No summary available.
ሐምል 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የፋ/የሥነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐ/ሕግ - ዐ/ሕግ ቀረበ ተጠሪዎች፡- እነ ካፍ መሐመድ /4 ሰዎች/ - ጠበቃ ቀረበ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሣኔ ተሰጥቷል።
የጉዲዩ አጀማመር የፋዳራል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ሕግ ተጠሪዎች የተጠረጠሩበትን የወንጀል ድርጊት በመጥቀስ በተሻሻለው የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 23 መሰረት በማድረግ ተጠርጣሪዎች መዝብረውታል ለተባለው እና ለወደፉቱ ላደረሱት ጉዲት ማካካሻ የሚሆነውን ንብረታቸውን እንዲያሸሹ ወደ ላላ ወገን እንዲያዛውሩ እና ወደ ጥሬ ገንዘብ ቀይሮ ስለሚያባክኑ መደብሮቹ እንዱታሹጉ እና ጥበቃ እንዱደረግለት በመጠየቁ ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ከላይ የተቀጠሱት ተጠርጣሪዎች ዐ/ሕግ ክስ መስርቶባቸው በክርክር ላይ መሆናቸውንና ንብረታቸውን ያሳገደ ቢሆንም ተጠርጣሪዎች የታገደው ንብረት ከደረሰው ጉዲት የበለጠ በመሆኑ ተመጣጣኝ የሆነው ታግድ ላላው ሉለቀቅልን ይገባል ያለትን ክርክር ባለመቀበል ዕግደ እንዱቀጥል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪ /ተጠርጣሪዎች/ በዚሁ ትዕዛዝ ባለመስማማት ክርክራቸውን በማጠናከር የታገደው ንብረትና የደረሰው ጉዲት አይመጣጠንም፣ ደረሰ በተባለው የጉዲት ልክ ብቻ ነው ሉታገድ የሚገባው የቀረው ሉለቀቅልን ይገባል በማለት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቧል። የጠቅላይ ፍ/ቤቱም የተሰጠውን ዕግድ እና በተጠርጣሪዎች የተነሣውን ተቃውሞ ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። በመሆኑም በአዋጅ ቁ. 434/97 አንቀፅ 9 መሰረት የታገደው የተጠርጣሪ ንብረት ተፈፅሟል ከተባለው ወንጀል ደርሷል ከተባለው ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ መሆን እንዲለበት በመግለፅ በሥር ፍ/ቤት ዐ/ሕግ ደርሷል የሚለው ከፍተኛ ሲሆን የተጠርጣሪዎችም ንብረቶች በጠቅላላው ከመታገደ ውጪ የታገደት ንብረቶች በባለሙያ ተገምተው እንዲልቀረበ ተረድቻለሁ፣ የሥር ፍ/ቤቱም ተመጣጣኝ ነው ያለው በግምት እንጂ የተረጋገጠ ነገር የለም። ስለዚህ የተጠርጣሪዎች /ተጠሪዎች/ የንግድ መደብር ከግለሰብና ከመንግስት ተከራይቶ ሲጠቀሙበት የነበረ ስለሆነ ታሽገው መቆየቱ ተገቢ አይደለም ምክንያቱም በተከራዩም ሆነ በአከራይ ላይ ጉዲት የማያደርስ በመሆኑ ተጠርጣሪዎች በንግድ መደብርነት ሲገለገለበት የቆዩት ቤቶች ውስጥ የነበሩት ዕቃዎች እንዱወጡ ተደርጏ የንግድ ቤቶቹ ተከፍተው የተለመደው የንግድ ስራ ይከናወን በማለት በማሻሻል ወስኖ የሥር ፍ/ቤት በውሣኔው መሰረት እንዱያስፈፅም አዟል።
