No summary available.
ጥቅምት 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢት/ያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን - ነ/ፈጅ ዝግአለ አሰፊ - ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ አቶ ተገኝ ማንደፍሮ /ሁለት ሰዎች/ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመው በድሬዲዋ ጊዜያዊ አስተዲደር አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድ ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሣሽ፣የአሁኑ አመልካች ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ።
የአሁኑ ተጠሪዎች ሰኔ ዐ5 ቀን 1994 ዓ.ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ ተከሣሽ መ/ቤት ቀደም ብል ከደንበኞች ከሚሰበሰበው የቆጣሪ ገንዘብ በኮሚሽን እየታሰበ ደመወዝ ሲከፍላቸው ከቆየ በኋላ የአከፊፈለን ሥርዓት በመለወጥ የኮሚሽን ክፍያውን ከማቋረጡም በተጨማሪ መደበኛ ደመወዝ እንዱስተካከልም የህብረት ስምምነቱ መሰረት ተደርጎ ቃለ ጉባዓ ተይዞ መጋቢት 27 ቀን 1993 ዓ.ም እንደቅጥር ዘመን ደረጃና ደመወዝ እንዱስተካከል መወሰኑንና ላልች መሰል ሰራተኞችም በክልላቸው አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድ ክስ አቅርበው በአዋጅ ቁጥር 42/1985 መሰረት የደረጃም ሆነ የደመወዝ መስተካከል የተፈፀመላቸው መሆኑን በመግለጽ ጉዲያቸው አንድና ተመሣሣይ በመሆኑ ትእዛዝ እንዱሰጥላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካች በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ የገንዘብ አሰባሰብ ሥርዓት ከ1991 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ መለወጡን በመግለጽ የከሣሾች ደመወዝና የደመወዝ ማስተካከያ ጥያቄ ስድስት ወር ውስጥ ሣይቀርብ ከሁለት ዓመት በኋላ የቀረበ በመሆኑ በይርጋ ቀሪ ላሆን እንደሚገባ፣ የመጋቢት 27 ቀን 1993 ዓ.ም ቃለ ጉባዓም በአዱስ አበባና አካባቢው ለሚሰሩት ሰራተኞች የሚሰራ ከመሆኑም በላይ የይርጋ ማቋረጫ ምክንያት ላሆን እንደማይገባ በመግለጽ ክሱ በብይን ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩ የቀረበለት ቦርድም የግራ ቀኙን ክርክር ከተመለከተ በኋላ የተጠሪዎች ክስ በአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 162 መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ወስኖ በዚህ ውሣኔ ያልተስማሙት የአሁኑ ተጠሪዎች ይግባኛቸውን ለድሬዲዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የተጠሪዎች ጥያቄ የውሣኔ ይፈፀምልኝ ሁኖ እያለ በይርጋ መታየቱ አግባብ አይደለም፣ በውሣኔው መፈፀም ዙሪያም ሆነ በውሣኔው ላይ የቀረበ መቃወሚያ ወይም የተያዘ ጭብጥ የለም በማለት ተጠሪዎች በጥያቄአቸው መሰረት በአመልካች ድርጅት ሉፈፀምላቸው ይገባል ሲል የቦርደን ውሣኔ በመሻር ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ነሐሴ 3ዐ ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዲዩን በአፈፃፀም ላታይ የሚገባው ነው፤ ማለቱ የተጠሪዎችን የስር ክስ ማመልከቻ በአግባቡ ያላገናዘበ መሆኑን፣ ለፍ/ቤቱ በይግባኝ ሰሚነቱ በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን የቦርደን ውሣኔ ለመሻር የሚያስችል አለመሆኑን በመዘርዘር ውሣኔው የሥነ-ሥርዓት ሕጉንና በስራ ላይ የነበረውን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ድንጋጌዎችን ያላገናዘበ ስለሆነ ሉሻር ይገባዋል በማለት ተከራክሯል።
