No summary available.
ሐምል 2 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ባይሳ ሸኔ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ይህ ጉዲይ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን የክርክሩም አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ አንደኛ ተጠሪ ለንግድ ስራ ማከናወኛ ብር 421,612.80 (አራት መቶ ሃያ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አስራ ሁለት ብር ከሰማንያ ሣንቲም) በ24/4/83 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል ከአመልካች ላይ ተበድረው ገንዘቡን በውለ መሰረት ያልከፈለ ስለሆነ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቦ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ በ19/11/96 ዓ.ም በዋለው ችልት ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ተከሳሹ ለከሳሽ ሉከፍለ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላም አመልካች የፍርድ አፈጻጸም ማመልከቻ አቅርቦ ንብረትነቱ የፍርድ ባለእዲው የሆነውንና በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞ አጠራር በወረዲ 7 ቀበላ 17 ክልል የሚገኘው የቤት 020 የሆነው ቤት በሐራጅ ተሸጦ እዲው እንዱከፈል ጠይቆ አፈጻጸሙን የያዘው የፍደራል መ/ደ/ፍ/ቤት በፍርድ አፈጻጸም መምሪያ በኩል አፈጻጸም የተጠየቀበት ይሄው ቤት በሐራጅ እንዱሸጥና ፍርደ እንዱፈጸም ትእዛዝ ሰጥቶ በዚሁ መሰረት የፍርድ አፈጻጸም መምሪያ ቤቱን ለመሸጥ ሲንቀሳቀስ የአሁን ሁለተኛ ተጠሪ እንዱሸጥ የተባለው ቤት የፍርድ ባለእዲው ሳይሆን የእኔ ንብረት ስለሆነ አፈጻጸሙ በዚህ ቤት ላይ ሉቀጥል ስለማይችል በዚህ ረገድ የተሰጠው ትእዛዝ ይነሳልን በማለት አቤቱታ አቅርበው ፍ/ቤቱም ቤቱ በማን ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ የሚመለከተውን አካል ጠይቆ በአመልካቹ ስም በአሁን ሁለተኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚታወቅ ስለመሆኑ ሲገለጽለት በፍርድ አፈጻጸም እንዱሸጥ ትእዛዝ የተሰጠበት ቤት የፍርድ ባለእዲ ሳይሆን የአመልካች መሆኑ ስለተረጋገጠ አፈጻጸሙ ይቁም በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል።
የፍርድ ባለመብቱ የአሁን አመልካች በዚሁ ትእዛዝ ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን የአመልካችም የቅሬታ ነጥብ ተጠቃል ሲታይ አመልካች የብድሩ ገንዘብ እንዱከፈለው በአንደኛ ተጠሪ ላይ ክሱን ካቀረበ በኋላ አንደኛ ተጠሪ ይህንኑ የአፈጻጸም ክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት ከ2ኛ ተጠሪ ባገኙት ውክልና መሰረት ለባለቤታቸው ለወይዘሮ ፀሐይ ጉልማ ገዝተው ስም እንዱዞርም ለሚመለከተው አካል አመልክተው ውለ ከቤቱ ማኀደር ጋር ተያይዞ እንደሚገኝና እንዱታገድ ለፍ/ቤቱ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ፍ/ቤቱ አምኖበት ቤቱ ተከብሮ እንዱቆይ በ26/11/92 ዓ.