በዚህም መሰረት /በጠቅላይ ፍ/ቤት/ የተሰጠውን እንዱያስፈፅም ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ለአፈፃፀም ይረዲ ዘንድ የቀረበውን የግራ ቀኙን የአማራጭ ሃሣብ መሰረት አድርጏ ቢያከራክርም ሉስማሙ ባለመቻላቸው የጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት በመደብሩ ውስጥ የነበሩት ዕቃዎች አሻጊዎች በተገኙበት ተቆጥሮ ወጥቶ የኮሚሽኑ ዐ/ሕግ በሚያስቀምጥበት ቦታ አሻጊዎች በተገኙት ታሽጏ ይቀመጥ ተጠርጣሪዎች የንግድ ቤቶቹን እንዱረከቡ በማለት አዟል።
የኮሚሽኑም ዐ/ሕግ በዚሁ ትዕዛዝ ባለመስማማት በቀን 22/7/2001 ባቀረበው የሰበር አቤቱታው የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ውሣኔ እና የሥር ፍ/ቤቱም የይግባኝ ሰሚውን ውሣኔ ተከትል የሰጠው የአፈፃፀም ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱታረምለት ጠይቋል።
እኛም ይህንኑ መሰረት በማድረግ ተጠርጣሪዎችን /ጠበቃ/ እና ዐ/ሕጉን በማስቀረብ የቃል ክርክራቸውን ሰምተናል። ጉዲዩ በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተፈለገው የንግድ መደብሮቹ ከነበሩበት የንግድ ቤት ወጥተው አመልካች /ዐ/ሕግ/ በሚያዘጋጀው ቦታ እንዱቀመጡ የተሰጠው የዕግድ ማሻሻያ ትዕዛዝ በማስረጃ ሕጉ ስለ እግደ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች አንጻር ለመመርመር ነው።
በዚህም መሰረት ይህን ነጥብ የግራ ቀኙ ወገኖች ካሰሙት የቃል ክርክር፣ አቤቱታ ካቀረቡበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበናል። ለጉዲዩ መነሻ የሆነው የፋዳራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐ/ሕግ በተጠርጣሪዎች ላይ በመሰረተው ክስ የንግድ መደብራቸውን በማሳገደ ተጠርጣሪዎች የታገደው ንብረት ከደረሰው ጉዲት የበለጠ በመሆኑ ተመጣጣኙ ታግድ ላላው ይለቀቅልን በማለት ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታ በማቅረባቸው ፍ/ቤቱም የተሰጠው ዕግድ ተመጣጣኝ ነው ሲል ዕግድ ይቀጥል ብል ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠርጣሪዎቹ ተመሣሣይ ክርክራቸውን በማጠናከር ይግባኝ ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በማቅረባቸው። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ጥያቄ በመመርመር የታገደው የንግድ መደብርና የደረሰው ጉዲት ይመጣጠናል? አይመጣጠንም? ለሚለው ጥያቄ በሁለቱም ተከራካሪዎች ንብረቱ በባለሙያ ተሰልቶ እንዲልቀረበ ተረድቻለሁ። ይሁን እንጂ ተጠርጣሪዎች የሚነግደበት የንግድ መደብር ከግለሰብና ከመንግሥት ተከራይቶ ስለሆነ በአከራዩም ሆነ በተከራዩ ጉዲት ሉያደርስ ስለሚችል የንግድ ቤቱ ታሽጏ የሚቀመጥበት ምክንያት አይኖርም።
በመደብሩ ውስጥ የሚገኙትን ንብረቶችን የኮሚሽኑ ዐ/ሕግ አውጥቶ ላላ ቦታ ያስቀምጥ ድርጅቶቹ ተከፍቶ አገልግልታቸውን ይቀጥለ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። ይህንኑ ውሣኔ /ትዕዛዝ/ መሰረት በማድረግ አፈፃፀም የቀረበለት የሥር ፍ/ቤትም ተከራካሪ ወገኖች በአፈፃፀሙ ላይ ሉስማሙ ባለመቻላቸው በጠቅላይ ፍ/ቤቱ ውሣኔ መሰረት ይፈፀም በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። የኮሚሽኑ ዐ/ሕግም ተቃውሞ በዚሁ ላይ ነበር።
