይችል መሆኑ እና ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍለ የተደረገውም የመሐንዱሱን ግምት ግማሽ ዋጋ መሆኑ የተረጋገጡ ጉዲዮች ናቸው።
የአመልካችና የተጠሪ በቤቱ ላይ ያላቸው የጋራ ባለሀብትነት በፍርድ የተቋቋመ ነው። በሕጉ መሰረት የተፈጠረ የጋራ ባለሀብትነት ደግሞ የሚገዛው አግባብነት ባለው ሕግ ነው። ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1259-1277 ያለት ድንጋጌዎች የሚያሣዩትም ይህንኑ ነው። የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 126ዐ/1/ ድንጋጌ የሚገልፀው ደግሞ እያንዲንደ የጋራ ባለሀብት ድርሻውን ለመሸጥ ወይም በላልች መንገድች የማስተላለፈ ወይም ለማስያዝ መብት ያለው መሆኑን ነው። በመሆኑም እነዚህ ስልጣኖች ላልች የጋራ ባለሃብቶች እየተቃወሙ ቢሆን እንኳን ባለድርሻው የጋራ ባለሃብት የሚተገብራቸው፣ በሕግ የተጠበቁ ናቸው።
በልላ በኩል የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1261፣ 1388 እና 14ዐ6 ድንጋጌዎች ይዘት ሲታይ የጋራ ባለሀብቶች ያልተከፈለውን የጋራ ንብረት ከማንኛውም 3ኛ ወገን በፉት፣ ሉሸጥ የታሰበውን ድርሻ አስገድድ ለመግዛት የቅድሚያ መብት ያላቸው መሆኑን ያስረዲል። በመሆኑም የበታች ፍ/ቤቶች ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት እንዱገዙት መወሰናቸው የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በዚህ ረገድ የቀረበ የሰበር አቤቱታም የለም።
ይሁን እንጂ የተጠሪ የቅድሚያ ግዢ መብት ሲጠበቅ የቤቱ ዋጋ በመሐንዱስ ተገምቶ በቀረበው መሆን አለበት ተብል የመወሰኑ አግባብነት የቤቱ ትክክለኛ ግምት ተደርጎ ሉወሰድ ከሚገባው ዋጋ መነሻ ባለመሆኑ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም። የመሐንዱሱ ግምት ቤቱን ለመስራት የወጣውን ወጪ /Book value/ ከሚያሣይ በስተቀር የቤቱ የወቅቱ የገበያ ዋጋን /Market value/ በሚያሣይ የተሰላና በዚህ ግንዛቤ የቀረበ አይደለም። በመሆኑም የመሃንዱስ ግምት የወቅቱን የገበያ ዋጋ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ሣይረጋገጥ የቤቱ ትክክለኛ የወቅቱ ግምት ተደርጎ ሉወሰድ የሚገባ አይደለም። አመልካችና ተጠሪ የቤቱን የወቅቱ የገበያ ዋጋ የተስማሙበትም አይደለም።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1261/2/ ድንጋጌ ሕጋዊ የሆነ የቀዲማይነት መብት በስራ ላይ የሚውልበት አኳኋን የሚመራው በፍትሐብሕር ሕጉ ሦስተኛ መጽሐፍ አንቀጽ 6 ምዕራፍ አራት በተነገረው ድንጋጌ ደንብ መሰረት ስለመሆኑ ያጣቅሣል።
በዚህ ምዕራፍ የተመለከቱት ስለቀዲሚነት ግዢ ይገባኛል የማለት መብት የሚገዙት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1386-14ዐ9 ድረስ ያለት ድንጋጌዎች ደግሞ የሽያጩ አኳኋን በሐራጅ ወይም ያለሀራጅ በሻጭና በገዢ ስምምነት ላደረግ የሚችል መሆኑን ያሣያለ። በመሆኑም የጋራ ንብረቱ ዋጋ ስምምነት ሉቆረጥ ካልቻለ የሽያጭ ሂደቱ በሐራጅ ተከናውኖ የንብረቱ የገበያ ዋጋ ይታወቃል። በዚህ ሂደት የንብረቱ ዋጋ ሲታወቅ የጋራ ባለሃብቱ የቅድሚያ ግዢ መብት ይኖረዋል። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ከላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መንፈስ የላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 11851 ኀዲር 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 6ዐ273 ጥር 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ በትዕዛዝ የፀናው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በነቀምቴ ከተማ ቀበላ ዐ2 ክልል ውስጥ የሚገኘው ቁጥር 864 የሆነ የመኖሪያ ቤት ግልጽ ጨረታ ከወጣበት በኋላ ተጠሪ ቤቱ ያወጣውን ከፍተኛ ዋጋ ግማሹን ለአመልካች ገቢ በማድረግ የጋራ ንብረቷን በቅድሚያ የመግዛት መብቷን ትጠቀም ብለናል።
ተጠሪ ቤቱ በግልጽ ጨረታ የሚያወጣውን ዋጋ ግማሹን ለአመልካች ገቢ ለማድረግ ካልቻለ ቤቱ ለጨረታ አሸናፉው ተሽጦ የቤቱን ግማሽ ዋጋ የማግኘት መብት የተጠበቀ ነው ብለናል። ግማሹን ለአመልካች ይከፈል ብለናል።
ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።