No summary available.
ሐምል 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ፊሲል ብርሃኑ - ቀርበዋል ተጠሪ፡- ዓቃቤ ሕግ /የኦሮሚያ ክልላዊ ብሓራዊ መንግስት/ - አልቀረቡም
የሰበር ችልት አመልካች በተወሰነበት የጥፊተኝነት እና ቅጣት ውሣኔ ላይ ባቀረበው ማመልከቻ መነሻነት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ይህን ፍርድ ሰጥቷል።
ለጉዲዩ መነሻ የሆነው ዓቃቤ ሕግ በአመልካቹ ላይ ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው። ዓቃቤ ሕግ በ1/8/2000 ዓ.ም በተፃፈ ክስ አመልካቹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 543(3) በመተላለፍ የካቲት 8 ቀን 2000 ዓ.ም በግምቱ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ በጂማ ዞን ስኮሩ ወረዲ በቲሮ ቁምቢ ቀበላ ውስጥ ኬላ ጏሼ በሚባል ቦታ የሰላዲ ቁጥሩ 3-42631 አ.አ የሆነ አይሱዚ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ያለጥንቃቄ ሲያሽከረክር መኪናው ተገልብጦ መኪናው ውስጥ ሲጓዙ የነበሩትን ሁለት ሰዎች በቸልተኝነት ገድሎል በማለት የወንጀል ክስ መስርቷል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ሶስት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን፣ የትራፉክ ኘላንና የመኪናው የቴክኒክ ምርመራ መግለጫ ከተቀበለ በኋላ ተከሣሹ እንዱከላከል በማዘዙ ሁለት የመከላከያ ምስክሮችንም ሰምቷል።
ፍርድ ቤት የቀረቡት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ከጂማ ወደ አዱስ አበባ በመሄድ ላይ እያለ ኩርባ ቦታ ላይ ሲደርሱ መገልበጡን አረጋግጠዋል። ከእነዚህ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች አንደኛው መኪናው በመካከለኛ ፍጥነት ይጓዝ እንደነበር ሲመሰክር ሁለተኛው የመኪናውን ፍጥነት መገመት እንዲልቻለ ገልጿል። ሦስተኛው ምስክር ግን ተከሣሹ በፍጥነት ሲያሽከረክር እንደነበርና ፍጥነቱን ሳይቀንስ ኩርባው ላይ በመድረሱ መኪናው መገልበጡን ገልጿል። ሦስቱም ምስክሮች በዚህ ምክንያት ሁለት ተሳፊሪዎች መሞታቸውንም መስክረዋል። የተከሣሹ ሁለት የመከላከያ ምስክሮችም እንደዚሁ በመኪናው ተሳፍረው ይጓዙ እንደነበረ ገልፀው በክሱ በተገለፀው ቦታ ላይ ሲደርሱ አንድ በሬና እረኛ ወደ መንገደ ድንገት ስለገቡበት እነሱን ለማዲን ሲል ተከሣሹ መኪናውን ኩርባው ላይ ከቀኝ ወደ ግራ ሲጠመዝዝ መኪናው ተንሸራትቶ መገልበጡንና በዚህ ምክንያት ሁለት ሰዎች መሞታቸውን መስክረዋል። ፍጥነቱን በሚመለከት አንደኛው ምስክር በጥሩ ሁኔታ በመጓዝ ላይ እንደነበር ሲመሰክር ላላኛው ግን በግምት ከ50- 60 ኪ.ሜ በሰዓት ይጓዝ እንደነበር ገልጸዋል።
