No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 2 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብደልቃድር መሐመድ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገረፈጅ ደረጀ ባዩ - ቀረቡ ተጠሪ፡- 1ኛ. አቶ ሞሣ ነጋሽ አልቀረቡም 2ኛ. ጣና ትራንስፖርት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጠበቃ አቶ አምሣለፀሐይ - ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች ሐምል 9 ቀን 2000 ዓ.ም በፅሐፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ችልት በመዝገብ ሰኔ 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከቱ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ ተጠሪ ሁለተኛው ተጠሪ በፍርድ የተወሰነበትን ብር 2,957,935.30 /ሁለት ሚሉዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሣ ሰባት ሺ ዘጠኝ መቶ ሰላሣ አምስት ብር ከሰላሣ ሣንቲም/ ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል የአፈፃፀም ትዔዛት ይሰጥልኝ በማለት ጠይቋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤትም በአንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ያቀረበውን ክርክር ከመረመረ በኋላ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለው የአክሲዮን ድርሻ በሃራጅ ተሸጦ በፍርድ ለተሰወሰነበት ዔዲ መክፈያ እንዱሆን ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከዚህ በኋላ አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ በፍርድ ቤት የተጀመረውን የአፈፃፀም ክርክር ከፍርድ ቤት ውጭ በስምምነት ለመጨረስ ተስሣምተዋል። አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውን ጠቅላላ ዋጋቸው 1,427,150 /አንድ ሚሉዩን አራት መቶ ሃያ ሰባት ሺ አንድ መቶ ሃምሣ ብር/ የሆነ የአክሲዮን ድርሻዎች በዔዲ መክፈያነት በአንደኛ ተጠሪ እንዱተላለፍ እንደዚሁም ሁለተኛው ተጠሪ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2006/2007 ከአክሲዮን ድርሻ ያገኘው ዱቪደንድ በዔዲ መክፈያነት ለአንደኛው ተጠሪ እንዱተላለፍ ተስማምተዋል። አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ ይህንን ስምምነታቸውን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል። የአፈፃፀሙን ክርክር የያዘው ፍርድ ቤትም የአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር በስምምነታቸው መሰረት እንዱፈፀም ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የአፈፃፀም ክርክሩ በዚህ ሂደት ላይ እያለ አመልካች በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ መብቱን ለማስከበር እንዱፈቀድለት አመልክቷል። አመልካች አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ባደረጉት ስምምነት ፍርድ ቤቱ ለሁለተኛው ተጠሪ ዔዲ መክፈያነት እንዱውል ትዕዛዝ የሰጠበት ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለው የአክሲዮን ድርሻና ሁለተኛ ተጠሪ ከአክሲዮን ድርሻው መሰረት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 2ዐዐ6/2ዐዐ7 ዓ.ም የሚከፈለው ዱቪደንድ እና ላልች ተያያዥነት ያላቸው መብቶች ላይ የቅድሚያ መብት አለኝ። ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለው የአክሲዮን ድርሻ ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለወሰደት ኦቨር ድራፍት ብድር በመያዣነት ይዠዋለሁ። የሁለተኛው ተጠሪ የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት የተያዘ መሆኑ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር የአክሲዮን መዝገብ ውስጥ ተመዝግቧል። የሁለተኛው ተጠሪ የአክሲዮን ሰርተፉኬትም በእጃችን ይገኛል። ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለው የአክሲዮን ድርሻና ዱቪደንድ ለአንደኛ ተጠሪ ዔዲ መክፈያነት ወደ አንደኛው ተጠሪ እንዱተላለፍ የሰጠውን የአፈፃፀም ትዕዛዝ ይሰርዝልን በማለት አመልክቷል።