ተጠሪዎች እንዱቀርቡ ተደርጎም ሰኔ ዐ5 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ የቅሬታ ነጥቦች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የማያሣዩ መሆናቸውን በሥነ-ሥርዓት ጉድለት ብቻ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ የሚሻርበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ መሆኑን በመዘርዘር መልሣቸውን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን ከመዝገቡ ግልባጭ፣ ከግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክርና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቦርደን ውሣኔ መሻሩ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ታይቶ ሉወሰን የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የቦርደን ውሣኔ ለመሻር ምክንያት ከአደረጋቸው ነጥቦች አንደ ተጠሪዎች ለቦርደ ያቀረቡት ጥያቄ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ይሰሩ የነበሩት/1ዐ1/አንድ መቶ አንድ/ ሰራተኞች አቅርበው ያስወሰኑት ውሣኔ መብቱ የሚመለከተን ስለሆነ በክርክሩ ተካፊይ ባንሆንም ተፈፃሚ ላሆንልን ይገባል የሚል በመሆኑና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5/4/ መሰረትም ተቀባይነት ያለው ነው በሚል ነው። ይህም የሚያሣየው የተጠሪዎች አቤቱታ ቀጥታ ክስ ሣይሆን የአፈፃፀም ክስ የነበረ ስለመሆኑ ከፍተኛው ፍ/ቤት ማመኑን ነው።
ይሁን እንጂ ተጠሪዎች ለቦርደ ክሣቸውን ሲመሰርቱ ላልች ተመሣሣይ ስራ በአዱስ አበባና አካባቢው የሚሰሩ እነ አቶ አያላው ልዐልሰገድ /1ዐ1 ሰዎች/ የተባለ ሰራተኞች በክልላቸው በሚገኘው የአሰሪና ሰራተኛ ጉደይ ወሣኝ ቦርድ ጥያቄያቸውን አቅርበው ማስወሰናቸውን ከመግለጽ ውጪ በላልች ሰራተኞች ውሣኔ እንዱፈፀምላቸው በግልጽ ዲኝነት መጠየቃቸውን የክርክሩ ሂደት አያሣይም። በላልች ተመሣሣይ በልላ አካባቢ የተሰጠ ውሣኔ እንዱፈፀምላቸው ዲኝነት ጠይቀው የነበሩ ስለመሆኑም ተጠሪዎች ያቀረቡት ክርክር የለም። ይህ ችልት መገንዘብ የቻለው የተጠሪዎች ጥያቄ በዋናው ክርክር የተሰጠውን ውሣኔ ቦርደ እንዱያስፈጽምላቸው የቀረበ የፍርድ አፈፃፀም ክርክር አለመሆኑን ነው።
በመሰረቱ የአንድ የፍርድ አፈፃፀም ክርክር አጀማመር "ሥርዓት" በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.378/1/ ስር ተመልክቷል። የዚህ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌ የፍርድ ባለመብት በፍርደ መሰረት እንዱፈፀምለት የአፈፃፀም ማመልከቻ ለፍ/ቤቱ ሲያቀርብ የፍርድ አፈፃፀም ክርክር እንደሚጀምርና የአፈፃፀም ጥያቄ የቀረበበት ጉዲይ በፍርድ የበሰለ ወይም የተፈረደ ፍርድ መኖሩን የሚያሣይ ማመልከቻ መያዝ እንደአለበት ያስገነዝባል። በያዝነው ጉዲይ ይህንኑ ሥርዓት አሟልቶ የቀረበ ማመልከቻ ስለመኖሩ የክርክሩ ሂደት አያሣይም።
ከፍተኛው ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5/4/ ለውሣኔው መሰረት ማድረግ ይችል የነበረው የተጠሪዎች ጥያቄ ከላይ በተጠቀሰው የአፈፃፀም ሥነ ሥርዓት አጀማመር ቢሟላ እና ውሣኔውን ለማስፈፀም የእነ አቶ አያላው ለዐልሰገድ /1ዐ1 ሰዎች/ ጉዲይ ተመልክቶ ውሣኔ የሰጠው በአዱስ አበባና አካባቢው የሚገኘው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድ የአፈፃፀም የውክልና ሥልጣን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 371 እና 372 መሰረት ሰጥቶት በሆነ ነበር። ከዚህ የውክልና የውሣኔ አፈፃፀም ውጪ ፍርድ ያልሰጠ ፍ/ቤት በልላ ፍ/ቤት ወይም ወሣኝ አካል የተሰጠ ፍርድ በራሱ የሚያስፈጽምበት ሥነ ሥርዓት የለም። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378/1/ ድንጋጌ የሚያሣየውም የፍርድ ማመልከቻ መቅረብ ያለበት ፍርደን ለፈረደው ፍ/ቤት መሆኑን ነው። በመሆኑም የከፍተኛው ፍ/ቤት የተጠሪዎች ጥያቄ የአፈፃፀም ማመልከቻ ነው ቢል እንኳ ፍርደን ለማስፈፀም የሚያስችለው የሥነ-ሥርዓት መሰረት የለውም።