ጉዲዩን የያዘው ፍ/ቤት ይህን በግራ ቀኙ የቀረበውን ማስረጃ ከተመለከተ በኋላ ተከሣሹ ኩርባ ላይ ከ50–60 ኪ.ሜ በሰዓት በመጓዙ ድንገት የገቡበትን በሬና እረኛ ለማትረፍ ብል ወደጏን ሲይዝ መኪናው ተንሸራቶ አደጋው ሉደርስ እንደቻለ ተረድቻለሁ በማለትና ተሳፊሪዎቹ ሉሞቱ የቻለትም ተከሣሹ ቀስ ብል መንዲት በነበረበት ቦታ ላይ በፍጥነት በማሽከርከሩ ነው በማለት ተከሣሹ የወንጀል ሕጉን 543(3) በመተላለፍ ጥፊተኛ ነው ብሎል። የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላም በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እና 10,000(አስር ሺህ ብር) እንዱቀጣ ወስኗል።
ተከሣሹ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በማቅረቡ የጥፊተኝነት ውሣኔን አፅንቶ ቅጣቱን ወደ ሦስት ዓመት ጽኑ እስራትና አምስት ሺ ብር መቀጮ ዝቅ እንዱልለት አድርጓል። የኦሮሚያ የሰበር ችልት ጉዲዩ በአቤቱታ ቀርቦለት በድምፅ ብልጫ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተገኘበትም በማለት መዝገቡን ዘግቷል። በዚህ ሁኔታ ጥፊተኛ ተብል የሦስት ዓመት እስር 5,000 ብር (አመስት ሺህ ብር) መቀጮ የተጣለበት ተከሣሽ ታህሣስ 14 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የፍርድ ቤቶቹ ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን በማተት ውሣኔው እንዱሻርለት ጠይቋል። የአሁኑ አመልካች በዚህ ሰበር ችልት አጥብቆ የሚከራከረው መኪናው የተገለበጠው ድንገት ኩርባ ላይ የገቡትን አንድ እረኛና አንድ በሬ ለማዲን በማሰብ መኪናውን ወደ ግራ አቅጣጫ ስለጠመዘዝኩት ነው፣ በመሆኑም በዚህ ሂደት ህይወታቸው የጠፊው ሁለት ተሳፊሪዎች በአደጋ ምክንያት ሞቱ ከሚባል በስተቀር በኔ ቸልተኝነት ሞቱ ተብል እኔ ጥፊተኛ ልሆን አይገባኝም በማለት ነው። ከዚህ በላይ ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀፅ 543(3) እግረኛን ገጭቶ ለገደለ እንጂ መኪና ተገልብጦ ሰው ለሞተበት አሽከርካሪ ተፈፃሚ ላሆን አይገባውም የሚል ክርክር አቅርቧል። የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መነሻ በማድረግ ተሳፊሪዎቹ የሞቱት በአሽከርካሪ ቸልተኝነት ነው ልባል ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚለውን የሕግ ነጥብ ለማጣራት ጉዲዩ ዓቃቤ ሕግም ባለበት ሁለቱ ባለጉዲዮች የቃል ክርክር እንዱያደርጉበት ተደርጓል።
የሰበር ችልት ከላይ የተጠቀሰው አጠቃላይ የክርክሩ ሂደት አግባብ ካላቸው የወንጀል ሕግ ድንጋጌ እና አመልካችና መልስ ሰጪ በዚህ ችልት ቀርበው ካሰሙት የቃል ክርክር ጋር በማገናዘብ ተመልክቷል። ከቀረበው ፍሬ ነገርና ከተወሰነው ውሣኔ አንፃርም አመልካችን በወንጀል ጥፊተኛ ለማለት በወንጀል ሕግ አንቀፅ 543(3) የተጠቀሱት መስፈርቶች ተሟልቷል? ወይስ አልተሟለም? የሚለውን ነጥብ አጣርቷል። አመልካቹ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ፈፅሟል