No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ታደሰ ገ/መስቀል - ወኪል በላይነሽ ሽፊው ቀረበች ተጠሪዎች፡- 1/ ሙለጌታ ዘካርያስ 2/ ወ/ሮ አበቡ ገበያው 3/ መሐመድ ይማም - ወኪልም ነው ቀረበ 4/ ዘውዳ ይማም 5/ ወ/ሮ ሩቅያ ይማም 6/ ወ/ሮ ዘይነባ ይማም 7/ ወ/ሮ አሚናት ይማም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአፈፃፀም ደረጃ ያለ የፍትሐብሕር ክርክር የሚመለከት ነው። የጉዲዩ ታሪክ እንደሚያመለክተው በውርስ ንብረት ክፍፍል መነሻነት አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች በአንድ በኩል፤ ከሦስተኛ እስከ ሰባት ድረስ ያለት ተጠሪዎች ደግሞ በልላ በኩል በመሆን ክርክር ከተደረገ በኋላ፤ በወቅቱ ከሣሾች የነበሩት ከሦስተኛ እስከ ሰባተኛ ድረስ ያለት ተጠሪዎች በአንደኛ እና በሁለተኛ ተጠሪዎች ላይ አስወስነው የፍርድ ባለመብት ሆነዋል። ይህን ውሣኔ መሰረት በማድረግም የአፈፃፀም መዝገብ ያስከፈቱ ሲሆን፣ በዚህን ጊዜም አመልካችንም የአፈፃፀም ተከሣሽ አድርገውት እንደነበር እና ፍ/ቤቱ ግን አመልካች ተከሶ የተፈረደበት የፍርድ ባለእዲ አይደለም በማለት ከአፈፃፀም ክሱ ውጪ እንዲደረገው ተገንዝበናል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ለአንደኛ እና ለሁለተኛ ተጠሪዎች ገንዘብ አበድሮ የነበረ በመሆኑ እና የውርስ ሃብት ነው ተብል ተጠሪዎች የሚከራከሩበት ቤትም በመያዣ ይዞ ስለነበር ይህን የብድር እና የመያዣ ውል መነሻ በማድረግ በአንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎችን በመክሰስ ቤቱን እንዱረከብ በፍ/ቤት አስወስኖአል። አመልካች ይህን ውሣኔ ያሰጠው በ1993 ዓ.ም ሲሆን፣ ከሦስተኛ እስከ ሰባተኛ ድረስ የተጠቀሱት ተጠሪዎች በአንደኛ እና በሁለተኛ ተጠሪዎች ላይ ያስወሰኑት በ1997 ዓ.ም እንደሆነ መዝገቡ ያመለክታል።
አመልካች በአፈፃፀም መዝገቡ ተጣምሮ መከሰሱን እንዲየ ከሦስተኛ እስከ ሰባተኛ ድረስ የተጠቀሱት ተጠሪዎች ቤቱን በተመለከተ ያሰጡት ውሣኔ መኖሩን ስላወቀ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 መሰረት መቃወሚያ አቅርቦ ክርክር ከተካሄደ በኋላ ቤቱ በመያዣ የያዘው ከመሆኑም በላይ፤ በፍርድም ለሱ ይገባል ስለተባለ ከሦስተኛ እስከ ሰባተኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተጠሪዎች ላሰጥ አይገባም በሚል ተወስኖለታል። በዚህም በተጠሪዎች መካከል በተደረገው ክርክር መሰረት ተሰጥቶ የነበረው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 36ዐ/2/ መሰረት ተሽሮአል። ከዚህ በኋላ ከሦስተኛ እስከ ሰባተኛ ድረስ የተጠቀሱት ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 36ዐ/2/ መሰረት የተሰጠውን ውሣኔ በመቃወም በአማራ ብ/ክ/መ/ ለደቡብ ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው የነበረ ሲሆን፣ በስር ወረዲ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በሚል ይግባኛቸው ሣይስተናገድ ቀርቶአል። በመጨረሻም አመልካች እና አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎችን መልስ ሰጭ በማድረግ ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረባቸው በዚህ ደረጃም ክርክሩ ተሰምቶአል። በመቀጠልም ፍ/ቤቱ በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጡትን ውሣኔዎች በመሻር አመልካች በቤቱ ላይ መብት የለውም። ቤቱ በተጠሪዎች መካከል ይከፊፈል በማለት ወስኖአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ግንቦት 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች ጥር 24 ቀን 1993 ዓ.