No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 44ዐ31 ሐምል 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ፈለቀች ኃ/ገብርኤል - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ - የዓቃቤ ሕግ አፀደ ረጋሣ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታው ውድቅ ከተደረገበት ዮሴፍ ከበደ ጋር በጋራ ባቀረበችው የሰበር አቤቱታ በመጠየቁ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በላል አሳቢ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ የሰበር አቤቱታው ውድቅ የተደረገበት ዮሴፍ ከበደ ጋር በመሆን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32/1/ሀ እና አንቀጽ 63ዐ/2/ሀ በመተላለፍ ነሐሴ 24 ቀን 1998 ከምሽቱ ሶስት ሰዓት በግል ተበዲይ ወ/ሪት ብርቱካን ደባለን አስገድድ መድፈር ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ክስ አቅርቦ የሰውና የጽሁፍ ማስረጃ አሰምቶ የወረዲው ፍርድ ቤት ተከሣሾች መከላከያ ሣያስፈልጋቸው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 141 መሰረት በነፃ እንዱሰናበቱ ወስኗል። ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቦ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ራሱ የአመልካችን መከላከያ ከሰማ በኋላ ከላይ የተሰጠቀሰውን የሕግ ድንጋጌ በተመላለፍ ወንጀል የፈፀመች ጥፊተኞች ናቸው በማለት ዮሴፍ ከበደ በሰባት ዓመት ጽኑ እስራት፣ አመልካች በሶስት ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ችልት ያቀረበች ሲሆን ይግባኙን ሰርዞታል። አመልካች ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ያቀረበችው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች የካቲት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ዮሴፍ ከበደ የግል ተበዲይን እንዱደፍር በመላው ሀሣቤና በድርጊት ያደረግሁት አስተዋጽኦ ስለመኖሩ የቀረበብኝ ማስረጃ ሣይኖር አላግባብ ጥፊተኛ ተብዬ መቀጣቴ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ጠይቃለች። ተጠሪ በበኩለ አመልካች ዮሴፍ ከበደ የግል ተበዲይን እንዱደፍራት ሁኔታውን በማመቻቸት ተሣትፊለች። ይህንንም በማስረጃ ያስረዲንበት ስለሆነ የክልለ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረትዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ሐምል 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በጽሁፍ ባቀረበው መልስ ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም አመልካች ዮሴፍ ከበደ የግል ተበዲይን አስገድድ ሲደፍር አመልካች የወንጀለ ተካፊይ በመሆኗን ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 33 እና የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 25 ድንጋጌዎች መሰረት በማስረዲት የአመልካችን ጥፊተኛነት አረጋግጧል ወይስ አላረጋገጠም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ዓቃቤ ሕግ ክስ ሲያቀርብ ወንጀለ የተፈፀመበትን ጊዜና ቦታ እንዱሁም ተከሣሾቹ ከአንድ በላይ ሲሆኑ እያንዲንዲቸው በወንጀለ ያላቸውን ተካፊይነት በዝርዝር መግለጽ ያለበት መሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 111 ድንጋጌዎች የተደነገገ ሲሆን ዓቃቤ ሕግ ይህንን በክስ የተገለፀውን ፍሬ ጉዲይ አጥጋቢ በሆነ ማስረጃ የማስረዲት ግዳታ ያለበት መሆኑን ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 141 እና 149 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል። የግል ተበዲይን ወ/ሪት ብርቱካን ደባለን መድፈሩ ተረጋግጦ በፍርድ የተቀጣው ዮሴፍ ከበደ የአመልካች ባል ነው። ዓቃቤ ሕግ ዮሴፍ ከበደ ወ/ሪት ብርቱካን ደባለን የደፈራት ነሐሴ 24 ቀን 1998 ከምሽቱ አራት ሰዓት በአመልካች መኖሪያ ቤት ውስጥ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን በጉዲዩ የምስክርነት ቃል የሰጠችው የግል ተበዲይ አመልካች ጊንቢ ከተማ እንሂድ ብላት አብረው ሄደው ዕቃ እንደገዙና ከዚያም በምሽት አመልካች በመኪና ትኬት ቆርጣ ከመኪናው ጋቤና ተቀምጠው እንደመጡና አመልካች እቤቷ አጠገብ ስትደርስ ወርዲ ዕቃውን አያይዥኝ ብላ ጠይቃ እቤት እንደገባችና የአመልካች ባል ዮሴፍ ከበደ ከምሽቱ ስምንት ሰዓት ሲሆን የአስገድድ መድፈር ወንጀል እንደፈፀመባት የመሰከረች መሆኑን ከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ የአማርኛ ትርጉም ለመረዲት ችለናል። ላልቹ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች የጽሁፍ ማስረጃ አመልካች የወንጀል ተካፊይ ስለመሆኗ የሚያስረደ አይደለም።
