No summary available.
መጋቢት 3 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካ ች፡- 1. አቶ ወልደፃድቅ ብርሃኑ - ቀረቡ 2. ወ/ሮ ፈንታነሽ ኃይለ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ስንታየሁ አያላው - ጠበቃ አቶ ሙለጌታ ገብሩ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር፣ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር ዐ3131 ሐምል 27 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ብይንና የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 1ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ሰኔ 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
የክርክሩ መሰረታዊ ጉዲይ አመልካ ች በሥር ፍርድ ቤት በከሣሽነት ቀርበው በሥር ተከሣሽ የሆነው ተጠሪ፣ በአዱስ አበባ ከተማ በወረዲ 11 ቀበላ 19 የቤት ቁጥር 671 የሆነውን የመኖሪያ ቤት ሐምል 5 ቀን 1992 ዓ.ም ሸጠውልናል። ቤቱንና ቤቱ የሚመለከቱ ሰነድችና ማስረጃዎችም አስረክበውናል።
ሆኖም ተከሣሽ /ተጠሪ/ ከቀድሞው የቤቱ ባለንብረቶች መስከረም 21 ቀን 1986 ዓ.ም ባደረገው የግዥ ውል መሰረት ስመንብረቱን ወደራሱ በማዛወር ካርታውን ለማስረከብ የተስማማ ቢሆንም ቤቱን በሸጡለት እነ አቶ መስፍን አሰፊ ስም የወጣ የሆነ ካርታ ከተረከቡ በኋላ ካርታውን ለእኛ ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ካርታውን እንዱያስረክቡና ስመንብረቱን እንዱያዛወሩ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። ተጠሪም በተከሣሽነት ቀርበው ቤቱ በሸጡልኝ ግለሰብ ስም ያለ በመሆኑ የሽያጭ ውለ የማይረጋ ነው። ከሣሾች /አመልካ ች/ ሚያዚያ 3ዐ ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ እድፈጽምላቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥተውኛል። ስለሆነም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እንደውለ ለመፈፀም ፈቃደኛ አለመሆኑን ያወቁ ስለሆነ ክሱን ያቀረቡት ማስጠንቀቂያ ከሰጡኝ ከአንድ ዓመት ከስምንት ወር በኋላ ስለሆነ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት ክሣቸው በይርጋ ይታገዲል በማለት የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በአማራጭ ላልች መከራከሪያዎችን አቅርበዋል። የተጠሪ ሚስት ወ/ሮ ስንታየሁ ሽፈራው በበኩላቸው በጣልቃ ገብነት በክርክሩ ለመግባት ያመለከቱ ሲሆን የበኩላቸውን ክርክር አቅርበዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪና በጉዲዩ ጣልቃ ለመግባት ባለመለከቱት ወ/ሮ ስንታየሁ ሽፈራው ወደ ቀረቡት ዝርዝር ክርክር ከመግባቱ በፉት የከሣሾች /አመልካ ች/ ክስ በይርጋ ይቋረጣል ወይስ አይቋረጥም?
