No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ በለጡ ጋሼ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- እነ አንደአለም ቴድሮስ /3 ሰዎች/ - ጠበቃ ዘውደ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለሰበር የቀረበው አመልካች የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 4931 የሰጠውን የአፈፃፀም ትእዛዝ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት ማጽደቃቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት። በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው።
የአቤቱታቸው ምክንያት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሐምል 18 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው የአፈፃፀም ትእዛዝ ነው።
የከፍተኛው ፍርድ የአሁን አመልካች በፍርድ የሚፈለግባቸውን ገንዘብ ከፍለው ያልቀረቡ በመሆኑ ቀደም ሲል በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ቤቱን ተጠሪዎች እንዱረከቡ በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል። አመልካች ይህ ትእዛዝ መሰረታዊ ስህተት አለበት በማለት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበች ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈፃፀም ትእዛዝ አጽንቶታል።
አመልካች የአፈፃፀም ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት የሰበር አቤቱታ ለክልለ ሰበር ችልት አቅርበው የሰበር ችልቱ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለት ወስኗል።
አመልካች አፈፃፀሙን የያዘው የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ቤቱ ሁለት ጊዜ በጨረታ፣እንዱወጣ ሣያደርግ ባለእዲዎች እንዱረከቡት ትእዛዝ ሰጥቷል። ይህም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው። የመጀመሪያው ጨረታ፣በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 426 መሰረት ለሰላሣ ቀናት በአየር ላይ ባለመዋለ ፍርድ ቤቱ ሰርዞ ድጋሜ ጨረታ እንዱወጣ አዝዟል። ከዚያ በኋላ ቤቱ በህጉ መሰረት ለጨረታ ያቀረበው አንድ ጊዜ ሆኖ እያለ፣ሁለት ጊዜ ለጨረታ ወጥቶ ገዥ እንዲልተገኘ በመቁጥር የተሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት፣ ስለዚህ በሰበር ታይቶ ሉታረምልኝ ይገባል በማለት አመልክታለች።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ቤቱ የካቲት 30 ቀን 1998 ዓ.ም ለጨረታ ቀርቦ የነበረ ሲሆን ታህሣስ 4 ቀን 1999 ዓ.ም እና ጥር 23 ቀን 1999 ዓ.ም ለሐራጅ ቀርቦ ገዥ ባለመገኘቱ ነው እኛ እንድንረከብ ፍ/ቤቱ ትእዛዝ የሰጠው።
ስለሆነም በህጉ መሰረት የተሰጠ የአፈፃፀም ትእዛዝ ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ቤቱን ይሸጥ ካለ በኋላ ብር 8000(ስምንት ሺህ) በችልት እንዱከፍል አድርጓል። ከዚህ በኋላ ቤቱ ይረከቡ ማለት መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት የመልስ መልስ ሰጥተዋል። ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርመረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው ተጠሪዎች ቤቱ የካቲት 30 ቀን 1998 ዓ.ም ለሐራጅ ቀርቦ ነበር በማለት ያቀረቡትን ክርክር ስንመረምረው፣ቤቱ ለሐራጅ ማስታወቂያ እንዱወጣበት ትእዛዝ ከተሰጠ በኋላ በአፈፃፀም የተሰጠው ትእዛዝ መብታችንን ይነካል የሚለ ጣልቃ ገቦች በመቅረባቸው ጨረታው ሂደት አፈፃፀሙን በያዘው ፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ በመሰጠቱ ምክንያት የተቋረጠ መሆኑን፣የከፍተኛው ፍርድ ቤት መጋቢት 5 ቀን 1998 ዓ.ም ከሰጠው ትእዛዝ ለመገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም ተጠሪዎች ቤቱ የካቲት 30 ቀን 1998 ዓ.ም የጨረታ ማስታወቂያ ወጥቶበት ለሐራጅ ቀርቧል በማለት ያቀረቡት ክርክር ተገቢነት ያለው ሆኖ አላገኘውም።
ከፍተኛው ፍ/ቤት የጣልቃ ገቦቹን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የተቋረጠው የሐራጅ ሂደት እንዱቀጥልና ቤቱ ታህሣስ 10 ቀን 1999 ዓ.ም ለሐራጅ እንዱቀርብ፣የጨረታው ማስታወቂያ እንዱወጣ ጥቅምት 20 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ መሰረት የሐራጅ ማስታወቂያው ታህሣሥ 3 ቀን 1999 ዓ.ም ወጥቷል። ፍርድ ቤቱም የሐራጅ ማስታወቂያው በአየር ላይ ለሰላሣ ቀናት መቆየት ያለበት ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ ስርአት ሕግ ቁጥር 426 የተደነገገ መሆኑን በመግለጽ ይህንን ስርአት ባሟላ መልኩ ቤቱ በሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ ጥር 23 ቀን 1999 ዓ.ም ለሐራጅ ሽያጭ እንዱቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል። የሐራጅ ማስታወቂያውም ጥር 3 ቀን 1999 ዓ.ም ወጥቶ ገዥ አልቀረበም ስለዚህ ቤቱን እንድንረከብ በማለት የፍርድ ባለመብት በጠየቁት መሰረት የፍርድ ባለመብት ቤቱን እንዱረከቡ በማለት ጥር 24 ቀን 1999 ዓ.ም ትእዛዝ ሰጥቷል።
No topics extracted.
