No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ - ነ/ፈጅ ትዔግስት አሰፊ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የተጀመረው በምዔራብ ሐረርጌ ከፍ/ፍ/ቤት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በኢትዮጵያ መንገድች ባለስልጣን ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የአመልካች የክስ ይዘትም የኢትዮጵያ መንገድች ባለስልጣን ከሸክ ሁሴን ሚጨታ ድረስ ያለውን መንገድ ለማሻሻል በአደረገው እንቅስቃሴ መሰረት አመልካች ለሰጠው ብድር መያዣ የነበሩት በሚጨታ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የማይንቀሣቀሱ ንብረቶች ውስጥ በአቶ ሚካኤል ከፍያለው ስም ተመዝግበው ያለት የመኖሪያና የድርጅት ቤቶች መፍረሣቸውን፣ ንብረቶቹ አቶ ሚካኤል ከፍያለው ለራሣቸውና ለአቶ መራቸው የማነ ከአመልካች ላይ ለወሰደት ብድር መያዣ መሆናቸውን፣ የኢትዮጵያ መንገድች ባለሥልጣን ለፈረሡት ቤቶች የሚከፈለውን ካሣ ለመያዣ ሰጪዎች ለመክፈል በዝግጅት ላይ መሆኑን አመልካች ገልፆ ይኸው አካል ከዚህ አድራጏት እንዱቆጠብ፣ ክፍያውን ለመያዣ ሰጪዎች ሣይሆን ለአመልካች እንዱከፍል እንዱደረግ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። ይኸው የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ የቀረበለት ፍ/ቤትም “ተከሣሹ” ባለሥልጣን መ/ቤት በተገቢው የክርክር ሂደት ባለመቅረቡ በስነ ሥርዓቱ መሰረት በላለበት እንዱታይ አድርጏ የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ተቀብል ወስኗል። ከዚህ በኋላ የአሁኑ ተጠሪዎች የካሣ ክፍያ እንዲይከፈልባቸው ውሣኔ ያረፈባቸውና በመያዣ ተይዘዋል የተባለት ንብረቶች ህጋዊ ባለቤቶች መሆናቸውን፣ ከአመልካች ጋር ህጋዊ ወይም ከውል የመነጨ ግንኙነት የላላቸው መሆኑን ዘርዝረው ቀደም ሲል የተሰጠው ውሣኔ እንዱነሣላቸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 ‘ን' መሰረት በማድረግ አቤቱታ አቅርበው ፍ/ቤቱም የተጠሪዎች አቤቱታ ለአመልካች እንዱደርሰው እና ግራ ቀኙ እንዱከራከሩ ከአደረገ በኋላ አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የብድርም ሆነ የመያዣ ግንኙነት እንደላለው ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ቀድሞ የተሰጠውን ውሣኔ በማንሣት ለንብረቶቹ ይከፈል የተባለው ካሣ ለተጠሪዎች ሉከፈላቸው ይገባል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ባለመስማማት በመቃወም ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ህዲር ዐ8 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በፃፊት 