No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 398ዐ3 ሐምል 2 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አለኸኝ ገ/ሕይወት - ጠበቃ አበባው መላኩ ተጠሪ፡- እነ እማሆይ አጢነሽ በቀለ /3 ሰዎች/ - ጠበቃ ብናልፈው ነጋ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ በየካ ክ/ከተማ ቀበላ 11/12 ክልል የሚገኘውን ቁጥር 492 የሆነውን ቤት ሟች ወ/ሮ ደለለች በቀለ በ1974 ዓ.ም. በተደረገ የስጦታ ውል በስጦታ ያስተላለፈልኝ ስለሆነ የስጦታ ውለ ይጽደቅልኝ የሚል አቤቱታ አቅርበው ፍ/ቤትም ስጦታውን በማጽደቅ ውሣኔ መስጠቱን ከመዝገቡ ተረድተናል።
ከዚህ በኋላም የአሁን ተጠሪዎች የሟች ወ/ሮ ደለለች በቀለ ሕጋዊ ወራሾች መሆናቸውን ገልጸው ፍ/ቤቱ ስጦታውን በማጽደቁ የሰጠው ውሣኔ መብታቸውን የነካ እንደሆነና የስጦታ ውለም የተደረገው የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ እንደመሆኑ መጠን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723/1/ ላይ እንደተመለከተው ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ያልተደረገ ስለሆነ ፍ/ቤቱ የሰጠው ውሣኔ ሉሰረዝ ይገባል በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሰረት አቤቱታ አቅርበዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ የስጦታ ውለ በተጠቀሰው ድንጋጌ መሰረት ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ያልተደረገ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 172ዐ/1/ ላይ እንደተመለከተው እንደ ረቂቅ ከሚቆጠር በስተቀር የፀና ውል ስላልሆነ ቀደም ሲል በ26/7/99 ዓ.ም. በዋለው ችልት ስጦታው ሉጸድቅ ይገባል ተብል የተሰጠው ውሣኔ በማይጸና ውል ላይ ተመስርቶ ስለሆነ ውሣኔው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 36ዐ/2/ መሰረት ተሰርዟል በማለት ፍርድ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ፍርድ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዟል።
የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችልት የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ የስጦታ ውለ በሕግ አግባብነት ያልተደረገ ስለሆነ እንደ ረቂቅ ከሚቆጠር በስተቀር የጸና አይደለም ተብል በሥር ፍ/ቤቶች መወሰኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2443፣ 881 እና 882 አኳያ አግባብነት ለሰበር ችልት ቀርቦ ሉወሰን እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን በቃል አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተጠቀሰው ሲሆን አቤቱታው ለሰበር ችልት ላቀርብ ይገባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ ጉዲዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ተጠሪዎች አጥብቀው የሚከራከሩት የሟች ወ/ሮ ደለለኝ በቀለ ሕጋዊ ወራሾች ነን፣ አመልካች ስጦታ እንዱጸድቅላቸው ያቀረቡት አቤቱታ በፍ/ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱ መብታችንን የነካ ከመሆኑም በላይ ስጦታውም ቢሆን በሕግ አግባብነት ያልተደረገ ስለሆነ ይህንኑ ስጦታ ፍ/ቤቱ በማጽደቅ የሰጠው ውሣኔ ሉሰረዝ ይገባል በማለት ነው።
ከፍ ብል እንደተጠቀሰው የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ስጦታው የፀና ስላልሆነ የቀድሞው ውሣኔ ሉሰረዝ ይገባል ወደሚል መደምደሚያ ሉደርስ የቻለው ስጦታው በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የተደረገ እንደመሆኑ መጠን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723/1/ ላይ እንደተመለከተው ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ያልተደረገ ስለሆነ የፀና አይደለም የሚል ነው።
በእርግጥ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723/1/ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለው የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ ውልች በሕግ ፉት የፀኑ ለመሆን ሁለት ሁኔታዎችን ማሟላት ይገባቸዋል። በአንድ በኩል ውለ በጽሁፍ መደረግ የሚገባው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ውለ በአዋዋይ ፉት ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ፉት መከናወን ያለበት መሆኑ ነው።
በልላ በኩልም በአመልካችና በሟች ወ/ሮ ደለለች በቀለ መካከል ተደርጓል የተባለው የስጦታ ውል ሲሆን በማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም በማይንሰሳቀስ ንብረት ላይ መብትን የሚሰጥ ስጦታ በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ አሰራር ዓይነት ካልተደረገ ፈራሽ እንደሚሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2443 ላይ ተመልክቷል። ግልጽ ኑዛዜ የሚደረግበት ሥርዓት ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 881 ላይ የተመለከተ ሲሆን ኑዛዜ በአራት ምስክሮች ፉት ካልተነበበና ይህም ሥርዓት ስለመፈጸሙና ኑዛዜውም የተደረገበት ቀን በሰነደ ላይ ካልተመለከተ እንደዚሁም ተናዛዡና ምስክሮቹ ወዱያውኑ ፊርማቸውን ወይም የአውራ ጣት ምልክታቸውን ካላደረጉበት ፈራሽ እንደሚሆን በሕጉ ላይ ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዲይም በአመልካችና በሟች ወ/ሮ ደለለች በቀለ መካከል የተደረገው የቤት ስጦታ ውል ይህንን ሥርዓት አሟልቶ የተከናወነ ስለመሆኑ በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ መረጋገጡን መዝገቡ ያስረዲል።
No topics extracted.