አመልካች በአፈፃፀም ክርክሩ ጣልቃ ለመግባት ካቀረበው ማመልከቻ ጋር በማያያዝ የፅሐፍ ማስረጃዎች አቅርቧል። አመልካች ክርክሩን ለማስረዲት ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አመልካች የኦቨር ድራፍት ብድር እንዱፈቀድለት ላቀረበው ጥያቄ መያዣ ይሆን ዘንድ ሁለተኛ ተጠሪ አቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ካለው የአክሲዮን ድርሻ ዋጋቸው 475,ዐዐዐ (አራት መቶ ሰባ አምስት ሺ ብር) የሆኑ የአክሲዮን ድርሻዎችንና ላልች ስምንት ሰዎች በአቢሲኒያ ባንክ ያላቸውን የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት ያቀረበ መሆኑን ገልፆ የፃፈው ደብዲቤ ከነ አባሪው አመልካች ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኦቨር ድራፍት ብድር ለወሰደው 4ዐ,ዐዐዐ,ዐዐዐ (አርባ ሚሉዮን ብር) መያዣ እንደሆነ ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ካለው የአክሲዮን ድርሻ ዋጋቸው 475,ዐዐዐ (አራት መቶ ሰባ አምስት ሺ ብር) የሆኑ የአክሲዮን ድርሻዎችንና የላልች ስምንት ሰዎች የአክሲዮን ድርሻዎች በመያዣነት የያዘ በመሆኑ የአክሲዮን ድርሻዎቹ አመልካች በመያዣነት የያዛቸው መሆኑ በአክሲዮን መመዝገቢያ መዝገብ እንዱመዘገብለት ለአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር የፃፈው ደብዲቤ፣ የአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር አመልካች ለሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለሰጠው የኦቨር ድራፍት ብድር በመያዣነት የያዛቸው የሁለተኛው ተጠሪና የላልች ስምንት ሰዎች የአክሲዮን ድርሻዎች አመልካች በመያዣነት የያዛቸው መሆኑ በአክሲዮኖች መመዝገቢያ መዝገብ የተመዘገበና ለሶስተኛ ወገን የማይተላለፍ መሆኑን በማረጋገጥ ለአመልካች በአድራሻው የፃፈውንና ለሁለተኛው ተጠሪ ግልባጭ የተደረገ ደብዲቤ፣ ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከአመልካች ብር 4ዐ,ዐዐዐ,ዐዐዐ (አርባ ሚሉዮን ብር) የኦቨር ድራፍት ብድር የወሰደበት የብድር ውልና ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኦቨር ድራፍት የወሰደውን ብድር ከነ ወለደ ያልከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዲቤ፣ አመልካች ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ብር 10,000,000 /አስር ሚሉዮን ብር/ በኦቨር ድራፍት ብድር ሲወሰድ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ካለው የአክሲዮን ድርሻ ዋጋቸው 600,000 /ስድስት መቶ ሺ ብር/ የሆኑ አክሲዮኖች በመያዣነት ያስያዘና መያዣው በመሆኑ በአክሲዮን መመዝገቢያ መዝገብ እንዱመዘገብለት ለአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር የፃፈው ደብዲቤ፣ አቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር አመልካች ለእስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለሰጠው የኦቨር ድራፍት ብድር በመያዣነት የያዛቸው የሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለው ዋጋቸው 600,000 /ስድስት መቶ ሺ ብር/ የሆኑ የአክሲዮን ድርሻዎች በመያዣነት የተያዙ መሆኑ በአክሲዮን መመዝገቢያ መዝገብ የተመዘገበ መሆኑንና ለላልች ሶስተኛ ወገኖች እንደማይተላለፈ በማረጋገጥ ለአመልካች በአድራሻው የፃፈውና ለሁለተኛው ተጠሪ ግልባጭ የተደረገ ደብዲቤ፣ በአመልካች እጅ የሚገኘውን ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለው የአክሲዮን ድርሻ ማረጋገጫ ሰርተፉኬትና አመልካች ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውን የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት መያዙን ገልፆ ሁለተኛው ተጠሪ የሚደርሰው ዱቪደንድ ለአመልካች