No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- በዛብህ አበበ - ቀረበ።
ተጠሪ፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ - ሕይወት ጥላሁን ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
አከራካሪው ጉዲይ ቀደም ሲል በተሰጠው ውሳኔ መሰረት የተጀመረውን የአፈጻጸም ሂደት የሚመለከት ነው።
ከመዝገቡ እንደሚታየው የአፈጻጸሙን ክርክር የያዘው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቀጠሮው ቀን የፍርድ ባለመብት (የአሁኑ አመልካች) ጠበቃ አልቀረበም በሚል ምክንያት በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል። ይህን ተከትል የቀረበለትን የመዝገብ ይከፈትልን ጥያቄም ሳይቀበለው ቀርቷል። ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም መዝገቡ አይከፈትም በመባለ የተፈጸመ ስህተት(ጉድለት) የለም ብሎል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
ይህ የሰበር ችልችም አመልካች ጥር 10 ቀን 2000 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቶአል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የአፈጻጸም መዝገቡ የተዘጋበትን አግባብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ (ትእዛዝ) እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ትእዛዝ የተሰጠበት መዝገብ ቀደም ሲል የተሰጠውን ውሳኔ ለማስፈጸም ሲባል የተከፈተ ነው። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መዝገቡን የዘጋው የፍርድ ባለመብቱ ጠበቃ በቀጠሮው ቀን አልተገኘም በሚል ብቻ ነው። ይህም ሆኖ ግን ለምን ዝም ብል አይጠብቅም ነበር ወይም ተለዋጭ ቀጠሮ አይሰጥም ነበር ልባል ስለማይቻል በመዝጋቱ ረገድ ስህተት ነበር ማለቱ ተገቢ አይሆንም። በልላ በኩል ግን አመልካች እንደፍርደ/ውሳኔው/ አልተፈጸመልኝም የሚል እስከሆነ ድረስ መዝገቡ ከነጭራሹ አይከፈትልህም (አይንቀሳቀስም) የሚባልበት የሕግ ምክንያት አይኖርም። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 384 እንደተደነገገው የአፈፃፀም ጥያቄ እንደገና ለማንቀሳቀስ የማይቻለው በሕጉ እንደተመለከተው በይርጋ ቀሪ ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ያቀረበው የአፈፃጸም ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ሆኗል አልተባለም። በመሆኑም ያልተፈጸመ ፍርድ አለ እስከተባለ ድረስ መዝገቡ ተከፍቶ አፈጻጸሙ የማይቀጥልበት የሕግ ምክንያት የለም። አቤቱታ የቀረበበት ትእዛዝ ከዚህ አንጻር ሲታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው።
አቤቱታ የቀረበበት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 20286 ሰኔ 5 ቀን 1999 ዓ.ም የተሰጠው ትእዛዝ እና ይህን ትእዛዝ በማጽናት በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57130 ጥቅምት 13 ቀን 2000 ዓ.ም የተሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተከፈተው የአፈፃጸም መዝገብ ተከፍቶ(ተንቀሳቅሶ) አፈጻጸሙ ይቀጥል በማለት ወስነናል።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.