ከዚህም በላይ የከፍተኛው ፍ/ቤት የቦርድን ውሣኔ የሻረው የስር ክርክሩ በተጀመረበት ወቅት ተፈፃሚነት የነበረው አዋጅ ቁጥር 42/1985 አንቀጽ 154/2/ ከሰጠው ስልጣን ውጪ መሆኑን ተገንዝበናል። የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 188/4/ ድንጋጌ የሚያሣየው አዋጁ ከመጽናቱ በፉት በስር ክርክር ሰሚ አካላት በመታየት ላይ የነበሩ የስራ ክርክሮች በወቅቱ ተፈፃሚነት በነበረው ሕግ መሰረት በተጀመረበት ሥርዓት ፍፃሜ ሉያገኙ እንደሚገባ ነው። በመሆኑም ከፍተኛ ፍ/ቤት የቦርደ ውሣኔ የሕግ ስሕተት ያለበት መሆኑን ካመነበት መያዝና ዔልባት ሉያገኝ የሚገባውን ጭብጥ በመመሥረት ለቦርደ መመለስ ሲገባው የቦርደን ውሣኔ በመሻር የራሱን ውሣኔ መስጠቱ በሕግ ተለይቶ ስልጣን ባልተሰጠበት ሁኔታ መሆኑን ተገንዝበናል። ስለሆነም ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች መሰረት የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆኑ የሕግ ስህተቶች የተፈፀሙበት ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል ከፍተኛው ፍ/ቤት የቦርደን ውሣኔ የሻረው በክርክሩ ወቅት መታየትና መወሰን የነበረው ጭብጥ የይርጋ ጥያቄ አለመሆኑን በመግለጽና በአዋጁ ላይ የተመለተው የይርጋ ጊዜም ጉዲዩን የማይመለከት ነው ሲል ነው።
ከዚህም መረዲት የሚቻለው ከፍተኛ ፍ/ቤት የተጠሪዎችን ጥያቄ የአፈፃፀም ነው በማለቱ ይርጋውንም ከዚሁ አንፃር መመልከቱን ነው። ይሁን እንጂ ይህ ችልት ከላይ እንደገለፀው ጉዲዩ የአፈፃፀም ጥያቄ ሣይሆን የቀጥታ ክስ መሆኑን ተረድቷል። ጉዲዩ የቀጥታ ክስ ነው ከተባለ ደግሞ አግባብነት ያለው የይርጋ ጊዜ ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ሕግ አኳያ ላታይ የሚገባው ነው። የከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዲዩ የቀጥታ ክስ መሆኑን በመገንዘብ የይርጋ ክርክሩንም ከዚህ አኳያ በማየት እንደገና እንዱወስን ጉዲዩን መመለሱ ሥነ-ሥርዓታዊ ነው ቢባልም ጉዲዩ ከወሰደው ጊዜ አኳያ የይርጋ ጥያቄውን ይህ ችልት እንዱመረምር እና ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥ ማድረጉ የሥነ ሥርዓት ሕጉን ዓላማ ሉያሣካ የሚችል ሆኖ በመገኘቱ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ለተጠሪዎች ደመወዙ በኮሚሽን ይከፈል የነበረው አሰራር ቀሪ የሆነው ከ1991 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ስለመሆኑ አመልካች ጠቅሶ የተከራከረ ሲሆን ተጠሪዎች ጉዲዩ በእናት መሥሪያ ቤት ተይዞ መቆየቱን ከመግለጽ ውጪ የተለየ የክርክር ነጥብ አላቀረቡም። በመሆኑም ደመወዙን በኮሚሽን ሲያስከፍል የነበረው አሰራር ቀሪ የሆነው ከ1991 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ተጠሪዎች የይርጋ ጊዜው መቆጠር ያለበት ከመጋቢት 27 ቀን 1993 ዓ.ም ቃለ ጉባዓ ጀምሮ መሆኑንና ለይርጋ ጊዜው አቆጣጠር መቋረጫ የሆነ ሕጋዊ ምክንያት እንዲላቸውም በመጥቀስ ተከራክረዋል።
