No summary available.
ሰኔ 02 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ማህደር አእምሮ - ጠ/ይሁን ፀሐይ ቀረቡ ተጠሪ፡- ላእከ ገ/መድህን- ጠ/ሙለጌታ ገብሩ ቀረቡ
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ክስ አመልካች ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ) ተበድረው በተዋዋለት ቀን ያልከፈለዋቸው በመሆኑ ዋናውን ገንዘብ፣ወለድ እና የገደብ መቀጫ እንዱከፍሎቸው ጠይቀዋል።
አመልካች በሰጡት መልስ ገንዘቡን መበደራቸውን አምነው ነገር ግን ጥር 14/1997 ዓ.ም መክፈላቸውንና በዋስትና ያስያዙትን መቆፈሪያ ማሸንና ቼክ ተጠሪ ያስረከቧቸው መሆኑን ገልፀው ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ የገንዘብ ሰነድ ለባለእዲው መመለሱ እዲው እንደተከፈለ ያስቆጥራል፤ መቆፈሪያ ማሽኑም ገንዘቡ በመከፈለ ተመልሷል በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር የማስረጃና የሕግ ድጋፍ አለው በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጏታል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የብድር መመለስን ማስረዲት የሚቻለው በፍ/ቤት በሚሰጥ የእምነት ቃለ መሐላ ወይም በጽሁፍ ብቻ ነው፤
አመልካች ደግሞ ብድሩ ስለመመለሱ ከነዚህ በአንደም አላስረደም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሮ አመልካች ዋናውን ገንዘብ ወለደንና የገደብ መቀጫ እንዱከፍለ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር ተሰኝተው ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል ሰርዞታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ በዚህ ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለተፈፀመ ይታረምልኝ በማለት የቀረበ ነው። የአመልካች ዋነኛ ቅሬታም ለብድሩ በዋስትና የተያዘው ቼክ እና የመቆፈሪያ ማሽን መመለሱ የብድሩ ገንዘብ መመለሱን ያረጋግጣለ፤ የስር ፍ/ቤቱ ውሣኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2020 እና 2845 “ን” ያላገናዘበ ነው የሚል ነው።
የሰበር ችልቱም የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም የአመልካችን አቤቱታ የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔና አግባብነት ካላቸው የሕጉ ድንጋጌዎች ጋር መርምሯል።
በዚህ መዝገብ አከራካሪ የሆነው ለብድሩ በዋስትና የተሰጡት ቼክና መቆፈሪያ ማሽን ለተበዲሪው መመለሳቸው ብድሩ ስለመከፈለ ያረጋግጣለ ወይ? የሚለው ነጥብ ነው።
ተጠሪ ለአመልካች ብር 120,000(መቶ ሃያ ሺህ) ያበደሯቸው እና ገንዘቡን ግን አመልካች ያልከፈለ መሆኑን በመግለጽ ክስ የመሰረቱ ሲሆን አመልካችም ብድሩን መውሰዲቸውን ሣይክደ ነገር ግን ገንዘቡን የከፈለ መሆኑን ገልፀው ተከራክረዋል። አመልካች መበደራቸውን ያልካደና ከፍያለሁ የሚለ ስለሆነ ገንዘቡ ስለመከፈለ በቅድሚያ የማስረዲት ሸክም አለባቸው። አመልካች ብድሩን ለመክፈላቸው ያቀረቡት ቀጥተኛ ማስረጃ የለም። የሚከራከሩት ለብድሩ በዋስትና ያስያዙት ቼክና መቆፈሪያ ማሽን ለእርሣቸው መመለሱ ብድሩ እንደተከፈለ የሚያስቆጥረው ነው በማለት ነው። በልላ አነጋገር ቼኩና ማሽኑ ለባለእዲው መመለሱ ገንዘቡ እንደተከፈለ የሕሉና ግምት እንዱወሰድላቸው ነው የሚጠይቁት።
የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረገው ከ500 ብር በላይ የሆነን የብድር ውል እንዱሁም ይህንኑ የገንዘብ መጠን የመመለስ ነገር ማስረዲት የሚቻለው በጽሁፍ ወይም ፍ/ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም በቃለ መሐላ ብቻ ነው በማለት ነው።
በእርግጥ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2472 ስር ይኸው በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የተገለፀው ነገር ተመልክቷል። ይሁን እንጂ በአንዲንድ ሁኔታዎች ሕጉ አንድ ፍሬ ነገር ከተረጋገጠ ማስረጃ ያልቀረበበት ላላ አዱስ ነገር እንደተረጋገጠ ግምት እንዱወሰድበት የሚያዝበት አጋጣሚ አለ። በመሆኑም በህሉና ግምት መርህ (principle) የግምቱ ተጠቃሚ የሆነው ተከራካሪ ወገን የመጀመሪያውን ፍሬ ነገር ካረጋገጠ ላላኛውን ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብ ሣያስፈልግ ፍ/ቤቱ ይኸው አዱስ ነገር እንደተረጋገጠ ግምት ሉወስድ ይገባል ማለት ነው። ከነዚህ የሕሉና ግምት ሉወሰድባቸው እንደሚገባ ሕጉ ከሚያስቀምጣቸው አንደ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2020 ስር የተመለከተው ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ሰነድ ለባለእዲው መመለሱ እዲው እንደተከፈለ የሚያስቆጥር መሆኑ ተመልክቷል። ይህም የሆነበት ምክንያት ባለገንዘቡ እዲውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እዲው ካልተከፈለው በቀር ለባለእዲው አይመልስም ተብል ስለሚገመት ነው።
No topics extracted.