ተከፊይ የሚሆንበትን ሁኔታ እንዱመቻች ለአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር በአድራሻው የፃፈውና ለሁለተኛው ተጠሪ ግልባጭ የተደረገ ደብዲቤ፣ አቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች አስረኛ መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ የሚካሄድ መሆኑንና ሁለተኛው ተጠሪ ያለት አርባ ሶስት የአክሲዮን ድርሻዎች በአመልካች በመያዣነት የተያዙ በመሆኑ አመልካች ካልፈቀደለት በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት የማይችል መሆኑ በንግድ ሕግ ቁጥር 329/1/ የተደነገገ መሆኑን ገልፆ ሁለተኛው ተጠሪ በስብሰባው ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት ከአመልካች ውክልና ይዞ መቅረብ እንዲለበት ለሁለተኛ ተጠሪ በአድራሻው የፃፈው እና ለአመልካች ግልባጭ ያደረገውን ደብዲቤ፣ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውንና ዋጋቸው 1,075,000 /አንድ ሚሉዮን ሰባ አምስት ሺ ብር/ የሆነ አርባ ሶስት አክሲዮኖች ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለወሰደት ብድር በዋስትና ያስያዘ መሆኑን በመግለፅ፣ ከባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤና ላልች ስብሰባዎች በመካፈል ድምፅ ለመስጠት እንዱፈቅድልንና ለአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ደብዲቤ እንዱፃፍልን በማለት ለአመልካች የፃፈውን ደብዲቤ በማስረጃነት አያይዞ አቅርቧል።
No topics extracted.
የአመልካች ማመልከቻና ማስረጃ ለተጠሪዎች ደርሷቸው ተጠሪዎች በተናጠል የመከላከያ መልስና ማስረጃ አቅርበዋል። አንደኛ ተጠሪ ባቀረበው የፅሐፍ ክርክር ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከአመልካች የኦቨር ድራፍት ብድር ሲወስድ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውን የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት አላስያዘም። አመልካች ከሁለተኛ ተጠሪ ጋር የፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2828 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት የመያዣ ውል ያተዋዋለ መሆኑን የሚያስረዲ የፅሐፍ ማስረጃ አላቀረበም። አመልካች ከሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና ለአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ጋር በተለያየ ጊዜ ያደረጋቸው መፃፃፍች በአመልካችና በሁለተኛ ተጠሪ መካከል የመያዠያ ውል አያቋቁሙም። አመልካች ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውን የአክሲዮን ድርሻ የህጉን ፍርማሉቲ በማሟላት በመያዣነት ያልያዘ መሆኑን በማመን የአመልካች የክሬዱት አገልግልትና የሕግ አገልግልት በተፃፃፎቸው ደብዲቤዎች አረጋግጧል። ስለሆነም አመልካች በሁለተኛው ተጠሪ የአክሲዮን ድርሻ ላይ የቀዲሚነት መብት አለኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
ሁለተኛው ተጠሪ በበኩለ ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር እና ስታር ቢዝነስ ግሩኝ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለወሰደት የኦቨር ድራፍት ብድር እኔ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለኝን የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት ለማስያዝ ከአመልካች ጋር ያደረግሁት የመያዣ ውል የለም። እኔ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለኝን የአክሲዮን ድርሻ አመልካች በመያዣነት እንዱይዝ አልተስማማሁም። አመልካች ከእኔ ፍላጏትና ፈቃድ ውጭ የኦቨር ድራፍት ብድር ከወሰደት የንግድ ድርጅቶችና ከአቢሲኒያ ባንክ ጋር በመፃፃፍ የአክሲዮን ድርሻዎቹን በመያዣነት ይዣለሁ በማለት የቀዲሚነት መብት እንዱረጋገጥለት የሚያቀርበው ጥያቄ ተገቢ አይደለም። በማለት ተከራክሯል።
አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ በተናጠል ያቀረቡትን ክርክር ያስረዲልናል በማለት፡-