ም ትእዛዝ ሰጥቶ ይሄው ትእዛዝ ለሚመለከታቸው ክፍልች ተላፍፎል። ፍ/ቤቱ ቤቱ እንዲይሸጥ እገዲ ከሰጠ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3041 መሰረት በፍርድ የተገኘ የመያዣ መብት (judicial mortgage) እንደተቋቋመና በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 መሰረትም እንደተመዘገበ ማረጋገጥ የሚቻል በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ክርክሩን ከእነዚህ ድንጋጌዎች አኳያ በመመልከት ሁለተኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ መብት እንደላላቸው ማረጋገጥ ሲገባቸው ቤቱ የሁለተኛ ተጠሪ ስለሆነ አፈጻጸሙ ሉቀጥል አይገባም በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ይህም ችልት የቀረበውን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ሁለተኛ ተጠሪ ይሄው ቤት እንዱሸጥ ውክልና ለአንደኛ ተጠሪ በሰጡበት ሁኔታ እንደዚሁም አንደኛ ተጠሪ ቤቱን ተረክበው እየኖሩ ባለበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤቶች ቤቱ ተመዝግቦ የሚገኘው በ2ኛ ተጠሪ ስም እንጂ በፍርድ ባለእዲው በአንደኛ ተጠሪ ስም ስላልሆነ አፈጻጸሙ ሉቀጥል አይገባም በማለት የሰጡት ውሳኔ ለሰበር ቀርቦ ሉመረመር እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
የተጠሪዎችም ክርክር ተጠቃል ሲታይ አንደኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በማን ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ የሚመለከተውን አካል ጠይቆ በሁለተኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ ተረጋግጦለታል። ይህም ሁኔታ ቤቱ በ26/11/92 ዓ.ም በፍ/ቤት ተሰጥቷል የተባለውን እግድ የሚያፈርስና እግድ እንደላለ የሚያስገነዝብ ነው። በአስተዲደር ክፍል የተሰጠ የባለሐብትነት የምስክር ወረቀት እስካልተሰረዘ ድረስ የባሐብትነት ማረጋገጫ እንደሆነ ይህ ሰበር ችልት በመ/ቁ. 14554 የሕግ ትርጉም የሰጠበት ሲሆን በተያዘውም ጉዲይ ካርታና ደብተሩ ተመዝግቦ የሚገኘው በሁለተኛ ተጠሪ ስም ስለሆነ የስር ፍ/ቤቶች አፈጻጸሙ በዚህ ቤት ላይ ሉቀጥል አይገባም በማለት የሰጡት ትእዛዝ የሰበር ችልቱ አስቀድሞ ከያዘው አቋም ጋር የተጣጣመ ነው።
No topics extracted.
ከዚህም ላላ አመልካች በቤቱ ላይ በፍርድ የተገኘ የመያዣ መብት አግኝቻለሁ የሚለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3041”ን” በመጥቀስ ነው። ሆኖም ቤቱ ቀድሞውንም ቢሆን በአንደኛ ተጠሪ ባለቤት በወ/ሮ ፀሐይ ጉልማ ስም ተመዝግቦ ይታወቅ የነበረ ባለመሆኑ ቤቱ ታግዶል ለማለት የማይቻል ከመሆኑም በላይ በፍርድ የሚሰጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የሚቋቋመው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3044 መሰረት ሲሆን ይህ የመያዣ መብትም የሚቋቋመው ፍ/ቤቶች በዲኝነት በሚሰጡት ፍርድ እንጂ በእግድ ሰበብ ሉቋቋም አይችልም።
ስለሆነም የበታት ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸሙ በሁለተኛ ተጠሪ ቤት ላይ ሉቀጥል አይችልም በማለት የሰጡት ትእዛዝ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ የሰበር አቤቱታው ከኪሳራ ጋር ሉሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ሁለተኛ ተጠሪም በይዘቱ ከአንደኛ ተጠሪ ጋር ተመሳሳይ የሆነ መልስ አቅርበዋል። በዚህም ምክንያት ዝርዝሩን መመዝገቡ ባለማስፈለጉ ታልፎል።
በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዲዩ ጭብጥ አመልካች የጀመረው አፈጻጸም በወረዲ 7 ቀበላ 17 ክልል ቁጥሩ 020 በሆነው ቤት ላይ ሉቀጥል ይገባል ወይንስ አይገባም? የሚለው ነው። ይህንኑ ጭብጥ ይዘን ጉዲዩን መርምረናል። እንደመረመርነውም የአሁን አመልካች በብድር የተወሰደ ገንዘብ እንዱከፈለው በክናፍ የቆዲ ውጤቶች አምራችና ላኪ ድርጅት እንደዚሁም በአሁን አንደኛ ተጠሪ በአቶ ክንዳ አፍራሶ ላይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክሱን ካቀረበ በኋላ የአንደኛ ተጠሪ ባለቤት በሆኑት በወ/ሮ ፀሐይ ጉልማ ስም የተመዘገበው በወረዲ 7 ቀበላ 17 ክልል የሚገኘው የቤ.