ም በመ.ቁ. 14/93 ክርክር ባስነሣው ቤት ላይ የሰጠው ውሣኔ በይግባኝ ባልተሻረበት ሁኔታ የጠ/ፍ/ቤቱ በተጠሪዎች መካከል የነበረውን ክርክር ሲመረምር በመ.ቁ. 14/93 ላይ የተሰጠውን ውሣኔ የመሻሩን አግባብነት ለመመርመር ተብል ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው አመልካች በመ.ቁ. 14/93 ጥር 24 ቀን 1993 ዓ.ም ባስወሰነው መሰረት ለክርክሩ መንስኤ በሆነው ቤት ላይ የፍርድ ባለመብት ሆኖአል። ውሣኔው የተሰጠው ከሱ ገንዘብ በተበደሩት እና ቤቱንም በመያዣ በሰጡት አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻነት ነው። ይህ ፍርድ ለየትኛውም ፍ/ቤት በይግባኝ ቀርቦ አልተሻረም። ከሦስት እስከ ሰባት ድረስ የተጠቀሱት ተጠሪዎች ይህን አመልካች በመክሰስ በቤቱ ላይ መብት አላገኙም።
ከዚህ የተነሣም አመልካች ቤቱን ያስረክባቸው ዘንድ የሚያስገድደበት ምንም የሕግ ምክንያት የለም። አመልካች በቤቱ ላይ ያገኘው በፍርድ ላይ የተመሰረተ የባለቤትነት መብት በተመሣሣይ ሁኔታ በፍርድ ሃይል እስካልተነሣ ድረስ ምን ጊዜም የቤቱ ባለቤት ሆኖ የሚቀረው አመልካቹ ነው።
የአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በስር ወረዲ ፍ/ቤትም ሆነ በከፍተኛ ፍ/ቤት በተሰጠው አመልካችን የቤቱ ባለቤት ባደረገው ውሣኔ ላይ ይግባኝ አልቀረበለትም። ቤቱ የአመልካች አይሆንም በማለት የወሰነው በይግባኝ ያልቀረበለትን ውሣኔ ተፈፃሚነት የሚኖረው ውሣኔ አይደለም የሚል ትችት በመስጠት እንደሆነ ከውሣኔው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል።
በመሰረቱ በሕግ አግባብ በፍ/ቤት የተሰጠን ውሣኔ የሞራልን ወይም የሕሉናን አስተሳሰብ መሰረት በማድረግ ዋጋ አልባ ሆኖ እንዱቀር ማድረግ በየትኛውም መለኪያ ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም። በተያዘው ጉዲይ እንደሚታየው አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች በክስ እንደላልቹ ተጠሪዎች በቤቱ ላይ የውርስ መብት እንደነበራቸው ተመልክተዋል። ቤቱን ለብድር በመያዣነት ለአመልካች የሰጡትም በእነሱ እጅ ስለነበረ እንደሆነ ይገመታል። ለምን እነሱ ብቻቸውን በመያዣነት ሰጡ ብል መጠየቁም አግባብ ላሆን ይችላል። ነገር ግን ከዚህ ሁለ በፉት አመልካች ቤቱን በፍርድ የሱ እንዱሆን አድርጓል።
በመሆኑም ላልችም የውርስ መብት አላቸው ስለተባለ ብቻ ያለምንም ሕጋዊ ምክንያት ፍርደ ተፈፃሚ እንዲይሆን ወይም ማምከን አይቻልም። ሲጠቃለል የአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 311/2ዐዐዐ ግንቦት 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል። የደቡብ ወል መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የደሴ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት የሰጡአቸው ትእዛዝና ውሣኔ ፀንተዋል።
አመልካች ጥር 24 ቀን 93 ዓ.ም በመ.ቁ. 14/93 በተሰጠው ውሣኔ በቤቱ ላይ ባለመብት ስለሆነ ለተጠሪዎች ሉያስረክብ አይገደድም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሣቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ፣፣
No topics extracted.