No summary available.
መጋቢት 17 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የህፃን ሰላማዊት ቴዎድሮስ ሞግዚት - ወ/ሮ ፍርቱና ገ/መድህን ቀረቡ ተጠሪ፡- መምህር ሚካኤል ግደይ - የቀረበ የለም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች በ17/07/1999 ዓ.ም በፃፈት የአፈፃፀም ክስ በ06/07/1999 ዓ.ም በተሰጠው ውሣኔ መሰረት እንዱፈጸምላቸው ይታዘዝላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ ተጠሪ ላይ በማእከላይ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመሰረቱት የአፈፃፀም ክስ መነሻ ሲሆን የአሁኑ ተጠሪም በፍርድ ባለእዲነታቸው ቀርበው ፍርደን እንዱፈጽሙና የማይፈጽሙበት ምክንያት ካለም እንዱያስረደ ተደርገው በዋናው ጉዲይ በተሰጠው ውሣኔ መሰረት መኪናዋን ለፍርድ ባለመብት ለሆኑት ለአሁኗ አመልካች እንዱያስረክቡ ታዝዞ አረካካቢ አካልም ተመድቦና መኪናዋ ላይ ጏድለዋል የሚባለትን እቃዎችን ከዋጋ ግምት ዝርዝር ጋር ለፍ/ቤቱ እንዱገልጽ ተደርጏ ይኸው ከተፈፀመ በኋላ የአፈፃፀም ከሣሽ የነበሩት አመልካች መኪናዋን ከእነጉድለቷ ተረክበዋል። አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤትም በመኪናዋ ላይ ጏደለ የተባለት እቃዎች በውሣኔ መኪናዋ ላይ እንዲለ አረጋግጦ መወሰኑንና የጏደለትም መኪናዋ በአፈፃፀም ተከሣሽ እጅ እንዲለች በርክክቡ ወቅት መሆኑን አረጋግጦ በርክክቡ ወቅት ጏድል የተገኙትን ዝርዝር ንብረቶች በአይነታቸውና በብዛታቸው የሚጨርሱትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ፕሮፍርማ ከሦስት የተለያዩ ድርጅቶች እንዱሰባሰብ አድርጏ ጏደለ የተባለት የመኪና እቃዎች ብር 66,520.00(ስልሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ብር) መሆኑን አረጋግጦ ይህንኑ ገንዘብ አፈፃፀም ተከሣሽ ለአፈፃፀም ከሣሽ እንዱተኩላቸው በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ትእዛዝ የአሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኛቸውን አቅርበው ይኸው ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤት ጏደለ በተባለት የመኪና እቃዎች ላይ የሰጠው ትእዛዝ መኪናዋ በቀጥታ ክስ ጊዜ ተገምታ የቀረበችበትንና በውሣኔው ላይም መኪናውን ከሣሽ ትረከብ ተብል ከተወሰነው ሁኔታ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ አፈፃፀሙ የተመራው ከስነ ስርአት ውጪ መሆኑን ጠቅሶ ጏደለ ለተባለት የመኪናዋ እቃዎች የአሁኗ አመልካች ሉከፍላት የሚገባው የገንዘብ መጠን በዋናው ክስ ጊዜ የተጠቀሰው ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር) ነው በማለት የስር ፍ/ቤትን ትእዛዝ በመሻር ወስኗል። የአሁኗ አመልካች በዚህ ቅር በመሰኘት አቤቱታቸውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት ስላላገኙ በዚህ ችልት የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
አመልካች ሐምል 21 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት 2/ሁለት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅረበዋል። ይዘቱም ባጭሩ በዋናው ጉዲይ በተወሰነው ውሣኔ መኪናዋን እንዱረከብ የሚል ሆኖ እያለና በርክክቡ ወቅትም የመኪናዋ እቃዎች በተጠሪ መጉደላቸው የተረጋገጠ መሆኑን አፈፃፀሙን የያዘው የስር ፍ/ቤት በገለፀበት ሁኔታ በዋናው ክስ ላይ የመኪናዋን ዋጋ ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር) ብለሽ ገምተሻል ተብል የእቃዎችን የገበያ ዋጋ ባላገናዘበ መልኩ የስር ፍ/ቤት ትእዛዝ መሻሩ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል የግራ ቀኙ የቃል ክርክር የካቲት 26 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት ተደምጧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ትእዛዝና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መረምረናል።
እንደመረመርነውም የመኪናዋ ርክክብ ሲፈጸም መጉደላቸው የተረጋገጡትን እቃዎችን ለመተካት የታሰበው የእቃዎች ዋጋ ውድቅ ሁኖ የእቃዎቹ ዋጋ ላሆን የሚገባው የዋናው ጉዲይ ክስ ሲመሰረት በአመልካች የተገለፀው ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኗ አመልካች በቀጥታ ክስ ወቅት መኪናውን የገመቱት በብር 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር) ሁኖ የጠየቁት ዲኝነት መኪናዋን እንዱረከቡ ይወሰንላቸው ዘንድ መሆኑን፣በቀጥታ ክስ ወቅት የተሰጠው ውሣኔም አመልካች መኪናዋን እንዱረከቡ የሚል መሆኑንና በአፈፃፀም ወቅት አመልካች መኪናዋን ሲረከቡ የጏደለት የመኪና እቃዎች ተረጋግጠው በወቅቱ የገበያ ዋጋም የጏደለትን እቃዎች ለመተካት ዝቅተኛው የጨረታ ዋጋም ብር 