No summary available.
የሰ/መ/ ሀምላ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሕብረት ባንክ(አ.ማ) - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቢሲኒያ ባንክ (አ.ማ) - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሣሥ 11 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሀምላ 11 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካች በዚህ ክርክር ተሣታፉ ያልሆነው የጉለላ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዲደር ጽ/ቤት ተጠሪ አመልካች ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በአመልካችነት ቀርቦ ደምሴ ኢንቨስትመንት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተባለ የንግድ ድርጅት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በሥር አመልካች ከሆነው ከአቢሲኒያ ባንክ ገንዘብ ተበድሯል። ተበዲሪው የንግድ ድርጅት ለወሰደው ብድር በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞ ወረዲ 8 ቀበላ 05 የሚገኘውን ቁጥሩ 343 የሆነውን ቤትና ድርጅት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንደኛ ደረጃ መያዣነት፣ ለአቢሲኒያ ባንክ በሁለተኛ ደረጃ መያዣነት አስይዟል። ሆኖም የአቢሲኒያ ባንክ በሁለተኛ ደረጃ በንብረቱ ላይ ያለውን የመያዣ መብትና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3081 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገውን በመፃረር የጉለላ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዲደር ጽ/ቤት ንብረቱ የህብረት ባንክ አንደኛ ደረጃ እንደሆነ በማድረግ የመዘገበ ስለሆነ ይኸ ምዝገባ ተሰርዞ ንብረቱ የአቢሲኒያ ባንክ አንደኛ ደረጃ መያዣ ነው ተብል እንዱወሰንልኝ በማለት አመልክቷል።
በዚህ ክርክር ተሣታፉ ያልሆነው የጉለላ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዲደር ጽ/ቤት በተጠሪነት ቀርቦ ስማቸው ደምሴ ኢንቨስትመንት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የማይንቀሣቀሥ ንብረት የሕብረት ባንክ አንደኛ መያዣ መሆኑን የመዘገብኩት ሕብረት ባንክ የንግድ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰደውን ብድር በመክፈል የንብረቱን የባለቤትነት ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ በመረከብና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አስፈቅድ በመቅረቡ ነው። ስለዚህ የመያዣ ቀዲሚነት አስመልክቶ ለቀረበው ክርክር ሕብረት ባንክ (አ.ማ) ጣልቃገብቶ እንዱከራከር በማለት አመልክቷል። የሥር ፍርድ ቤት የሰበር አመልካች በጉዲዩ ጣልቃ ገብ ሆኖ በክርክሩ እንዱገባ ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች ለሥር ፍርድ ቤት ባቀረበው መልስ በንብረቱ ላይ የመያዣ ቀዲሚነት አለኝ። ምክንያቱም በባለዔዲው ጠያቂነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደሩትን ብድር በመክፈል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተይዘው የነበሩ ሰነድች ተቀብያለሁ። ስለሆነም በንብረቱ ላይ የአንደኛ ደረጃ መያዣ መብት ባለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተዲረኩ (የተተካሁ) በመሆኔ በንብረቱ ላይ አንደኛ ደረጃ መያዣ እንዲለኝ መመዝገቡ ትክክል ነው በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ አመልካች በመሆን ያቀረበውን አቤቱታና ማስረጃ በሥር ተጠሪ የሆነው የጉለላ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዲደር እና አመልካች በጣልቃ ግብ ተከራካሪነት ያቀረበውን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች በንብረቱ ላይ የአንደኛ ደረጃ መያዣ መብት ያለውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዔዲ በመክፈልና በማስፈቀድ በዲረጎት መብቱን ያረጋገጠ ስለሆነ በመያዣው ላይ የቀዲሚነት መብት አለው በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኝ አቅርቦ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጠሪንና የአመልካችን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመዲረግ ቀድሞውንም በንብረቱ ላይ የመያዣ መብት ያለው መሆን ይገባዋል። አመልካች ከዚህ በፉት በንብረቱ ላይ የመያዣ መብት የላለው በመሆኑ ባለዔዲው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለበትን ዔዲ የከፈለ ቢሆንም በመያዣው ላይ የቀዲሚነት መብት የለውም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚ ችልቱ ይግባኙን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ነሐሴ 2 ቀን 2000 ዓ.