No summary available.
ሐምል 23 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
ወ/ሮ ዓለምሸት ካሣሁን - ቀረቡ።
አቶ ብርሃኑ ካሣሁን
አቶ ዲንኤል ካሣሁን ተጠሪ፡- አቶ ሽመልስ እንዲለ - ጠበቃ ግርማቸው ኢላላ - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር ዐ5596 ሐምል 18 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እና የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዝያ 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ በመቅረቡ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሣሽ ተጠሪ ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካቾች የአባታቸው የአቶ ካሣሁን አስረስ ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በፍርድ ቤት የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ በማያያዝ ሟች አባታችን በህይወት በነበረበት ጊዜ ሚያዝያ 3ዐ ቀን 1989 ዓ.ም. በተፃፈ የቤት ሽያጭ ውል ተከሣሹ ከአያታቸው አቶ ጥላሁን ሀይላ በኑዛዜ ወራሽነት ያገኙነትን በቀድሞ አጠራር በወረዲ 21 ቀበላ 25 የቤት ቁጥር 424 የሆነውን በብር 1ዐዐ,ዐዐዐ /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ገዝተዋል። ሆኖም የቤቱ ስመ ንብረት በተከሣሽ /ተጠሪ/ አያት ስም ያለ በመሆኑ የቤቱን ስመ ንብረት ወደራሳቸው ካዛውሩ በኋላ ካርታውን እንዱሰጡን ይወስንልን በማለት ክስ አቅርበዋል።
ተጠሪ በተከሣሽነት ቀርበው ውል አልተዋዋልኩም። የከሳሾችን /የአመልካቾችን/ አባት ወክል በውለ ላይ የተፈረመው ሰው ሟችን በመወከል ቤት ለመግዛት ስልጣን የላላቸው ሰው ናቸው። ከእኔ ጋር 1989 የተደረገው ውል አባቴ ጋር 1987 የተደረገውን ውል የሚያጣቅሰው ነው። የቤቱን ሰነድ ለማስረከብ ግዳታ የገቡት ውለ በተደረገ በአንድ ወር ውስጥ ስለሆነና ከሣሾች በአንድ ዓመት ውስጥ ውለ እንዱፈፀምላቸው ያልተጠየቁ ስለሆነ ውለን ለመፈፀም አልገደድም በማለት መልስ ሰጥቷል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሣሽ /ተጠሪ/ የአሁን አመልካቾች /ከሣሾች/ በሽያጭ ውለ ምክንያት የያዙትን ቤት እንዱለቁና ኪራይ እንዱከፍሎቸው ከዚህ በፉት በመዝገብ ቁጥር 3754 ክስ አቅርበው በአመልካቾች /ከሣሾች/ አባትና በተጠሪ /በተከሣሽ/ መካከል ሚያዝያ 3ዐ ቀን 1989 ዓ.ም. የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ያለመሆኑ በፍርድ ውሣኔ ያገኘ በመሆኑ ተጠሪ /ተከሣሽ/ ውለንና ፊርማቸውን በመካድ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
በልላ በኩል አመልካቾች ውለ ከተደረገበት ከሚያዝያ 3ዐ ቀን 1989 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውለ እንዱፈፀምላቸው ያልጠየቁ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት ተከሣሽ /ተጠሪ/ ውለን ተገድድ የመፈፀም መብታቸውን አጥተዋል በማለት ወስኗል።
አመልካቾች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም የከፍተኛው ፍርድ ቤት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል። አመልካቾች ሐምል 18 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ አመልካቾች በውል የተረከቡትን ቤት እንዱያስረክቡትና የቤት ኪራይ እንዱከፍለት ክስ አቅርቦ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የውለን መደረግና የቤት ሽያጭ ውለን አስመልክቶ ያቀረቡትን ክርክር ማስረጃ በመመዘን በአመልካቾች አባትና በተከሣሽ መካከል ሕጋዊ የቤት ሽያጭ ውል ያለ መሆኑ በመዝገብ ቁጥር 3754 መጋቢት 2ዐ ቀን 1997 ዓ.