No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሸንቁጤ ተ/ማርያም - ቀርበዋል ተጠሪ፡- አቶ ገብሬ ጎንጤ - ቀርበዋል ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል።
ይህ አቤቱታ የቀረበው አመልካች ሐምል 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 6833፣ሰኔ 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ፍርድ የሰሜን ሸዋ መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 17ዐ74፣ ግንቦት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ ተቀብል ማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለቱ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚሁ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች ከሣሽ፣ የአሁኑ ተጠሪ ደግሞ ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። ክርክሩ የተጀመረው ስር ከሣሹ ህዲር 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡትን ክስ መሰረት በማድረግ ሲሆን አጭር ይዘቱ ደግሞ ወኪል አድራጊዬን በመወከል ሐምል 1ዐ ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ ውል በወኪል አድራጊዬ ተመዝግቦ የሚታወቀውን የሰላዲ ቁጥር 3- ዐ81ዐ6 ኦሮ የሻንሲ ፣ የሞተር ቁጥሩ OME ዐ3 - 41-3000-056326 የሆነ ጣሉያን ሰራሽ ፉያት መኪና ለተከሣሹ በብር 5ዐ,ዐዐዐ /ሃምሣ ሺህ ብር/ ሸጨላቸው ከዚህ ገንዘብ ብር 19,ዐዐዐ /አስራ ዘጠኝ ሺህብር ከፍለውኝ እኔም መኪናውን ህዲር ዐ9 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ መረካከቢያ አስረክቤአቸዋለሁ፤ ይሁን እንጂ ቀሪውን ብር 31,ዐዐዐ /ሰላሣ አንድ ሺህ ብር/ ከፍለው መኪናው በስማቸው እንዱያዞሩ ተከሣሹን ብጠይቃቸው ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የተጠቀሰው ቀሪው ገንዘብ በመክፈል መኪናውን በስማቸው ተገድደው እንዱያዞሩ ይደረግልኝ፤ በተጨማሪም ታህሣሥ 18 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ የብድር ውል ብር 1474 /አንድ ሺህ አራት መቶ ሰባ አራት ብር/ ተከሣሹ ተበድረው የወሰደ ሲሆን ይህንን ብድር እንዱመልሱልኝ እንዱሁም ወለድና ወጪና ኪሣራ አክለው እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ተከሣሹም በሰጡት መልስ ሐምል 1ዐ ቀን 1998 ዓ.ም ባደረግነው የመኪና ሽያጭ ውል ውስጥ መኪናው የካምቢዮን ጥርስ ችግር ስላለው ከሣሹ ወደፉት እስከ ህዲር 3ዐ ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ ይህንን ጉድለት እንዱስተካከል አድርገው በስሜ እንዱዛወር የማድረግ ግዳታ ገብተው ሲያበቁ ይህንን ግዳታቸው ባልተወጡበት ሁኔታ ያቀረቡት የመኪናው ሽያጭ ቀሪ ገንዘብ ይስጡኝ ጥያቄ ተገቢነት የለውም፤ እንዱሁም ከመኪናው ሽያጭ ውል ጋር ምንም አይነት ዝምድና የላለው የብር 1474 /አንድ ሺህ አራት መቶ ሰባ አራት ብር/ ብድር አጣምረው መክሰሣቸው ተገቢነት የለውም፤