እንግዱህ በአንድ በኩል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723/1/ ላይ እንደተመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን የሚመለከቱ ውልች ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጣቸው አካላት ፉት ካልተደረጉ የጸኑ ሉሆኑ እንደማይችለ የተመለከተ ሲሆን በልላ በኩል ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለተ የሚደረጉ የስጦታ ውልች ይህንን ሥርዓት ተከትለው መከናወን እንዲለባቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2443 ላይም ሆነ 881 ላይ አልተመለከተም። እነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች እርስ በርሳቸው ያልተጣጣሙ ከሆነ ገዢው ድንጋጌ መሆን ያለበት የትኛው ነው የሚለው ዔልባት የሚያሻው ነው።
ከሕጉ አቀራረጽ እንደሚታየው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723 የሚገኘው ጠቅላላ ስለ ውልች በሚመለከተው የፍትሐብሕር ሕጉ ምዔራፍ ስለ ውልች አመሰራረት መሪ ደንቦች በሚደነግገው ክፍል ሥር ነው። በዚህ ጠቅላላ የውል ሕግ ድንጋጌ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት ማንኛውም ዓይነት ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ካልተደረገ የጸና ስለማይሆን ፈራሽ ላሆን እንደሚችልና ለመብትም ሆነ ለግዳታ ምንጭ ላሆን እንደማይችል መገንዘብ ይቻላል።
ይሁንና የማይንቀሳቀስ ንብረትን ስጦታ በተመለከተ በተለይ በሚገዛው ከፍ ብል በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2443 እና 881 ድንጋጌ መሰረት ይህ ሥርዓት መከናወን እንዲለበት አልተመለከተም። በጠቅላላ ሕግና በልዩ ሕግ መካከል አለመጣጣም ወይንም ልዩነት በሚኖርበት ጊዜ ልዩ ሕግ የበላይ ሆኖ ተፈፃሚነት ሉኖረው እንደሚችል /The Special prevail over the general/ ከሕግ አተረጓጎም መርህ መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም አመልካችና ሟች ወ/ሮ ደለለች በቀለ ያደረጉት የቤት ስጦታ ውል፣ ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ያልተደረገ ቢሆንም የማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ በሚደረግበት ጊዜ ይህ ሥርዓት መከናወን እንዲለበት ለጉዲዩ አግባብነት ባለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2443 እና 881 ላይ ያልተመለከተ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች የፍትሐብሕር ሕ/ቁ. 1723/1/ በመጥቀሱ የስጦታ ውለ የፀና አይደለም በማለት ይህንኑ መሰረት በማድረግ አስቀድሞ የተሰጠው ውሣኔ ሉሰረዝ ይገባል ሲለ የሰጡት ውሣኔ ከሕግ አተረጓጎም መርህ አንፃር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
6886ዐ በ1ዐ/11/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በአመልካችና በሟች ወ/ሮ ደለለኝ በቀለ መካከል የተደረገው ውል በሕግ አግባብ ስለሆነ የጸና ነው ተብል ተወስኗል።
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በ26/7/99 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት ሉሰረዝ አይገባም ተብል ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።