No summary available.
ጥር 19 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ብርቁ ገላነው /አቶ/ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የአማራ ብ/ክ/መ/የስነ- ምግባርና ፀረ- ሙስና ኯሚሽን - አልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ ተጠሪ በአመልካች ላይ የመሰረተውን የወንጀል ክስ የሚመለከት ነው።
ከመዝገቡ ማየት እንደተቻለው ተጠሪ በሶስት ወንጀል ድርጊቶች አመልካችን ከሶ የነበረ ሲሆን፣አመልካች በሁለቱ ብቻ ጥፊተኛ ተብል ቅጣት ተወስኖበታል። ጥፊተኛ የተባለባቸው ክሶች በልዩ ወ/መ/ሕግ አዋጅ ቁ. 214/74 አንቀጽ 23/1//ሀ/ እና አንቀጽ 17/1/ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። አመልካች እነዚህን የወንጀል ድርጊቶች ፈጸመ የተባለው በወረዲ ፍ/ቤት የዲኝነት ስራው ላይ እንዲለ ነው። ዝርዝሩም በተከፈተው የፍትሐብሕር መዝገብ ተከሣሽ የከነበረችው ግለሰብ ሳትቀርብ ቀርባ መልስ እንደሰጠች አድርጏ በመመዝገብ ውሳኔ ሰጥቶአል። ለፍ/ቤት የተላከውን ሰነድ በመሰረዝ /በመደለዝ/ በሕዝብና በመንግስት ሰነድ ላይ ወንጀል ፈጽሞአል በሚል ሉጠቃለል እንደሚችል ለመገንዘብ ችለናል። በዚህ መልክ ክሱ የቀረበለት በአማራ ብ/ክ/መ/የምእራብ ጏጃም ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት አመልካች ወንጀልቹን ለመፈጸሙ በምስክሮች አረጋግጫለሁ በማለት የጥፊተኛነት ውሳኔ በመስጠት አመልካች በሰባት አመት ጽኑ እስራት እና በብር 200(ሁለት መቶ) መቀጫ እንዱቀጣ አዞአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማለቱ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን፣በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በቅጣት ረገድ የተሰጠውን ውሳኔ ብቻ በማሻሻል አመልካች በሁለት አመት እስራት እና በብር 200(ሁለት መቶ) መቅጫ እንዱቀጣ ወስኖአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ሐምል 26 ቀን 99 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች የዲኝነቱን ስራ በሚሰራበት ጊዜ በልዩ ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አዋጅ ቁ. 214/74 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት ተደርጏ በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ፈጽሞአል በሚል የመከሰሱንና ጥፊተኛ የመደረጉን አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው አመልካች የተከሰሰው የዲኝነት ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ በስልጣኑ ያለአግባብ ተገልግልአል እንደዚሁም የመንግስትና የሕዝብ ሰነድችን ወደ ሐሰት ለውጦአል ተብል ነው። ወንጀልቹና ፈጸመ የተባለው የፍትሐብሕር ክርክር በሰማበት መዝገብ እንደሆነም ተገንዝበናል። እንደሚታወቀው የፍትሐብሕር ክርክር የሚመራው በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕጉ ነው። በአንደኛው ክስ እንደተገለጸው ተከሣሽ የነበረችው ግለሰብ ሳትቀርብ እንደቀረበች ተደርጏ ተወስኖ ወይም ተመዝግቦ ላሆን ይችላል። እዚህ ላይ በጥንቃቄ ላታይ የሚገባው ነገር