አመልካች ተካፊይ ሆናበታለች ተብላ የተከሰሰችበት የአስገድድ መድፈር ወንጀል በወንጀል ሕግ ቁጥር 32 ድንጋጌዎች መሰረት አመልካች ተካፊይ ለመሆን የማትችልበትና ወንጀለ በተቃራኒው ጾታ (ወንድ) ሉፈጸም የሚቻል በመሆኑ ከጅምሩ ዓቃቤ ሕግ አመልካች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና አንቀጽ 63ዐ በመጥቀስ የቀረበው ክስ የአመልካች የወንጀል ተካፊይነት ባግባቡ የሚገልጽ አይደለም። አመልካች በወንጀለ ተካፊይ ነበረች ለማለት ዓቃቤ ሕግ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 33 የተነገገውን ሁኔታ በአጥጋቢ ማስረጃ የማስረዲት ሸክም አለበት። በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 33 መሰረት ኦዱት ሴት ላላኛዋ ሴት ለተፈፀመባት የአስገድድ መድፈር ወንጀል ተካፊይ ሆናለች ብል ለመክሰስና ጥፊተኛ ለማሰኘት ሴትዮዋ በሙለ ፈቃዶና ዕውቀቷ የወንጀለ ተካፊይ የነበረች መሆኑን ከሣሽ የማስረዲት ግዳታ እንዲለበት ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 33 ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል።
ዓቃቤ ሕግ አመልካች ባሎ የግል ተበዲይን አስገድድ ሲደፍር በሙለ ፈቃዶና ዕውቀቷ የወንጀለ ተካፊይ መሆኑን ለማስረዲት ያቀረበው ብቻኛ ማስረጃ የግል ተበዲይ የሰጠችው የምስክርነት ቃል ሲሆን ምስክሯ አመልካች ጊንቢ ሃኪም ቤት አብራት እንድትሄድ ጠይቃት ቀን ጊንቢ ከተማ አብረው የዋለ መሆኑን ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ የተመለሱና አመልካች የገዛችው ዕቃ ስታወርድ ተሣፍራበት የነበረው መኪናው ጥሎት የሄደ መሆኑን ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አመልካችና የአመልካች ባል ዮሴፍ ከበደ ከቤታቸው ያስገቧት መሆኑን ከላሉቱ ስምንት ሰዓት ሲሆን ዮሴፍ ከበደ የአስገድድ መድፈር ወንጀል የፈፀመባት መሆኑን የመሰከረች መሆኑን መዝገቡ ያሣያል። ይህንንም ስንመለከተው አመልካች ከግል ተበዲይ ጋር ጊንቢ ከተማ ሄዲ የዋለችው እና አምሽተው የመጡት ከላሉቱ ስምንት ሰዓት በመነሳት ባሎ ዮሴፍ ከበደ የአስገድድ መድፈር ወንጀል እንደሚፈጽምባት ሙለ እውቀት የነበራትና በሙለ ፈቃደኝነት በወንጀለ ስራ ተካፊይ መሆኗን የሚያስረዲ የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ አይደለም። ይልቁንም በግል ተበዲይ ላይ ዮሴፍ ከበደ አስገድድ መድፈር ወንጀል በፈጸመበት ጊዜ ከላሉቱ 8 ሰአት አመልካች ያደረገችው ተሣትፍ ያለ ስለመሆኑ የግል ተበዲይ ለመመስከሯ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 25 ንዐስ አንቀጽ 1 በተደነገገው የአስገድድ መድፈር ወንጀለ በተፈፀመበት ጊዜ ማለትም ከላሉቱ ስምንት ሰዓት አመልካች የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 33 በሚደነግገው መሰረት በሙለ ፈቃዶና ዕውቀቷ በወንጀለ ሥራ ያልተካፈለች መሆኑን የሚያሣይ ነው። ስለሆነም ዓቃቤ ሕግ በቂ ማስረጃ በማቅረብ አመልካች ባለቤቷ በላሉት ስምንት ሰዓት ጓደኛዋ በሆነችው የግል ተበዲይ ላይ የፈፀመው የአስገድድ መድፈር ወንጀል በሙለ ፈቃዶና ዕውቀቷ ተካፊይ የነበረች መሆኑን ባላስረዲበት ሁኔታ የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች በወንጀለ ተካፊይ ልትሆን የምትችልበትን ልዩ ሁኔታና የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 33 ድንጋጌ ሣያገናዝብ አመልካች ከግል ተበዲይ ጋር ጊንቢ ከተማ ውላ የመጣች መሆኑን የአስገድድ መድፈር ወንጀለን ለማመቻቸት ነው የሚለውን ግምታዊ መደምደሚያ በመመልከት ብቻ አመልካች ላይ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ከላይ የዘረዘርናቸውን የሕግ ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና በስር ችልት ይህንን ግድፈት ሣያርሙ ማለፊቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የሰጠው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ ሙለ በመለ ተሽሯል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት ስለ አመልካች የሰጡት ትዕዛዝ ተሽሯል።
አመልካች ባለቤቷ አቶ ዮሴፍ ከበደ ጥፊተኛ ሆኖ በተቀጣበት የአስገድድ መድፈር ወንጀል በሙለ ፈቃዶና ዕውቀቷ ተካፊይ ስላልሆነች በነፃ ትሰናበታለች ብለናል።
አመልካች ላይ ተሰጥቶ የነበረው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ የተሻረ መሆኑ ለሚመለከተው ይፃፍ። አመልካች በዋስትና ያስያዘችው ገንዘብ ካለ ይመለስ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.