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ በአመል ችና በተጠሪ መካከል በውልና ማስረጃ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል የተደረገው መስከረም 21 ቀን 1992 ዓ.ም መሆኑን ገለፆና አመልካ ች ለተከሣሹ ማስጠንቀቂያ ከሰጡበት ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ ስለሆነ ይኸም ክሱ የቀረበው አመልካ ች ማስጠንቀቂያ ከሰጡበት ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ ስለሆነ ክሱ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት በይርጋ ይቋረጣል በማለት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 245/2/ መሰረት መዝገቡን ዘግቶታል።
አመልካ ች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔን አጽንቷል። አመልካ ች ተጠሪ ውለን ለመፈፀም ፈቃደኛ ነኝ ካርታና þላኑን አስጨርሸ አስረክባለሁ በማለት ጥር 1ዐ ቀን 1993 ዓ.ም በጽሐፍ መተማመኛ የሰጠ ከመሆኑም በላይ ማስጠንቀቂያ ከፃፍንለትም በኋላ በውለ መሰረት ግዳታውን ለመፈፀም ፈቃደኛ መሆኑንና þሮሰሱን እያስጨረሰ መሆኑን እያነጋገረን ነበር።
በመጨረሻ ሚስቱ ቤቴን በላለሁበት ነው የገዛችሁት ብላ በነገረችን በሶስተኛ ቀን ክስ መሥርተናል። የሥር ፍርድ ቤቶች ውለ የሚፈፀምበት የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠለት ጅምር ቤቱን ተረክበን አሰርተን ያጠናቀቅንና ሰርቪስ ቤቶችም ያሰራን መሆኑንና ተጠሪ ውለን ለመፈፀም ፈቃደኛ መሆኑን ሲገልፅልን የቆየ መሆኑን ከግምት ውስጥ ሣያስገቡ፣ ለፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892/3/ የተሣሣተ ትርጉም በመስጠት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩለ አመልካ ች በውለ መሰረት እንዱፈፀምላቸው ማስጠንቀቂያ ከሰጡበት ከሚያዚያ 3ዐ ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ እንደማልፈጽምላቸው የሚያውቁ መሆኑን ባቀረቡት ክስ ገልፀዋል። አመልካ ች በሥር ያላነሱትን ውለ እንደማይፈፀም የነገረችን ሚስቱ ናት በማለት ያቀረቡት ክርክር በሕጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ክሱን ያላቀረቡ በመሆናቸው ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት በጽሐፍ መልስ ሰጥቷል። አመልካ ች በሰበር አቤቱታ ያቀረቡትን ክርክር በማጠናከር በጽሐፍ የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡ ከዚህ በተጨማሪ አመልካ ችና የተጠሪ ጠበቃ የካቲት 19 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በቃል ክርክር አድርገዋል።
የክርክሩ አመጣጥ የክርክሩ መሰረታዊ ጉዲይና አመልካ ች እና ተጠሪ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የሥር ፍርድ ቤቶች የአመልካ ች ክስና ጥያቄ በአንድ ዓመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 በመጥቀስ የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ ለተያዘው ጭብጥ እልባት ለመስጠት የማይንቀሣቀስ ንብረት የገዛ ሰው ሻጭ በውለ መሰረት እንዱፈፀምለት ሰለሚጠይቅበት ሁኔታና ጥያቄውን ስለሚያቀርብበት የጊዜ ገደብ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን፣ መመልከት ያስፈልጋል። አመልካ ች ተጠሪ ሐምል 5 ቀን 1992 ዓ.ም በገባው የቤት ሽያጭ ውል መሰረት ለመፈፀም ፈቃደኛ ባለመሆኑ በፍርድ ተገድድ እንዱፈፀምልን በማለት ያቀረቡት ክስ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1776 እና 2892 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት የቀረበ ነው።
