No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ፍሉነሰቶን ኢንጂነሪንግ - ጠበቃ ብሥራት ሐመልማል - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- እነ ወ/ት ሃና ተስፊዬ /6 ሰዎች/ - ጠበቃ ኮ/መላኩ ካሰኝ - ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በዚሁ ፍ/ቤት ተጠሪዎች ከሳሾች የነበሩ ሲሆን አመልካች ሁለተኛ ተከሣሽ ነበረ። ተጠሪዎቹ ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ክስ አንደኛ ተከሣሽ ወ/ሮ ወርቅይጠሩ ሰርፀመድኀን ከመሞታቸው በፉት ለክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት በስጦታ ስለሰጡኝ ይጽደቅልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ የተጠሪዎች አባት ተቃውመው የስጦታ ውለ በፍ/ቤቱ ፈራሽ እንዱሆን ተወስኗል። ነገር ግን ቤቱን አንደኛ ተከሣሽ ለአመልካች የሸጡ በመሆኑ ተከሣሾች ቤቱን እንዱያስረክቡና ቤቱን በቁጥጥራቸው ሥር ካዋለበት ጊዜ ጀምሮ ተከራይቶ የተገኘው ገቢ ብር 2ዐ1,ዐዐዐ /ሁለት መቶ አንድ ሺህ/ ይክፈለ በማለት ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ለአንደኛ ተከሣሽ በቤቱ ላይ መብት ሰጥቷቸው የነበረው የስጦታ ውል የፈረሰ በመሆኑ የሥር አንደኛ ተከሣሽ በቤቱ ላይ ከመነሻው ጀምሮ የባለቤትነት መብት የላቸውም ማለት ይቻላል። አመልካችም ቤቱን የገዛው መብት ከላለው ሰው ላይ በመሆኑ የሽያጭ ውለ ለአመልካች ባለቤትነት የማስተላለፍ ውጤት ያለው ሕጋዊ ድርጊት አይደለም። አመልካች በሽያጭ ውለ መሰረት ከአስተዲደር አካል የተሰጠው የቤት ባለቤትነት ሰነድ የሚያጎናጽፈው የባለንብረትነት የሕግ ግምት ሰነደ የተገኘው ሕጋዊ ውጤት በላለው ውል ላይ ተመስርቶ በመሆኑ ፈራሽ ነው። ስለዚህ አመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች ያስረክብ፤ ካሣውን የመክፈል ግዳታ ግን የለበትም። በልላ በኩል የሥር አንደኛ ተከሣሽ የስጦታ ውለ ላይ ክርክር መነሳቱን አውቀው መልስ ከሰጡ ቀን ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ያለውን በወር ብር 5ዐዐ /አምስት መቶ/ እየታሰበ ከወለድ ጋር ይክፈለ በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የስር ውሣኔ አጽንቶታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም አመልካች ቤቱን እንዱመልስ የተሰጠው ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች አንፃር እንደሚከተለው መርምሯል። በዚሁ መሰረት በዚህ ችልት ሉመለስ የሚገባው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤትን አስመልክቶ የተሰጠው የስጦታ ውል በመፍረሱ አመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች ሉመልሱ ይገደዲለ ወይ? የሚለው ጭብጥ ነው።
ከክርክሩ ሂደት ለክርክር ምክንያት የሆነው ቤት ወ/ሮ ወርቅይጥሩ ሰርፀመድኀን ለሥር አንደኛ ተከሣሽ በ28/ዐ2/1993 በተፃፈ የስጦታ ውል ሰጥተው የነበረ መሆኑን፤ የሥር አንደኛ ተከሣሽ በ16/ዐ4/1994 በስማቸው የቤት የባለቤትነት ማስረጃ ተሰጥቷቸው የነበረ መሆኑን፤ በ28/ዐ8/1998 በአዋዋይ ፉት በተደረገ የሽያጭ ውል ለአመልካች መሸጡና አመልካችም የቤት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው መሆኑን፤ ቤቱ ለአመልካች ከተሸጠ በኋላ የስጦታ ውለ ክርክር ቀርቦበት ስለነበር በ25/ዐ2/1997 ዓ.ም. ፈራሽ ነው ተብል መወሰኑን ተገንዝበናል።
ከላይ እንደተመለከተው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው የሥር አንደኛ ተከሣሽን ባለቤት አድርጓቸው የነበረው የስጦታ ውል መፍረስ ነው። ስጦታ ከውል አይነቶች አንደ ነው። የስጦታ ውል ካለው የራሱ የሆነ ባሕሪ አኳያም የስጦታ ውል ግንኙነትን የሚገዙ የተለያዩ የሕግ ድንጋጌዎች በፍ/ብሕር ሕጋችን ተካተው ይገኛለ። ምንም እንኳን የስጦታ ውል በእነዚህ የተለያዩ ድንጋጌዎች የሚዲኝ ቢሆንም ስጦታን የሚመለከቱት እነዚህ ድንጋጌዎች የማይሸፍኗቸው ጉዲዮች ሲገጥሙ ስለ ውልች በጠቅላላ የተመለከቱት ደንቦች ተፈፃሚ ይሆናለ /የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1676(1) ይመለከቷል/። ስጦታን የሚመለከቱ የሕጉ ድንጋጌዎችም የስጦታ ውል ፈራሽ የሚሆንባቸው የተለያዩ ምክንያቶችን የሚዘረዝሩ ቢሆንም የስጦታ ውል ሲፈርስ ምን ውጤት ሉያስከትል እንደሚችል የሚገልጽ ድንጋጌ ግን አላካተቱም። ስለዚህ የስጦታ ውል መፍረስ የማያስከትለውን ውጤት በተመለተ ተፈፃሚ ሉሆኑ የሚገባቸው ስለ ውል በጠቅላላው የሚናገሩት ደንቦች ናቸው።
