No summary available.
የሰ/መ/ ህዲር 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ረዲት ሳጂን አያኖ አንጀል - ቀረበ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ዓለሚቱ ጫላቦ- ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ብ/ክ/መ/ በወላይታ ዞን በአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች በአንደኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ተከሳሽ ንብረትነቱ የእራሷና የሟች ባለቤቷ የሆነውን በ270 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተሰራ ቤት በ26/10/94 በተጻፈ ውል ሸጣልኝ ቤቱን አስፊፍቼ ለመሥራት እንሰት ለመንቀል ስጀምር አላስነቅልም፣ ቤቱንም ቦታውንም አልሸጥኩም በማለት ሁከት የፈጠረችብኝ ስለሆነ ይሄው ሁከት ይወገድልኝ በማለት ጠይቀዋል።
አንደኛ ተከሳሽ የአሁን አመልካች ቀርበው ሁከት ተፈጥሮበታል የተባለውን ቤት ለከሳሽ እንዲልሸጡና በውለ ላይም እንዲልፈረሙ ከሳሽ በቤቱ ውስጥ የሚኖረው በተከራይነት መሆኑን ገልጸው ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል ሁለተኛ አመልካችም በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት ጠይቀው ተፈቅድላቸው የሟች አባታቸው ወራሽ መሆናቸውን ገልጸው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በሽያጭ ለከሳሽ እንዲልተላለፈና በቤቱ ውሰጥ በኪራይ እንደሚኖሩ ጠቅሰው ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር ተመሳሳይ የሆነው ክርክር አቅርበው ክሱ ሉሰረዝ ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሳሽ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ቤት ከአንደኛ ተከሳሽ የገዙት መሆኑን ቢገልጽም በአስረጂነት ያቀረቡት ሰነድ በአንደኛ ተከሳሽ ያልተፈረመበት መሆኑ ስለተረጋገጠና ከሳሽም እራሱ በሰነድ ላይ ስለመፈረሙ በዚህ ሁኔታ ሁከት ይወገድልኝ ተብል የቀረበው ክስ አግባብነት የለውም በማለት አቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ የሥር ፍ/ቤት ለጉዲዮ እልባት መስጠት የነበረበት ሁከት አለ ወይንስ የለም? ከሚለው ጭብጥ አኳያ መሆን ሲገባው የውለን ሕጋዊነት በጭብጥነት ይዞ ጉዲዮን በመመርመር ውለ በአግባቡ ስላልተደረገ ሁከት የለም በማለት ውሳኔ መስጠቱ በተገቢው አይደለም ካለ በኋላ ሁከት ስለመፈጠሩ በይግባኝ ባይ ማስረጃ መረጋገጡን መገንዘብ ስለሚቻል የተፈጠረው ሁከት ሉወገድ ይገባል በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር ውሳኔ ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላም ተጠሪዎች የይግባኝ ቅሬታቸውን በክልለ ጠ/ፍ/ቤት አቅርበው ጠቅላይ ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙ አከራክሮ መልስ ሰጭ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ያቀረቡት በሕግ የማይጸና ውልን መሰረት አድርገው ስለሆነ ጉዲዮን በመጀመሪያ የዲኝኘነት ሥልጣኑ በተመለከተው የአረካ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውለ በሕግ አግባብነት ያልተቋቋመ ስለሆነ የቀረበው የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ማለቱ አግባብነት ያለው ሆኖ ሳለ የከፍተኛው ፍ/ቤት ይህንኑ ውሳኔ መሻሩ በአግባቡ አይደለም በማለት የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱን ውሳኔ አጽንቷል።
የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመበትም በማለት የሰበር አቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ለዚህ ችልትም የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ያቀረቡት ክስ ሁከት ይወገድልኝ የሚል ሆኖ ሳለ የቤት ሽያጭ ውለ የሚጸና አይደለም ተብል መወሰኑ አግባብነቱ ለሰበር ቀርቦ መጠራት እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን በጽሐፍ አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብስ አኳያ የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ እነደሚከተለው ተመርምሯል።
በጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር አቤቱታው ያስበቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
በሥር ፍ/ቤት አመልካች በአንደኛ ተጠሪ ላይ ክስ ያቀረቡት የመኖሪያ ቤት በውል ሸጠውልኝ ይህንኑ ቤት አስፊፍቼ ለስራት በነበረኝ ፍላጏት ሥራውን ስጀምር እንዲልሰራ የከለከለኝ ስለሆነ የተፈጠረው ሁከት ይወገድልኝ በማለት ነው።
ይዞታው የተወሰደበት ወይም በይዞታው ላይ ሁከት የተነሳበት ሰው የተወሰደበት ነገር እንዱመለስለት ወይም የተነሳው ሁከት እንዱወገድለት ዲኝነት መጠየቅ እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ1149/1/ ላይ ተመልክቷል። ይዞታ ማለት ደግሞ አንድ ሰው አንድን ነገር በእጁ አድርጏ በእውነት የሚያዝበት ሆኖ ሲገኝ እንደሆነም በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1140 ላይ ተመልክቷል።
No topics extracted.