ከፈለጉ ራሱን በቻለ ክስ መጠየቅ ይችላለ እንጂ ከመኪና ሽያጩ ጋር አያይዘው ክስ ሉያቀርቡ አይችለም ብለዋል።
የሥር ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አግባብነት አላቸው ካላቸው ህጎች ጋር በማገናዘብ በመ/ቁ. 17ዐ74 ግንቦት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ፍርድ የሰጠ ሲሆን፣ የፍርደ ይዘትም ግራ ቀኙ ወገኖች ባደረጉት የመኪናው ሽያጭ ውል መኪናው የካምቢዮ ጥርስ ችግር ያለበትና ይህንን ጉድለት ከሣሹ እስከ ህዲር 3ዐ ቀን 1999 ዓ.ም ለማስተካከል ግዳታ የገቡ ስለሆነ ይህንን ግዳታቸውን ባልተወጡበት ሁኔታ የመኪናው ሽያጭ ቀሪ ገንዘብ ይከፈለኝ ጥያቄ ማንሣታቸው ተቀባይነት የለውም፤ ከብር 19,ዐዐዐ /አስራ ዘጠኝ ሺህ ብር/ በተጨማሪ ከሣሹ ብር 1ዐ,416 / አስር ስሺህ አራት መቶ አስራ ስድስት ብር/ ከተከሣሹ መቀበላቸው በተከሣሹ የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ስለሚያሣይና በከሣሹም ያልተካደ በመሆኑ ከሣሹ ከተከሣሹ ላይ የሚቀራቸው ገንዘብ ብር 31,000 /ሰላሣ አንድ ሺህ ብር/ ሣይሆን ብር 2ዐ,584 /ሃያ ሺህ አምስት መቶሰማኒያ አራት ብር/ እንደሆነና ተከሣሹ በቀሪው ያልከፈለት ገንዘብ መኪናው እንዱታደስና ቀሪ ገንዘብ የመኪናውን ጉድለት ለማሣደስ የማይበቃ ከሆነ በደረሰኝ መሰረት ለሚረጋገጥ ተጨማሪ የማሣደሻ ወጪ ከሣሹ እንዱከፍለና መኪናውን አሟልተው ለከሣሹ እንዱያስረክቡ፤ ከሣሹና ተከሣሹ ሐምል 1ዐ ቀን 1999 ዓ.ም ያደረጉት የመኪናው ርክክብ ውል በሚመለከተው አካል ፉት ቀርቦ የተመዘገበ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤ ከሣሹ ከመኪናው ሽያጭ ውል አለመፈፀም ጋር አያይዘው ያቀረቡት የብር 1474 /አንድ ሺህ አራት መቶ ሰባ አራት ብር/ ጥያቄ ራሱን የቻለ ክስ አቅርበው መጠየቅ እንጂ ተጣምሮ መቅረቡ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
ከላይ የሰፈረውን የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ በመቃወም ስር ከሣሹ ወደ አማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ በፍ/ይ/መ/ቁ. 6833/ሰኔ 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል።
No topics extracted.
አመልካቹም በሥር ፍርድ ቤቶቹ የተሰጠውን ፍርድ በመቃወም ሐምል 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ወደዚህ ሰበር ችልት ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም ስር ተከሣሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በውለ መሰረት መኪናው እንደተረከቡ የሚገልጽ ሰነድ ፈርመውና ይህ ሰነድም ለስር ፍ/ቤት ቀርቦለት እያለ ስሙን እንዲዞርላቸው እና ቀሪውን ገንዘብ እንዱከፍለኝ ጥያቄ አቅርቤ እያለሁ መኪናው አሟልተህ ለተጠሪው አስረክብ ብል ፍርድ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው፤ ተጠሪው መኪናው ተረክበው ሲያበቁ በመኪናው ለሚደርስ ጉዲት ሻጭ አሰራ መባላ ተገቢ አይደለም፤ ፍ/ቤት ተዋዋይ ወገኖች በውላችን ካስቀመጥነው ግዳታ ውስጥ ላላ አዱስ ግዳታ ሉፈጥር አይችልም፤