በእነዚህ ደንቦች መሰረት አንድ ውል ሲፈርስ ወይም ሲሰረዝ ተዋዋዮች በተቻለ መጠን ውለ ከመደረጉ በፉት ወደ ነበሩበት ቦታ እንዱመለሱ ማድረግ ነው /ፍ/ብ/ሕ/ቁ 1815/1/ ይመለከቷል።/ የውል መፍረስ ወይም መሰረዝ ውጤቱ ውለ ከጅምሩ እንዲልተደረገ መቁጠር በመሆኑ ውለታው ለመፈፀም የተሰሩ ሥራዎች ሁለ ቀሪ ሆነው በማናቸውም አኳኋን ውጤት አይኖራቸውም /ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1815/2//። አሁን አንዲየነው በመርህ ደረጃ የውል መፍረስ ውጤት ተዋዋዮችን ወደ ነበሩበት ቦታ መመለስ ነው። በልላ በኩል ግን ምንም እንኳን ውለ ቢፈርስ ወይም ቢሰረዝም የተለያዩ ሁኔታዎች ባጋጠሙ ጊዜ ውለን ተክትለው የተሰሩ ሥራዎችን ቀሪ በማድረግ ተዋዋዮችን ወደነበሩበት ቦታ ከመመለስ ይልቅ እንደረጉ መቆየቱ የተሻለ አማራጭ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ተዋዋዮቹን ወደነበሩበት ቦታ መመለስ የማይቻል ወይም አስቸጋሪ ሲሆን አለበለዚያም ከፍ ያለ መሰናክል የሚያስከትል ሲሆን የተሰሩ ሥራዎች እንደረጉ እንዱቀሩ ሕጉ ያዛል /ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1817/1//። በተመሣሣይ ሁኔታ እነዚህ የተሰሩ ሥራዎች በቅን ልቦና ለተዋዋለ ሦስተኛ ወገን ጠቃሚ ሆነው ከተገኙ የተሰሩ ሥራዎች ሳይፈርሱ እንደረጉ እንዱቆዩ ማድረግ እንደሚገባ ሕጉ ያዛል /ፍ/ብ/ሕ/ቁ 1816/።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ከእነዚህ ድንጋጌዎች አኳያ የተያዘውን ጉዲይ ስንመረምር ከፍ ሲል እንደተመለከትነው ለክርክር ምክንያት የሆነው ቤት ለሥር አንደኛ ተከሣሽ በስጦታ የተሰጣቸው በ28/3/1993 ነው። ተከሣሹም ይህንን የስጦታ ውል መሰረት አድርገው በ16/ዐ4/1996 በቤቱ ላይ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ አግኝተዋል። የአስተዲደር ክፍል የአንድን ንብረት ባለሃብትነት በማወቅ የባለቤትነት ምስክር ወረቀት የሰጠው ሰው የንብረት ባለሃብት ሆኖ እንደሚቆጠር ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195 መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም በአስተዲደር መስሪያ ቤት ተረጋግጦ የባለቤትነት ምስክር ወረቀት ከተሰጣቸው ቀን ጀምሮ የሥር አንደኛ ተከሣሽ የቤቱ ባለሃብት ሆነው ይቆጠራለ ማለት ነው። ይህንንም ሰነድ ይዘው ነው ቤቱን ለአመልካች በ28/ዐ8/1996 የሸጡለት። አመልካች ቤቱን ሲገዛ የቤቱ ባለቤት የነበሩት የሥር አንደኛ ተከሣሽ ናቸው፤ የሽያጩ ውልም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፉት ተደርጓል፤ ከዛም አልፍ የቤቱ ባለሃብትነት ከሥር አንደኛ ተከሣሽ ወደ አመልካች ተዛውሮ አመልካች ቤቱ የባለቤትነት ምስክር ወረቀት አውጥቶ የቤቱ ባለቤት ሆኗል። ከሁለም በላይ ደግሞ አመልካች ቤቱን ሲገዛ የስጦታ ውለ አልፈረሰም። እንግዱህ አመልካች ቤቱን ሲገዛ ቤቱ የሥር አንደኛ ተከሣሽ ሳይሆን የላላ ሰው እንደሆነ ሉያውቅ የሚችልበት ምንም አይነት ሁኔታ አልነበረም ብቻ ሳይሆን የቤቱ ባለቤት ተብለው በሕጉ ፉት ይቆጠሩ የነበረው እኚሁ የሥር አንደኛ ተከሣሽ ናቸው። ከመዝገቡ ላይ የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ሁለ አመልካች የቅን ልቦና ተዋዋይ የነበረ መሆኑን የሚያመለክቱ ናቸው። ምንም እንኳን ለሥር አንደኛ ተከሣሽ የተደረገው የስጦታ ውል በመጨረሻ ፈራሽ ቢሆንም የስጦታውን ውል ተከትለው የተሰሩ ሥራዎች ቀሪ ማድረጉና ተዋዋዮቹን ወደነበሩበት ቦታ መመለሱ በቅን ልቦና የተዋዋለውን የአመልካችን መብት በእጅጉ የሚጎዲ በመሆኑ እነዚህ ሥራዎች እንዱረጉ ማድረጉ የተሻለና የሕግ መሰረትም ያለው ነው። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ከላይ የተመለከቱትን የሕግ ድንጋጌዎች በአግባቡ ሳያገናዝቡ የስጦታ ውለ ፈራሽ በመሆኑ ብቻ አመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች እንዱመልስ መወሰናቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 46947 በ25/ዐ2/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 34278 በዐ7/ዐ2/2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች ቤቱን ሉያስረክቡ አይገባም ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።