No summary available.
ሐምል ዐ7 ቀን 2ዐዐ1 ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ኒያላ ኢንሹራንስ አ/ማ - ጠ/ ተካ አስፊው ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በሥር ፍ/ቤት ከሣሽ የነበሩት የአሁኖቹ ተጠሪዎች ናቸው። በክሣቸውም ንብረታቸው የሆነ ህንፃ በረቂቅ የሽያጭ ውል መሰረት አመልካች ስለያዘው እንዱያስረክባቸው እና አላግባብ ለተጠቀመበትም ኪራይ እንዱከፍላቸው ጠይቀዋል።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ውለ በውልና ምዝገባ ጽ/ቤት ያልተደረገው በተጠሪዎች ክፈ ልቦና መሆኑን፣ ንብረቱን ፈቅደው ለአመልካች ማስረከባቸው ውለም ረቂቅ ሣይሆን ያለቀ መሆኑን ኪራይም ሉከፈላችው እንደማይገባ ተከራክሯል።
በበኩለም ቤቱን ገዝቶ የያዘው በመሆኑ ስም እንዱይዛወርለት ይህ ካልሆነ ለህንፃው መግዣ የከፈለው ብር 6,5ዐዐ,ዐዐዐ (ስድስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ) እንዱመለስለት የተከሣሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የሺያጭ ውለ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ወይም በዲኛ ፉት ባለመደረጉ በህግ ፉት አይፀናም በማለት ውለ ፈርሶ አመልካች ህንፃውን ለተጠሪዎች እንዱያስረክቡና ተጠሪዎች የተቀበለት ብር 6, 5ዐዐ,ዐዐዐ ለአመልካች እንዱመልሱ በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ይግባኙ ተቀባይነት አላገኘም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው።
የአመልካች አቤቱታም ለሰበር ችልት ያስቀርባል በመባለ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት ካላችው የህጉ ድንጋጌዎች አንፃር ተመልክቶታል።
ከፍ ሲል እንደተገለፀው የተጠሪዎች ክስ የመሰረቱት አመልካች በረቂቅ የሺያጭ ውል የያዘውን ህንፃ ያስረክበን በሚል ነው ከተጠሪዎች ክስም ሆነ ከክርክሩ ሂደት በአመልካችና በተጠሪ መሐከል የህንፃ ሽያጭ ውል የተደረገ መሆኑ፣ በዚህ ውል መሰረት ተጠሪዎች ህንፃውን ለአመልካች ማስረከባችውና የሺያጩ ገንዘብ ብር 6,5ዐዐ,ዐዐዐ መቀበላቸው አከራካሪ ያልሆኑ ነገሮች ናችው፤ ተጠሪዎች ለመክሰስ ምክንያት የሆናችው ይህ የሺያጭ ውል ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ወይም በዲኛ ፉት ያልተደረገ መሆኑ ነው። በመሆኑም ይህ ችልት ይህ የሺያጭ ውል ፈርሶ አመልካች ህንፃውን ለጠሪዎች ሉያስረክብና ተጠሪዎችም የሺያጩን ገንዘብ ለአመልካች ሉመልሱ ይገባል ወይ? የሚለውን ጭብጥ መስርቷል።
