No summary available.
የካቲት 19 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡- እነ ጀሚላ መሐመድ ሀጏስ - ጠበቃ እሸቴ ጓንጉል ቀረቡ ተጠሪ፡- የፍዳራል የመ/ደ/ዓ/ቃህ - ፋሲል ገብሬ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ መዝገብ ለሰበር ችልቱ የቀረበው አመልካቾች በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጠው የጥፋተኛነት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረምልን ይገባል በማለት ግንባት 26 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ዘርዝረው ስላቀረቡ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፍዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካቾች ላይ የመሰረተው ክስ የግል ተበዲይ ወ/ሮ ዘርፍ ጥላሁን በአቶ መሐመድ ሐጏስ ቤት በቤት ሰራተኛነት ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ ግለሰቡ በ1990 ዓ.ም ወደ ኤርትራ ሲባረሩ ቤታቸውን በኃላፊነት እየጠበቁ እንዲለ ሐምል 21 ቀን 1997 ዓ.ም አመልካቾች የግል ተበዲይን እቃ ከቤት አውጥተው ግቢ ውስጥ በማስቀመጥ በግብረአበርነት በፈፀሙት ህገ ወጥ በሆነ መንገድ መብትን የማስከበር ወንጀል በኢ.ፍ.ዳ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1ሀ/ እና 436/1/ሀ/ መሰረት ጥፋተኛ ተብለው ሉቀጡ ይገባል የሚል ሲሆን አመልካቾችም የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ በክሱ ላይ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን በመግለጽ የድርጊቱን አፈፃፀም በተመለከተ ግን ጥፋተኛ አይደለንም ሲለ አስመዝግበዋል። የስር ፍ/ቤትም የዓ/ህግን ማስረጃዎች ከሰማ በኋላ አመልካቾች እንዱከላከለ ትዕዛዝ ሰጥቶ የአመልካቾችን የሰው እና የጽሐፍ ማስረጃዎችን በመስማት ጉዲዩን በመመርመር የአመልካቾች የመከላከያ ማስረጃዎች የዓ/ህጉን ማስረጃዎችን ለማስተባበል በቂ አይደለም የሚል ምክንያት ይዞ አመልካቾችን በዓ/ህግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበባቸው ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ አድርጏ እያንዲንዲቸውን በብር 800.00 /ስምንት መቶ/ የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጡ ወስኗል። ከዚህ በኋላም አመልካቾች ይግባኛቸውን ለፍዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ አመልካቾች ጥፋተኛ መባላቸው ባግባቡ መሆኑን በመግለጽ ድርጊታቸው የሚሸፈንበትን ድንጋጌ ብቻ በማሻሻል ቅጣቱንም በማጽናት ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን የጥፋተኛነት ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካቾች ግንቦት 26 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፉት የሰበር ማመልከቻ ተፈፀመ የተባለው ድርጊት የጥፋተኛነት ውሣኔ የተሰጠበትን አንቀጽ የወንጀል ማቋቋሚያ ነጥቦችን የሚያሟላ የወንጀል አላፊነትን የሚያስከትል መሆኑን ያሳያለ ያሎቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ሉታዩ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርቦ የአመልካቾች ድርጊት ወንጀለን የሚያቋቁም መሆኑንና ጥፋተኛ መባላቸውም ባግባቡ መሆኑን ጥቅምት 17 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ዘርዝሮ የጥፋተኛነት ውሣኔው ሉፀና ይገባል ሲል ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘበ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል እንደመረመረውም አመልካቾች ፈፀሙ የተባለው ድርጊት የወንጀል ድርጊት ያቋቁማል ወይም አያቋቁምም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
አመልካቾች የተከሰሱትና በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የጥፋተኛነት ውሣኔ የተሰጠባቸው የኢ.ፍ.ዱ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1ሀ/ እና 436/1/ ስር የተመለከተውን ተላልፈዋል በሚል ሲሆን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በአመልካቾች የተሰጠውን የጥፋተኛነት ውሣኔ አንቀፁን በመለወጥ አጽንቷል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካቾችን ጥፋተኛ ያደረጋቸው በኢ.ፍ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 436/ሐ/ ስር ነው።
ህገ ወጥ በሆነ መንገድ መብትን ማስከበር ድርጊት በኢ.ፍ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 436/ሐ/ መሰረት ሉያስጠይቅ የሚችለው ማንም ሰው መብት ሳይኖረው ወይም ህግን ተቃራኒ በሆነ መንገድ በጠቅላላው የላለውን ወይም በህጉ መሰረት ሉሰራበት የማይችለውን መብት የተጠቀመበት እንደሆነ ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካቾች የግል ተበዲይ ወ/ሮ ዘርፍ ጥላሁን ቤቱን እንዱለቁ ሲያደርጉ የግል ተበዲይዋ ቤቱን የያዙት በጠባቂነት በነበራቸው ኃላፊነት ስለመሆኑ አንደኛ አመልካች ደግሞ የቤቱ ባለቤት የተባለት ግለሰብ የአቶ መሐመድ ሐጏስ ልጅ ሁለተኛ አመልካች ደግሞ ድርጊቱ ሲፈፀም በቦታው ላይ የተገኙት ከአንደኛ አመልካች በተሰጣቸው ውክልና መሰረት ስለመሆኑ የተረጋገጡ ጉዲዮች ናቸው። በመሆኑም አንደ1ኛ አመልካች በቤቱ ላይ በጠቅላላው መብት የላላቸው ወይም በህጉ መሰረት ሉሰሩበት በማይችለት መብት የተጠቀሙ ሳይሆን በቤቱ ላይ መብት ያላቸው ስለመሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
በመሰረቱ አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀለን የሚያቋቁምበት ህጋዊ፣ ግዙፋዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተጣምረው ሲገኙ ብቻ ስለመሆኑ የኢ.ፍ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ በአንቀጽ 23/2/ ስር አስቀምጧል እጃችን ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የአመልካቾች ድርጊት የጥፋተኛነት ውሣኔ የተሰጠባቸው የህግ ድንጋጌ የወንጀል ማቋቋሚያ ነጥቦች የተሟለበት አይደለም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ የኢ.ፍ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 23/2/ እና 436/ሐ/ ስር የተመለከቱትን የህጉን መስፈርቶች ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህ መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.