No summary available.
ሐምል 22 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አቶ ደረሱ ዓለሙ - አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- አቶ ሙሉሣ ወርቁ - አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው በምስራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ ነበሩ።
የክሱም ምክንያት በ10/8/98 ዓ.ም በተፃፈ የብድር ውል በ29/9/98 ዓ.ም ለመመለስ ብር 11,750 (አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ) ተበድረው በተባለው ቀን ካልከፈለ እጥፍ አድርገው ብር 23,500(ሃያ ሦስት ሺህ አምስት መቶ) ለመክፈል ገንዘቡን ተቀብለው ስላልከፈለ በውለ መሰረት ገንዘቡን እጥፍ አድርገው እንዱከፍለ እንዱወሰን በማለት ውላቸውን ጨምሮ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ የሚል ነው።
ሁለተኛ ተከሳሽ የነበሩት ዋስ የብድሩን ገንዘብ በማመን ከዋናው ተበዲሪ ጋር ይከራከር በማለት መልስ የሰጡ ሲሆን አንደኛ ተከሳሽ የአሁኑ አመልካች ግን የተበደረውን ያህል ብቻ እንጂ እጥፍ ተደርጏ መክፈል እንደላለባቸው በመግለጽ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል።
ግራ ቀኙን ያከራከረው ፍ/ቤት አመልካች የተበደሩትን ገንዘብ ወለድ በማድረግ 23,500 (ሃያ ሦስት ሺህ አምስት መቶ) በውለ መሰረት እንዱከፍለ ዋና ተበዲሪው ካልከፈለ ዋሱ እንዱከፍለ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት የሰረዘው ሲሆን ሰበር ሰሚ ችልትም በተመሳሳይ ሁኔታ በማጽናቱ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ጥር 3 ቀን 2001 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ቅሬታ መሰረት የብድሩ ገንዘብ እጥፍ ተደርጏ እንዱከፍል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ተጠሪን በማስቀረብ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሐፍ አቅርበዋል።
እኛም ክርክራቸውን እንደሚከተለው መርምረናል።
ከግራ ቀኙ ክርክር በፍሬ ነገረ ረገድ የተረጋገጠውና የማይካካደት 11,750.00 (አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሐምሳ ብር) አመልካች ከተጠሪ በብድር የወሰደ መሆኑን ነው። አከራካሪ የሆነው የተጠቀሰው የብድር ገንዘብ በተባለው ቀን ባለመከፈለ ምክንያት እጥፍ አድርጏ የመመለሱ ጉዲይ ነው። በመሰረቱ ተዋዋዮች የብድሩን ገንዘብ እጥፍ አድርጏ ማለትም መቶ ፏርሰንት ወለድ ለመክፈል ቢዋዋለ የሕግ መሰረት ይኖራል ወይ? የሚለው ነጥብ ምላሽ ሉያገኝ የሚገባ ነው። ተዋዋዮች በወለድ የሚከፈለውን ገንዘብ በአመት በመቶ ከአስራ ሁለት በላይ እንዱሆን ለመዋዋል እንደማይቻል በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2479/1/ የተመለከተ ከመሆኑም በላይ በወለድ የሚከፈለው ገንዘብ በመቶ አስራ ሁለት በላይ በዓመት እንዱሆን በጽሁፍ የተደረገ ውል ቢኖር እንኳ ተበዲሪው በመቶ ዘጠኝ ብቻ በአመት ወለድ መክፈል እንዲለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2479/3/ በአስገዲጅ ሁኔታ ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ተዋዋዮች የብድርን ገንዘብ እጥፍ አድርጏ ለመክፈል መስማማትን ሕጉ የማይፈቅድ መሆኑን ከፍ ሲል ከተጠቀሱ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
ተጠሪ በስር ፍ/ቤት በግልጽ የጠየቁት ዲኝነት አመልካች በ10/8/98 ዓ.ም በተፃፈ ውል በ29/9/98 ሉመልስልኝ በዚህ ቀን ሳይመልስ ቀኑን ካሳለፈ የተበደረውን ገንዘብ እጥፍ አድርጏ ሉከፍለኝ ብር 11,750(አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ) ተበድሮ እስካሁን አልመለሰልኝም። ስለዚህ በገቡት ግዳታ መሰረት እጥፍ አድርገው ብር 23,500(ሃያ ሦስት ሺህ አምስት መቶ) እንዱከፍለ እንዱወሰንልኝ የሚል ነው። ፍ/ቤቱም እጥፍ ተደርጏ የመከፈለን ጥያቄ ተቀብል በስምምነቱ መሰረት እጥፍ የተባለውን ወለድ ለማድረግ 23,500 ብር እንዱከፍል በማለት መወሰኑ ከፍ ሲል ስለወለድ አከፊፈል በሕጉ የተመለከተውን ድንጋጌ ያላገናዘበ ነው። የተጠሪ ጥያቄ በውለ በተመለከተው ቀን ባለመከፈለ ምክንያት ገንዘቡ እጥፍ ተደርጏ እንዱከፈላቸው እንጅ ክፍያው ስላዘገየባቸው ወለድ ተሰልቶ እንዱከፈላቸው አልጠየቁም። በፍ/ቤቶች መብትም ሆነ ግዳታ በፍርድ ሉረጋገጥ የሚችለው በሕግ በተመለከቱ ስርአቶች ብቻ እና በግልጽ በተጠየቀው ዲኝነት አንፃር ነው። በተያዘው ጉዲይ የብድርን ገንዘብ ከመነሻው እጥፍ አድርጏል ለመክፈል ውል ለመዋዋል ሕጉ የሚከለክል ሲሆን ከፍ ሲል ከተመለከቱት የሕግ ድንጋጌዎች መንፈስ ባፈነገጠ መልኩ የምእራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተጠቀሰውን ገንዘብ እንደወለድ እጥፍ አድርጏ ይክፈል በማለት የሰጠውን ውሳኔ ይግባኝ ሰሚም ሆነ ሰበር ሰሚ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ማረም ሲገባቸው በማጽናት የሰጡት ውሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ትርጉም ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
No topics extracted.
ይፃፍ።
አመልካች 11,750(አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ) ስለመበደራቸውና ይህንኑ ብር ብቻ እንደሚከፍለ ያመኑ በመሆኑ ከውለ ጊዜ ማለትም ከ10/8/98 ዓ.ም እስከ 29/9/98 ዓ.ም ድረስ ያለውን የአንድ ወር ከ19 ቀን ብቻ 11,750 ብር የሚያስገኝውን ወለድ 9% በዓመት ስላት ታስቦ ለተጠሪ እንዱከፈለ በማለት ተወስኗል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለን መዝገቡን ዘግተናል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።