ቁ. 020 የሆነው ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 154 መሰረት እንዱከበርለት አቤቱታ አቅርቦ ፍ/ቤቱም የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ የተጠቀሰው ቤት ጉዲዩ እልባት ከማግኘቱ በፉት ቢሸጥ ወይም ለላላ ሦስተኛ ወገን ቢተላለፍ ከሳሽ ወደፉት በፍርደ ተጠቃሚ ቢሆን ፍርደን የሚያስፈጸምበት ንብረት በማጣት ሉተካ የማይችል ጉዲት ሉደርስበት እንደሚችል ያቀረበው ቃለመሐላ ተቀባይነት አለው በማለት በትእዛዙ ላይ ካሰፈረ በኋላ የተጠቀሰው ቤት በግለሰቧ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ከሆነ ተለዋጭ ትእዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ እንዲይሸጥ እንዲይለወጥ በማናቸው ወገን ለሦስተኛ ወገን ሳይተላለፍ ተከብሮ ይቆይ በማለት ሐምል 26 ቀን 1992 ዓ.ም የእግድ ትእዛዝ መስጠቱን ከመዝገቡ ተረድተናል።
ከዚህ በኋላም ቤቱን ከሁለተኛ ተጠሪ ገዝተዋል የተባለት የአንደኛ ተጠሪ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ፀሐይ ጉልማ በዚህ ቤት ላይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 154”ን” በሚጻረር ሁኔታ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 158 መሰረት እንዱነሳልኝና ስለመነሳቱም አስቀድሞ የእግደ ትእዛዝ ተላልፍላቸው ለነበሩት አካላት ይተላለፍልኝ ሲለ ጥር 18 ቀን 1993 ዓ.ም አቤቱታ አቅርበው ፍ/ቤቱም አቤቱታውን መርምሮ የእግደ ትእዛዝ የተሰጠው ቤቱ የክርክሩ ምክንያት ነው ተብል ሳይሆን ለፍርድ ማስፈጸሚያነት በሚል ስለሆነ አስቀድሞ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ሉነሳ አይገባም በማለት አቤቱታውን ሳይቀበለው መቅረቱንም ከመዝገቡ ተረድተናል።
በልላ በኩልም የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት አፈጻጸሙ በዚህ ቤት ላይ ሉቀጥል አይገባም የሚል መቃወሚያ በሁለተኛ ተጠሪ አማካይነት ሲቀርብለት የቤቱ ባለቤት በማን ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ የሚመለከተው አካል እንዱያረጋግጥ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ባለሐብትነቱ በሁለተኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ የሚመለከተው አካል የገለጹለት ቢሆንም ባለሃብትነት ከሕግ ወይም ከውል የሚመነጭ እንደመሆኑ መጠን በ6/4/84 ዓ.ም በተደረገ ውል የአንደኛ ተጠሪ ባለቤት ወ/ሮ ፀሐይ ጉልማ ይህንኑ ቤት ከሁለተኛ ተጠሪ የገዙ እንደመሆኑ መጠን ባለሐብትነታቸው በውል እንደተቋቋመ መገንዘብ ስለሚቻል የባለቤትነት ስሙ ወደ ገዢ ሳይዛወር በሻጭ ስም ተመዝግቦ መገኘቱ ይህ የሂደት ጉዲይ እንጂ የወለን አመሰራረት ጥያቄ ውስጥ የሚከተው አይሆንም። ሐምል 26 ቀን 1992 ዓ.ም ፍ/ቤቱ የሰጠው የእግድ ትእዛዝም የሚመለከተው አካል ተቀብል ተግባራዊ ያደረገው በዚሁ የሽያጭ ውል መሰረት ቤቱ ከሁለተኛ ተጠሪ ወደ ወ/ሮ ፀሐይ ጉልማ መተላለፈን በማረጋገጡ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ ወ/ሮ ፀሐይ ጉልማ እግደ እንዱነሳ ማመልከት ባላስፈለጋቸው ነበር። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3041 ላይ እንደተደነገገው መያዣ ከውል ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ከሕግ ወይንም ደግሞ በፍርድ ሉቋቋም ይችላል። በዚህም ጉዲይ ፍ/ቤቱ በዚህ ቤት ላይ የሰጠው የእግድ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3044 ላይ እንደተመለከተው ለአመልካች ከፍርድ የመነጨ የመያዣ መብትን (judicial mortgage) ያጏናጽፊል። ይህ ሰበር ችልትም በመ/ቁ. 25863 በሰጠው የሕግ ትርጉም በፍ/ቤት በንብረት ላይ የሚሰጥ የእግዲ ትእዛዝ ከፍርድ የመነጨ የመያዣ መብት ተቋቁሟል ለማለት እደሚያበቃ በመጥቀስ ውሳኔ ሰጥቷል።