የሥር ፍርድ ቤት የአመልካችን ማመልከቻና ማስረጃ እንደዚሁም ተጠሪዎች ያቀረቡትን መከላከያና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ ያለውን የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት የያዘ መሆኑን ለማስረዲት ያቀረባቸው ማስረጃዎች በአመልካችና በተጠሪ መካከል በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2828 ንዐስ አንቀፅ 2፣ በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 1725 እና በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 1727 ድንጋጌዎች መሰረት የመያዣ ውል የተደረገ መሆኑን አያስረደም። ስለሆነም አመልካች በሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ባለው የአክሲዮን ድርሻ ላይ የመያዣና የቅድሚያ መብት የለውም በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍታብሕር ችልት አቅርቧል።
ይግባኝ ሰሚ ችልቱም የሥር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚነቀፍበት ምክንያት የላለ መሆኑን በግለፅ የአመልካችን ይግባኝ ሰርዞታል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ችልት የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውን የአክሲዮን ድርሻ ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለወሰደት የኦቨር ድራፍት ብድር በመያዣነት ያስያዘ መሆኑን በግልፅ በማመን በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሣተፍና ድምፅ ለመስጠት የውክልና ደብዲቤ እንዱፃፍለት አመልካችን የጠየቀበት ደብዲቤ በማስረጃነት ቀርቧል። ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ ያለው የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት የተያዘ መሆኑንና በአክሲዮን መመዝገቢያ መዝገብ የመዘገበ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ አቅርበናል። ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውን የአክሲዮን ድርሻ የሚያረጋግጠው የአክሱዮን ሰርተፉኬት እስካሁን በእጃችን እንደሚገኝ አስረድተናል። የሥር ፍርድ ቤት የአክሱዮን ድርሻ በመያዣነት የሚያዙበትን ልዩ ሁኔታ ሣያገናዝብ አግባብነት የላላቸውን የፍታብሕር ሕግ ድንጋጌዎች በመጥቀስና በመተርጏም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። ይግባኝ ሰሚ ችልትም ይህንን መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትን የሥር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አፅንቷል። ስለሆነም ጉዲዩ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪዎች በተናጠል በሰጡት መልስ አመልካች የኦቨር ድራፍት ብድር ሲሰጥ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውን የአክሲዮን ድርሻ በዋስትና ለማስያዝ ከአመልካች ጋር አልተዋዋለም። አመልካች ከሁለተኛው ተጠሪ ጋር በፍታብሕር ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት የተዋዋለው የመያዠያ ውል በላለበት ሁኔታ አመልካች የሚያቀርበው የቀዲሚነት ጥያቄ የሕግ ድጋፍ የለውም። አመልካች የአክሲዮን ድርሻ ማረጋገጫ ሰርተፉኬቱን በእጁ ያስገባው ከሁለተኛው ተጠሪ ፈቃድና ፍላጏት ውጭ ነው። ስለዚህ አመልካች ያቀረባቸው የፅሐፍ ማስረጃዎች በአመልካችና በሁለተኛው ተጠሪ መካከል የመያዣ ውል ያለ መሆኑን ስለማያስረደ የሥር ፍርድቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም። ሰበር ችልት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ያድርግልን በማለት ተከራክረዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
