No summary available.
ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ - ዓቃቤ ሕግ አውግቸው መኮንን ቀረበ።
ተጠሪ፡- ከበደ ወርቅነህ - አልቀረቡም።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 1384ዐ ኀዲር 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.
የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ታህሣሥ 29 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በመጠየቁ ነው። የክርክሩ መነሻ የምዕራብ ጎጃም ዞን ዓቃቤ ሕግ በከሣሽነት ተጠሪ በተከሳሽነት ተከራክረዋል። የዞኑ ዓቃቤ ሕግ በተጠሪ ላይ፣ መጋቢት 28 ቀን 1998 ዓ.ም. ከምሽቱ በግምት አራት ሰዓት ሲሆን የግል ተበዲይ የመኩሪያው ተጋፊውን ቤት በማቃጠል በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ተኝተው የነበሩት ይታይሽ አለማየሁ፣ አለባቸው መኩሪያውና ፊሲካ መኩሪያው በእሳት ተቃጥለው እንዱሞቱ ያደረገ በመሆኑና ድርጊቱን የፈፀመው በእሳት ቃጠል ምክንያት በውስጥ ያለ ሰዎች ሉሞቱ እንደሚችለ እያወቀ በ1996 ዓ.ም. የወጣውን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ 539/1/ሀ/ በመተላለፍ የሆነው ይሁን በሚል ተነሳስቶ በመሆኑ ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል፤ ይህ የሚታለፍ ቢሆን በአማራጭ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 543/2/ የተመለከተውን በመተላለፍ በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል፤ እንደዚሁም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 494 ንዐስ አንቀጽ 2 የተመለከተውን በመተላለፍ ግምቱ ከብር 2ዐ,ዐዐዐ /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ የሆነ ንብረት ሙለ በሙለ እንዱወድም አድርጓል የሚለ ክሶችን አቅርቦበታል።
ተጠሪ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ የገለፃቸውን የወንጀል ድርጊቶች አልፈፀምኩም በማለት ክድ በመከራከሩ ዓቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮች አሰምቷል። ተጠሪ ለወረዲ ፍርድ ቤት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 35 መሰረት የሰጠውን የዕምነት ቃል በሰነድ ማስረጃነት አቅርቧል። የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ቤቱ ከውጭ እንደተቆለፈ በእሳት የተቀጣጠለ መሆኑንና በክሱ ስማቸው የተገለፀው ሰዎች በእሳት ተቃጥለው መሞታቸውን ልዩነት በላለው ሁኔታ የመሰከሩ መሆኑንና ሁለተኛው የዓቃቤ ሕግ ምስክር በእሳት ተቃጥላ የሞተችው ሴት ተከሣሽ መኩሪያው ተጋፊውን ከነ ቤተሰቦቹ ቆልፋ በእሳት አቃጥላለሁ እያለ ይዝት እንደነበር ከዚያ ቀን በፉት ነግራኛለች በማለት የመሰከረ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ያሣያል።
ላላው በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበው ማስረጃ ተጠሪ በወንጀለኛ መቀጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 35 መሰረት የሰጠው የዕምነት ቃል ሲሆን መጋቢት 29 ቀን 1998 ላሉት 4 ሰዓት ሲሆን የመኩሪያው ተጋፊውን ቤት አቃጥየዋለሁ፤
ያቃጠልኩት መጋቢት መባቻ ላይ በደላ ስለመታኝ ነው፤ ቤቱ ከውጭ ተቆልፍ የነበረ በመሆኑና የቤቱ ባለቤት ወደ ማኀበር ሲሄድ ስላየሁት ቤተሰቦቹም ሄደዋል ብዬ ነው ያቃጠልኩት፤ ቤቱም ከውጪ ተቆልፍ ነበር የሚል ይዘት ያለው ነው። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ መከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ ተጠሪ በወቅቱ በአካባቢው ያልነበረ መሆኑን ሁለት የመከላከያ ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 543/3/ የተመለከተውን በመተላለፍ በቸልተኝነት ሶስት ሰዎችን የገደለ ጥፊተኛ ነው፤
እንደዚሁም በወንጀል ሕጉ 691 የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው በማለት ፍርድ ሰጥቷል።
ቅጣቱን በተመለከተ ለመጀመሪያው ጥፊት በሰባት ዓመት ጽኑ እስራትና በአንድ ሺህ አምስት መቶ ብር መቀጮ፣ በሁለተኛው ጥፊት በሁለት ዓመት ጽኑ እስራትና በአምስት መቶ ብር መቀጮ በጥቅለ በዘጠኝ ዓመት ጽኑ እስራትና በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ በማለት ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ፍርድ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በእሳት ተቃጥለው የሞቱትን ሰዎች በተመለከተ ተጠሪ ሉያደርገው የሚችለው ጥንቃቄ አልነበረም፤ የሀሣብ ሁኔታው አልተሟላም በማለት ሙለ በሙለ በነፃ እንዱለቀቅ የወሰነ ሲሆን የሁለት ዓመት ጽኑ እስራትና አምስት መቶ ብር ቅጣት በማጽናት ወስኗል።
አመልካች ይህ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው የሕግ ትርጉምና ውሣኔ መሰረታዊ ስህተት አለበት፤ ተጠሪ ቤቱን በማቃጠል የግል ተበዲይ ያደረሰበትን ጉዲት ለመበቀል አስቦ ያደረገው መሆኑ በሰው ምስክርም ሆነ በጽሁፍ ማስረጃ ተረጋግጧል፤ ተጠሪ ከምሽቱ አራት ሰዓት በመሄድ ቤት ያቃጠለው ንብረት ለማውደም ብቻ ሣይሆን ሰዎች የሚተኙበት የእንቅልፍ ሰዓት በመሆኑ የግል ተበዲይን ከነቤተሰቡ በእሳት ለማቃጠል በነበረው ሀሣብ እንደሆነ በማስረጃ አስረድተናል፤
