No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3632ዐ ጥቅምት 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ዘውዳ ገ/ስላሴ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሕይወት ባሕታ - ቀረቡ።
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። አመልካች በላልች 4 ተከሣሾች ላይ ባቀረቡት ክስ ተከሣሾች መብት ሣይኖራቸው የሟች አባቴን ቤትና ቦታ ስለያዙ ለቀው ያስረክቡኝ በማለት ጠይቀዋል። ተከሣሾችም ተከራይና አከራይ በመሆናቸው የቤቱ ባለቤት ናቸው የተባለት የአሁኗ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ተተክተው እንዱገቡ ተደርጎ ተጠሪዋ ቤቱና ቦታው የሣቸው መሆኑንና አመልካች በቤቱ ላይ መብት ያላቸው ለመሆኑ አግባብ ያለው ማስረጃ ስላላቀረቡ ክሱ ውድቅ እንዱደረግባቸው ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮችን ከሰማ በኋላ ቤቱና ቦታው የአመልካች አባትና የሚስታቸው የአሁኗ ተጠሪ የጋራ ንብረት በመሆኑ ተጠሪ የአመልካች አባት ድርሻ የሆነውን ግማሽ ንብረት ለአመልካች ታካፍል በማለት ወስኗል። ይግባኝ የቀረበለት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትም የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ውሣኔ በድምጽ ብልጫ አጽድቆታል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ላይ በድጋሚ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቤቱታ አቅርበው ችልቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ እያከራከረ ያለው የማይንቀሳቀስ ንብረት በመሆኑ ክስ ሉመሰርቱ ይገባ የነበረው የቤትና የቦታውን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ በማቅረብ ነው በማለት ክሱን ለማቅረብ በንብረቱ ላይ መብት ወይም ጥቅም ያላቸው መሆኑን አላስረደም ሲል የሥር ፍ/ቤቶችን ውሣኔ ሽሮታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህን ውሣኔ ለማስለወጥ ነው። የአመልካች አቤቱታ ተጠሪ ቦታና ቤቱን የያዙት የአባቴ ባለቤት ስለሆኑ እንጂ እራሳቸው ተመርተው አይደለም፤ ቦታውና ቤቱ አሁንም ድረስ በአባቴ የሚጠራ ነው፤
በፈረስ ማይ ከተማ እስካሁን ድረስ ለቤትና ለቦታ የተሰጠ ሰነድ የለም፤ ምክንያቱም ከተማው ራሱ እንደከተማ እየተዋቀረ ያለው አሁን ነው፤ የሚል ነው። ተጠሪም ለሰበር አቤቱታው መልስ እንዱሰጡ ተደርጎ በሰጡት መልስ አመልካች በንብረቱ ላይ መብት ያላቸው መሆኑን አላስረደም፤ በስር ያልተነሣ ክርክር አሁን ሉነሳ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝቦ መርምሯል። በዚህም መሰረት አመልካች ክስ በመሰረቱበት ንብረት ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም ወይ? የሚለው ነጥብ ሉመረመር ይገባል።
አመልካች በክሣቸው የአባታቸውን ቤት ተጠሪ እንዱያስረክቧቸው ጠይቀዋል። በእርግጥ አንድ ሰው ክስ በሚያቀርብበት ንብረት ላይ መብት ወይም ጥቅም ያለው መሆኑን ካላረጋገጠ በስተቀር ክስ ማቅረብ እንደማይፈቀድለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/ ሥር ተመልክቷል። በመሆኑም አመልካች ክርክር ባስነሣው ቤትና ቦታ ላይ መብት ወይም ጥቅም ያላቸው መሆኑን የማስረዲት ሸክም አለባቸው። በዚህም መሰረት አመልካች ንብረቱ የአባታቸው መሆኑን ያስረደልኛል ያሎቸውን የሰው ምስክሮች አቅርበዋል። የሰበር ችልቱ ግን ክርክር የሚደረግበት ንብረት የማይንቀሣቀስ ንብረት በመሆኑ መብት መኖሩ ሉረጋገጥ የሚገባው የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ወይም ሰነድ በማቅረብ ነው በማለት ወስኗል። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 ላይ የባለቤትነት ምስክር ወረቀት የተሰጠው ሰው ምስክር ወረቀቱ ለተሰጠበት ንብረት ባለሃብት ሆኖ እንደሚቆጠር ተመልክቷል። በመሆኑም ለአንድ ቤትና ቦታ የባለሃብትነት ምስክር ወረቀት የተሰጠው ሰው የዚሁ ንብረት ባለቤት ለመሆኑ ሕጉ ግምት ይወስዲል። በልላ በኩል ግን አመልካች ክርክር የተነሣበት ንብረት የሚገኝበት የፈረስ ማይ ከተማ ለማንኛውም ቤትና ቦታ የሰነድ ማስረጃ ያልሰጠ መሆኑን ጠቅሰው ያቀረቡትን ክርክር ተጠሪም አላስተባበለም። ተጠሪም ራሣቸው ቢሆኑ ቦታው የራሣቸው ለመሆኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ በልላ መዝገብ የተሰጠ ውሣኔ እና የሰው ምስክር ከማቅረብ በቀር የቤቱና የቦታው ባለሃብት ለመሆናቸው የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አላቀረቡም። ይህም የሚያሣየው ክርክር የተነሣበት ቤትና ቦታ የሰነድ /የባለሃብትነት ምስክር ወረቀት/ ያልወጣለት መሆኑን ነው። ከፍ ሲል የተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት የያዘ ሰው የንብረቱ ባለሃብት ለመሆኑ ሕጉ ግምት ይወስዲል ከማለት በቀር ማንኛውም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነት በልላ መንገድ ሉረጋገጥ እንደማይችል አያመለክትም። በአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ብዙ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የባለሃብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አልተዘጋጀላቸውም። ስለዚህ አመልካች ክርክር የተነሣበት ንብረት ላይ በተመለከተ የባለሀብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ባለማቅረባቸው በንብረቱ ላይ ጥቅም ወይም መብት የላቸውም ሉባለ አይገባም።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
በልላ በኩል ግን ክርክር የተነሣበት ቤትና ቦታ ያለበት አካባቢ በከተማነት እየተዋቀረ መሆኑ የተገለጸ ስለሆነ ይህ ቦታ ቀደም ሲል የማን እንደነበር፣ በአሁኑ ጊዜ ለማን እንደተሰጠ፣ በአሁኑ ጊዜ በስሙ የተመዘገበው ሰው ቦታውን እንዳት እንዲገኘ ከሚመለከተው የከተማ አስተዲደር ተጣርቶ ሉወሰን የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም መሰረት ጉዲዩ መጀመሪያ የቀረበለት ፍ/ቤት የቦታው ባለሃብት ማን እንደሆነ በሚገባ አጣርቶ ሉወስን ይገባል ብለናል።
ው ሣ ኔ
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ. 21523 ታህሣሥ 11 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
ክርክር የተነሣበት ቤትና ቦታ ቀደም ሲል የማን እንደነበር፣ በአሁኑ ጊዜ ለማን እንደተሰጠና በማን ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ ከሚመለከተው የከተማው አስተዲደር አካል ተጣርቶ እንዱወሰን ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343 መሰረት ለትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተመልሷል። ይፃፍ።