No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ አመልካች፡-
ይህ ጉዲይ የወንጀል ክርክር ሲሆን ተጠሪ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በአመልካቾች ላይ ያቀረበው የወንጀል ክስ የወንጀል ሕግ ቁጥር 32/1/ሀ/ እና 692/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ሚያዝያ 16 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ከምሽቱ 4፡45 ሲሆን በአዱስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበላ 15/16 ክልል የግል ተበዲይ አቶ ኢሳያስ ካሣ ግሮሰሪ በመሄድ ውስኪ እንፈልጋለን ብለው መኪና ውስጥ ሆነው አንድ ብላክ ላብል ውስኪ አዘው እሱን ከተመለከቱ በኋላ ላላ ብላክ ላብል ጨምረን ብለው ሉጨምርላቸው ሲሄድ መኪና አስነስተው በማምለጣቸው ተከሰዋል የሚል ነው።
አመልካቾች ቀርበው ክሱ ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ በክሱ ላይ መቃወሚያ እንዲላቸው ተጠይቀው ክሱን እንደማይቃወሙ ካረጋገጡ በኋላ የዕምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ ድርጊቱን ፈፅመናል ጥፊተኛም ነን ብለዋል።
ፍ/ቤቱም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 134/1/ መሰረት የጥፊተኛነት ውሣኔ ከሰጠ በኋላ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብሎል። በዚህም መሰረት ከሣሽ ዐቃቤ ሕግ በሰጠው የቅጣት አስተያየት ተከሣሾች የወንጀለን ድርጊት የፈፀሙት ግብረአበር በመሆን ስለሆነ ፍ/ቤቱ ይህንን በቅጣት አወሳሰን ረገድ ከግምት እንዱያስገባልን ካለ በኋላ ተከሣሾች የትምህርት ደረጃቸው ሲታይ የወንጀልን አስከፉነት ከላላው ሰው በተሻለ መልኩ ሉያውቁና ሉረደ የሚችለ መሆኑን መገንዘብ ስለሚቻል ይህንንም ከግምት በመክተት እንደዚሁም ፍ/ቤት ቀርበው ማመናቸውንም ከግምት በማስገባት ፍ/ቤቱ ተገቢ ነው ብል ያመነበትን ቅጣት እንዱወስንባቸው በማለት አመልክቷል።
ተከሣሾችም በበኩላቸው ድርጊቱ በአጋጣሚ የተፈፀመ መሆኑን፣ ወጣቶች እንደሆኑ፣ በድርጊታቸውም እንደተፀፀቱና ከግል ተበዲይም ጋር እንደታረቁ ገልፀው የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቅሰው ቅጣቱ በገደብ እንዱሆን ይወሰንልን በማለት የቅጣት አስተያየት መስጠታቸውን ተገንዝበናል።
በዚህ መልኩ የቅጣት አስተያየት የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ተከሣሾች የተከሰሱበት ወንጀል እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እሥራት የሚያስቀጣ ቢሆንም ተከሣሾች አስቀድሞ ወንጀል የፈፀሙ ስለመሆኑ ሪከርድ ያልቀረበባቸው ስለሆነና ይህንንም ወንጀል ስለመፈፀማቸው ያመኑ በመሆኑ ይህም ሁኔታ በወንጀል ሕግ ቁጥር 82/1/ሰ/ መሰረት ቅጣት ማቅለያ ተደርጎ ሉወሰድ ስለሚችል ተከሣሾች እያንዲንዲቸው በ6 /ስድስት/ ወር ቀላል እስራት እንዱቀጡ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተከሣሾች የጥፊተኛነት ውሣኔውን ተቀብለው ነገር ግን በቅጣት ማቅለያነት ያቀረቡት ምክንያቶች የተወሰነውን ቅጣት በወንጀል ሕግ ቁጥር 192 መሰረት በገደብ ለማቆየት የሚያስችል ሆኖ ሳለ ቅጣቱ ሳይገደብ መቅረቱ ተገቢነት የላለው ነው በማለት የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ በአመልካቾች ላይ የተወሰነውን ቅጣት በገደብ ለማቆየት የሚያበቃ ሁኔታ ስለመኖሩ ለማጣራት አቤቱታው ለሰበር ችልት ይቅረብ ብል ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተጠቀሰው ሲሆን በበኩላችንም አቤቱታው ለሰበር ይቅረብ ከተባለበት ነጥብ አኳያ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
በአንድ የወንጀል ተከሣሽ ላይ የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ የተወሰነው የእሥራት ቅጣት ሳይፈፀም በገደብ እንዱቆይ ላደረግ የሚችልባቸው ምክንያቶች በወንጀል ሕግ በቁጥር 192 ላይ ተመልክቶ ይገኛል።