ም ወስኗል። የሥር ፍርድ ቤት ቤቱን በሕጋዊ ሽያጭ ውል ነው የያዛችሁት ቤቱን ለተጠሪ አታስረክቡም ኪራይም አትከፍለም በማለት በልላ መዝገብ ከወሰነ በኋላ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 የተዛባ ትርጉም በመስጠት ውለን በግዲጅ ለማስፈፀም አትችለም በማለት የሰጠው ውሣኔ የሕጉን ድንጋጌ ይዘት፣ መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና የማይንቀሳቀስ ንብረት የሽያጭ ውል አፈፃፀም የሚያስተጓጉል የሕግ ትርጉም በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው ሚያዝያ 14 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ አመልካቾች ውለ በፍርድ ሀይል እንዱፈፀምላቸው የጠየቁት ውለ ከተደረገ ከዘጠኝ ዓመት ከሁለት ወር ካለፈ በኋላ ነው። በልላ በኩል የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 3754 ውሣኔ ከሰጠ በሦስት ዓመት በኋላ ስለሆነ ውለ በግዲጅ ይፈጽምልኝ ብለው የመክሰስ መብታቸውን ያጣለ በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው የሕግ ትርጉም ስህተት የለበትም። ስለዚህ በሥር ችልቱ የኖሩበትን ቤት ኪራይ ከፍለው እንዱያስረክቡ ውሣኔ ይስጥልኝ በማለት ተከራክረል። አመልካች በበኩለ በዚህ ጉዲይ የሚሰራው የአሥር ዓመት የይርጋ ጊዜ የሚደነግገው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 ድንጋጌ እንጂ የሥር ፍርድ ቤት የጠቀሰው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 አይደለም። ተጠሪ በፍርድ የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘውን ጉዲይ ከሥነ ሥርዓት ውጭ በማንሣት ሰበር ችልቱ ቤቱን እንዱረከብና ኪራይ እንዱከፈለው እንዱወሰንለት ያቀረበው ጥያቄ የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት የመልስ መልስ ሰጥቷል።
No topics extracted.
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና አመልካቾችና ተጠሪዎች በሰበር ያደረጉት የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የአመልካቾች አባትና በተጠሪ መካከል ሚያዝያ 3ዐ ቀን 1989 ዓ.ም. የተደረገው ውል በፍርድ ቤት ውሣኔና አስገዲጅነት እንዱፈፀምላቸው አመልካቾች ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ ለተያዘው ጭብጥ እልባት ለመስጠት ይህ ችልት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 አተረጓጎም አስመልክቶ በሰበር መዝገብ መጋቢት 3 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠውን የሕግ ውሣኔና በዚህ መዝገብ ያለውን ልዩ ሁኔታ ማገናዘብ ያስፈልጋል። የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰው ገዢው ውለን በፍርድ ቤት ውሣኔ እንዱፈጽምለት ለመጠየቅ የሚችልበት የጊዜ ገደብ ያለፈበት ስለሆነ ውለን ለመፈፀም አልገደድም የሚለውን መከራከሪያ ማቅረብ የሚችለውና ክርክሩ ተቀባይነት የሚያገኘው ውለን ለመፈፀም ፈቃደኛ አለመሆኑን ለገዢ በማያሻማ ሁኔታ ያሣወቀ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማስረዲት ሲችል እንደሆነ ከላይ በተገለፀው መዝገብ ትርጉም ተሰጥቶበታል። ስለዚህ ተጠሪ 1989 ዓ.ም. ጀምሮ አመልካቾች ቤቱን እንዱያስረክቡት ኪራይም እንዱከፍለት ክስ ከማቅረቡ በፉት ውለን ለመፈፀም ፍላጎት የላለው መሆኑን በማያሻማ መንገድ ለአመልካቾች ያሣወቀ ስለመሆኑ የቀረበው ማስረጃ ባለመኖሩ 1989 ጀምሮ አመልካቾች ውለ እንዱፈፀምላቸው ባለመጠየቃቸው መብታቸውን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 ታግዶል በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
ሻጭ የሽያጭ ውለን ለመፈፀም ፈቃድና ፍላጎት የላለው መሆኑን በማያሻማ መንገድ ለገዢ ከሚያሣውቅበት አንደኛው መንገድ የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ ለፍርድ ቤት የሚያቀርበው ክስ መሆኑ በሰበር መዝገብ ሻጭ ለገዢ በማያሻማ መንገድ ውለን ለመፈፀም ፍላጎት የላለው መሆኑን አሳውቋል የሚባለው ምን ምን ሁኔታዎች ሲሟለ ነው የሚለውን ነጥብ ለመተንተን በሰጠው ምክንያት በግልጽ ተቀምጧል። ሆኖም ሻጭ የቤት ሽያጭ ውለ ይፍረስልኝ የሚል ክርክር ማቅረቡ ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ አንፃር የሚኖረው ውጤት ምንድነው?