ከዚህ የሕጉ ድንጋጌ አኳያ አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ ባለይዞታ እንዱባል ነገሩ በእጁ መገኘት እንደሚገባውና የነገሩ በእጁ መገኘትም ይዞታ ያለው ስለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ አንደሆነ መገንዘብ ይቻላል እዚህ ላይ ትኩረት ሉሰጠው የሚገባ ነጥብ አንድ ሰው ንብረቱ በእጁ አድርጏ በእውነት የሚያዝበት የመሆኑ ጉዲይ ነው። በእውነት የሚያዝበት የሚለው አባባል የሚያስገነዝበው ንብረቱን በእጁ አድርጏ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን በዚህ ንብረት ላይ በእውነት ማዘዝ እንዱችል የንብረቱ አያያዝ ያልተጨበረበረና በማናቸውም መንገድ ሕገወጥ በሆነ ሁኔታ ያልተገኘ መሆን እንደሚገባው ነው።
አመልካች ከፍ ብል እንደተጠቀሰው ቤቱ የያዙት አንደኛ ተጠሪ ጋር ባደረጉት የቤት ሽያጭ ውል መነሻነት እንደሆነ ጠቅሰዋል። አንደኛ ተጠሪም በበኩላቸው ቤቱን ለአመልካች እንዲልሸጡና በአመልካች በኩልም የሽያጭ ውል መኖሩን ያረጋግጣል ተብል የቀረበው ሰነድ በሕግ አግባብነት ያልተቋቋመ መሆኑን ገልጸው ይልቁንም ከሳሽ በቤቱ ውስጥ የሚገኙት በኪራይ ውል መነሻነት እንደሆነ ጠቅሰው ተከራክረዋል።
ከዚህ የተጠሪ ክርክር ሁከት ተፈጥሮበታል የተባለው ቤት በተጭበረበረ አኳኋን አመልካች እጀ ሉገባ እንደቻለ መገንዘብ አይቻልም። በመካከላቸው ተደርጓል የተባለው ውል ተገቢውን የአጻጻፍ ሥርአት /Form/ ተከትል አልተደረገም ቢባል እንኳን ይህ ሁኔታ በእራሱ አመልካች ቤቱን በተጭበረበረ መንገድ እንደያዙትና በእውነት የሚያዙበት እንዲልሆነ የሚያረጋግጥ አይደለም። የውለ ተገቢውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትል አለመደረግ ይዞታው በተጨበረበረ መንገድ ስለመያዙ ወይንም በማናቸውም ሕገወጥ ሁኔታ ስለመያዙና አመልካችም በይዞታው በእውነት ሉያዙበት እንደማይችለ ስለማያረጋግጥ በዚህ ረገድ ውለ ጉድለት አለበት ከተባለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1808(2) ላይ እንደተመለከተው ውለ ፈራሽ ነው እንዱባል የክስ ምክንያት ከሚሆን በስተቀር ሁከት ይወገድልኝ ተብል በቀረበ ክስ ላይ ሉስተናገድ የሚችል አይሆንም ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንደኛ ተጠሪ አመልካች ቤቱን ይዘው የሚገኙት በመካከላችን በተደረገው የቤት ሽያጭ ውል መነሻነት ነው በማለት የጠቀሱት ቤቱ በአመልካች በተጭበረበረ ሁኔታ እንዲልተያዘና በተገቢው መንገድ እንደተያዘና በእውነትም የሚያዙበት መሆኑን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው። ስለሆነም ጉዲዮን በይግባኝ የተመለከተው የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በጭብጥነት ተይዞ መፈታት የሚገባው ጉዲይ ሁከት አለ ወይንስ የለም? የሚለው ነው በማለት በዚህ ጭብጥ ላይ ተመስርቶ ጉዲዮን በመመርመር በአመልካች ይዞታ ላይ ተጠሪ ሁከት ስለመፈጸማቸው የተረጋገጠ ስለሆነ ይኸው ሁከት ይወገድ ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ በእኛ በኩልም ተቀባይነት ያለው ሆኖ ተገኝቷል። ነገር ግን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የቤት ሽያጭ ውለ በሕግ አግባብነት ስላልተቋቋመ በዚህ ውል ላይ ተመስርቶ የቀረበው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ተቀባይነት የለውም ሲል የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትን ውሳኔ ማጽናቱ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።