No summary available.
ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ዓብደልሐኪም ሁሴን - ከጠበቃ ወ/ሥላሴ ብርቱ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡-
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ክርክሩም የማይንቀሣቀስ ንብረት በፍርድ አፈፃፀም የሚሸጥበትን ሁኔታ የሚመለከት ነው።
በዚህም መሰረት በአንደኛ ተጠሪና በሁለተኛ ተጠሪ መካከል የነበረው የፍርድ አፈፃፀም ክርክር ቀጥል ንብረትነቱ የአንደኛ ተጠሪ የሆነ ቤት በሐራጅ ተሸጦ ለሁለተኛ ተጠሪ መከፈል የሚገባው ዔዲ እንዱከፈል የአፈፃፀም ትእዛዝ ተሰጥቶ ይኸው ቤት ለአሁን አመልካች ከተሸጠ በኋላ አንደኛ ተጠሪ የሐራጅ ሽያጩ በሚካሄድበት ጊዜ ግዙፍ የሆነ ጉድለት የተፈፀመ ስለሆነ ሽያጩ ሉፈርስ ይገባል በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 445 መሰረት አቤቱታ አቅርበው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ንብረትነቱ የአንደኛ ተጠሪ የሆነው ቤት የተሸጠው ከግምት በላይ ከመሆኑም በላይ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.
445 መሰረት በማይንቀሣቀስ ንብረት ላይ የተደረገ ጨረታ ሉፈርስ የሚችለው በአሻሻጡ ሥርዓት ላይ ግዙፍ የሆነ ጉድለት ወይም ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር ወይንም የማታለልና የማጭበርበር ተግባር ተፈጽሞ የተገኘ ከሆነና ይህም አቤቱታ በሚያቀርበው ወገን ላይ ቀጥተኛ ጉዲት ያደረሰ መሆኑ ከተረጋገጠ ነው፤ በተያዘው ጉዲይ ተገቢ ያልሆነ ተግባር ተፈጽሟል ቢባል እንኳን አንደኛ ተጠሪ በዚህ ድርጊት ጉዲት የደረሰባቸው ስለመሆኑ ያላስረደ ስለሆነ የሐራጅ ሽያጩ እንዱፈርስ የቀረበው አቤቱታ አግባብነት የለውም በማለት ሣይቀበለው ቀርቷል።
አንደኛ ተጠሪ በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን የአሁን አመልካችም በክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ ተፈቅድላቸው ግራ ቀኙን እንደዚሁም የጣልቃ ገቡን ክርክር መርምሮ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 423/መ/ መሰረት ፍ/ቤቱ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ በሚወጣበት ጊዜ ገዢው ንብረቱን ከመግዛቱ በፉት ማወቅ ይገባዋል ተብል የሚገመተውን ማንኛውንም ዝርዝር ሁኔታ በትክክል መግለጽ እንዲለበት የተመለከተ ሲሆን ይሁን እንጂ የፍርድ አስፈፃሚው ተወካይ ከተጫራ ች ለሽያጭ የቀረበው ቤት የፍ/ባለእዲ የግል ንብረት ነው ወይስ የመንግሥት በማለት ለቀረበለት ጥያቄ "የቀበላ ወይም የኪራይ ቤቶች" ላሆን ይችላል በማለት በሐራጅ ስለሚሸጠው ቤት ትክክለኛውንና አስፈላጊ የሆነውን መረጃ ለገዥዎች አለመስጠቱ እንደዚሁም የአሁን አመልካች በጨረታው ለመሣተፍ ከመጡት ሰዎች ለተወሰኑትም ቢሆን ቤቱን ከአሁን አንደኛ ተጠሪ ላይ የተከራዩት መሆኑን በመግለጽ እንዲይጫረቱባቸው ለዚህም ውለታ ብር 1ዐዐዐ(አንድ ሺህ) እንደሚሰጡ ይናገሩ እንደነበር በምስክሮች የተረጋገጠ በመሆኑና በአጠቃላይ ሲታይም በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላቀርብ ባለመቻለና ይህም በቀጥታ ተጎጂ የሚያደርገው ይግባኝ ባይን /የአሁን አንደኛ ተጠሪን/ ስለሆነ የሥር ፍ/ቤት እነዚህን ግድፈቶች በአግባቡ ሣይመለከት ጨረታው ሉፈርስ አይገባም በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ አይደለም በሚል የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሯል።
በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይህንኑ ውሣኔ በመቀበል ይግባኙን ሰርዟል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ለማስለወጥ ሲሆን ይህም ችልት የሐራጅ ሽያጩ ግዙፍ የሆነ ጉድለት ያለበት ስለሆነ ሉፈርስ ይገባል ተብል በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት መወሰኑ ለሰበር ቀርቦ ሉመረመር እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
አንድ የማይንቀሣቀስ ንብረት በፍርድ አፈፃፀም በሐራጅ በሚሸጥበት ጊዜ በሽያጩ አካሄድ ጉድለት የተፈፀመ ስለሆነ ሐራጁ ሉፈርስ ይገባል የሚለው ወገን አቤቱታውን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 445 መሰረት ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን የዚህ ድንጋጌ ይዘትም፡- "በፍርድ አፈፃፀም ምክንያት የማይንቀሣቀስ ንብረት የተሸጠ እንደሆነ የፍርድ ባለገንዘቡ ወይም ከሽያጩ ገንዘብ ድርሻ ያለው ወይም የንብረቱ ተካፊይ የሆነ ወይም በንብረቱ መሸጥ ምክንያት መብቱ የሚነካ ማናቸውም ሰው በአሻሻጡ ሥርዓት ላይ ግዙፍ የሆነ ጉድለት ወይም ትክከለኛ ያልሆነ ተግባር ወይም የማታለልና የማጭበርበር ተግባር ተፈጽሟል በማለት ሽያጩ እንዱፈርስ ወይም እንዱታገድ ማመልከቻ ለማቅረብ ይችላል።
No topics extracted.
ስለሆነም የተጠቀሰው ተግባር በአመልካቹ መብት ላይ ቀጥታ ጉዲት ያደረሰ መሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀር ሽያጩ እንዱፈርስ ወይም እንዱታገድ ለማዘዝ አይቻልም"። በሚል ይነበባል።
በተያዘው ጉዲይ አንደኛ ተጠሪ የሐራጅ ሽያጩ ሉፈርስ ይገባል በማለት አቤቱታቸውን ለፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረቡት በሐራጅ እንዱሸጥ የታዘዘው የቤት ቁጥር 236 ሆኖ ሣለ የተሸጠው ግን የቤ.ቁ. 244 ተብል ነው፤ የሐራጅ ሽያጩ በሚከናወንበት ጊዜም ተጫራ ች "ቤቱ የቀበላ ነው ወይንስ የኪራይ ቤቶች" ብለው ሲጠይቁ አጫራቹ " የቀበላ ወይንም የኪራይ ቤቶች" ይሆናል ብል የተናገረ ከመሆኑም በላይ ቤቱን የገዛው ሰው ላልች ተጫራ ች ብልጫ ገንዘብ ሰጥተው እንዲይጫረቱ ለእያንዲንዲቸው ብር 1000(አንድ ሺህ) በቼክ እንደሚሰጣቸው ተናግሯል የሚለትን በምክንያትነት በመጥቀስ ነው።
በፍርድ አፈፃፀም ማንኛውም ንብረት በሐራጅ እንዱሸጥ በሚወሰንበት ጊዜ የሐራጅ ሥርዓቱ የሚከናወንበት ሁኔታ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 423 ላይ የተዘረዘረ ሲሆን በዚህም ድንጋጌ መሰረት ገዢው በሐራጅ ስለሚሸጠው ንብረት ማወቅ ስለሚገባው ዝርዝር በሐራጅ ማስታወቂያው መጠቀስ እንዲለበት ተመልክቷል።
በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያው የቤ.ቁ. 244 "ን" እንደሚመለከት ለተጫራ ች ይፊ ሆኖ የተሸጠው ግን የቤት ቁጥር 236 ስለመሆኑ ተረጋግጧል። ሆኖም ግን በሐራጅ ማስታወቂያው ሽያጩ የሚመለከተው የቤት ቁጥር 244"ን" እንደሆነ ቢጠቀስም በፍርድ አፈፃፀም መምሪያ በኩል የተገመተውና ገዢዎችም እንዱመለከቱት ተደርጎ የተጫረቱት በማስታወቂያው ላይ የተመለከተውን የቤ.ቁ. 244”ን” ሣይሆን ቁጥር 236”ን” እንደሆነም ጭምር መረጋገጡን ተገንዝበናል። ይህ ሁኔታ በአፃፃፍ ስህተት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን መገንዘብ የሚቻል ሲሆን አንደኛ ተጠሪም በዚህ ስህተት ምክንያት ከፍ ብል በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 445 መሰረት ቀጥተኛ የሆነ ጉዲት የደረሰባቸው ስለመሆኑ አላስረደም።