ተብል የተቀጣ በመሆኑ በሕጉ ቸልተኝነት የሚያቋቁሙ መስፈርቶች መሟላት አለመሟላታቸውን አጣርቷል። ይህ ችልት በዋናነት የመረመረው የሕግ ነጥቡን ብቻ ቢሆንም የሕጉን አግባብነት በትክክል ለመመዘን በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች በቅድሚያ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዲዩ በሥር ፍ/ቤቶች ሲታይ አመልካች ከጂማ ወደ አዱስ አበባ ሲጓዝ መኪናው መገልበጡና ከተሳፊሪዎች መካከል ሁለቱ መሞታቸው ተረጋግጧል። መኪናው ሉገለበጥ የቻለው መኪናው ከ 50 – 60 ኪ.ሜ በሰዓት ሲጓዝ ከፉት ለፉት አንድ እረኛ በሬውን ለመመለስ በቅርብ ርቀት ስለገባበት እንደሆነም በስር ፍ/ቤቶች ግንዛቤ ተወስድበታል። እረኛው መኪናው መንገድ ውስጥ የገባበትና መኪናው የተገለበጠበት ቦታ ኩርባ እንደሆነም በሂደቱ ተጣርቷል። መኪናው የቴክኒክ ብልሽት ያልነበረበት መሆኑም ከቀረበው የቴክኒክ ሪፕርት ተረጋግጦአል። እነዚህ በፍርደ ሂደት የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ሲሆኑ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ሕግ ይዘት ደግሞ ከዚህ ቀጥል እንመለከታለን።
አመልካቹ በዓቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543(3)”ን” በመተላለፍ ሁለቱ ሰዎች በቸልተኝነት ገድሎል በማለት ነው። በመሆኑም የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች የተጠቀሰውን ሕግ የሚያቋቁሙ መሆን አለመሆናቸው ለማረጋገጥ ሕጉ ቸልተኝነት አለ የሚለው ምን ምን ሁኔታዎች ሲሟለ እንደሆነ መመልከቱ ተገቢ ነው።
በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 57 በግልፅ እንደሰፈረው “ለድርጊቱ ኃላፉ ላሆን የሚገባው ሰው አስቦ ወይም በቸልተኝነት አንድ ወንጀል ካላደረገ በቀር በወንጀል ጥፊተኛ አይሆንም” በአንፃሩ አንድ ሰው “የፈፀመው ድርጊት በሕግ የሚያስቀጣ ቢሆንም ምንም ጥፊት ሳያደርግ ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ኃይል ምክንያት ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ ነገር የተፈፀመ ወይም የደረሰ ሆኖ ሲገኝ በወንጀል ሕግ ሉፈረድበት አይገባውም በማለት የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 57(2) ይደነግጋል። ከዚህ የሕጉ አጠቃላይ አባባል መገንዘብ የሚቻለው በአንድ ድርጊት ምክንያት አንድን ሰው በወንጀል ጥፊተኛ ነው ለማለት ከሳሽ የሆነው ዓቃቤ ሕግ ድርጊቱ የተፈፀመው ሆን ተብል ወይም በቸልተኝነት መሆኑን ማስረዲት የሚጠበቅበት መሆኑን ነው። ድርጊቱ ሆን ተብል ወይም በቸልተኝነት የተፈፀመ መሆኑ ማስረጃ ካልቀረበ ወይም ድርጊቱ ከአቅም በላይ ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የተፈፀመ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ በተከሣሽ በኩል ከቀረበ የተከሰሰውን ሰው በወንጀል ሕግ ጥፊተኛ ብል መፍረድ ከሕጉ መንፈስ ውጪ ነው። በወንጀል የተከሰሰ ሰው ቸልተኛ ነበር ወይስ አልነበረም የሚለው ጥያቄ በወንጀል ሕጉ በአንቀፅ 59 የሰፈረውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የሚወሰን ነው። የዚሁ አንቀፅ ንዐስ አንቀጽ አንድ አሁን ለተያዘው ጉዲይ በቀጥታ አግባብነት ያለው በመሆኑም የሕጉን ይዞታ እንዲለ ማስቀመጡ ጠቃሚ ነው።
“59(1) ማንም ሰው በቸልተኝነት የወንጀል ተግባር አድርጓል የሚባለው፡- (ሀ) ድርጊቱ በወንጀል ሕግ የሚያስቀጣ ውጤት ሉያስከትል እንደሚችል እያወቀ አይደርስም የሚል ግምት ወይም ባለማመዛዘን፣ ወይም (ለ) ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ውጤት ሉያስከትል እንደሚችል ማወቅ እያለበት ወይም እየቻለ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ነው።” “ የእንግሉዘኛው ትርጉም ደግሞ እንደሚከተለው ይደነግጋል Article 59
አሁን በቀረበልን ጉዲይ አመልካች የሚከራከረው ከላይ የተቀጠሱት መስፈርቶች ስላልተሟለ በቸልተኝነት ሰው በመግደል ጥፊተኛ ልሆን አይገባም በማለት ሲሆን ዓቃቤ ሕግ በልላ በኩል የሕግ መስፈርቶች ተሟልተዋል የሚል ሙግት አቅርቦአል። ጉዲዩን መጀመሪያ ያየው የጂማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካችን በቸልተኝነት ሰው በመግደል ጥፊተኛ ያለው ቢሆንም የቀረቡለትን ማስረጃዎች በዝርዝር ሕጉ ካስቀመጠው መስፈርት አንፃር ስለመመዘኑ በፍርደ በግልፅ ያሰፈረው ነገር የለም።
ከላይ እንደተገለፀው አመልካች ጥፊተኛ ነህ የተባለው ከጂማ ወደ አዱስ አበባ በአመልካች አሽከርካሪነት ሲደረግ በነበረ ጉዞ መኪናው በመገልበጡና ሁለት ተሳፊሪዎች በመሞታቸው ነው። መኪናው ሲገለበጥ ከ50 - 60 ኪ.ሜ በሰዓት ፍጥነት የነበረው መሆኑ ምስክሮች የገለፀ ሲሆን በጉዞ ላይ እያለ ኩርባ ላይ ሲደርስ አንድ እረኛ ከበሬ ጋር ወደ መንገደ እንደገቡበትም ተመስክሯል። መኪናው ሉገለበጥ የቻለው ሹፋሩ እረኛውንና በሬውን ላለመግጨት ሲል ወደ ግራ ሲጠመዘዝ መኪናው በመንሸራተቱ ነው። በዚህ ሁኔታ የተከሰተው የሁለት ሰዎች ሞት አመልካችን ሉያስጠይቅ የሚችለው በአሽከርካሪነት ስራው ማድረግ የነበረበትን ጥንቃቄ ሳያደርግ ቀርቶ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 59(1) የተገለፀውን ያሟላ እንደሆነ ነው።
ከማህደሩ ዝርዝር ለመገንዘብ እንደቻልነው ሹፋሩ /አመልካች/ መኪናውን ከ50-60 ኪ.ሜ በሰዓት ያሽከረክር ነበር የሚል ምስክርነት የተሰጠው በባለሞያ አይደለም። መኪናው በዚህ ፍጥነት ይጓዝ ነበር ያለት መኪናው ውስጥ የነበሩ አንድ የዓቃቤ ሕግ ምስክር እና አንድ የከሳሽ ምስክር ናቸው። በመሰረቱ እነዚህ ሁለት ተሳፊሪዎች መኪናው ይጓዝበት የነበረውን ፍጥነት በትክክል ይናገራለ ብል መገመት የሚቻል አይደለም። በመሆኑም ፍ/ቤቱ መኪናው በዚህ ፍጥነት ይጓዝ ነበር በማለት ለደረሰበት መደምደሚያ የሚያበቃ በቂ ማስረጃ አልቀረበለትም።