ከክርክሩ ሂደት እንደተገነዘብነው ግራ ቀኙ የህንፃ የሺያጭ ውል ማድረጋቸውን እንዲልተካካደ ሁለ ውለ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ወይም በፍ/ቤት ያልተደረገ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። የማይንቀሣቀስ ንብረትን የባለቤትነት መብት ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል ሁለ በፁሁፍና በሚገባ አኳኋን በፍ/ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ፉት መሆን እንዲለበት የፍ/ብ/ህ/ቁ 1723(1) ያመለክታል። ይህን የአፃፃፍ ሥርዓት መከተል ውለ በህግ ፉት የፀና እንዱሆን ከሚያስፈልጉ መስፈርቶች አንደኛው ነው። ስለሆነም በህግ ፉት ውጤት እንዱኖረው የማይንቀሣቀስ ንብረት ሺያጭ በህጉ የተመለከተውን የአፃፃፍ ሥርዓት ሉከተል ይገባል። ይህን ስርዓት ካልተከተለ ውጤቱ ምን ላሆን እንደሚችል በፍ/ብ/ህ/ቁ 18ዐ8(2) ተገልጿል። ውለ በህግ የተመለከተውን የአፃፃፍ ሥርዓት ካልጠበቀ ከተዋዋዩቹ አንደ ወይም ማንኛውም ጥቅም ያለው ሰው ውለ እንዱሰረዝ ሉጠይቅ ይችላል። በዚህም መሰረት ውለ እንዱፈርስ ሉወሰን ይችላል። የውለም መፍረስ ውጤቱ በተቻለ መጠን ውለታ ከመደረጉ በፉት ወደነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ ማድረግ ነው። (በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1815(1)) ተዋዋዩቹ ወደነበሩበት እንዱመለሱ ሲወሰን ውለታውን ለመፈፀም የተሰራ ሥራ ሁለ ቀሪ እና ውጤት የላለው እንደሚሆን የተጠቀሰው አንቀፅ ንዐስ ቁጥር 2 ይገልፃል።
በመርህ ደረጃ ከፍ ብለው የተጠቀሱት ጉድለቶች ሲያጋጥሙ ውለ ፈርሶ ተዋዋዮች ወደነበሩበት ቦታ የሚመለሱ ቢሆንም የፍትሐብሕር ሕጉ አንቀፅ 1817 ጉድለት ኖሮም ቢሆን ውለ የሚረጋበት ሁኔታ ሉኖር እንደሚችል ይደነግጋል። ይኸው የፍትሐብሕር ሕጉ አንቀፅ 1817(1) “ውለታውን ለመፈፀም የተሰራውን ሥራ ለማፍረስ የማይቻል ሲሆን ወይም አስቸጋሪ ሆኖ ሉገኝ ወይም ከፍ ያለ መሰናክል የሚያመጣ ሲሆን እነዚህ የተሰሩት ሥራዎች እንደረጉ እንዱቀሩ ይደረጋል” በማለት ይደነግጋል። የዚሁ ድንጋጌ የእንግሉዘኛው ትርጉም “Acts done in performance of the contract shall not be invalidated where such invalidation is not possible or would involve serious disadvantages or inconvenience” ይላል። ከሕጉ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ውለታውና (contract) ውለን ለመፈፀም የተሰሩ ስራዎች (acts) የሚለያዩ መሆናቸው ነው። ስለሆነም ውለ በራሱ በአንድ በኩል፣ ውለን ለመፈፀም የተከናወኑ ተግባራትን በልላ በኩል ለይቶ ማየት አስፈላጊ ነው። ተዋዋዮች በፈቃድ ጉድለት፣ በችልታ ማጣት ወይም በህግ የተመለከተውን የአፃፃፍ ሥርዓት ባለመከተል የውል ስምምነት አድርገው ላሆን ይችላል። ይህንንም ጉድለት ያለበትን ውል ለመፈፀም የተለያዩ ተግባራትን ፈፅመውም ላሆን ይችላል። ነገር ግን ውለ የማይፀናበትን ምክንያት በመግለፅ ውል እንዱፈርስ ሲጠየቅ ውለ ፈርሶ ግራ ቀኙ ወደነበሩበት ሉመለሱ የሚገባ ቢሆንም