አመልካችና ተጠሪዎች ለሰበር በፅሐፍ ካቀረቡት ክርክር በተጨማሪ ችልቱ የአመልካች ነገረ ፈጅና የተጠሪዎች ጠበቆች የቃል ክርክር ሰምቷል። የአመልካች ነገረ ፈጅ ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለወሰደት ኦቨር ድራፍት ብድር ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውን የአክሲዮን ድርሻ በንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች መሰረት በአክሲዮን መመዝገቢያ መዝገብ አስመዝግበን ይዘናል። ሁለተኛው ተጠሪም ይህንን በማመን የፃፈው ደብዲቤ አለ። ስለዚህ የሥር ፍርድ ቤት የአክሲዮን ድርሻ በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2828(2) መሰረት አልተያዘም በማለት የሰጠው የሕግ ትርጉም መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት የሚል ይዘት ያለው ሰፉ የቃል ክርክር አቅርቧል።
በተናጠል የቃል ክርክራቸውን ያሰሙት የአንደኛና የሁለተኛ ተጠሪ ጠበቆች በበኩላቸው አመልካች ለሰጠው የኦቨር ድራፍት ብድር ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ ያለው የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት ለማስያዝ ያደረገው ስምምነት የለም። ሁለተኛው ተጠሪ በባለአክሲዮኖች ስብሰባ ለመካፈል አመልካችን በፅሐፍ የጠየቁበት ደብዲቤ በስህተት የተፃፈ ደብዲቤ ነው። አመልካችም በስህተት የፃፍነው መሆኑን፣ አውቆ ዋናውን ደብዲቤ መልሶ ለሁለተኛው ተጠሪ ሰጥቶታል። ስለሆነም የሕጉን መስፈርት የሚያሟላ የመያዣ ውል ሣይኖር አመልካች ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ባለው የአክሲዮን ድርሻ ላይ የቀረበውን የቀዲሚነት የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ነው። ትዔዛዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም የሚል ይዘት ያለው ሰፉ የቃል ክርክር አቅርበዋል።
በሥር ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪዎች ያደረጉት ክርክር የሥር ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ትዕዛዝና በሰበር አመልካችና ተጠሪዎች በፅሐፍና በቃል ያደረጉት ክርክር በአጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት ለመያዝ የሚደረገው የመያዣ ውል ላልች ግዙፍነት ያላቸው ተንቀሣቃሽ ንብረቶች ለመያዝ በሚያስፈልገው ፍርማሉቲ መሰረት መፈፀም አለበት ወይ? የሚለው ነጥብ የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ ሆኖ አግኝተነዋል።
የአክሲዮን ድርሻ አንድ የተፈጥሮ ወይም ሕግ ወለድ ሰው ካፒታለ አስቀድሞ በታወቀ በአክሲዮን በተከፊፈለና ለዔዲውም ንብረቱ ብቻ ዋስትና በመሆኑ የአክሲዮን ማህበር ውስጥ ያለትን አክሲዮኖች ብዛትና ዋጋ የሚያረጋግጥ ነው።
አንድ ባለ አክሲዮን በአክሲዮን ማህበሩ ውስጥ በባለቤትነት የያዛቸው አክሲዮኖች ግዙፍ ያልሆኑ ሃብቶች ናቸው።
በአገራችን ዔውቅና እና ጥበቃ የተሰጣቸው ሁለት አይነት አክሲዮኖች እንዲለ የንግድ ሕግ ቁጥር 325 ንዐስ አንቀፅ 1 ይደነግጋል።
የመጀመሪያው አይነት አክሲዮን ለአምጭው ተብል የተፃፈባቸው አክሲዮኖች ሲሆኑ እነዚህን አክሲዮኖች ለላላ ሰው ለማስተላለፍም ሆነ በመያዣነት ለመያዝ እንደማንኛውም ተላላፉ የንግድ ወረቀት የአክሲዮን ድርሻ ማረጋገጫ ሰነደን አሳልፍ በመስጠት ያለአንዲች አይነት አሰራር /ፍርማሉቲ/ ማከናወን እንደሚቻል የንግድ ሕግ ቁጥር 340 ንዐስ አንቀፅ 1 እና ከፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2866(2) ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል።
ሁለተኛው አይነት አክሲዮን የባለ አክሲዮኑ ስም የተፃፈበት አክሲዮን ነው። ስም የተፃፈበት አክሲዮን የአክሲዮን ማረጋገጫ ሰነደን አሳልፍ በመስጠት ብቻ ለማስተላለፍና በመያዣነት ለማስያዝ አይቻልም። ስም የተፃፈበት አክሲዮን ለማስተላለፍም ሆነ በመያዣነት ለማስያዝ አክሲዮኖቹ ለላላ ሰው የተላለፈ ወይም በመያዣነት የተያዙ መሆኑን በአክሲዮን ማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው የአክሲዮን መዝገብ ማስመዝገብ እንደሚያስፈልግ ሕግ ቁጥር 341(2) እና የፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2865(1) ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል። ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለት አክሲዮኖች የሁለተኛው ተጠሪ ስም የተፃፈባቸው አክሲዮኖች መሆናቸውን አመልካች በማስረጃነት ካቀረበው የአክሲዮን ድርሻ ማረጋገጫ ሰርተፉኬት ለመረዲት ይቻላል። የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለት የአክሲዮን ድርሻዎች እንደማንኛውም ግዙፍነት ያላቸው ተንቀሣቃሽ ንብረት በመቁጠር የፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2828 ንዐስ አንቀፅ 2 እና ላልች የውል ሕግ ጠቅላላ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ መወሰናቸው ከጅምሩ በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል ያለው ክርክር ግዙፍነት የላላቸው ሃብቶች (አክሲዮኖች) በመያዣነት መያዝን የሚመለከትና ለጉዲዩም ተፈፃሚነት ያላቸው ከፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2863 እስከ ፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2874 የተደነገጉትና አግባብነት ያላቸው የንግድ ሕግ ድንጋጌዎች መሆናቸውን ባለማገናዘብ የተሰጠ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች የሁለተኛው ተጠሪ ስም የተፃፈባቸውን ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለት የአክሲዮን ድርሻዎች ለመያዝ ይህንን በሕግ የተደነገገ ፍርማሉቲ ማሟላት ይገባዋል። ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ካለት የአክሲዮን ድርሻዎች ውስጥ አመልካች ለሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለሰጠው ብር 40,000,000 /አርባ ሚሉዮን ብር/ ኦቨር ድራፍት ብድር መያዣ ይሆኑ ዘንድ ብር 475,000 /አራት መቶ ሰባ አምስት ሺ ብር/ ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖች በአመልካች በመያዣነት የተያዙ መሆኑና መያዣው በአቢሲኒያ አክሲዩን ማህበር የአክሲዮን መዝገብ የተመዘገበ መሆኑን አቢሲኒያ ባንክ ሚያዚያ 6 ቀን 1992 ዓ.ም ለአመልካች በአድራሻው ለሁለተኛው ተጠሪ በግልባጭ የፃፈው ደብዲቤ ያረጋግጣል። ከዚህ በተጨማሪ እስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከአመልካች በኦቨር ድራፍት ለወሰደው ብር 10,000,000 /አስር ሚሉዮን ብር/ መያዣ ይሆኑ ዘንድ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ካለት አክሲዮኖች ዋጋቸው ብር 600,000 /ስድስት መቶ ሺ ብር/ የሆኑ አክሲዮኖችን አመልካች በመያዣነት የያዛቸውና መያዣውም በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር የአክሲዮን መዝገብ የተመዘገበ መሆኑን አቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ሚያዚያ 4 ቀን 1992 ዓ.ም ለአመልካች በአድራሻ ለተጠሪ በግልባጭ የፃፈው ደብዲቤ ያስረዲል። ይኸም አመልካች ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲንያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ካለው የአክሲዮን ድርሻ ዋጋቸው 1,075,000 /አንድ ሚሉዮን ሰባ አምስት ሺ ብር/ የሆኑ አርባ ሶስት አክሲዮኖች በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2865 ንዐስ አንቀፅ 1 እና በንግድ ሕግ ቁጥር 341 አንቀፅ 2 የተቀመጠውን ፍርማሉቲ በማሟላት በመያዣነት የያዘ መሆኑን ለማስረዲት የሚችል ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪዎች የአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር የሁለተኛው ተጠሪ የአክሲዮን ድርሻዎች በአመልካች በመያዣነት የያዛቸው መሆኑን በአክሲዮን መዝገብ ላይ የመዘገበው ያለ ሁለተኛው ተጠሪ ፈቃድና ስምምነት ነው የሚል ክርክር አቅርበዋል። አቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ሁተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ ያለውን የአክሲዮን ድርሻ አመልካች ለሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና ለስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላበደረው የኦቨር ድራፍት ብድር በመያዣነት የያዙ መሆኑን የመዘገበው ሁለተኛው ተጠሪ ሁለቱ እህት ኩባንያዎች ከአመልካች ለወሰደት ብድር ያለት የአክስዮን ድርሻዎቹ አስፈላጊውን ፍርማሉቲ አሟልቶ በመያዣነት እንዱያዙ እንዱያደርግ ግንቦት 26 ቀን 1991 ዓ.