ሐራጅ አስፈፃሚው ቤቱ የቀበላ ወይንም የኪራይ ቤቶች ይሆናል ብል ስለመናገሩ አንደኛ ተጠሪ ባቀረቧቸው ምስክሮች የተረጋገጠ ቢሆንም ይህ ሁኔታ ተጫራ ችን እንዲይጫረቱ ስለማድረጉና በዚህም ሣቢያ ጉዲት የደረሰባቸው ስለመሆኑ በማስረጃ አላረጋገጡም። ምክንያቱም ሕጉ በአሻሻጡ ሂደት ግድፈት /irregularity/ እንዲይኖር የሚከላከለውን ያህል ይህ ተፈጽሟል የሚባል ግድፈት በአመልካቹ መብት ላይ ቀጥተኛ ጉዲት ያደረሰ ስለመሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀር ጨረታው መፍረስ እንደማይገባው እኩል ጥበቃ ስለሚያደርግ ነው። ንብረቱን የገዙት ተጫራች /የአሁን አመልካች/ ያለ ተቀናቃኝ ብቻቸውን ለመግዛት ባላቸው ፍላጎት ላልች ተጫራ ች እንዲይጫረቱ ለእያንዲንዲቸው ብር 1000(አንድ ሺህ) በቼክ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል የተባለውን በተመለከተ አንደኛ ተጠሪ ካቀረቧቸው ምስክሮች መካከል የተወሰኑት ይህ ፍሬ ነገር ሲነገር መስማታቸውን በመጠቀስ ለፍ/ቤቱ የምስክርነት ቃል መስጠታቸውን ከመዝገቡ ተረድተናል።
በልላ በኩልም ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የተሸጠው በ2ኛ ጨረታ ሲሆን 2ኛ ጨረታ በሚከናወንበት ጊዜም የሐራጅ ሽያጩ የሚደረገው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 428 መሰረት ነው። ከዚህ ድንጋጌ አኳያም ንብረቱ የሚሸጠው በሁለተኛው ጨረታ ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ለሚያቀርብ ተጫራች እንደሆነ ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ ሁለተኛ የሐራጅ ማስታወቂያ ሲወጣ 44 ሰዎች በጨረታው ተመዝግበው እንደነበር 37 ሰዎች ደግሞ በጨረታው ተካፊይ እንደነበሩና በመጨረሻም 1ዐ ከፍተኛ ዋጋ በሰጡ ተጫራ ች መካከል ፈክክሩ ቀጥል አመልካች ብር 1ዐ1.ዐዐዐ/ አንድ መቶ አንድ ሺህ/ በመስጠት ጨረታውን እንዲሸነፈና የቤቱ የግምት ዋጋም ብር 88,83ዐ /ሰማንያ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሣ/ እንደነበር ከመዝገቡ ተገንዝበናል።
ከዚህም የተረዲነው ለጨረታው ከተመዘገቡት 44 ሰዎች መካከል 37 ሰዎች በጨረታው ተሣትፈው መገኘታቸውና በመጨረሻም 1ዐ ሰዎች ቀርተው ጨረታውን መቀጠላቸው ሲታይ አመልካች ላልች ሰዎች እንዲይጫረቱ የብር 1000(አንድ ሺህ) ቼክ ለመስጠት ቃል ገብተዋል ተብል በአንደኛ ተጠሪ ምስክሮች የተነገረው ጥርጣሬ ውስጥ የሚገባ መሆኑን ነው። ከዚህም ላላ በዚህ ምክንያት አንደኛ ተጠሪ ቀጥተኛ የሆነ ጉዲት የደረሰባቸው ስለመሆኑም አላስረደም።
ሲጠቃለልም አንደኛ ተጠሪ ጨረታው ሉፈርስ ይገባል በማለት በምክንያትነት የጠቀሷቸው ሁኔታዎች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 445 ላይ እንደተመለከተው በመብታቸው ላይ ቀጥተኛ ጉዲት ያደረሱባቸው ስለመሆኑ ያላስረደ መሆኑን የተገነዘብን ስለሆነ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ጨረታው ሉፈርስ አይገባም በማለት የሰጠው ውሣኔ አግባብነት ያለው ሆኖ ሣለ ነገር ግን የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጨረታው ሉፈርስ ይገባል በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር የሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 21375 በ8/2/98 ዓ.ም ጨረታው ሉፈርስ አይገባም በማለት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ስለሆነ አጽንተነዋል።
የፋዳራል ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 4238ዐ ኀዲር 26 ቀን 1999 ዓ.ም ጨረታው ሉፈርስ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሰለሆነ ሽረነዋል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።