የሚለው ነጥብ ውሣኔ ያላገኘ ነጥብ በመሆኑ በዚህ መዝገብ እልባት ማግኘት ያለበት ነጥብ ሆኖ አግኝተነዋል።
ሻጭ የውል ይፍረስልኝ ክስ ለፍርድ ቤት ማቅረቡ ውለን ለመፈፀም ፍላጎት የላለው መሆኑን ለገዢ በማያሻማ መንገድ ከማሣወቅ ያለፈ ምክንያትና ውጤት ያለው ተግባር ነው። ሻጭ ውለ እንዱፈርስ ሲጠይቅ ውለ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለማቋቋም የሚያስችለ ጉድለቶች ያለበት በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች እንደ ሕግ ሆኖ ሉገዙበት የማይገባ መሆኑን የሚያሣዩ የውለን ሕልውና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባና የውል ሕጋዊነት በፍርድ ቤት ተመርምሮ ፈራሽ እንዱባል ወይም እንዱሰረዝ የሚቀርብ ነው። የውለ ሕጋዊነትና ሕልውና ጥያቄ ተነስቶ በፍርድ ቤት በሚመረመርበት ጊዜ ገዢ ውለ ሕጋዊ መሆኑን ከማሣየትና ከማስረዲት አልፍ ውለ በግዲጅ እንዱፈጽምለት የመጠየቅ ግዳታ አይኖርበትም። ከዚህ አንፃር ውለ በፍርድ ቤት ፈራሽ እንዱሆን ወይም እንዱሰረዝለት በውለ የሚገደድበት ሁኔታ ይቋረጣል። በልላ በኩል በክርክሩ ከተረታ ገዢ ሕጋዊ ተፈፃሚነትና አስገዲጅነት ባለው ውለ ንብረቱን የገዛ መሆኑ ከሻጭ ጋር ባደረገው የውል ሰነድ ብቻ ሣይሆን በፍርድ ቤት ውሣኔ የተረጋገጠለት የፍርድ ባለመብት ይሆናል። ስለሆነም ገዢ ፍርድ ቤቱ ሕጋዊነቱንና አስገዲጅነቱን መርምሮ በፍርድ ያረጋገጠውን ውል እንዱፈጽምለት ሻጭን የመጠየቅ መብቱ በፍርድ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 384/ሀ/ በተደነገገው አስር ዓመት ጊዜ ውስጥ እንጂ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 በተደነገገው የአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ የሚገደብ አይደለም። ስለዚህ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀፅ 3 የተቀመጠው የጊዜ ገደብ በዚህ ጉዲይ አግባብነት የለውም።
በልላ በኩል ፍርድ ቤቶች ለቀረበላቸው ጉዲይ የሚሰጡት ውሣኔ የተያዘውን ጉዲይ ለመቋጨት የሚችል መሆን እንዲለበት ከፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 182 ንዐስ አንቀጽ /1/ ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 3754 የሰጠው ውሣኔና በዚህ ጉዲይ የሰጠው ውሣኔ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ እና ጉዲዩ በእንጥልጥል የሚያስቀሩ ናቸው። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካች ቤቱን እንዱመልስላቸውና ኪራይ እንዱከፍላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ከአመልካች ጋር የገቡትን የቤት ሽያጭ ውል መሰረት በማድረግ ተቀባይነት የለውም በማለት በመዝገብ ቁጥር 3754 ወስኗል። አመልካች ያቀረቡት የውል ይፈፀምልኝ ጥያቄ ደግሞ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት በማድረግ ውድቅ አድርጓል። እነዚህ ውሣኔዎች ተጠሪም ቤቱን ለማስመለስ የማይችለበት አመልካችም የቤቱ ባለሀብት በማይሆኑበት ሁኔታ ጉዲዩን በእንጥልጥል የሚያስቀሩ ናቸው። ስለሆነም አመልካች እና በተጠሪ መካከል ሕጋዊ አስገዲጅነት ያለው ውል እንዲለ በፍርድ ካረጋገጠ በኋላ አመልካች ያቀረቡትን የውል ይፈፀምልኝ ጥያቄ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 በመጥቀስ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች ውለ እንዱፈፀምላቸው ያቀረቡት ጥያቄ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 ቀሪ አይሆንም ብለናል።
ተጠሪ ከአመልካች ጋር ያደረጉትን ውል ለመፈፀም ይገደዲለ ብለናል።
ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።