No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 35ዐዐ3 ህዲር 9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አቶ አሸናፉ ዓብደልቃድር - ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ሽቶ ኢብራሂም/ 4 ሰዎች/ - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው የውርስ ንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ጉዲይ ነው።
የአሁኑ አመልካች በሻሸመኔ ወረዲ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ሟች አባታቸው በኑዛዜ ያወረሷቸውን ቤት ተጠሪዎች እንዱያካፈሎቸው ጠይቀዋል አንደኛ ተጠሪ የሟች ሚስት በሕይወት እያለ የውርስ ንብረት ክፍፍል ሟች በኑዛዜያቸው ስለገለፁ ክፍፍለ ሉፈፀም አይገባም በማለት ተጠሪዎች መልስ ሰጥተዋል ፍ/ቤቱም የውርስ ንብረት አጣሪ አቋቁሞ የውርሱ ንብረት እንዱጣራ አድርጎ የውርስ ንብረት የሆነው በሻሸመኔ ከተማ ቀበላ ዐ8 ክልል ውስጥ የሚገኝ ቁጥር 544 የሆነ በ5ዐዐ ካ.ሜ. ላይ የሰፈረ ቤት መሆኑን ተረጋግጦ ቀርቦለታል። ከዚህም በኋላ ይኸው ቤት በባለሙያ ተገምቶ ግምቱ ብር 41,078.77 (አርባ አንድ ሺህ ሰባ ስምንት ብር ከሳሰባት ሳንቲም)መሆኑ ተገልጿል። ፍ/ቤቱም አንደኛ ተጠሪ የሟች ሚስት በመሆናቸው የቤቱ ግማሽ የሣቸው ድርሻ ነው የግምቱን ግማሽ ግን አመልካችና ቀሪዎቹ ተጠሪዎች ይካፈለ በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት በመጀመሪያ ለምስ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀጥልም ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ይግባኛቸው ተቀባይነት ሣያገኝ ቀርቷል በመጨረሻም አቤቱታቸውን ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ለሰበር ችልት ያቀረቡ ሲሆን ችልቱም የሥር ፍ/ቤቶችን ውሣኔ አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ነው የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ አባቴ ቦታ ላይ በራሴ ገንዘብ የሰራሁት ቤት ግምት ውስጥ አልገባልኝም ቤቱ በገበያ ዋጋ አልተገመተም የሚል ነው ይህ ችልትም የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት ቀርቦ ሉጣራ የሚገባው ነጥብ መኖሩን በማመን ተጠሪዎች ቀርበው እንዱከራከሩ አድርጓል። ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታውን የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ከተባለው ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝቦ መርምሯል።
ከመዝገቡ እንደተረዲነው አንደኛ ተጠሪ የሟች ሚስት አመልካችና ቀሪዎቹ ተጠሪዎች ደግሞ የሟች ልጆችና ወራሾች ናቸው። የሥር ፍ/ቤት ለክርክር ምክንያት የሆነው ቤት የሟችና የአንደኛ ተጠሪ የጋራ ንብረት በመሆኑ የቤቱ ግማሽ ለአንደኛ ተጠሪ ይገባል በማለት በሰጠው የውሣኔ ክፍል አመልካች ያቀረቡት ቅሬታ ባለመኖሩ ውሣኔውን እንደተቀበለት ይቆጠራል። በልላ በኩል ግን አመልካች በአባታቸው ቦታ ላይ በራሣቸው ገንዘብ የሰሩት ቤት ከግምት ውስጥ ሣይገባ የክፍፍል ውሣኔ እንደተሰጠ ገልፀዋል። ይህ ቤት በሟች ስም የተመዘገበና ቤቱ የአመልካች ለመሆኑ ምንም ማስረጃ ያልቀረበ ምስክርም ያልተቆጠረ መሆኑን የሻሸመኔ ወረዲ ፍ/ቤት በውሣኔው አስፍሯል። በመሆኑም አመልካች ቤቱ በገዛ ገንዘባቸው የሰሩት መሆኑን ማስረዲት ሣይችለ ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ላላው የአመልካች ቅሬታ የውርስ ንብረት በገበያ ዋጋ ሣይገመት በአነስተኛ ግምት ክፍፍለ መፈፀሙ ተገቢ አይደለም የሚል ነው። በልላ አነገጋገር የውርስ ንብረቱ በወራሾች መሃከል እኩል አልተከፊፈለም የሚል ነው። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደሚቻለው አመልካች ክስ ያቀረቡት የውርስ ንብረቱን በሟች ኑዛዜ መሰረት ለመካፈል ነው።
ፍ/ቤቶቹም የቤቱ ግማሽ የአንደኛ ተጠሪ ድርሻ መሆኑንና ቀሪውን የሟች ግማሽ ድርሻ ልጆቹ እኩል እንደካፈለ በሰጡት ውሣኔ በግራ ቀኙ የቀረበ ቅሬታ ባለመኖሩ ሟች ንብረቱን በዚሁ መሰረት እንዱካፈለ የተናዘዙ መሆኑን ችልቱ ግንዛቤ ወስዶል። ንብረቱን በዚሁ መሰረት ለመካፈልም የንብረቱ ትክክለኛ ዋጋ ሉታወቅ ይገባል። የስር ፍ/ቤት የንብረቱ ዋጋ በመሐንዱሶች የቀረበው ግምት ነው በማለት በዚሁ መሰረት ክፍፍለን መወሰኑን ተረድተናል። የንብረቱ ትክክለኛ ዋጋ ነው ማለት የሚቻለው ግን ቤቱን ለመስራት የወጣው ወጪ /book value/ ብቻ ሣይሆን ይልቁንም ቤቱ በወቅቱ ለገበያ በቀረበ ሉያወጣ የሚችለው ዋጋ /market value/ ነው በሥር ፍ/ቤት እንደተደረገው ቤቱ የተሰራበት ዋጋ ብቻ በባለሙያ ተገምቶ በቀረበው ግምት መሰረት ገንዘቡን መከፊፈለ ንብረቱን የሚያስቀረው ወገን የበለጠ ጥቅም እንዱያገኝና በልላው ወገን ላይ ጉዲት የሚያደርስ በመሆኑ የእኩልነት መርህን የሚንድ ይሆናል። ስለሆነም የውርስ ንብረት ክፍፍለ መፈፀም ያለበት በንብረት የገበያ ዋጋ መሰረት ስለሆነ የሥር ፍ/ቤቶች ንብረቱ ለመስራት የወጣውን ወጪ መሰረት በማድረግ ክፍፍለን መወሰናቸው የእኩልነት መርህን የሚጥስ ሆኖ አግኘትነዋል።
ው ሣ ኔ
የሻሸመኔ ወረዲ ፍ/ቤት የመ/ቁ. ባልተጠቀሰ በ24/6/98 የሰጠው ውሣኔ የምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ9775 በ28/ዐ7/98 እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 4ዐ4ዐ5 በ4/9/98 የሰጡት ትእዛዞች እንዱሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ. 41ዐዐ6 በዐ7/ዐ4/2ዐዐዐ የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሎል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
የውርሱ ንብረት በገበያ ዋጋ ተገምቶ በሚቀርበው ግምት መሰረት ክፍፍለ እንዱፈፀም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343/1/ መሰረት ጉዲዩ ለሻሸመኔ ወረዲ ፍ/ቤት ተመልሷል።