አመልካች በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1776 እና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 1 እና 2 ድንጋጌዎች መሰረት ያቀረቡት የቤት ሽያጭ ውል ይፈጽምልኝ ክስ በሕግ የተደነገገው የይርጋ ሕግ የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመወሰን በመጀመሪያ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ እንደዚሁም ድንጋጌው ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2875 መሰረታዊ መርህና ስለ ሽያጭ እና ጠቅላላ ውል ከተደነገጉ ድንጋጌዎች ጋር ሉኖረው የሚገባውን ተፈፃሚነት መመርመር ያስፈልጋል።
1.የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2893 ንዐስ አንቀጽ 3 "ስለሆነም ሻጭ ውለን እንደውለ ቃል ለመፈፀም መዘግየቱን ከተረዲበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውለ እንዱፈፀምለት ካልጠየቀ በቀር ገዢው ውለ በግዳታ እንዱፈፀም የማድረግ መብቱን ያጣል" በማለት ይደነግጋል። እዚህ ላይ በአማርኛው "መዘግየቱን ከተረዲበት" በሚለው ቃልና በእንግሉዘኛው "ascertained" በሚለው ቃል መካከል ልዩነት ያለመሆኑን ለመገንዘብ እንችላለን። የድንጋጌው መንፈስ ገዥ በአንድ ዓመት ውስጥ ውለ እንዱፈፀምለት ለፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ያለበት ሻጭ በሽያጭ ውለ መሰረት ለመፈፀም ፈቃደኛ አለመሆኑን ካረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ የእንግሉዘኛውን የቃል አጠቃቀም በማየት ለመረዲት ይቻላል።
እዚህ ላይ የሚነሣው ጥያቄ ሻጭ በሽያጭ ውለ መሰረት ለመፈፀም እንደማይፈልግ ገዥ ያረጋገጠ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ ያለበት ማን ነው? የሚለው ነው። ለዚህ መሰረታዊ ነጥብ እልባት ለመስጠት ስለውል እና ተዋዋይ ወገኖች በፍትሐብሕር ሕጉ የተቀመጠ የሕግ ግምቶችን ማየት አስፈላጊ ነው።
በሕግ አግባብ የተቋቋሙ ውልች ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ሕግ ናቸው በማለት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1731 ንዐስ አንቀጽ 1 የደነገገ ሲሆን ውልች በተዋዋይ ወገኖች መካከል ሉኖር የሚገባውን የቅንነት የመተማመን ግንኙነት መሰረት በማድረግ በቅን ልቦና ሉተረጎሙ እንደሚገባ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1732 ይደነግጋል። ከዚህ አንፃር ስናየው ተዋዋይ ወገኖች በተዋዋለት የውል ቃል መሰረት ውለን የመፈፀም ፍላጎትና ቅን ልቦና ያላቸው መሆኑ የውል ሕግ ግምት የሚወስድበት ጉዲይ በመሆኑ ገዥ ሻጭ በሽያጭ ውለ በገባው የውል ቃል መሰረት እንደሚፈጽም የተለያዩ የተስፊ ቃልችን ሲሰጠው የቆየ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ የለበትም።
በተቃራኒው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌን ጠቅሶ የሚከራከር ሻጭ ከገዥ ጋር ባደረገው የቤት ሽያጭ ውል መሰረት ለመፈፀም ፍላጎት የላለው መሆኑን ገዥ በማያሻማ ሁኔታ እንዱያውቅ እና እንዱረዲው ያደረገ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ አለበት። ሻጭ በውለ መሰረት ለመፈፀም እንደማይፈልግ በእርግጠኝነት ገዥ እንዱያውቅ ካደረገው ከአንድ ዓመት በኋላ የሽያጭ ውለ በፍርድ ኃይል እንዱፈፀምለት የጠየቀ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ አለበት። ስለሆነም የማይንቀሣቀስ ንብረት የሸጠ ሰው ሻጭ የሽያጭ ውለ መሰረት የቤቱን ይዞታና የባለቤትነት ሰነድች ለገዥ ያላስረከበ ከሆነ ውለን ለመፈፀም ፈቃደኛ አለመሆኑንና በጽሐፍና በማያሻማ ሁኔታ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1789 ንዐስ አንቀጽ 3 በሚደነግገው አይነት ለገዠ ካሣወቀው ከአንድ ዓመት በኋላ የውል ይፈፀምልኝ ክስ ያቀረበ መሆኑን ማስረዲት ይጠበቅበታል።
ሻጭ በውለ መሰረት የቤቱን ይዞታ ለገዥ አስተላልፍ ከሆነ ገዥ ሻጭ በውለ መሰረት ይፈጽማል የሚለውን ዔምነት የሚያጠናክርና ውለም በከፉል መፈፀም መጀመሩን የሚያሣይ መሆኑን ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2875 እና ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2274 ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል። ሰለሆነም ሻጭ የቤቱን ባለሀብትነት ለገዥ ለማስተላለፍ እንደማይፈልግና የቤቱን ይዞታ ሻጭ በመልቀቅ እንዱያስረክበው የከፈለውንም ገንዘብ ገዥ እንዱወስድ በማያሻማ ሁኔታ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1789 ንዐስ አንቀጽ 3 በሚደነግገው አይነት ለገዥ ያሣወቀ መሆኑን ማስረዲት ይጠበቅበታል።
ሻጭ የቤቱን ሰነድች ለገዥ አስተላልፍ የቤቱን ይዞታ ይዞ በሚገኝበት ጊዜ የቤቱን ሰነድች ሻጭ እንዱመልስለት የከፈለውን ገንዘብ እንዱወስድ በማያሻማ ሁኔታና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1789 ንዐስ አንቀጽ 3 በሚደነግገው አይነት ለገዥ ያሣወቀ መሆኑን ማስረዲት የሚጠበቅበት ሲሆን ከላይ ከተጠቀሱት ሁኔታዎች በአማራጭ ሻጭ ውለ እንዱፈርስለት ወይም እንዱሰርዝለት በፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ በውለ መሰረት የመፈፀም ፍላጎት የላለው መሆኑን ገዥ እንዱረዲው ከተደረገ ከአንድ ዓመት በኋላ የውል ይፈፀምልኝ ክስ ገዥ ያቀረበ መሆኑን ወይም በሕግ እውቅና ላለው የሽምግልና ተቋም ሻጭና ገዥ በነበራቸው ድርድር ሻጭ ውለን ለመፈፀም እንደማይፈልግ ገዢ እንዱረዲው ከተደረገ ከአንድ ዓመት በኋላ ክሱን ያቀረበው መሆኑን የማስረዲት ግዳታ አለበት። በአጠቃላይ ሻጭ በገባው የሽያጭ ውል ቃል መሰረት ለመፈፀም ፍላጎት የላለው መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ለገዥ ካሣወቀውና ገዥም ይህንኑ ከተረዲና ካረጋገጠ ከአንድ ዓመት በኋላ የውል ይፈፀምልኝ ክስ ገዥ ያቀረበ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ አለበት።
ሻጭ በውለ መሰረት ለመፈፀም የማይፈልግ መሆኑን ገዥ ያረጋገጠ መሆኑን ገዥ ውለ እንዱፈፀምለት ማስጠንቀቂያ መስጠቱንና ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ ሻጭ በውለ መሰረት አለመፈፀሙን በማየት ብቻ ለማረጋገጥ አይችልም። ሻጭ ገዥ ማስጠንቀቂያ ከሰጠው በኋላም ቢሆን የተለያዩ ችግሮችን እያነሣ በመካከላቸው ያለውን የመተማመንና የቅን ልቦና ግንኙነት ተጠቅሞ ከአንድ ዓመት በላይ ውለን ሣይፈፀም የሚቆይበት አጋጣሚ ያለ ሲሆን በዚህ ጉዲይም ተጠሪ በሽያጭ ውለ መሰረት ለመፈፀም የተለያየ þሮሰስ እየፈፀመ መሆኑን ለአመልካ ች በመግለጽ አመልካ ች ክስ ከማቅረብ እንደዘገዩ ያደረጋቸው መሆኑን በማንሣት አመልካ ች ተከራክረዋል። ስለዚህ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 ይርጋ ተፈፃሚነት የሚኖረው ገዥ ለሻጭ ማስጠንቀቂያ የሰጠበትን ቀን መነሻ በማድረግና ጊዜውን በማስላት ሣይሆን ሻጭ በውለ መሰረት የመፈፀም ፍላጎት የላለው መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ገዥ እንዱያውቀው ያደረገበትን ቀን መነሻ በማድረግ መሆን ይገባዋል። ከዚህ አንፃር ስናየው የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካ ች በውለ መሰረት እንዱፈፀምላቸው ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ የሰጡበትን ቀን መነሻ ጊዜውን አስልቶ የአመልካ ች ክስ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በሁለተኛ ደረጃ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚነት የሚኖረው በሻጭና በገዥ መካከል የተደረገው ውል የማይፈፀምበት የመጨረሻ ቀን በጥብቅ የተወሰነ ከሆነ በውለ የተወሰነው ነው የጊዜ ገደብ ካለፈ ከአንድ ዓመት በኋላ ገዥ የውል ይፈፀምልኝ ክስ ማቅረቡን በማስረዲት እንደሆነ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2875 መሰረታዊ መርህና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌዎች ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2331 ንዐስ አንቀጽ 1 እና 2 ድንጋጌዎች ጋር አጣምሮ በማየት ለመረዲት ይቻላል። ከዚህም አንፃር ስናየው በአመልካ ችና በተጠሪ መካከል የተደረገው ውል፤ ውለ የሚፈፀምበትን ጭብጥ የጊዜ ገደብ የማያስቀምጥ በመሆኑ በጉዲዩ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2875፣ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 እና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2331 ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት የላቸውም።
በሶስተኛ ደረጃ የሚነሣው ጥያቄ በዚህ ጉዲይ ተጠቃሽና ተፈፃሚ መሆን ያለበት የይርጋ ሕግ ድንጋጌ የትኛው ነው? የሚለው ነው። ሻጭ በውለ መሰረት የመፈፀም ፍላጎት የላለው መሆኑን ለገዥ በማያሻማ ሁኔታ ያሣወቀ መሆኑን ባላስረዲበት ሁኔታ ወይም የሽያጭ ውለ ውለ የሚፈፀምበትን ጥብቅ የጊዜ ገደብ ባልተገለፀበት ሁኔታ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ አንቀጽ 3 የተደነገገው የአንድ ዓመት የይርጋ የጊዜ ገደብ ተፈፃሚነት የለውም።
በልዩ የሕግ ድንጋጌ የተቀመጠዉ የይርጋ ጊዜ ገደብ ተፈፃሚነት በማይኖረው ጊዜ ወይም በልዩ ሁኔታ የተደነገገ የይርጋ የጊዜ ገደብ ከላለ ውል ይፈፀምልኝ በሚል መነሻ የሚቀርቡ ክርክሮች ላይ ተፈፃሚነት ያለው የይርጋ ሕግ ድንጋጌ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1845 እንደሆነ የዚህን ድንጋጌ ይዘት በመመርመር ለመረዲት ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ከአመልካ ች ውለን ለመፈፀም ፍላጎት የላለው መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ካሣወቀችው ከአንድ ዓመት በኋላ ክሱን ያቀረቡ ስለመሆኑ አላስረዲም። ስለሆነም በዚህ ጉዲይ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2892 ንዐስ 3 ተፈፃሚነት የለውም።
የሥር ፍርድ ቤቶች ከላይ በዝርዝር ያስቀመጥናቸውን ምክንያቶችና የሕግ ድንጋጌዎች ሣያገናዝቡ የአመልካ ች ጥያቄ በአንድ ዓመት ይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
አመልካች ያቀረቡት የውል ይፈፀምልኝ ክስ በይርጋ የማይታገድ በመሆኑ አመልካችና ተጠሪ ላልች ተከራካሪዎች የሚያቀርቡትን ክርክር በመመርመርና በመመዘን ጉዲዩን ውሣኔ እንዱሰጥበት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341/1/ መሰረት መልሰን ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መልሰን ልከንለታል።
የአመልካ ች ክስ በይርጋ አይታገድም ብለናል።
በሥር ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭ ግራ ቀኙ ለየራሣቸው ይቻለ ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት መጋቢት 3 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.