7/ሰባት/ ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ክርክር ያስነሡት ንብረቶች በመያዣነት የተሰጠ በመሆኑ የካሣ ክፍያው ለእኔ ይገባል በማለት አመልካች ያቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት ያጣው ባግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ ይቅረብ ተብል ይህ ሰበር ችልትም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ሚያዝያ 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በዋለው ችልት ሰምቷል።
ቀረቡ የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት ያጣው በህጉ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የተጠሪዎች ልጅ አቶ ሚካኤል ከፍያለው ለራሣቸው ለአቶ መራቸው የማነ ከአመልካች ላይ ለወሰደት ብድር መያዣ ይሆኑ ዘንድ ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን የመኖሪያና የድርጅት ቤቶችን መስማማታቸውን፣ የመያዣ ንብረቶች ስመ ሀብትም በዚህ ግለሰብ ስም የሚታወቅና የመያዣ ውለም ንብረቱ በሚገኝበት የሚጨታ ልዩ ቀበላ መመዝገቡ፣ ተጠሪዎች በአቶ ሚካኤል ከፍያለው ይታወቃል የተባለው የከተማ ይዞታ ምስክር ወረቀት በተጭበረበረ መንገድ የተሰጠ ነው በማለት የሚከራከሩና ይኸው ምስክር ወረቀት እስከአሁን ድረስ በተገቢው አካል እንዱሰረዝ ያላደረጉ መሆናቸውን ነው። እንግዱህ የአሁን ተጠሪዎች ልጅ አቶ ሚካኤል ከፍያለው ራሣቸውና እና አቶ መራቸው የማነ ከአሁኑ አመልካች ላይ ለወሰደት የብድር ገንዘብ በካርታ ቁጥር ዐዐ5፣ ዐ34 እና ዐ84 ላይ የተመለከቱትን በሚጨታ ከተማ የሚገኙትን የመኖሪያና የድርጅት ቤቶች መያዣ መስጠታቸው፣ እነዚህ ንብረቶች የመያዣ ሰጪው ይዞታ ለመሆናቸው የከተማ ይዞታ ምስክር ወረቀት ከመቅረቡም በላይ የሚጨታ ልዩ ቀበላም ለአመልካቹ ተጨማሪ ደብዲቤ ፅፍለት የመያዣ ውለ ከተደረገ በኋላ የመያዣ ውል ምዝገባ ማካሄደ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡ ጉዲዮች ናቸው። የስር ፍ/ቤት የምስክር ወረቀቱን ዋጋ ሣይሰጠው ያለፈው የካርታ ቁጥር ዐዐ5 በሐምል 1992 ዓ.ም.፣ የካርታ ቁጥር ዐ34 በግንቦት ወር 199ዐ ዓ.ም. እንዱሁም የካርታ ቁጥር ዐዐ5 በጥቅምት ወር 1989 ዓ.ም. ውስጥ የተሰጡ፣ በአማርኛ ቋንቋ የተፃፊ፣ የደርግ መንግስትን የሚመለከትና በተለይም የከተማ ቦታ ስም፣ ወረዲ፣ የመሣሰለትና በሚለው ላይ ስርዝ ያለው እውነትነቱ አጠራጣሪ ነው በማለት ነው። ከዚህ የስር ፍ/ቤት መደምደሚያ መገንዘብ የሚቻለው በወቅቱ በክልለ የሚሰራው በኦሮምኛ ሆኖ የምስክር ወረቀቱ እንዳት በአማርኛ ላሆን ቻለ ከሚል ጥርጣሬ ብቻ መሆኑን ነው። የምስክር ወረቀቱ ሐሰተኛ ስለመሆኑ በተጨባጭ የተረጋገጠ ነገር የለውም።
No topics extracted.