ም ለአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር በፅሐፍ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት መሆኑን ተጠሪዎች በማስረጃነት ይጠቅመናል ብለው ባቀረቡት የአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ግንቦት 14 ቀን 1999 ዓ.ም ከፃፈው ደብዲቤ በመግቢያው ላይ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለት የአክሲዮን ድርሻዎች አመልካች ለሚና ትሬዱንግና ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ለሰጠው የኦቨር ድራፍት ብድር በፍላጏቱና በፈቃደ በመያዣነት ያስያዘ መሆኑን “ኩባንያችን በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለውን የብር 1,075,000 /አንድ ሚሉዮን ሰባ አምስት ሺ ብር/ ዋጋ ያላቸው አርባ ሶስት አክሲዮኖች ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያና ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከባንኩ ለተበደሩት ብድር በዋስትና ያስያዘ መሆኑ ይታወቃል” በማለት አመልካች ከአቢሲኒያ ባንክ የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ለመካፈል እንዱፈቀድለት በቁጥር ጣትኩ 701/37/99 ህዲር 9 ቀን 1999 ዓ.ም የፃፈው ደብዲቤ ያረጋግጣል። ከዚህ በተጨማሪ አቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ አክሲዮኖቹን በማያዣነት በአክሲዮን መዝገብ ውስጥ ሲመዘገብ ሁለተኛው ተጠሪ በግልባጭ እንዱያውቅ እያደረገ መሆኑን የቀረቡት የፅሐፍ ማስረጃዎች ያሣያለ። በአመልካች በኩልና ተጠሪዎች ክርክራቸውን ለማጠናከር ያቀረቧቸው የፅሐፍ ማስረጃዎች ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ያለት አርባሶስት አክሲዮኖች በመያዣነት የያዘውና መያዣው በአክሲዮን መመዝገቢያ መዝገብ የተመዘገበው የፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2865 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት በሁለተኛው ተጠሪ ፈቃድና ስምምነት መሆኑን የሚያረጋግጥ ግልፅ የፅሐፍ ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ በመሆኑ ተጠሪዎች መያዣው በአቢሲኒያ ባንክ አከሲዮን መዝገብ የተመዘገበው ከሁለተኛው ተጠሪ ፈቃድና ስምምነት ውጭ ነው በማለት ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም።
ተጠሪዎች ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ ባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ለመሣተፍ እንዱፈቀድለት ለአመልካች የፃፈው ደብዲቤ በስህተት የተፃፈ ነው። የአመልካች የሥራ ኃላፉዎች ሁለተኛው ተጠሪ ያለውን የአክሲዮን ድርሻ የሕጉን መስፈርት በሚያሟላ የመያዣ ውል ያልተያዘ መሆኑን በተፃፃፈት ፅሐፍ አረጋግጠዋል። ስለሆነም አክሲዮን ድርሻው በመያዣነት አልተያዘም ተብል እንዱወሰንልን የሚል ክርክር አቅርበዋል።
የሁለተኛ ተጠሪ እህት ኩባንያዎች የሆኑት ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና ሚና ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለአመልካች በኦቨር ድራፍት ብድር ሲወስደ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አከሲዮን ማህበር ያለው የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት እንዱያዙ የተስማማ መሆኑ በአመልካች የቀረቡት የፅሐፍ ማስረጃዎች ያረጋግጣለ። አመልካች ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ ያለውን የአክሲዮን ድርሻ መያዣ በማድረግ ለሁለቱ የንግድ ድርጅቶች የኦቨር ድራፍት ብድር ፈቅድ ሁለቱ የንግድ ድርጅቶች ብድሩን ወስደዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሁለቱ የንግድ ድርጅቶች