ከዚህ በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍርድ ባለመብት የሆኑት ተጠሪዎች ቤቱን እንዱረከቡ በተደጋጋሚ ትእዛዝ ሲሰጥ ቆይቶ ሰኔ 8 ቀን 1999 ዓ.ም አመልካች በፖሉስ ተይዘው እንዱቀርቡ አድርጓል። በዚህ ቀን አመልካች ብር 8000(አምስት ሺህ ብር) የከፈለ ሲሆን ቀሪውን እዲ አጠቃልላ ከፍላ እንድትቀርብ በማለት ለሐምል 18 ቀን 1999 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። አመልካች ሐምል 18 ቀን 1999 ዓ.ም እዲውን አጠቃልለው ከፍለው ባለመቅረባቸው፣የከፍተኛው ፍ/ቤት የፍርድ ባለመብት ቤቱን እንዱረከቡ የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል።
አፈፃጸሙን የያዘው የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪዎች ቤቱን እንዱረከቡ ትእዛዝ የሰጠው በሕጉ የተቀመጠውን፣ሥርዓት በማሟላት አይደለም። ምክንያቱም የካቲት 30 ቀን 1998 ዓ.ም የተደረገውን የሐራጅ ሑደት ራሱ ፍርድ ቤቱ አግድታል። ከዚህ በኋላ የሚከናወኑ የሐራጅ ሂደቶች እንደ አዱስ መደረግ ያለባቸው ናቸው። ጥር 10 ቀን 1999 ዓ.ም የተከናወነው፣ሐራጅ የሐራጅ ማስታወቂያው ጥር 3 ቀን 1999 ዓ.ም ወጥቶ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 426 የተደነገገውን አስገዲጅ ስርአት ያላሟላና የሐራጅ ማስታወቂያው ሰባት ቀን ብቻ በአየር ላይ ውል የተፈፀመ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ይህ ስርአት ያልተሟላ መሆኑን በማየት ሰርዞታል።
ቤቱ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 426 መስፈርት ባሟላ ሁኔታ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ ለሐራጅ ያቀረበው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 428 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት የፍርድ ባለመብቱ እንዱረከብ የሚያደርገው የሕጉን ስርአት በተከተለና ባሟላ ሁኔታ ሁለት ጊዜ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶና ቤቱ ለሐራጅ ቀርቦ ገዥ ሣይገኝ ሲቀር ብቻ ነው። በያዝነው ጉዲይ ቤቱ በትክክለኛው መንገድ ለሐራጅ የቀረበው ጥር 23 ቀን 1999 ዓ.ም ብቻ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ቤቱ በድጋሚ ለሐራጅ እንዱቀርብና የሕጉን ስርአት ባሟላ ሁኔታ የሐራጅ ማስታወቂያ እንዱወጣ ሣያደርግ ቀደም ብለው ያወጣውንና የህጉን አስገዲጅ ሁኔታ የማያሟላውን የሐራጅ ስርአት፣ እንደትክክለኛ ሐራጅ በመቁጠር ቤቱ ሁለት ጊዜ ለሐራጅ ቀርቦ ገዥ አላገኘም በማለት ተጠሪዎች ቤቱን እንዱረከቡ የሰጠው ትእዛዝ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 428 ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ የሚጥስ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ቤቱን ይረከቡ በማለት የሰጠውን ትእዛዝ በመተው አመልካች እዲቸውን በጥሬ ገንዘብ እንዱከፍለ የፈቀደና በዚህም መሰረት አመልካች ሰኔ 8 ቀን 1999 ዓ.ም ስምንት ሺ ብር/8000/ በችልት የከፈለ መሆኑን የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ያሣያል። ከዚህ በኋላ አፈፃጸሙ በማይንቀሣቀስም ንብረት ላይ እንዱቀጥል ለማድረግ ካስፈለገ፣የአፈፃፀም ስርአቱን እንደ አዱስ በቤቱ ላይ እንዱቀጥልና የሐራጅ ማስታወቂያ ማውጣት ሲገባው የተወውና የተቋረጠውን የአፈፃፀም ስርአት በማስታወስ ቤቱን ተጠሪዎች እንዱረከቡ በማለት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ ግድፈት ያለበት ነው። በመሆኑም የከፍተኛ ፍርድ ቤት አፈፃፀሙን ሲመራ የጣሳቸውን አስገዲጅ የስነ-ሥርአት ድንጋጌዎች እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልትና ሰበር ችልት ትእዛዙን ማጽናታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወሰነናል።
የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሐምል 18 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ሙለ በሙለ ተሽሯል።
የደቡብ ብሕር ብሕረሰቦችና ህዝቦች ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች በፍርድ የተወሰነባቸውን የቀረባቸውን እዲ ለመክፈል የሚችለ ከሆነ እንደ ክሱ እንዱያደርግ አመልካች እዲውን ለመክፈል ካልቻለ፣ቤቱ የሕጉን ሥርአት በጠበቀ ሁኔታ በሐራጅ ተሸጦ የተጠሪዎች እዲ እንዱከፈል ያደርግ ዘንድ ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት መጋቢት 24 ቀን 2001 ዓ.ም በሙለ ድምጽ ተሰጠ።