No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- መሐመድ እስማኤል ተርቢ ተጠሪ፡- መሐመድ አሕመድ ኑር መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዲይ በአፈፃፀም ደረጃ ያለውን ክርክር የሚመለከት ነው። አመልካች ተጠሪ ገንዘብ ይከፍለው ዘንድ ያስወሰነ የፍርድ ባለመብት ነው። እንደውሣኔው ለማስፈፀምም የአፈፃፀም መዝገብ አስከፍቶ ገንዘቡን ገቢ ለማድረግ ሲባል የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶበት ገዢ አልተገኘለትም የተባለውን የተጠሪን ቤት እንዱረከብ አሣዝዞአል። ከመዝገቡ እንዲየነው ተጠሪ በዚህ ላይ ለበላይ ፍ/ቤቶች ይግባኝ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ክርክሩ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አፈፃፀሙን የጀመረው በሶማላ ብ/ክ/መ/የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተጠሪን ቤት አመልካች እንዱረከብ በድጋሚ አዟል። በልላ በኩል ደግሞ የክልለ ጠቅላይ /ፍ/ቤት ሰበር ችልት ተጠሪ እና ላልች ስድስት ሰዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 መሰረት መቃወሚያ አቅርበውልኛል በማለት የቀድሞ ውሣኔውን /የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን የአፈፃፀም ውሣኔ በማጽናት ሰጥቶት የነበረውን/ በመለወጥ አመልካች ቤቱን ሉረከብ አይገባም በማለት ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ሐምል 24 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ባለመቅረቡ ክርክሩ እሱ በላለበት ነው የተሰማው። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የስር ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 መሰረት የቀረበለትን መቃወሚያ ያስተናገደበትን እና የቀድሞውን ውሣኔ የሻረበትን አግባብ ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ ለስር ፍ/ቤቶች ከቀረበው ክርክር፣ ከአመልካች አቤቱታ እና አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እንዱሁም ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምናየው ተጠሪ ለአመልካች የሚከፍለው ገንዘብ አለ ተብል የተወሰነበት ሰው ነው። ይህን ገንዘብ ለማስከፈል ሲባልም ንብረቱ ነው በተባለው ቤት ላይ የአፈፃፀም ትእዛዝ ተሰጥቷል። ይህን የአፈፃፀም ትእዛዝ በመቃወም ለሶማላ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የተለየ ትእዛዝ /ውሣኔ/ አሰጥቶ የነበረ ቢሆንም አመልካች ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ባቀረበው አቤቱታ መነሻነት ክርክር ከተደረገ በኋላ አፈፃፀሙ የከፍተኛው ፍ/ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት እንዱቀጥል ተወስኗል። ይህ ሁለ ከሆነ በኋላ ነው ተጠሪ ተቀዋሚ በመሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 መሰረት ለሰበር ችልቱ አቤቱታ ያቀረበው።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 መሰረት አቤቱታ /መቃወሚያ/ የሚቀርበው ቀደም ሲል የተሰጠን ውሣኔ ለመቃወም ነው። መቃወሚያውን ማቅረብ የሚችለትም ቀደም ሲል በተደረገው ክርክር ተካፊይ ያልነበሩት ወገኖች ናቸው። ተጠሪ ቀደም ሲል በተደረገው የአፈፃፀም ክርክር ተካፊይ የነበረ እና የተወሰነበት ሰው ነው። በመሆኑም ከዚህ በኋላ ተቃዋሚ ሆኖ የሚቀርብበት አግባብ የለም። ላልቹ ሰዎችም ተቃዋሚ ሆነው የቀረቡት የአፈፃፀም ትእዛዝ የተሰጠበት ንብረት የተጠሪ ብቻ ሣይሆን የውርስ ሃብት ነው በሚል እንደሆነ ከመዝገቡ ተመልክተናል። በእርግጥ እነሱ እንደሚለት ንብረቱ የእነሱም የውርስ ሃብት ከሆነ የአፈፃፀም መዝገቡ ለተከፈተበት የከፍተኛው ፍ/ቤት በጊዜው ሉያቀርቡ ይችለ /ይገባቸው/ ነበር። በአፈፃፀም በተያዘ ወይም በተከበረ ንብረት ላይ መብት አለን ባዮች አቤቱታ ማቅረብ የሚችለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 418 መሰረት ሆኖ ማቅረብ ያለባቸውም ሣይዘገዩ እንደሆነ በዚሁ ቁ. 418/1/ ተመልክቶአል። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው ሰዎቹ አቤቱታቸውን ያቀረቡት አፈፃፀሙን ለያዘው ለከፍተኛው ፍ/ቤት ሣይሆን የመጨረሻ ውሣኔ ለሰጠው ለሰበር ችልቱ ነው። ከዚህም በላይ በንብረቱ ላይ ከተጠሪ ጋር የጋራ መብት አለን ባዮች ሆነው ሣለ ተጠሪ በከፍተኛው ፍ/ቤት ከአንዳም ሁለቴ በጠ/ፍ/ቤት እና በሰበር ችልትም እንደዚሁ በክርክር በቆየበት ጊዜ ተቃዋሚ ሆነው አልቀረቡም።
ይህም ሲታይ ለረዥም ጊዜ በንብረቱ ላይ መብት አለን በማለት መቃወሚያ ሣያቀርቡ ዝም ብለው መቆየታቸውን ያስገነዝባል። በዚህ ሁኔታ የቀረበን አቤቱታ ፍ/ቤቱ እንደማይመረምረው በተጠቀሰው ድንጋጌ ተመልክቶአል። በመሆኑም አቤቱታው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 418 መሰረት እንደቀረበ ይቆጠር እንኳን ቢባል ያለበቂ ምክንያት በመዘግየቱ የተነሣ የሚመረመርበት የሕግ ምክንያት የለም። ሰበር ችልቱ የሰጠው ውሣኔም ከዚህ አንፃር ሲታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ልባል የሚችል ነው።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
አቤቱታ የቀረበበት በሶማላ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ.ቁ. ኤም.ጂ. 12/99 ሰኔ 2ዐ ቀን 99 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 418/1/ መሰረት ተሽሮአል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ያለው የአፈፃፀም ጉዲይ የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 15/95 ሰኔ 26 ቀን 1998 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ይቀጥል ብለናል።
መዝገቡ ይመለስ።