ከአመልካች የወሰደትን የኦቨር ድራፍት ብድር ፈቅድ ሁለቱ የንግድ ድርጅቶች ብድሩን ወስደዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሁለቱ የንግድ ድርጅቶች ከአመልካች የወሰደትን የኦቨር ድራፍት ብድር አልከፈለም። ከዚህ ሁለ ሂደት በኋላ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ ያለኝ የአክሲዮን ድርሻዎች አመልካች በመያዣነት የያዛቸው መሆኑን በመግለፅ የፃፍኩት ደበዲቤ በስህተት የተፃፈ ነው በማለት ያቀረበው ክርክር የሕግ ድጋፍና ተቀባይነት የላለው ክርክር ሆኖ አግኝተነዋል። ሁለተኛው ተጠሪ አመልካች በአክስዮን ድርሻዎቹ ላይ የሕጉን መስፈርት የሚያሟላ የመያዣ ውል የላለው መሆኑን በመግለፅ የባንክ ኃላፉዎች በፁሐፍ አረጋግጠዋል በማለት የሚከከራከረው የባንኩ ኃላፉዎች የውስጥ መፃፃፉያ ሚሞ በማስረጃነት በማቅረብ ነው። እነዚህ የውስጥ መፃፃፉያዎቹ በዚህ ጉዲይ የአስረጅነት ዋጋ የላላቸው በመሆኑ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም። ከዚህ በተጨማሪ የአመልካች ኃላፉዎችና የሕግ ክፍል እርስ በርሳቸው በፅሐፍ የተለዋወጡት ሃሣብ በጉዲዩ ተፈፃሚነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች ያላገናዘበና የሕግ አረዲድ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ካለው የአክሲዮን ድርሻ ውስጥ ዋጋቸው 1,075,000 /አንድ ሚሉዮን ሰባ አምስት ሺ ብር/ የሆኑ የአክሲዮን ድርሻዎችን አመልካች በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2865 ንዐስ አንቀፅ 1 እና በንግድ ሕግ ቁጥር 341 ንዐስ አንቀፅ 2 የተደነገገውን መስፈርት በማሟላት በመያዣነት የያዛቸው ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች የአክሲዮን ድርሻዎቹን በመያዣነት የያዘውና በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ የአክሲዮን መዝገብ ያስመዘገበው የፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2865 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት በሁለተኛው ተጠሪ ፈቃድና ሙለ ስምምነት መሰረት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ግዙፍ ያልሆኑ ሃብቶች በመያዣነት በሚያዙበት ወቅት ገዥነት ያላቸውንና ተፈፃሚ ሉሆኑ የሚገቡ የሕግ ድንጋጌዎች ሣያገናዝቡ አመልካች የሁለተኛ ተጠሪን የአክስዮን ድርሻ በመያዣነት የያዘ ስለመሆኑ በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2828 ንዐስ አንቀፅ 2 እና ላልች ጠቅላላ የውል ሕግ ድንጋጌዎችን የሚጠይቁትን ፍርማሉቲ ያላሟላ በመሆኑ ሕጋዊ ውጤት የለውም በማለት የሰጡት ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሰኔ 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
አመልካች ለእስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና ለሚና ትሬዱንግ ኃላፉቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኦቨር ድራፍት ብድር ሲያበድር ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ካለው የአክሲዮን ድርሻ ዋጋቸው 1,075,000 /አንድ ሚሉዮን ሰባ አምስት ሺ ብር/ የሆነ አርባሶስት አክሲዮኖች በመያዣነት ይዟል። በእነዚህ አክሲዮኖች ላይ የቀዲሚነት መብት አለው ብለናል።
አመልካች በመያዣነት የያዛቸውና ከላይ ዋጋቸው የተገለፀው አርባሶስት አክሲዮኖች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2006/2007 እና ከዚያ ወዱህ ያስገኙትን የአክሲዮን ድርሻ ትርፍ /ዱቪደንድ/ የመቀበል የቀዲሚነት መብት አለው ብለናል።
አንደኛ ተጠሪ ለፍርድ ማስፈፀሚያ ማድረግ የሚችለው አመልካች በመያዣነት ያልያዛቸውን የሁለተኛው ተጠሪ አክሲዮኖችና ከእነርሱ የሚገኘው የአክሲዮን ድርሻ ትርፍ /ዱቪደንድ/ ብቻ ነው ብለናል።
ለሰበር ያወጡትን ወጭ አመልካችና ተጠሪዎች ለየራሣቸው ይቻለ።
በትውስት የመጣው የከፍተኛው ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ።
ይኸ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ቀን 2001 ዓ.ም በሙለ ድምፅ ተሰጠ።