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ለወሰደት ብድር ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ) የያዘ ቼክ መስጠታቸው አላከራከረም። በተጨማሪም ይህንኑ ለዋስትና የተሰጠውን ቼክ ተጠሪ ለአመልካች የመለሱላቸው መሆኑን በስር ፍ/ቤት በምስክሮች ተረጋግጧል። ቼኩ ለተጠሪው የተሰጠው እዲ መኖሩን በማረጋገጥ ለእዲው አከፊፈል ዋስትና እንዱሆን ነው።
በመሆኑም ተጠሪ እዲ ካልተከፈላቸው ቼኩን ባንክ ወስደው በመመንዘር ለእዲው መክፈያ ከማዋል ፊንታ እዲው ሣይከፈላቸው ለአመልካች የሚመልሱበት ምክንያት አይኖርም። ቼኩን ለተጠሪ ከመለሱ ደግሞ እዲው እንደተከፈለ እንደሚቆጠር ሕጉ ያመለክታል። በመሆኑም ለአመልካች ቼኩ መመለሱ የብድሩ ገንዘብ እንደተከፈለ የሕሉና ግምት ሉወሰድበት የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል አመልካች ለብድሩ በመያዣ የሰጡት የመቆፈሪያ ማሽንም ቢሆን ለአመልካች መመለሱ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተረጋግጧል። በእርግጥ በክርክሩ ሂደት ማሽኑ በባንክ በመያዣ መያዙን ተመልክተናል። ነገር ግን በባንክ በመያዣ መያዙ ብቻ ሣይሆን ተጠሪ በፈቃዲቸው ማሽኑን ለአመልካች መመለሣቸው በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጧል።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2846 መያዣ የተቀበለ ባለገንዘብ ሉከፈለው የሚገባው በሙለ እስኪከፈለው ድረስ የመያዣውን እቃ በእጁ የማቆየት መብት ያለው መሆኑ ተመልክቷል። ተጠሪ ሉከፈላቸው የሚገባው እዲ በሙለ ተከፍል ካላለቀ መያዣውን ለአመልካች የሚመልሱበት ምክንያት አይኖርም። ለእዲው አከፊፈል በመያዣ የተሰጣቸውን ንብረት ዔዲው ሳይከፈላቸው ለባለዔዲው ይመልሣለ ብል መገመትም ያስቸግራል። በተቃራኒው መያዣውን የተቀበለ ባለገንዘብ ለእቃ አስያዡ ዔቃውን የሚመልሰው ገንዘቡ ሲከፈለው ወይም በልላ ምክንያት የመያዣው ውል ሲያልቅ መሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2845/1/ ስር ተመልክቷል። ተጠሪም በዋስትና የያዙትን ማሽን ለባለገንዘቡ መመለሣቸው አመልካች ያለባቸውን ገንዘብ በመክፈላቸው መሆኑን ችልቱ ተገንዝቧል።
በአጠቃላይ ከላይ የተመለከቱትን የሕጉን ድንጋጌዎች ሣያገናዝብ ብድሩ ስለመከፈለ በጽሁፍ ወይም በፍ/ቤት በተሰጠ እምነት ቃል ወይም በቃለ-መሐላ ያልተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች የብድሩን ገንዘብ ከወለድና መቀጫ ጋር ይክፈለ በማለት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 58565 በ06/09/2000 የሰጠው ውሣኔ እና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 39461 በ04/02/2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሽረዋል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 30571 በ20/10/99 የሰጠው ውሣኔ ጸንቷል።
አመልካች ክስ የቀረበበትን የብድር ገንዘብ ሉከፍለ አይገባም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።