66,520.00(ስልሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ብር) መሆኑን ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ የአፈፃፀም ክስ የሚቀርበው በውሣኔው መሰረት እንዱፈጸም ስለመሆኑ ከ1958ቱ የፍትሐብሕር ሥነ ስርአት ህግ ሰባተኛ መጽሐፍ ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመመልከት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። አከራካሪውና ምላሽ የሚያስፈልገው ጉዲይ በቀጥታ ክስ ወቅት የተገመተ የንብረት ግምት በአፈፃፀም ወቀት ንብረቱ በዓይነት ካልተገኘ እና ንብረቱን በዓይነት ለመተካት የንብረቱ ዋጋ ቀድሞ ከተገመተው ግምት በልጦ ሲገኝ አፈፃፀሙ ላሆን የሚገባው በቀድሞው ግምት ወይስ ንብረቱን በዓይነት ለመተካት በሚያስችል የወቅቱ ተገቢ ዋጋ? የሚለው ነጥብ ነው። ለዚህ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ሉገኝ የሚችለው በቀጥታ ክስ ወቀት የተሰጠውን ውሣኔ እና የገበያን ተለዋዋጭ ባህርይ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ሲቻል ነው። እንዱሁም አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤት ለአፈፃፀሙ ተስማሚ በሆነ መንገድ ፍርደ እንዱፈጸም ትእዛዝ የመስጠት ሥልጣን ያለው መሆኑም ሉስተዋል ይገባል። በመሆኑም በቀጥታ ክስ ወቀት የነበረው የንብረት ግምት በአፈፃፀም ወቅት ንብረቱ በፍርድ ባለእዲ እጅ በነበረበት ሁኔታ ጏድል መገኘቱ ከተረጋገጠ በዓይነት ለፍርድ ባለመብቱ እንዱያስረክብ እስከተወሰነ ድረስ የጏለውን የንብረቱን ክፍል እንዱተካ ማድረግ በዋናው ፍርድ ከተሰጠው ውሣኔ ውጪ ልባል የሚችልበት ምክንያት የለም። የመኪና እቃዎች ዋጋ ከፍና ዝቅ የሚል መሆኑ እየታወቀም አንዳ ተገምቶ የቀረበ ዋጋ ሁል ጊዜ ተቀባይነት አለው ለማለት አይቻልም። የፍርድ ባለመብት ንብረቱን በዓይነት እንዱረከብ ከተወሰነ እና የፍርድ ባለእዲው እንደፈርደ የማይፈጽምበት ምክንያት ያለመኖሩ ሲረጋገጥ የፍርድ ባእዲው ንብረቱን በዓይነት እንዱያስረክብ፣ በዚህ ወቅትም ለአፈፃፀሙ ተስማሚ የሆነ መንገድ መከተል የፍርድ አፈፃፀም ስርአት የግድ የሚለው ጉዲይ ነው። ከዚህ ውጪ አንድ ፍርድ ለፍርድ ባለመብት እንደፍርደ ተፈጽሞለታል ለማለት እይቻልም። በመሆኑም በትግራይ ብ/ክ/መንግስት የማእከላይ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ለክርክሩ ምክንያት የሆነችው መኪና ጏደለ የተባለትን እቃዎች በተመለከተ ለአመልካች እንዱተካላቸው ፕሮፍርማ እንዱሰባሰብ በማድረግ ዝቅተኛው ዋጋ እንዱከፈል ማድረጉ የአፈፃፀም ክስ አቀራረብና የአፈፃፀም ውሣኔ አሰጣጥ ሥርአትን ባልተከተለ አኳኋን ልባል የሚችል አይደለም።
ይልቁንም የዚህ ፍ/ቤት አካሄድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 እና 392 ስር የተመለቱትን ድንጋጌዎችንና መኪናዋ በፍርድ ባለእዲ እጅ በነበረችበት ወቅት እቃዎቹ የመጉደላቸውን ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔ ግን አመልካች በዋናው ፍርድ መኪናዋን እንዱረከቡ የተወሰነውን ውሣኔ እና የመኪና እቃዎች የገበያ ዋጋን ተለዋዋጭነት እንዱሁም አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤት ለአፈፃፀሙ ተስማሚ በሆነ መንገድ ፍርደ እንዱፈጸም ትእዛዝ ለመስጠት ስልጣን ያለው መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 392/1/ ያስቀመጠውን መንገድ ያላገናዘበ ሆኖ ተገኝቷል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልትም ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ትእዛዝ ሣያርም መቅረቱ ባግባቡ ሁኖ አልተገኘም። ሲጠቃለልም መጋቢት 06 ቀን 1999 ዓ.ም በተሰጠው ዋና ውሣኔ ላይ የሰላዲ ቁጥር ትግ 03-00778 መኪና አመልካች እንዱረከቡ ከተወሰነ በኋላ በአፈፃፀም ደግሞ መኪናውን ሣይሆን ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር) ይከፈላት ተብል መወሰኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 እና 392 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በትግራይ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 23377 ግንቦት 26 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጠቶ በዚሁ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በፍ/መ/ቁ. 25095 ሰኔ 26 ቀን 2000 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የትግራይ ብ/ክ/መንግስት የማእከላይ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 08699 የካቲት 17 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ለጏደለት የመኪና እቃዎች ለተጠሪ ለአመልካች ብር 66,520.00(ስልሳ ስድስት ሺህ አምስት አቶ ሃያ ብር) ሉከፍለ ይገባል ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።