ም ባቀረበው የሰበር አቤቱታ አመልካች ስማቸው ደምሴ ኢንቨስትመንት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ህዲር 6 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለበትን የብድር ዔዲ 68.72 /አስራ አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ስልሣ ሁለት ሺ ሰባት መቶ ስልሣ ስምንት ብር ከሰባ ሁለት ሣንቲም/ በመክፈል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንድንተካ በጠየቀን መሰረት ክፍያውን በሲፒኦ ፈፅሟል ገንዘቡ ባለዔዲው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለበትን ዔዲ የተከፈለ መሆኑ በመያዥያውን ንብረት ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተረክቧል። አመልካች በመያዣው ላይ የቀዲሚነት መብት ያለውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዔዲ በመክፈል በመብቱ የተዲረገ ሆኖ እያለ በባለ ዔዲውና በአመልካች መካከል የተደረገው የብድር ውል ገንዘቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ዔዲ ለመክፈል የሚውል ስለመሆኑ አይገልፅም በሚል ምክንያት ብቻ የመዲረግና በመያዣው ላይ ያለውን የቀዲሚነት መብት የላቸውም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ፍትሐብሕር ሕጉ ስለመዲረግና ስለመተካት የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ አመልካች ለባለዔዲው ብድር የሰጠው ለሥራ ማስኬጃ ማከናወኛ እንጅ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዔዲ ለመክፈል አለመሆኑን በአመልካችና በተበዲሪው መካከል የተደረገው ውል ያሣያል። አመልካች የቆረጠው ሲፒኦ ገንዘቡ ለተበዲሪው እንጅ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባለዔውን ዔዲ የከፈለ መሆኑን የሚያሣይ ደረሰኝ አላቀረበም። አመልካች በባለዔዲው ፈቃድ ለመዲረግ የሚያስችለ እነዚህን መስፈርቶች ባላሟላበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ተዲርጌአለሁ በማለት የሚያቀርበው የህግ መሰረት የለውም። አመልካች በንብረቱ ላይ አንዲችም የመያዣ መብት ሣይኖረው በንብረቱ ላይ ሁለተኛ ደረጃ የመያዣ መብት ያለውን ተጠሪ በመቅደም በንብረቱ ላይ የመያዣ መብት አለኝ እያለ የሚያቀርበው ክርክርም የህግ መሰረት የለውም። ስለሆነም ከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት የህግ ትርጉም ምንም አይነት ስህተት የላለበት በመሆኑ የአመልካችን አቤቱታ በመሰረዝ እንዱያሰናብተኝ በማለት በፅሐፍ መልስ ሰጥቷል። አመልካች በበኩለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለባለዔዲው የሚፈልገውን ዔዲ በሙለ አጠቃልዬ የከፈልኩ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሰጥቶኛል። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባለዔዲውን ንብረት በቀዲሚነት በመያዣነት ሲይዝ የተረከባቸውን የንብረቱን ባለቤትነት የሚያረጋግጡ ሰነድች ለእኛ አስረክቦናል። እኛም በንብረቶች ላይ አንደኛ የመያዣ መብት ባለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመዲረግ መያዣውን አስመዝግበናል። ስለሆነም ከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር እንዱታረምልን በማለት በፅሐፍ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመዲረግ የባለዔዲውን ንብረቶች በመጀመሪያ ደረጃ መያዣነት የመያዝ መብት አለው ወይስ የለውም? የሚለው የጉዲዩ መሰረታዊ ጭብጥ ሆኖ አግኝተነዋል።
የመዲረግ መብት ምንጩና መሰረቱ የአበዲሪው ፈቃድ ወይም የተበዲሪው ፈቃድ ወይም ህግ ላሆን እንደሚችል ለመገንዘብ ይቻላል።
በአገራችንም የባለዔዲውን ዔዲ ለአበዲሪው የከፈለ ሶስተኛ ወገን በአበዲሪው መብት ለመዲረግ የሚቻልባቸው ሁኔታዎችና መዲረጉ ስለሚያስከትለው ውጤት ገዥነት ያላቸው ድንጋጌዎች ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1968 እስከ ፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1974 በዝርዝር ተደንግጓል። የፍትሐብሕር ህጉ የባለዔዲውን ዔዲ ለአበዲሪው የከፈለ ሶስተኛ ወገን በአበዲሪው ፈቃድ ስለሚዲረግበት ሁኔታ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1968፣ በተበዲሪው ፈቃድ ስለሚዲረግበት ሁኔታ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1969 እና በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1970 በህግ መዲረግ የሚቻልበትን ሁኔታ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1971 በዝርዝር ደንግጓል። የተበዲሪው ዔዲ ለአበዲሪው የከፈለ ሶስተኛ ወገን በአበዲሪው መብት ለመተካትና ለመዲረግ የሚቻለው ከሶስቱ የዲረጎት አይነቶች አንደኛው የተሟላ ሆኖ ሲገኝ እንደሆነና ሶስቱ የዲረጎት አይነቶች የሚጠይቁት መስፈርት የተለያየ መሆኑን ከላይ የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎች ይዘት በማየት ለመረዲት ይቻላል።