እንደዚሁም የቅጣት ውሣኔ በገደብ ሉቆይ የማይችልባቸው ምክንያቶችም በቁጥር 194 ሥር ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት ከቁጥር 192 አኳያ የተወሰነውን የእስራት ቅጣት በገደብ ለማቆየት የሚቻለው ጥፊተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈፀሙ በፉት ለተወሰነው ጊዜ ቅጣቱ ታግድለት አመለ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፊት ከማድረግ የሚታገድ መሆኑንና ስለጠባዩም መሻሻል አንድ ጽኑ ማስጠንቀቂያ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያመነበት ከሆነ ነው። በተያዘው ጉዲይ አመልካቾች ቀደም ሲል ወንጀል ስለመፈጸማቸው ሪከርድ ያልቀረበባቸው እንደመሆኑ መጠን ያለፈ የሕይወት ታሪካቸው መልካም እንደነበር ይገመታል። አሁን ጥፊተኛ ሆነው የተገኙበትንም ወንጀል በየዋህነት ወይም ባልታሰበና ድንገተኛ አጋጣሚ የፈፀሙት ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል። ከዚህም ላላ አመልካቾች ወንጀለን ከፈፀሙ በኋላ ከግል ተበዲዩ ጋር ወዱያውኑ መታረቃቸው ድርጊቱን በድንገተኛ አጋጣሚ በየዋህነት የፈፀሙት መሆኑና በዚህም መጸጸታቸውን የሚያሳይ ነው። በልላ በኩልም የወንጀል ሕግ ግብ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 1 ላይ የተመለከተ ሲሆን ይዘቱም የወንጀል ሕግ ግብ ወንጀል እንዲይፈጸም መከላከል ሲሆን ይህንን የሚያደርገው ስለወንጀልችና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ላላ ወንጀል ከመፈፀም እንዱቆጠቡና ለላልች ማስተማሪያ እንዱሆኑ ወይም እንዱታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀልች እንዲይፈፀሙ ዕርምጃዎች እንዱወሰድባቸው ማድረግ እንደሆነ ተመልክቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በወንጀል ሕግ ቁጥር 82 መሰረት ቅጣቱን በማቅለል ከወሰነ በኋላ አመልካቾች ከፍ ብል እንደተመለከተው የቀድሞ የወንጀል ሪከርድ ያልቀረበባቸው ከመሆኑ አኳያ ይህንንም ወንጀል የፈፀሙት በድንገተኛ አጋጣሚ በየዋህነትና ባለማስተዋል ከመሆኑ አንፃር በአጠቃላይም ከወንጀል ሕግ ግብ አኳያ ሲታይ አንድ ጽኑ ማስጠንቀቂያ ብቻ ተሰጥቷቸው የተወሰነባቸው ቅጣት ሳይፈፀም ተግድ ቢቆይ ዲግም ጥፊት ከመፈፀም ሉታቀቡ እንደሚችለ ከአጠቃላይ የወንጀለ አፈፃፀምና ከአመልካቾች ሁኔታ መገንዘብ እየተቻለና ቅጣቱንም በወንጀል ሕግ ቁጥር 194 መሰረት በገደብ ላለማቆየት የሚያበቃ ምክንያት በላለበት ሁኔታ ቅጣቱን ለመገደብ የሚያበቃ በቂ ሕጋዊ ምክንያት እያለ እንዱገደብ ሳያደርግ መቅረቱ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይህንኑ ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በወ/መ/ቁ/7933 በ21/8/2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠውን የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ እንደዚሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንኑ በማጽናት በመ.ቁ. 45568 በ9/9/2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠውን ውሣኔ በበኩላችንም በማጽናት ነገር ግን በአመልካቾች ላይ የተወሰነው የ6 /ስድስት/ ወር ቀላል እሥራት ከፍ ብል በተመለከቱት ምክንያቶች ሳይፈፀም በ2 /ሁለት/ ዓመት ገደብ ይቆይ በማለት በወንጀል ሕግ ቁጥር 192 እና 197/1/ መሰረት ወስነናል።
በአመልካቾች ላይ የተወሰነው የእስራት ቅጣት የተገደበ ስለመሆኑ እንዱታወቅ ለሥር ፍ/ቤቶችና ለአ.አበባ ማረሚያ ቤት ይገለጽለት ብለናል።
አመልካቾች በዚህ ችልት ክርክር ሲደረግ እያንዲንዲቸው ለዋስትና በሞዳል 85 ያስያዙት ብር 2ዐዐዐ /ሁለት ሺህ/ እንዱመለስላቸው ለሚመለከተው ይፃፍ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተን ወደ መ/ቤት መልሰናል።
No topics extracted.