No summary available.
ጥር 28 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ያለው ድልነሳው - ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአንደኛ ተጠሪ ከሳሽነትና ከሁለት እስከ አራተኛ በተጠቀሱት ተጠሪዎች ተከሳሽነት የነበረውን ክርክር መርምሮ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/358 መሰረት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥም ባጭሩ ሲታይ አንደኛ ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሁለት እስከ አራተኛ በተጠቀሱት ተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በአዱስ አበባ ከተማ ወረዲ 22 ቀበላ 04 ክልል በቤት ቁጥር 596 ተመዝግቦ የሚገኘውን የንግድ ቤት መንግሥት ስለ ንግድ ቤቶች መግለጫ ካወጣም በኋላ በስሜ ውል ተዋውዬ ባለሁበት ሁኔታ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ከአራተኛ ተጠሪ ጋር በውል ላይ ውል በማድረግ የንግድ ቤቱን አሳልፈው የሰጡ ስለሆነ የተፈጠረው ሁከት ይወገድልኝ በማለት ክስ አቅርበው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ከሳሽ ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ የመንግሥት መመሪያ ከወጣ በኋላ በስማቸው ተከራይተው በይዞታቸውም ሥር አድርገው በንግድ ቤቱ ሲጠቀሙበት የነበረ ስለሆነና ተከሳሾች መመሪያው ከወጣ በኋላ ከከሳሽ ጋር የተደረው ውል በስህተት እንደተደረገ ከማንሳት ውጭ ውለ የጸና ላሆን እንደማይችል ያቀረቡት ክርክርም ሆነ ማስረጃ ስለላለ በዚህ ሁኔታ በተከሳሾች የተፈጸመው ድርጊት በሕግ የተፈቀደ መብትን ተከትል የተፈጸመ ባለመሆኑ አድራጎቱ ከሁከት ስለሚፈረጅ ባለይዞታ ለሆኑት ለከሳሽ ቤቱ ሉመለስላቸው ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላም የአሁን አመልካች በወረዲ 22 ቀበላ 04 ክልል በቤት ቁጥር 596 የተመዘገበውን የንግድ መደብር የካቲት 16 ቀን 1992 ዓ.ም በንግድ ቤቱ ላይ እዲና እገዲ እንደላለበት አጣርቼ ውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በመቅረብ ከሦስተኛ ተከሳሽ /ከአሁን ሦስተኛ ተጠሪ/ ላይ ገዝቼ ሽያጩም ሕጋዊ መሆኑ በቀበላው አስተዲደር በኩል ታምኖበት የኪራይ ውለ በስሜ ተዛውሮ ኪራይ የምከፍል ከመሆኑም በላይ የንግድ ፈቃድም አውጥቼ በመስራት ላይ እንዲለሁ የንግድ ቤቱን አስቀድሞ በተሰጠ ፍርድ መነሻነት ለከሳሽ ለአሁን አንደኛ ተጠሪ እንዲስረክብ የተገደድኩ ስለሆነ ይሄው ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/360(2) መሰረት ይሰረዝልኝ በማለት አመልክተው ፍ/ቤቱም ከሳሽና ተከሳሾች የነበሩት በመጥራት ካከራከረ በኋ በቀድሞው ውሳኔ ክርክር ያስነሳው የንግድ ቤት የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ስለ ንግድ ቤቶች መግለጫ ከማውጣቱ በፉትም ሆነ በኋላ ከአንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች ተከራይተው ይጠቀሙበት እንደነበርና ይዞታቸው እንደሆነ የተረጋገጠ ከመሆኑም ላላ ከሳሽ መመሪያው ከወጣ በኋላ ከአንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች ጋር ያደረጉት ውል ፈራሽ ነው ሳይባል ከሦስተኛ ተከሳሽ ጋር ያደረጉት ውል መብትና ግዳታን ሉያቋቁም እንደማይችል ስለተወሰነና ከዚህም ውሳኔ ሦስተኛ ተከሳሽ አንዲችም መብት እንደላላቸው መገንዘብ ስለሚቻል የመቃወም አመልካችም የንግድ ቤቱን ገዛሁ የሚለት መብት ከላላቸው ከሦስተኛ ተከሳሽ ላይ ስለሆነ በዚህ ሁኔታ የቀድሞው ውሳኔ ይሰረዝልኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ተገቢነት የለውም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል። ይሄው ውሳኔም የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ ጉድለት የለውም ተብል እስከ አዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ድረስ እንደፀና ከመዝገቡ ተረድተናል።
ለዚህ ችልት የቀረበውም የሰበር አቤቱታ ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ችልቱም አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ በየደረጃው የሚገኙ የሥር ፍ/ቤቶች ሳይቀበለ የቀሩበት ምክንያት ተጠሪዎች ባለበት ተጣርቶ ሉወሰን እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን በጽሁፍ አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን የዚህን ችልት ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዲዩ ጭብጥ፡አመልካች ባቀረቡት መቃወሚያ መነሻነት አስቀድሞ የተሰጠው ፍርድ ሉሰረዝ ይገባል ወይንስ አይገባም?
የሚለው ነው። ከዚሁ ጭብጥ አኳያም የሰበር አቤቱታው እንደሚከተለው ተመርምሯል።
No topics extracted.
አንድ ፍርድ በአንድ ፍ/ቤት ከተሰጠ በኋላ ይሄው ፍርድ በዚያው ፍ/ቤት በድጋሚ ከሚታይባቸው ሥርዓቶች መካከል አንደ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/358 መሰረት መቃወሚያ በሚቀርብበት ጊዜ ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረትም በክርክሩ ውስጥ ተካፊይ መሆን የሚገባው ወይም በክርክሩ ውስጥ ለመግባት የሚችልና እንደዚሁም ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካበት ማንኛም ሰው ተካፊይ ባልሆነበት የተሰጠው ፍርድ ከመፈጸሙ በፉት መቃወሚያውን ማቅረብ እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዲይ አስቀድሞ ፍርድ ያረፈበትንና ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን በአዱስ አበባ ከተማ ወረዲ 22 ቀበላ 04 ክልል በቤት ቁጥር 596 ተመዝግቦ የሚገኘውን የንግድ ቤት አመልካች በስማቸው የንግድ ፈቃድ አውጥተው ሲሰሩበት ከነበረው የሥር ሦስተኛ ተከሳሽ የአሁን አራተኛ ተጠሪ ላይ