በመሰረቱ በአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ162/1/ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው በቅጥር ላይ ከተመሰረተ ግንኙነት የመነጨ ማንኛውም ክስ የጊዜ ገደቡ በአዋጁ ወይም አግባብ ባለው ላላ ሕግ በልላ አኳኋን ካልተወሰነ በቀር የመብቱን ጥያቄ ለማቅረብ ከሚቻልበት ቀን ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል። የተጠሪዎች ጥያቄ ደረጃና ደመወዝ እንዱስተካከል ሆኖ ለቦርደ ክስ የቀረበው ሰኔ ዐ5 ቀን 1994 ዓ.ም የደመወዝ በኮሚሽን የክፍያ አሰራር ከተለወጠ ከሁለት ዓመት በላይ ቆይቶ ነው። ተጠሪዎች የይርጋ ጊዜ ገደቡ ተፈፃሚነት የለውም በማለት የሚከራከሩት አሰሪው መ/ቤት በገንዘብ ሰብሣቢነት ለተመደብን ሰራተኞች እንደማንኛውም የድርጅቱ ሰራተኞች እኩል ክፍያ እንድናገኝ በቃለ ጉባዓ ከእናት ማህበራችን ጋር በመደራደር ላይ ስለነበር ከዋናው መ/ቤት እስከሚላክ ድረስ እንድንጠባበቅ በመደረጉ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ነው በማለት ነው። በእርግጥ የአዋጅ ቁጥር 42/1985 አንቀጽ 166 ድንጋጌ አንድ የስራ ክርክርን የሚመለከት ክስ የይርጋ ጊዜ አልፍ ቢቀርብ እና ለጊዜው ማለፍ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት መሆኑ በተገቢው ውሣኔ ሰጪ አካል ከተረጋገጠ ክሱ ላቀርብ የሚችል መሆኑንና የተጠቀሰው ምክንያት በተወገደ በአስር ቀን ውስጥ ካልቀረበ ግን ተቀባይነት የላለው መሆኑን ያስረዲል። ይሁን እንጂ ተጠቃሽ ድንጋጌ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ትርጉም የለም ድንጋጌው ከአቅም በላይ ሉሰኙ የሚችለ ምክንያቶችን ያላመለከተ መሆኑም በግልጽ ይታያል። ሆኖም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ትርጓሜንና አመላካች ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1792 እና 1793 ድንጋጌዎች አኳያ መመልከት የሚቻል ስለመሆኑ ይህ ሰበር ችልት በ/ቁ. 16648 የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በዚህም መሰረት የስራ ክርክር ክስ በጊዜው ያልተመሰረተው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1792 እና 1793 በተመለከተው አኳኋን መሆኑ ከተረጋገጠ ጊዜው ያለፈበት ክስ ተቀባይነት አንደሚኖረው ተሰምሮበታል።
የአዋጅ ቁጥር 42/1985 አንቀጽ 166 ድንጋጌ ከ”አቅም በላይ የሆነ ምክንያት” ትርጓሜ ያልሰጠና አመላካች ሁኔታዎችን ያላስቀመጠ ቢሆንም እንደ "በቂ ምክንያት" ተደርገው የሚወሰደትን ምክንያቶችን አመልክቷል። እነዚህም ምክንያቶች የሰራተኛው መታመም፣ የሰራተኛው በትእዛዝ ከመደበኛ የመኖሪያ ስፍራ ውጭ መዛወር እና የሰራተኛው ከብሕራዊ ጥሪ ላይ መገኘት መሆናቸውን ገልፆል። ከድንጋጌው መንፈስ መረዲት የሚቻለውም እነዚህ ምክንያቶች መኖራቸው በበቂና አጥጋቢ ማስረጃ ማረጋገጥ ጊዜው ያለፈበትን የስራ ክርክር ክስ ለመቀበል የሚያስችል መሆኑን ነው።
በእጃችን ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪዎች ለቦርደ አቅርበውት የነበረው ክስ አመልካች መ/ቤት ቀድሞ ይከተል የነበረውን የደመወዝ ክፍያ አሰራር በመለወጥ አዱስ አሰራር መከተለንና ላልች ሰራተኞችም በልላ አካባቢ በሚገኘው ቦርድ ጉዲያቸውን አቅርበው ማስወሰናቸውን መጋቢት 27 ቀን 1993 ዓ.ም በተደረገው ቃለ ጉባዓም አገልግልታቸውን ያገናዘበ የደመወዝ ማስተካከያ እንዱደረግ በመ/ቤቱ þርሶኔል ዲሬክተር ቢሮ ተሰብስበው መወሰኑን ይህ ውሣኔም ከእናት መ/ቤት ምላሽ እስከሚሰጠው እንዱጠባበቁ መደረጉ ከአቅም በላይ "የሆነ" ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ የተከራከሩ ሲሆን አመልካች ክሱ በይርጋ ሉታገድ ይገባዋል በማለት ተቃውሞውን አቅርቦ ተከራክሯል። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው ጉዲይ በእናት መ/ቤት ተይዟል ተብል ምላሹን እንዱጠባበቁ መደረጉ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ነው?
ወይንስ አይደለም? የሚለው ጥያቄ ከላይ ከተሰጠው ትርጉም አኳያ መታየት እና ምላሽ ማግኘት ያለበት መሆኑን ነው።
በመሆኑም ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1792 እና 1793 እንዱሁም ከአዋጅ ቁ
No topics extracted.