ተጠሪው በመረጡት ጋራጅ መኪናውን ስላሣደስኩላቸው የከፈልኩትን ብር 1ዐ,416 /አስር ሺህ አራት መቶ አስራ ስድስት ብር/ የመለሱልኝን ገንዘብ የስር ፍ/ቤቱ ይህ ገንዘብ ለመኪናው ሽያጭ ተብል እንደተቀበልኩ በማድረግ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው የሚል ነው።
ተጠሪም የካቲት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም አመልካቹ ለተጠቀሰው መኪና ሽያጭ ተብል /ሃያ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ አስራ ስድስት ብር/ ከእኔ ወስዶል፤ አመልካቹ የሸጠልኝ መኪና ጉድለት የነበረበትና በእዲ የተያዘ ነው፤መኪናው ቀደም ብል በልላ ምክንያት ለነበረው ዔዲ መክፈያ እንዱሆን የሐራጅ ሽያጭ ወጥቶበት ይገኛል፤ አመልካቹ በውላችን መሰረት የነበረበትን ግዳታ ሣይወጣ መኪናው ተጠሪው ተረክቧልና እዲ የለብኝም በማለት ያቀረበው አቤቱታ ተገቢነት የለውም፣ መኪናው እንዱያሣድስልኝ አመልካችን አልወከልኩትም፣ ስለሆነም እኔ ለአመልካች የሰጠሁት ብር 1ዐ416 /አስር ሺህ አራት መቶ አስራ ስድስት ብር/ ለመኪናው ዋጋ ተብል የተሰጠው ተጨማሪ ክፍያ እንጂ ለመኪና ማሣደሻ አይደለም፤ ስለሆነም አመልካቹ የወሰደውን ጠቅላላ ገንዘቤ /ሃያ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ አስራ ስድስት ብር/ ከሕጋዊ ወለደ ጋር ደምሮ ሉመልስልኝ ይገባል የሚል ነው።
ይህ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጥ ከላይ እየተዘረዘረ በመጣው መልኩ በመገንዘብ፣ 1/ አመልካቹ በመኪና ሽያጭ ውለ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዳታ ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም?
2/ አመልካቹ በስር ፍ/ቤት የመሰረቱት ክስ ተጠሪው የመኪና ሽያጭ ቀሪ ገንዘቤ ይክፈለኝና መኪናው በስሙ ይዛወርለት የሚል ሆኖ እያለ በፍርደ የተመለከቱትን ላልች ግዳታዎች በአመልካቹ ላይ ሉፈረደ ይገባል ወይስ አይገባም? በልላ አገላለጽ የፍርደ ገደብ እስከየት ድረስ ላሆን ይገባል?
የሚለትን መሰረታዊ ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ መንፈስ መረዲት የሚቻለው አመልካቹ የሚለት ከተጠሪው ጋር ባደረጉት የመኪና ሽያጭ ውል መሰረት ከእርሣቸው የሚጠበቅ ማንኛውም አይነት ግዳታ እንደተወጡና መኪናውም ለተጠሪው እንዲስረከቡ በመግለጽ ቀሪ ገንዘባቸውን ተጠሪው ከፍለው መኪናዋ በገዢው ስም እንድትተላለፍ ነው፤ የስር ፍርድ ቤቶቹም አመልካቹ ቀሪ ገንዘብ እንዱከፈላቸው ከመጠየቃቸው በፉት ሉወጡት የሚገባ መኪናውን የማስጠገን ግዳታ አለባቸው ማለታቸው አመልካቹ ፍ/ቤቱ የፈጠረባቸው አዱስ ግዳታ አድርገው ያስቀምጡታል። ተጠሪው ደግሞ አመልካቹ የሸጡላቸው መኪና ችግር ያለበት እንደሆነና በውላቸውም መሰረት መኪናውን የማስጠገን ወይም የጎደለውን የማሟላት ግዳታ አለባቸው የሚል ነው። ግራ ቀኙ ወገኖች ሐምል 1ዐ ቀን 1998 ዓ.ም አደረጉት በተባለው የመኪና ሽያጭ ውል ውስጥ የአመልካቹ ግዳታ ሆኖ መስፈሩን የስር ፍርድ ቤቱ በውሣኔው የገለፀው መኪናው የካምቢዮ ብልሽት እንዲለውና ይህንን የማሰራት ወይም የመተካት ግዳታ እንዲለባቸው ነው። የመኪናው ካቢዮን አሰርተው መኪናው ለተጠሪው ስለማስረክባቸው የሚገልጽ ማስረጃ አመልካቹ አላቀረቡም። ተጠሪው መኪናው ተረክበው በእጃቸው አስገብተዋልና የመኪናው ጉድለት አርሜ መኪናው ማስተላለፋ ያሣያል የሚለው የአመልካቹ ክርክር ሲታይም ምንም እንኳ የስር ፍ/ቤቱ ሐምል 1ዐ ቀን 1999 ዓ.