ይህ ጉድለት ያለበትን ውል ለመፈፀም የተከናወኑትን ተግባራት (acts) ማፍረስ ፈፀሞ የማይቻል ወይም ከፍ ያለ መሰናክል ወይም አስቸጋሪ የሚሆንበት አጋጣሚ ይኖራል። ይህ በሆነ ጊዜ ደግሞ ከፍ ሲል እንደተገለፀው ዳኞች ሉወስኑ የሚገባው ግራ ቀኙ ወደነበሩበት እንዱመለሱ ሣይሆን የተሰሩት ሥራዎች እንደረጉ እንዱቆዩ ነው። ምናልባት ወደነበሩበት መመለስ ባለመቻለ የደረሰ ጉዲት ካለ ጉዲቱን በካሣ መልክ ወይም ፍ/ቤቱ ተገቢ ነው የሚለውን መፍትሕ በመስጠት ሉስተካከል ይችላል (የፍ/ብ/ህ/ቁ/1817(2))። በመሆኑም ውለ የሚፈርስበት ወይም የሚሰረዝበት ምክንያት ሲከሰት ውለ ፈርሶ ግራቀኙ ወደነበሩበት የመመለስ ውሣኔ ላሰጥ የሚገባው ውለን ለመፈፀም የተሰራው ሥራ ቀሪ ለማድረግ የሚቻል ከሆነ ብቻ ነው።
በዚህ መሰረት የቀረበልንን ጉዲይ ተመልክተናል። አመልካች በ1994 ዓ.ም 6,500,000(ስድስት ነጥብ አምስት ሚሉዮን) ሚሉዮን ብር በመክፈል ከመልስ ሰጪ ሕንፃ መረከቡ ተረጋግጦአል። ህንፃውን ከተረከቡ በኋላ የኢንሹራንስ ሥራ ለማካሄድ እንዱያስችለው ህንፃው ላይ የተለየዩ ማስተካከያዎች የተደረጉበት ስለመሆኑም ለመገንዘብ ችለናል።
በሰበር ችልት ባለጉዲዮች የቃል ክርክር ባደረጉበት ወቅት አመልካች ለመኪና ማቆምያ አገልግልት የሚውል ላላ ተጨማሪ ቦታ ገዝቶ የጨመረበት መሆኑንም ለማወቅ ችለናል። ከዚህ አንፃር ይህ ችልት በሙለ አመሰራረት ሂደት የነበረውን ጉድለት መሰረት በማድረግ ተዋዋዮቹ ወደነበሩበት እንዱመለሱ ማድረግ ተገቢ መሆን አለመሆኑን አገናዝቧል።
አሁን በቀረበልን ጉዲይ ተዋዋይ ወገኖችን ወደነበሩበት ሁኔታ መመለስ ማለት አመልካች የከፈለውን ብር 6,500,000(ስድስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ) እንዱቀበል በማድረግ መልስ ሰጪዎች ደግሞ ቤቱን እንዱረከቡ ማድረግ ማለት ነው። ክፍያውን የመፈፀምም ሆነ ቤቱን የመረከብ ሥራ በፍትሐብሕር ሕጉ አንቀፅ 1815(2) መሰረት ውለታው ለመፈፀም የተሰሩ ሥራዎች (acts) በመሆናቸው በመርህ ደረጃ ውለ ሲፈርስ አብረው ዋጋ የሚያጡ ናቸው። ሆኖም አሁን በቀረበልን ጉዲይ እነዚህን ሥራዎች (acts) ዋጋ እንዱያጡ ማድረግ አስቸጋሪና ከፍ ያለ መሰናክል የሚያመጣ ሆኖ (involving serious disadvantage and inconvenience) አግኝተነዋል። በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ችልት ዔምነት የሽያጭ ዋጋውን በመመለስና ቤቱን በመረከብ ተዋዋዮቹን ወደነበሩበት ቦታ መመለስ የሚቻል አይደለም። ገንዘቡ ከተከፈለበት ከ1994 ዓ.ም ወዱህ በመንግስትም ዔውቅና ያገኘ የገንዘብ ግሽበት (inflation) ያለ በመሆኑ የተከፈለው ገንዘብ አሁን ከሚመለሰው ገንዘብ ጋር ተመጣጣኝ ነው ልባል አይችልም። በልላ በኩል የሚመለሰው ቤት ደግሞ በአንፃራዊነት የዋጋ ጭማሪ እንደሚያሳይ ይገመታል። ይህ ግምት እንኳን ቢታለፍ ቤቱን ገዝቻለሁ በሚል ዔምነት አመልካች በህንፃው ላይ ለያዘው ንግድ የሚመች ለማድረግ የተለያዩ ወጪዎችን አውጥቶበታል። በመሆኑም አሁን