እንዲለ ግን ልብ ልባል ይገባል። በእርግጥም በተባለችው ግለሰብ ስም የቀረበ የጽሐፍ መልስ የለም አልተባለም። በመሆኑም መልሱ ውክልና በላለው በተሳሳተ/በማይመለከተው/ ሰው ተዘጋጅቶ ቀርቦአል እንኳን ቢባል ይህን መሰል ስህተት ሲከሰት ለማስተካከል በሚል በተደነገጉት የስነ-ስርአት ሕጉ ድንጋጌዎች የሚስተካከል ይሆናል እንጂ የተፈጠረው ስህተት በቀጥታ ዲኛው/አመልካች/ሆነ ብል ስልጣኑን ያለአግባብ በመገለገል የፈጸመው የወንጀል ድርጊት ነው ወደሚለው የሚያደርስ የሕግ ምክንያት የለም። ከመዝገቡ እንዲየነውም ሳትቀርብ እንደቀረበች ተደርጏ ተመዝግባ ውሳኔ ተሰጥቶአል የተባለችው ግለሰብ ወይም በዚህ ሂደት መብቴ ተጏድቶአል የሚል ወገን በፍትሐብሓሩ መዝገብ አቤቱታ አላቀረቡም ወይም አቅርበዋል አልተባለም። ይህን በራሱ የሚያሳየው በክሱ አመራርም ሆነ ውሳኔ የተጏዲ ወገን አለመኖሩን ነው። የተጏዲ የለም ከተባለ ደግሞ በተቃራኒው ከሕግ ውጪ ውሳኔ የተሰጠበት ወይም የተጠቀመ ተከራካሪ ወገን የለም ማለት ነው። ከሁለ በላይ ደግሞ አመልካች በተያዘው የፍትሐብሕር ክርክር ከማንኛወም ተከራካሪ ወገን ጥቅም ወይም መደለያ /ጉቦ/ ተቀብልአል የሚል ክስ አልቀረበም። በአጠቃላይ በግለሰብዋ አቀራረብ ወይም መልስ አሰጣጥ ረገድ ስህተት ነበር የሚባል እንኳን ቢሆን፣በግለሰብዋ ወይ ጉዲይ ይመለከተኛል በሚል ወገን አግባብ ባለው የስነ-ስርአት ሕጉ መሰረት አቤቱታ ሲቀርብ የሚታይ እንጂ በአቃቤ ሕግ ክስ እንደተነገረው በልዩ ወ/መ/ሕግ አዋጅ ቁ. 214/74 ድንግጌዎች ስር የወንጀል ድርጊት የሚያቋቁም ጥፊት ተፈጽሞአል የሚያሰኝ አይደለም።
በ2ኛ ደረጃ የተጠቀሰው ክስም እንዲየነው ለክርክሩ ምክንያት የነበረው ቤት በተመለከተ ከማዘጋጃ ቤት የተጻፈውን ደብዲቤ ቁጥሩንና ቀኑን ለውጦ ጽፍአል በሚል የቀረበ ነው። ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም ይህን በሰው ምስክር አረጋግጫለሁ በማለት ነው አመልካችን ጥፊተኛ ያደረገው። ሁለም በግልጽ እንደሚያውቀው በአንድ የክርክር መዝገብ ላይ ውሳኔ የሚሰጠው የተሰየመው ዲኛ ቢሆንም፤ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው በዲኛው ቁጥጥር ስር ሆኖ ይቆያል ማለት ግን አይደለም። ከሁለም በላይ ግን በተባለው ደብዲቤ ላይ የቁጥር እና በቀን አጻጻፍ ረገድ የተፈጠረ ችግር አለ በመባለ ብቻ በዲኛ ላይ የወንጀል ክስ መመስረት የሚቻል አይሆንም። ሲጠቃለል ተፈጠሩ የተባለት ክስተቶች ካለም ከዲኝነት ስራ ስነምግባርና ዱሲፔሉን አኳያ የሚታዩ ናቸው። ከዚህ ባለፈ ግን አመልካች በወ/መ/ሕግ አዋጅ ቁ. 214/74 በተመለከቱት ድንጋጌዎች ስር ወንጀልን የሚያቋቁም ድርጊት ፈጽሟአል በሚል የቀረበው ክስም ሆነ የተሰጠው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ የሕግ መሰረት ያለው ነው የሚባል አይደለም። በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል። ስለዚህም አቤቱታ የቀረበባቸው በአማራ ብ/ክ/መ/ በምእራብ ጏጃም ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 10588 በ14/07/99 ዓ.ም የተሰጠው እና በክልለ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 12083 ሰኔ 13 ቀን 1999 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕግ ሥ/ሥ/ቁ. 195/2//ለ//1/ መሰረት ተሽረዋል። አመልካችም በነጻ ተለቆአል። ለሚመለከተው ይፃፍ።
No topics extracted.