ስለሆነም ተጠሪዎች የቤቱ ባለሐብት ሁለተኛ ተጠሪ ስለሆኑ በዚህ ንብረት ላይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተፈፃሚ አልሆነም በማለት ያነሱት ክርክር ተገቢነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩልም የሽያጭ ውለ በሕግ አግባብነት ያልተደረገ ስለሆነ የሽያጭ ውል አለ ለማለት አይቻልም በማለት ተጠሪዎች ያነሱትን ክርክር በተመለከተም ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን ለመሸጥ የሚያበቃ ውክልና መስጠታቸውን አልካደም።
አንደኛ ተጠሪ የሽያጩን ውል ያደረጉት የሿሚውን ጥቅም በሚጏዲና የጥቅም ግጭት (conflict of interest) ባለበት ሁኔታ ነው ወይንም ደግሞ ውለን ያደረጉት ከእራሳቸው ጋር ነው የሚለ ከሆነ አግባብነት ያላቸውን የውክልና ድንጋጌዎችን በመጥቀስ ውለ እንዱፈርስ መጠየቅ ይገባቸው ነበር። ነገር ግን በዚህ መልኩ የውል ይፍረስልኝ ክስ ያላቀረቡ ሲሆን ይልቁንም በቤቱ ላይ የእግድ ትእዛዝ ሲሰጥ እግደ እንዱነሳ አቤቱታ ያቀረቡት ሁለተኛ ተጠሪ ሳይሆኑ ወ/ሮ ፀሐይ ጉልማ መሆናቸው ሲታይ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን በሽያጭ ማስተላለፊቸውን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው።
የቤት ሽያጭ ውለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723/1/ ላይ እንደተመለከተው ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፉት ያልተደረገ ስለሆነ ውጤት የላለው ነው በማለት ተጠሪዎች ያቀረቡት ክርክን በተመለከተ ይህ ጉዲይ በጭብጥነት ተይዞ ላታይ ይችል የነበረው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1808/2/ ላይ እንደተመለከተው በተዋዋይ ወገኖች ወይንም ጥቅም ባላቸው ሦስተኛ ወገኖች የውል ይፍረስልኝ ክስ በቀረበ ጊዜ ነው። ነገር ግን በዚህ መልኩ የቀረበ አቤቱታ ስለላለ የሚስተናገድ አይሆንም።
ሲጠቃለልም ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ባለሐብትነቱ በሽያጭ ውለ መሰረት የአንደኛ ተጠሪ ባለቤት ለሆኑት ወ/ሮ ፀሐይ ጉልማ የተላለፈ ስለሆነና በዚህ የሽያጭ ውልም ላይ ተመስርቶ አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3041 እና 3044 መሰረት ከፍርድ የመነጨ የመያዣ መብት ያለው ሆኖ ሳለ የስር ፍ/ቤቶች የቤቱ ባለሐብትነት በሁለተኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ የሚመለከተው አካል ያረጋገጠ ስለሆነ አፈጻጸሙ በዚህ ቤት ላይ ሉቀጥል አይችልም ሲለ የደረሱበት ድምዲሜ የሽያጩን ውለንም ሆነ ሕጉን ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
59710 በ9/8/2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በአዱስ አበባ ከተማ በወረዲ 7 ቀበላ 17 ክልል የሚገኘውና ቁጥር 020 የሆነው ቤት ለአንደኛ ተጠሪ ባለቤት ለወ/ሮ ፀሐይ ጉልማ በሽያጭ በመተላለፈ ምክንያት አመልካች በቤቱ ላይ ከፍርድ የመነጨ የመያዣ መብት ያቋቋመ ስለሆነ አፈጻጸሙ በዚሁ ቤት ላይ እንዱቀጥል ብለናል።
አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው ብር 1000(አንድ ሺህ ብር) በድምሩ ብር 2000(ሁለት ሺህ) ወጭና ኪሣራ ለአመልካች እንዱከፍለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘገቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።