No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ወልደዮሐንስ ሀብትየስ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ያምሮት ሸዋረጋ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን የአሁን አመልካች አቶ ተክለ በቀለ በተባለ ግለሰብ ላይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ የሟች ወ/ሮ እልፍነሽ በቀለ የሕግ ባል ነኝ። ሟች ባለቤቴ በሕይወት እያለች ሁለት ልጆችን የወለድን ሲሆን በአዱስ አበባ ከተማ በወረዲ 19 ቀበላ 58 ክልል ባለቤቴ ከባንክ ገንዘብ ተበድራ ቤት ሰርታለች። ይህም ቤት የሟችና የእኔ የጋራ ቤት ሲሆን ተከሣሽ ምንም መብት ሣይኖራቸው ቤቱን ይዘው የሚገኙ ስለሆነ ለቀው እንዱያስረክቡኝና ኪራይም እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ከሣሽም ተከሣሽም የሟች ባል እንደነበሩ ተረጋግጧል ካለ በኋላ የቤቱ ግማሽ የሚስት ድርሻ ሆኖ ቀሪውን ግማሹን ደግሞ ሁለቱ የሟች ባልች ድርሻቸው ስለሆነ በዚሁ መሰረት ከሣሽ የቤቱን ¼ኛው ይገባቸዋል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ይህ ውሣኔም በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እንደፀና ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል።
ከዚህ በኋላም አመልካች አፈፃፀም ቀጥለው በክርክሩ ሂደት የፍርድ ባለእዲ የነበሩት አቶ ተክለ በቀለ በመሞታቸው ምክንያት ባለቤታቸው የሆኑት የአሁን ተጠሪ በፍርድ ባለእዲነት ተመዝግበው አፈፃፀሙን የያዘው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፍርደን በምን መልኩ ማስፈፀም እንዲለበት ፍርደን ለሰጠው ችልት ማብራሪያ ጠይቆ የቤቱ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ¼ኛው ለፍርድ ባለመብቱ በመክፈል በዚሁ መልኩ ፍርደ እንዱፈፀም በማለት መልስ ሰጥቷል።
የፍርድ አፈፃፀሙን የያዘው ችልትም በአዱስ አበባ ከተማ የሚገኙ ቤቶችን የቤት የገበያ ግምት የሚሰጠው የሚመለከተው የአስተዲደር ክፍል ሲሆን በዚሁ መሰረትም የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ ከዚሁ አካል ግምቱን አስቀርቦ የባለመብትን ድርሻ ¼ ከባለእዲዎች ላይ ከሚያስከፍል ውጭ ውሣኔውን ከሰጠው ፍ/ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት እንዱፈፀም ከተሰጠው ትእዛዝ በመውጣት በሐራጅ ተሸጦ ለባለመብት እንዱከፈላቸው የሚያደርግበት ሥርዓት ስለላለ የፍርድ ባለመብት በዚህ መልኩ እንዱፈፀምላቸው ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ስለላለው በፍርድ አፈፃፀም በኩል የተየዘውን ድርሻቸውን ይውሰደ በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል።
የፍርድ ባለመብት በዚሁ ትእዛዝ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን የሥር ፍ/ቤት ትእዛዝ ጉድለት የላለው ነው በማለት ይግባኙን ሰርዟል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችልትም አቤቱታውን መርምሮ የቤቱ ወቅታዊ ዋጋ ¼ኛው ለአመልካች ይከፈላቸው ተብል ፍርድ በተሰጠበት ሁኔታ የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ከሚመለከተው አስተዲደር ክፍል የተላከለትን ግምት መሰረት በማድረግ ፍርደ እንዱፈፀም በማለት የሰጠው የአፈፃፀም ትእዛዝ ተጠሪ ባለበት ለሰበር ቀርቦ ላታይ እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል። በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተጠቀሰው ሲሆን የሰበር አቤቱታውም ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ ተመርምሯል።
ከፍ ብል እንደተጠቀሰው የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ የሰጠው የፍርድ ባለመብት /የአሁን አመልካች/ የቤቱን ወቅታዊ ዋጋ ¼ ሉከፈላቸው ይገባል በማለት ነው። የከተማው አስተዲደር ቤቱን አስመልክቶ የሚሰጠው የዋጋ ግምትና ወቅታዊ ዋጋ ልዩነት እንዲላቸው መገመት አያዲግትም። ስለሆነም ፍ/ቤቱ የቤቱ ወቅታዊ ዋጋ ¼ኛው ለፍርድ ባለመብቱ ሉከፍል ይገባል በማለት ውሣኔ እስከሰጠ ድረስ ወቅታዊ ዋጋውን የሚወስነው በሐራጅ በሚደረግ ሽያጭ ስለሆነ በዚሁ መልኩ ፍርደን ማስፈፀም ከውሣኔው እንደማፈንገጥ የሚቆጠር አይሆንም።
በልላ በኩልም በዚህ ችልት ክርክር ሲደረግ ይሄው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በልላ የአፈፃፀም መዝገብ በሐራጅ እንዱሸጥ ታዞ በብር 364,ዐዐዐ ሐምል 9 ቀን 2ዐዐ0 ዓ.ም እንደተሸጠ ግራ ቀኙ ወገኖች ተማምነውበታል።
ይህም የቤቱ ወቅታዊ ዋጋ መሆኑን የሚያሣይ ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 373 አኳያ ተገቢነት የላለውና የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ት ዔ ዛ ዝ
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 65156 ኀዲር 27/2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በመ.ቁ. 6189ዐ በ16/7/2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽራል።
No topics extracted.
ከቤቱ ሽያጭ ላይ ለአመልካች ሉደርሳቸው የሚገባው ¼ኛ ድርሻ ብር 91.ዐዐዐ /ዘጠና አንድ ሺህ/ እንዱከፈላቸው ፍርደንም የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት እንዱያስፈጽም ታዟል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።