ለዚህ የሰበር ችልት ተያይዘው ከቀረቡት መዝገቦች ለመገንዘብ እንደቻልነው ለአሁኑ ክርክር መነሻ የሆነው የአሁኑ መልስ ሰጪዎች በተጠረጠሩበት የወንጀል ጉዲይ ከፍተኛው ፍ/ቤት እንዱታገደ ያደረጋቸው ንብረቶች በወንጀለ ምክንያት ደርሷል ከተባለው ጉዲት የበለጠ ዋጋ ያላቸው በመሆኑ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ብቻ ታግደው ቀሪዎቹ ይለቀቁልን በማለት ለከፍተኛው ፍ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ነው። ከፍተኛው ፍ/ቤት ይህን ማመልከቻ ውድቅ አድርጏታል። በትዕዛዙ ቅር ተሰኝተው መ/ሰጪዎች ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሲለ ግን ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በአንድ በኩል የታገደው ንብረት ግምት ደረሰ ከተባለው ጉዲት በላይ ነው ልባል አይችልም ሲል በልላ በኩል ግን የታገደት የመልስ ሰጪ ድርጅቶች ሥራቸውን እንዱቀጥለ ፈቅዶል። በመሰረቱ ከፍተኛው ፍ/ቤት የታገደው ንብረት ደረሰ ከተባለው ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ ነው? አይደለም? የሚለውን ሲመዝን ግምት ውስጥ ያስገባው አሁን ሥራ ይስሩ የተባለትን ድርጅቶች እንደ ድርጅት በመውሰድ ነው ጠቅላይ ፍ/ቤትም በመርህ ደረጃ የታገደው ንብረት ከጉዲቱ አይበልጥም የሚለውን መደምደሚያ ተቀብልታል። በከፍተኛ ፍ/ቤት ከተያያዙት ሰነድች ለመገንዘብ እንደቻልነው የዕግድ ትዕዛዝ የተጠየቀውም ሆነ የተሰጠው በንግድ መደብሮችም ጭምር ነው። የመደብሮቹ ዋጋ ሲሰላም ግምት ውስጥ የሚገባው የመደብሩ ውስጥ የሚገኙ ሸቀጥ ብቻ ሳይሆን የመደብሩ መልካም ስም (good will) ጭምር ነው። በመሆኑም የዕግደ ዓላማ ደረሰ የተባለውን ጉዲት የሚመጥን ንብረት ይዞ ማቆየት እንደመሆኑ መደብሩ ከሸቀጡ ተነጥል እንዱታይ መደረጉ የዕግደን ዋና ዓላማው የሚያስቀር ነው። በመሆኑም ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የመደብሩ ዋጋ ደረሰ ከተባለው አደጋ በላይ ነው ልባል አይቻልም ካለ በኋላ መደብሩ ከዕግድ ትዕዛዙ ውጪ እንዱሆን መደረጉ እርስ በርሱ የሚጋጭ ውሣኔ መስጠቱን የማያመለክት ነው። መደብሮቹ ታሽገው መቆየታቸው መልስ ሰጪዎች ሉጏደ እንደሚችለ ይገመታል። ነገር ግን በመልስ ሰጪዎች ሉደርስ የሚችለው ጉዲት ደረሰ ከተባለው የወንጀል ጉዲት ጋር በማመዛዘን መመልከትም ያስፈልጋል።
በመደብሩ ውስጥ ያለ ሸቀጦች ተለይተው የተቀመጡም ቢሆን በመልስ ሰጪዎች ላይ የኢኮኖሚ ጉዲት ሉደርስ እንደሚችል መገመት ይችላል። ጠቅላይ ፍ/ቤቱ መደብሮቹን አግድ ማቆየቱ በአከራይም ሆነ በተከራይ ጉዲት የሚያደርስ ነው በማለት ብቻ ሸቀጡን ከመደብሩ መነጠለ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም። በዚህም ምክንያት የጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ መሻር ያለበት ነው ወደሚል መደምደሚያ ደርሰናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ.4180 ጥር 8/2001 በሰጠው ትዕዛዝና የከፍተኛው ፍ/ቤት ይህንኑ ትዕዛዝ ለማስፈፀም የካቲት 12 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ወ/ቁ. 64231
No topics extracted.