አመልካች ባለዔዲው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነበረበትን ዔዲ እንድንከፍልለት በፅሐፍ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ባለዔዲም ስማቸው ደምሴ ኢንቨስትመንት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚፈለግበትን 68.72 /አስራ አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ስልሣ ሁለት ሺ ሰባት መቶ ስልሣ ስምንት ብር ከሰባ ሁለት ሣንቲም/ በሲፒኦ የከፈለ መሆኑን ይህም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሰጠው ማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን በማንሣት ተከራክሯል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሰረት በመብቱ የተዲረገ መሆኑንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመብቱ ለመዲረግ የሚያስችለውን በመያዣነት የያዛቸውን የባለዔዲውን ንብረቶች የባለቤትነት ሰነድ አሳልፍ በመስጠት በንብረቶቹ ላይ ያለውን የቀዲሚነት የመያዣ መብት እንዱሰራበት እንዲደረገው በመግለፅ የተከራከረ መሆኑን ለበታች ፍርድ ቤቶች እና በሰበር ከተደረገው ክርክር ተገንዝበናል።
አመልካች በባለዔዲው ንብረቶች ላይ የቀዲሚ የመያዣ መብት ባለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምትክ የመዲረግ መብቴን አረጋግጫለሁ የሚለው በባለዔዲው በስማቸው ደምሴ ኢንቨስትመንት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፈቃድና ስምምነት መሰረት ሣይሆን በአበዲሪው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፍቃድና ስምምነት መሰረት መሆኑን በመግለፅ በየደረጃው ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤት ይህንን የአመልካች ክርክር በጭብጥነት በመያዝ ውሣኔ የሰጠ ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች የመዲረግ መብቴ ምንጭ ነው ብል ያልጠቀሰውን በተበዲሪው ፈቃድና ስምምነት ስለመዲረግ ፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1969 እና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1970 የተደነገጉት ሁኔታዎች አልተሟለም በማለት ውሣኔ መስጠታቸውን ለመገንዘብ ችለናል። ከዚህ አንፃር ስንመዝነው የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች በአበዲሪው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈቃድ የመዲረግ መብቴን አረጋግጫለሁ በማለት ያቀረበውን ክርክር በማለፍ አመልካች የመዲረግ መብቴ ምንጭና መሰረት ነው ብል ባልተከራከረበት በባለዔዲው ፈቃድ ስለመዲረግ የሚደነግጉትን የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1969 እና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1970 ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ መወሰናቸው ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
የመዲረጉ ሁኔታ እንዳት መፈፀም እንዲለበት የሚደነግገው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1968 ንዐስ አንቀፅ 2 የአማርኛው ቅጅም ሆነ የእንግሉዘኛው ቅጅ የባለዔዲውን ዔዲ የከፈለ ሶስተኛ ወገን አበዲሪውን በመዲረግ መብቱን እንዱሰራበት የተስማማ መሆኑን ግልፅ በሚያደርግ መንገድ ዲረጎቱ መፈፀም እንዲለበትና የመዲረግ ሁኔታው ክፍያው በተፈፀመበት ጊዜ መከናወን እንዲለበት የሚገልፁ ናቸው። እዚህ ላይ አበዲሪው የባለዔዲውን ዔዲ የከፈለ ሶስተኛ ወገን በእሱ መብት ተዲርጎ እንዱሰራበት መሥማማቱን በግልፅ ለማሣየት የሚቻለው እንዳት ነው? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ሉሰጠው ይገባል። የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1968 ንዐስ አንቀፅ 2 በመስፈርትነት ያስቀመጠው የተበዲሪውን ዔዲ የከፈለው ሶስተኛ ወገን በመብቱ ተዲርጎ እንዱሰራበት አበዲሪው የተስማማ መሆኑን ለባለዔዲው እና ለላልች ወገኖች በግልፅ በሚያሣይ ሁኔታ ፈቃደን መስጠቱን እንጅ አበዲሪው የባለዔዲውን ዔዲ የከፈለው ሶስተኛ ወገን እንዱዲረግ የተስማማ መሆኑን በሚገልፅ ልዩ ፍርማሉቲ ባለው ፅሐፍ ወይም ስለመዲረግ በተደረገ ውል የመግለፅ ግዳታ እንዲለበት የሚደነግግ ድንጋጌ አይደለም። ስለሆነም አመልካች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈቃድና ስምምነት ለመዲረግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመልካች በመብቱ እንዱዲረግ ፈቃድና ስምምነቱን የሰጠ መሆኑን በማያሻማ መንገድ ለማሣየት የሚችለ የፅሐፍ ማረጋገጫዎችን ወይም የተለያዩ ተግባራትን የፈፀመ መሆኑን ማስረዲት ይጠበቅበታል። ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለዔዲው የነበረበት ዔዲ በአመልካች የተከፈለው መሆኑን በመግለፅ የሰጠው ማስረጃና በመያዣነት ይዟቸው የነበሩ የባለዔዲውን ንብረቶች የባለቤትነት ሰነድ ለአመልካች አሳልፍ መስጠቱ አመልካች መያዣውን በእሱ እግር ተተክቶ (ተዲርጎ) በቀዲሚነት እንዱያስመዘግብ የተስማማ መሆኑን በግልፅ የሚያሣዩ ናቸው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመልካች የባለዔዲውን ዔዲ የከፈለ መሆኑን በማረጋገጥ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች የባለቤትነት ሰነድ ለአመልካች አሳልፍ መስጠቱ አበዲሪው ዔዲውን የከፈለው ሶስተኛ ወገን በመዲረግ መብቱ ሉሰራበት እንዱችል በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች የባለቤትነት ሰነድ እና ላልች ማስረጃዎች አሳልፍ የመስጠት ግዳታውን በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1974 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት የተወጣ መሆኑን የሚያረጋግጥ በቂ ማስረጃ ነው። ስለሆነም አመልካች የባለዔዲውን ዔዲ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመክፈል በአበዲሪው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈቃድና ስምምነት መሰረት በባለዔዲው ንብረቶቹ ላይ የቀዲሚ የመያዣ መብት ባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተዲርጓል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በተበዲሪው ፈቃድ ስለመዲረግ የሚደነግጉትንና ለጉዲዩ አግባብነት የላላቸው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1969 እና የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1970 የተደነገገው መሥፈርት አልተሟላም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት መሻሩና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የዚህ ድንጋጌ የእንግሉዘኛው ቅጅ “Any mortgage may pay a creditor having the priority with the consent of the creditor, or where the immovable attached on the cotter’s request with out such consent” የሚል ነው።ድንጋጌ በይዘቱ ሁለት ገዥ የሆኑ የተለያዩ ደንቦችን የያዘ ነው። የመጀመሪያው ድንጋጌው በመሰረታዊነት ባለዔዲው ንብረት በቀዲሚነት መያዣ ያደረገው አበዲሪ የባለዔዲውን ዔዲ የከፈለውን ሶስተኛ ወገን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1968 መሰረት የመዲረግ መብት ሙለ በሙለ የሚከላከል ወይም የሚገድብ አይደለም።
ተጠሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባለዔዲው የሚፈልገውን ገንዘብ በመክፈል በንብረቶቹ ላይ ቀዲሚ የመያዣ መብት ሉኖረው የሚችለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህንን ጥያቄውን ሲቀበለውና ሲፈቅድለት ነው። ስለሆነም ከባለዔዲው የሚፈልገውን ገንዘብ ከላላ ሶስተኛ ወገን በመቀበል ክፍያውን የፈፀመው ሶስተኛ ወገን አመልካች በመብቱ እንዱዲረግ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1968 የመፍቀድ ወይም በንብረቶቹ ላይ ሁለተኛ ደረጃ የመያዣ መብት ካለው ተጠሪ ያበደረውን ገንዘብ በመቀበል ተጠሪ በንብረቶቹ ላይ የቀዲሚ የመያዣ መብት እንዱኖረው የመስማማትና የመምረጫ መብቱ የተሰጠው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን ከፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3083 ንዐስ አንቀፅ 1 የመጀመሪያው ክፍል ገዥ ደንብ ለመረዲት ይቻላል።
ሁለተኛው ከእሱ የቀዲሚነት መብት ያለውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈቃድና ስምምነት ሣይጠይቅ ባለዔዲው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መክፈል የሚገባውን ገንዘብ በመክፈል ተጠሪ በንብረቶቹ ላይ ቀዲሚ የመያዣ መብት ሉኖረው የሚችለው ተጠሪ ንብረቶቹን በፍርድ ያሣገደ ስለመሆኑ ማስረጃ ሲያቀረብ ብቻ እንደሆነ ከፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3083 ንዐስ አንቀፅ 1 ሁለተኛው ክፍል ገዥ ደንብ ለመረዲት ይቻላል። ተጠሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀዲሚ መያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች በፍርድ ያሣገደ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላቀረበ መሆኑ ያለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈቃድና ስምምነት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመተካትና በመብቱ ተዲርጎ ሉሰራበት አይችልም። ስለሆነም ምርጫውን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሰጠውንና ፈቃጅ የሆነውን ፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3083 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ እንደ አስገዲጅ የህግ ድንጋጌ በመቁጠር ተጠሪ የቀዲሚነት መብት እንዱሰጠው የሚያቀርበው ክርክር የህግ መሰረትና ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ተጠሪ የባለዔዲውን ንብረት በቀዲሚ መያዣነት ለመያዝ በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈቃድና ስምምነት ማግኘት አለበት። በሁለተኛ ደረጃ ባለዔዲው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መክፈል የሚገባውን ዔዲ አጠቃልል የከፈለ መሆን እንደሚገባው ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3083 ንዐስ አንቀፅ 1 ይደነግጋል። ተጠሪ አመልካች ባለዔዲው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መክፈል የሚገባውን ገንዘብ ከመክፈለ በፉት የባለዔዲውን ዔዲ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃልል በመክፈል በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3083 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ለመዲረግ ያቀረበው ጥያቄ የለም። ተጠሪ የባለዔዲውን ዔዲ አጠቃልል በመክፈል መብቱ ለመዲረግ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥያቄ ሣያቀርብና ባለዔዲው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሉከፍል የሚገባውን ገንዘብ ሣይከፍል በባለዔዲው ንብረቶች ላይ ሁለተኛ ደረጃ የመያዣ መብት ስላለው ብቻ በንብረቶቹ ላይ ቀዲሚ የመያዣ መብት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3083 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ሉረጋገጥልኝ ይገባል በማለት የሚያቀርበው ክርክር የህጉን ድንጋጌ መሰረታዊ አቀራረፅ፣ ይዘት መንፈስና ዓላማ እና የድንጋጌውን ተፈፃሚነት ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ አመልካች በባለዔዲው ንብረቶች ላይ ቀዲሚ የመያዣ መብት ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባለዔዲው የሚጠይቀውን ገንዘብ አጠቃልል በመክፈል በባለገንዘቡ (አበዲሪው) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈቃድና ስምምነት መሰረት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1968 ድንጋጌዎች መሰረት ተዲርጓል። አመልካች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመተካት ንብረቶቹን በአንደኛ ደረጃ መያዣነት ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ የባለዔዲው ንብረት ሰነድችና ማስረጃዎች የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1974 ንዐስ አንቀፅ 1 በሚደነግገው መሰረት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመረከብ ንብረቶቹን በቀዲሚ መያዣነት አስመዝግቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ለጉዲዩ አግባብነትና ተፈፃሚነት የላላቸውን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1969 የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1970 እና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3083 ድንጋጌዎች በመጥቀስ አመልካች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የመዲረግ መብት የለውም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከመዝገብ የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 26 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
አመልካች የባለዔዲው የሰማቸው ደምሴ ኢንቨስትመንት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንደኛ ደረጃ መያዣነት አሲዟቸው በነበሩ ንብረቶች ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በመዲረግ ቀዲሚ የመያዣ መብት አለው ብለናል።
ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ድምፅ ተሰጠ።