ሆኖም የከፍተኛው ፍርድ ቤት በአማራጭ የቀረበውን በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል ተጠሪን ጥፊተኛ ሲል ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ያልጠየቀ በመሆኑ በከባድ ሰው መግደል ተጠሪ መጠየቅ አለበት ብለን ለመከራከር የሥነ ሥርዓት ገደብ ቢኖርብንም ከዚህ አልፍ የጠቅላይ ፍርድ ቤት በተጠሪ በኩል ቸልተኝነት የለም በማለት መወሰኑ ለወንጀል ሕጉ አንቀጽ 59 እና 543/3/ የተዛባ ትርጉም የሰጠና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የሰራ መሆኑን ሰለሚያሣይ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ ለአመልካች አቤቱታ መልስ ይዞ እንዱቀርብ መጥሪያ የደረሰው ሲሆን መልሱን ይዞ አልቀረበም። ስለሆነም በላለበት ጉዲዩ እንዱታይ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ከሥር የክርክሩ አመጣጥና የክርክሩ ፍሬ ጉዲይ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው ተጠሪ ቤቱን ከምሽቱ አራት ሰዓት ያቃጠለው ከግል ተበዲይ መኩሪያው ተጋፊው ጋር ከዚያ በፉት ተጣልተው የግል ተበዲይ በደላ ስለደበደበው መሆኑን የዓቃቤ ሕግ የሰነድ ማስረጃ ያረጋግጣል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ የግል ተበዲይን ቤት ከውጭ ቆልፋ ከነቤተሰቡ ነው የማቃጥለው በማለት ይዝት እንደነበር አንደኛዋ ሟች ነግራኛለች በማለት አስረድቷል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ከነሙለ ይዘቱ መመዘን አለበት በማለት የሰጠው ትችት ተቀባይነት ያለው የማስረጃ አመዛዘን መርህ በመሆኑ የሚነቀፍ አይደለም። ሆኖም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበውን ማስረጃ ከነሙለ ይዘቱና መልዕክቱ የመዘነ ሆኖ አላገኘነውም። ዓቃቤ ሕግ የጽሁፍ ማስረጃ አድርጎ ባቀረበው የተጠሪ ዕምነት ቃል የግል ተበዲይ ወደ ማኀበር ሲሄድ ስላየሁት ቤተሰቦቹም ሄደዋል ብዬ በማሰብ ቤቱን አቃጠልኩት የሚል ፍሬ ጉዲይ አለ። ከዚህም የምንረዲው ተጠሪ በእሳት ቃጠል ሕይወታቸው ያለፈው የግል ተበዲይ ቤተሰቦች ወደ ማኀበር ሲሄደ ያላያቸው መሆኑን ነው። ተጠሪ ሟቾች ወደ ማኀበር ስለመሄዲቸው እርግጠኛ ባልሆነበት ሁኔታ ማኀበር ሄደዋል ብል ስለገመተ ብቻ ቸልተኝነት የለበትም ለማለት አይቻልም። ወቅቱ ላሉት ከመሆኑ አንፃር ሲታይ የግል ተበዲይን ቤትና ንብረት የሚጠብቅ ሰው ከቤት ሉኖር እንደሚችል ማወቅ ሲገባው ወይም እያወቀ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 59 የተደነገገውን ቸልተኝነት የሚያሟላ ነው። የሟቾች ከቤታቸው ውስጥ ተኝተው መገኘት ከተጠሪው አቅም በላይ የሆነ ኃይል ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የተፈፀመ ጉዲይ አይደለም። ሰለሆነም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 543 ንዐስ አንቀጽ 3 ጥፊተኛ ነው በማለት የሰጠው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበው ማስረጃ ተጠሪ ከግል ተበዲዩ ጋር በነበረው ጠብ በቂም በቀል ተነሳስቶ የግል ተበዲይን ቤት በእሳት ያቃጠለ መሆኑን ያረጋግጣል። ተጠሪ በለኮሰው እሳት ተቃጥለው ሰዎች ሞተዋል። ተጠሪ ቤቱን የማቃጠል እንጂ ሟቾቹን የመግደል ሀሣብ አልነበረውም ቢባል አንኳን በቸልተኝነት ሟቾችን በመግደለ ተጠያቂ የማይሆንበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም። ስለዚህ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ ሉያደርገው የሚገባው ጥንቃቄ አልነበረም በቸልተኝነት በሰው መግደል ወንጀል ጥፊተኛ መባል የለበትም በማለት የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 1384ዐ ኀዲር 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተጠሪ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 543/3/ በመተላለፍ በቸልተኝነት የሰው መግደል ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው ተብል ሉጠየቅ አይገባውም በማለት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የዞኑ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በመ”ዝገብ ሀምላ 23 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። ይፃፍ።
ተጠሪ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 543 ንዐስ አንቀጽ 3 የተደነገውን በመተላለፍ ሟች ይታይሽ አለማየሁ፣ አለባቸው መኩሪያውና ፊሲካ መኩሪያውን በቸልተኝነት የገደለ ጥፊተኛ ነው ብለናል። ለዚህ ጥፊቱም ከፍተኛው ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት በሰባት ዓመት ጽኑ እስራትና በአንድ ሺህ አምስት መቶ ብር መቀጮ ይቀጣል ብለናል።
ይህንን ቅጣት ተከታትለው እንዱያስፈጽሙ ለክልለ ፕሉስ ኮሚሽንና ለክልለ ማረሚያ ቤቶች አስተዲደር ይፃፍ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.