ም የተደረገው የመኪናው ማረካከቢያ ውል በሚመለከተው አካል ፉት ቀርቦ የተመዘገበ አይደለም በማለት ውጤት እንደላለው አስመስል መወሰኑ ተገቢነት ባይኖረውም በዚህ ሰነድም ቢሆን መኪናው የካምቢዮን ችግር እንዲለበት የተቀመጠ በመሆኑ አመልካቹ በውለ መሰረት ሉወጡት የሚገባ ግዳታ ሙለ በሙለ ተዋጥተዋል ማለት አይቻልም።
በውል የተመለከተ ግዳታቸው ሣይወጡ ደግሞ የቀሪ ገንዘብ ክፍያና የመኪናው ስም መዛወር ጥያቄ ማንሣታቸው አግባብነት የለውም፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1757 እንደደነገገውም ውለ እንዱፈፀምለት የሚጠይቀው ወገን በውለ መሰረት አስቀድሞ ሉወጣው የሚገባ ግዳታ ከተወጣ በኋላ መሆን እንዲለበት ነው። ስለሆነም የስር ፍ/ቤቱ አመልካቹ የመኪናው ካምቢዮን የማስተካከል ግዳታቸውን ሣይወጡ የቀሪ ገንዘብ ክፍያ ጥያቄ ማንሣት አይችለም በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው።
በልላ በኩል የስር ፍ/ቤቱ ከላይ ከተቀመጠው ማጠቃለያ ማለትም አመልካቹ በውለ መሰረት አስቀድሞ ሉወጣው የሚገባ ግዳታ ሣይፈጽም ክስ ማቅረብ አይችልም ከሚለው ውሣኔ አልፍ ላልች በአመልካቹ መብት ላይ ያስተላለፊቸው ውሣኔዎች ማለትም ተጠሪው ያቀረቡት ክስ ሣይኖር ለአመልካቹ የከፈለት ተጨማሪ ገንዘብ ብር 1ዐ,416 /አስር ሺህ አራት መቶ አስራ ስድስት/ አለ ብል ማረጋገጡና ላልች ተጨማሪ ነጥቦችን መተንተኑ ከክርክር ሂደት አኳያ ሲታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል፤ አመልካቹ ግዳታውን ሣይወጣ ክስ ማቅረብ አይችልም ተብል ተጠቃልል እያለ ፍ/ቤቱ ከዚህ አልፍ ወደ ሂሣብ ስራ ገብቶ ውሣኔ መስጠቱ ተገቢነት የለውም፤ ስለሆነም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ 1/ በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.17ዐ74፣ ግንቦት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እንዱሁም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ.ቁ. 6833/ ሰኔ 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽለዋል፤ ይፃፍ።
2/ አመልካቹ በመኪና ሽያጭ ውለ የተመለከተውን ግዳታቸው ሣይወጡ ቀሪ ገንዘብ ተጠሪው ይስጠኝ በማለት ክስ ሉያቀርቡ አይችለም።
3/ ተጠሪው ክስ ሣያቀርቡ አመልካቹ ባቀረቡት ክስ ተጠሪው ለአመልካች ከመኪናው ሽያጭ ብር 1ዐ,416 /አስር ሺህ አራት መቶ አስራ ስድስት ብር/ ከፍለዋል የተባለውና ላልች ትችቶች የክርክር አካሄድ ስርዓት የተከተለ ውሣኔ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም፣ 4/ ታህሣሥ ዐ3/2ዐዐ1 ዓ.ም የተላለፈው እግድ ተነስቷል። ይፃፍ።
5/ ግራ ቀኙ ወገኖች በዚህ ፍ/ቤት ላካሄደት ክርክር ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ፤ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።