ያለው ህንፃ መጀመሪያ ከተረከበው ህንፃ ጋር አንድ ዓይነት ነው ልባል የሚችል አይደለም። በመሆኑም በዋጋ ግሽበት ምክንያት የሚረከበው ገንዘብ እሴት (value) በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ከሚያስረክበው ህንፃ ዋጋ በተለያዩ ምክንያቶች መጨመር ጋር ተዲምሮ ወደነበሩበት የመመለሱ ሥራ ለመልስ ሰጪ ያልተገባ ጥቅም የሚሰጥና አመልካችን የሚጏዲ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ኩባንያ ህንፃውን ለንግድ የሚጠቀምበት መሆኑ ህንፃው ከሚገኝበት ቦታ ጋር የተያያዘ መልካም ስም (good will) እንዱያጣ ስለሚያደርገው የጉዲቱም መጠን በዚያው መጠን መጨመሩ የሚቀር አይሆንም። በክርክሩ ሂደት አመልካች ቤቱን ገዝቻለሁ በሚል ዔምነት ተጨማሪ ለመኪኖች የሚሆን ቦታ ገዝቶ እየተጠቀሙበት መሆኑ ሲታከልበት ደግሞ ወደነበሩበት የመመለስ (reinstatement) አማራጭ በፍትሃብሕር ሕጉ አንቀፅ 1817 እንደተገለፀው ከሞላ ጏደል የማይቻል ያደርገዋል።
በመሆኑም ግራ ቀኙ ያላቸው የሽያጭ ውል በረቂቅ ደረጃ ያለ ነው የሚለው የመልስ ሰጪ ክርክርም ሆነ የሥር ፍ/ቤቶች ድምዲሜ በመሰረቱ ትክክል ቢሆንም በዚህ ረቂቅ ውል መነሻነት የተፈፀሙ ላልች ድርጊቶችን ወደኋላ ተመልሶ እንዲልነበሩ መቁጠር ግን ከላይ በዘረዘርነው ምክንያት ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ፍርድ ቤቶች ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ወደነበሩበት ይመለሱ ብለው ከመፍረዲቸው በፉት በሕጉ እንደሰፈረው የውለ መፍረስ ወይም መሰረዝ ብቻ ሳይሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዘው የተፈፀሙ ላልች ሥራዎች (acts) እንዲልተሰሩ የመቁጠር ውጤት ሉመዝኑ ይገባል አሁን በያዝነው ጉዲይ ክሱ የቀረበለት ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍ/ቤት ክርክርሩን ከዚህ አቅጣጫ ተመልከተው አግባብነት ያለውን የሕግ ድንጋጌ ተፈፃሚ አላደረጉም። ስለዚህ በግራ ቀኙ የተከናወኑትን ድርጊቶች ከግምት ሣያስገቡ የሥር ፍ/ቤቶች የሽያጭ ውለ የአፃፃፍ ሥርዓትን ባለመከተለ ብቻ ውለ ፈራሽ ሆኖ ግራ ቀኙ ወደነበሩበት ይመለስ በማለት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ21/6/2000 የሰጠው ውሣኔ እና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በ3/11/2000 የሰጠው ትዕዛዝ ተሽረዋል።
የሽያጭ ውለ የአፃፃፍ ሥርዓትን ያልተከተለ ቢሆንም ውለ ፈርሶ ግራ ቀኙ ወደነበሩበት እንዱመለሱ ማድረጉ አስቸጋሪና ከፍ ያለ መሰናክል የሚያመጣ በመሆኑ ውለ ባለበት ሁኔታ እንዱቆይ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1817(1) መሰረት ወስነናል። በመሆኑም የተጠሪዎች ክስ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.