ከዚያም በላይ መኪናው ከ50 – 60 ኪ.ሜ በሰዓት ይጓዝ ነበር እንኳን ቢባል ከከተማ ውጪ በነበረ ጉዞ በዚህ ፍጥነት ማሽከርከር በአሽከርካሪው በኩል ጥንቃቄ ጉድለት ነበር ለማለት የሚያስችል አሳማኝ ማስረጃ አልቀረበም መኪናው የሕዝብ ትራንስፕርት በመሆኑ ከጂማ ወደ አዱስ አበባ ሲጓዝ በዚህ ፍጥነት መንቀሳቀሱ ጥፊት ልባል የሚችል አይደለም። መኪናው በተገለበጠበት ቦታ አካባቢ የፍጥነት ጣሪያ የነበረ መሆኑ አልተረጋገጠም ወይም ከጅማ እስከ አ/አ ባለው መንገድ ወይም በአጠቃላይ ከከተማ ውጪ በሚደረግ ጉዞ ከ50 ኪ.ሜ በሰዓት በላይ መንዲት ክልከላ ስለመኖሩም አልተገለፀም። መኪናው ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ማስረጃ የቴክኒክ ችግር እንዲልነበረበት በመረጋገጡ በመኪናው ልዩ ባህርይ ምክንያት ተከሳሹ ከ50 ኪ.ሜ በሰዓት በታች መንዲት ይጠበቅበት ነበር ልባል አይችልም። ስለሆነም መኪናው ከመገልበጡ በፉት ሹፋሩ መፈፀም የነበረበት የጥንቃቄ እርምጃ አለመወሰደ የሚያሳይ ነገር የለም።
መኪናው በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ አንድ እረኛ ድንገት ከገባበት አሽከርካሪው ማድረግ የሚጠበቅበትን ፈፅሟልን?
የሚለው ጥያቄ መልስ የሚፈልገው ላላው ነጥብ ነው። ኩርባው ላይ ሲደርስ በቅርብ ርቀት እረኛና በሬ መኪናው መንገድ ላይ ሲገቡ አሽከርካሪው የተለያዩ አማራጮች እንደነበሩት መገመት ይቻላል። አንደኛው ዕረኛውንና በሬውን ገጭቶ ማለፍ ነው፣ ሁለተኛው ወደ ቀኝ ለመጠምዘዝ እረኛውን ከነከብቱ ለማዲን መሞከር ነው። በማስረጃ እንደተረጋገጠው መኪናው ወደቀኝ ቢጠመዘዝ ገደል ውስጥ ይገባ ነበር። በመሆኑም አሽከርካሪው ይህንን አማራጭ አለመውሰደ የጥንቃቄ ጉድለት ፈጽሟል ሉያሰኘው አይችልም። ወደግራ በመጠምዘዝ መንገድ ውስጥ ድንገት የገባውን ሰው ለማዲን መሞከሩና እርግጥም ይህንን ሰው ከሞት አደጋ መታደጉም የጥንቃቄ ጉድለት ልባል አይችልም። እንዱያውም ሰውዬውን ለማዲን ምንም ሙከራ ሣያደርግ ፉት ለፉት የሚያየውን ሰው ጨፍልቆ ቢያልፍ ከፍ ያለ ወንጀል ይፈፅም እንደነበረ ግልፅ ነው።
አመልካች የቀረውን የመጨረሻ አማራጭ በመጠቀም መኪናውን ወደግራ ሲጠመዝዝ መኪናው እንደሚገለበጥና ከተሳፊሪዎች መካከል ከፉልቹ እንደሚሞቱ ያውቅ ነበር? ይህንስ እያወቀ ነው ድርጊቱን የፈፀመው? አያውቅም ከተባለስ የወሰደው አማራጭ ለሰዎች ሞት ምክንያት ላሆን እንደሚችል ማወቅ ነበረበት ማለት ይቻላል? የሚለት ጥያቄዎች ቸልተኝነት ነበረ ወይም አልነበረም ለማለት መመለስ የሚገባቸው ጥያቄዎች ናቸው። በመሰረቱ ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት አመልካችን የቸልተኝነት ወንጀል ፈፅሟል ሉያሰኝ የሚችል ማስረጃ ወይም የሞያ አስተያየት በዓቃቤ ሕግ በኩል አልቀረበም። በበኩላችን ከፉት ለፉት ካጋጠመ አደጋ ለመዲን መኪና ወደ ቀኝ ይሁን ወደግራ ሲጠመዘዝ ሁላም ይገለበጣል ወይም የመገልበጥ ዕድለ ሰፉ ነው ለማለት አልቻልንም። በመሆኑም አሽከርካሪው የመኪናውን መገልበጥ ቀደም ብል ያውቅ ነበር ለማለት የሚቻል አይደለም። መኪናው ሉገለበጥ እንደሚችል ማወቅ ነበረበት ማለትም የሚቻል አይደለም። በመሆኑም አሽከርካሪው የመኪናው መገልበጥ በጉዞ ላይ በተፈጠረና ከአሽከርካሪው ቁጥጥር ውጪ በሆነ የዕረኛው ድንገት መግባት የተፈጠረ አደጋ (accident) እንጂ በአሽከርካሪው ቸልተኝነት የተፈፀመ የወንጀል ድርጊት ነው ማለት አልቻልንም። ከተሳፊሪዎቹ መካከል የሁለቱ መሞትም የዚሁ አደጋ ውጤት እንጂ የቸልተኛ ድርጊት (negligent act) ውጤት ነው ማለት አልቻልንም። የሰው መሞት በሕግ ሉያስጠይቅ እንደሚችል ግልፅ ነው። ሆኖም ይህ ውጤት በሕግ ሉያስጠይቅ የሚችለው ለሞቱ ምክንያት የሆነው ሰው ጥፊተኛ ሆኖ ሲገኝ ነው። ጥፊተኛ የሚሆነው ደግሞ ድርጊቱ ሆነ ተብል ወይም በቸልተኝነት የተፈፀመ እንደሆነ ነው። አሁን በቀረበልን ጉዲይ የሁለት ተሳፊሪዎች ሞት የተከሰተው በአሽከርከሪው ቸልተኝነት ሳይሆን በድንገተኛ አጋጣሚ በሆነ የመኪና መገልበጥ አደጋ ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የአሁኑን አመልካች በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል ጥፊተኛ ያለው የቀረበለትን ማስረጃ ከሕጉ ጋር በተገቢው ሁኔታ ሳያገናዝብ ነው። ለውሣኔው መሰረት ያደረገው የመኪናው መገልበጥ ለሁለት ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን ብቻ ነው። አመልካቹ ሰዎቹ የሞቱት በአደጋ (accident) እንጂ በቸልተኛ የወንጀል ድርጊት (negligent criminal offence) አይደለም እያለ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተከራከረ ቢሆንም ፍ/ቤቶቹ ለዚህ ክርክር ትኩረት በመስጠት በአደጋና በቸልተኛ ድርጊት መካከል ያለውን ልዩነት አልመረመሩም በዚህም ምክንያት በሕጉ መንፈስ ወንጀለኛ መባል ያልነበረበት ሰው ጥፊተኛ በማለት በእስርና በገንዘብ እንዱቀጣ ውሣኔ መስጠታቸው የሕጉን ግልፅ ድንጋጌ የሚጥስ ሆኖ ስላገኘነው በዚህ ጉዲይ የጂማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤትና ሰበር ችልት የሰጡት የጥፊተኛነትም ሆነ የቅጣት ውሣኔ መሻር አለበት ብለናል።
ው ሣ ኔ
የጂማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ጥቅምት 18 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 26 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የኦሮሚያ ሰበር ችልት በወ/ ታህሣሥ ቀን 2001 ዓ.ም የሰጡት ውሣኔ ተሽረዋል።
አመልካች የወንጀል ሕግ አንቀፅ 543(3) ተጠቅሶ ከቀረበበት ክስ ነፃ ነው ብለናል።
አመልካች በዚሁ ችልት ትዕዛዝ ያስያዘው የዋስትና ገንዘብ ካለ ይመለስላቸው።
No topics extracted.