በምስክር ወረቀቱ ላይ ያለት እንደ ማህተም ያለት ነገሮች የአስተዲደር ጽ/ቤት አይደለም የሚል ግልፅና ተጨባጭ ምክንያት ስለመኖሩም የስር ፍ/ቤት አልገለፀም። ፍርድ ቤቱ ማህተሙ የአስተዲደር ጽ/ቤቱ አይደለም የሚል በቂ ምክንያት ካለውም ተቃራኒ ማስረጃ እንዱቀርብ ባደረገ ነበር። ለጉዲዩ ቀጥተኛ ኃላፉነት ያለውና ይመለከተዋል የተባለው የቀበላ ጽ/ቤቱም ለአመልካች የፃፈው ደብዲቤ የይዞታ ምስክር ወረቀቱን አጠራጣሪነት የሚያሣይ አይደለም። በመሆኑም ተቃራኒ ማስረጃ ሣይቀርብና የማህተሙ ሀሰተኛ መሆን ሣይረጋገጥ በጥርጣሬ ብቻ የሚደርስ ድምዲሜ ህጋዊ ተቀባይነት ሉኖረው አይችልም። ስለሆነም አመልካች ለማስረጃነት ላቀረበው የከተማ ይዞታ ምስክር ወረቀት ዋጋ የማይሰጥበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
የምስክር ወረቀቱ ዋጋ አለው ከተባለ ደግሞ ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ንብረቶች ህጋዊ ባለቤት መያዣ የሰጠው ግለሰብ አቶ ሚካኤል ከፍያለው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ. 1195 ድንጋጌ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። የንብረቶቹ ህጋዊ ባለቤት ይኸው ግለሰብ መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ ከንብረቶቹ ጋር ተያይዞ የሚጠየቀውን ማንኛውንም መብትና ጥቅም ህጉ ጥበቃ የሚያደርገው ለዚሁ ባለንብረት ነው። ተጠሪዎች በንብረቶቹ ላይ አቶ ሚካኤል ከፍያለው ይዟል የተባለውን የምስክር ወረቀት በተቃራኒ ማስረጃ አላስተባበለም፤ ስልጣን ባለው አካልም እንዱሰረዝ አላደረጉም ወይም በንብረቶቹ ላይ በህጉ አግባብ ያቋቋሙት የባለሀብትነት መብት የለም። ይህ የሚያሣየውም ተጠሪዎች በንብረቶቹ ላይ ህጉ ጥበቃ የሚያደርግላቸው መብትና ጥቅም የላላቸው መሆኑን ነው። ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ላይ መብትና ጥቅም የላለው ወገን ደግሞ የዲኝነት ጥያቄ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/ ድንጋጌ ያስረዲል።
በመሆኑም የተጠሪዎች የዲኝነት ጥያቄ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/ እና 359 ድንጋጌዎች ጋር ተዛምድ ሲታይ ከመነሻውም ቢሆን ህጋዊ መሰረት የላለው ነው ልባል የሚችል ነው።
አመልካች የያዘው የመያዣ ንብረት በህጉ አግባብ የአቶ ሚካኤል ከፍያለው ነው እንጂ የይዞታ ምስክር ወረቀት በተጭበረበረ መንገድ የተያዘ ነው ከተባለም የመያዣ ውለ ህጋዊ አይደለም ልባል ይችል የነበረው አመልካች ከቅን ልቦና ውጪ በሆነ ሁኔታ መያዣውን መያዙን ሲረጋገጥ ነበር። ይህም በፍ/ብ/ህ/ቁ. 3ዐ51/2/ ድንጋጌ በግልፅ ተመልክቷል።
በመሆኑም የአስተዲደር ክፍል የማይንቀሣቀስ ንብረት ባለሀብት መሆኑን አውቆለት የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ከሰጠው ሰው ጋር የተደረገ የንብረት መያዣ ውል በህግ ፉት የፀና ሲሆን የምስክር ወረቀቱ የተሰጠበት ማስረጃ ፍርስ ሆኖ የተሰረዘ ቢሆንም በመያዣው የሚከራከረው ሰው በቅን ልቦና አለመሆኑ ካልተገለፀ በቀር የርስት መያዣው ውል የሚፀና ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3ዐ51/1/ እና /2/ ድንጋጌዎች ያሣያለ። በዚህም መሰረት የአመልካች መያዣ በህግ ፉት የማይፀናበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
ሲጠቃለልም የበታች ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሣኔ ከላይ የተመለከቱትን የህግ ድንጋጌዎችን ያላገዘበ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በምዔራብ ሐረርጌ ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ ዐ4527 ሚያዝያ ዐ9 ቀን 1999 ዓ.ም. ተሰጥቶ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ለክርክሩ መነሻ በሆኑ ንብረቶች ላይ አመልካች የፀና የመያዣ ውል ስላለው ለንብረቶቹ በሚከፈለው ካሣም መብት አለው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
ህዲር 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ይፃፍ።