No summary available.
ጥር 07 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው በአመልካቾችና በሁለተኛና ሦስተኛ ተጠሪዎች መካከል ግንቦት 04 ቀን 1997 ዓ.ም የተደረገው የንግድ ድርጅት እና የንግድ ድርጅት ህንፃ ሽያጭ ውል በህግ መሰረት የተፈፀመ ውል አይደለም ተብል በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በመወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አመልካቾች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ በተጀመረበት በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሣሾች የነበሩት የአሁኑ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ሲሆኑ ህዲር 26 ቀን 1998 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአዱስ አበባ ከተማ ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቀድሞው በቀበላ 08 የሚገኘውን በሁለተኛ ተጠሪ ባለቤት እና በሦስተኛ ተጠሪ አባትና አውራሽ በሆኑት በሟች አቶ ከበደ ዘለቀ ስም በካርታ ተመዝግቦ የሚታወቀውንና በ2825 ካ.ሜ. ቦታ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን ሴንትራል ቬንዩ ሆቴል ከእነ መገልገያ ዔቃዎቹ ጭምር በ04/09/1997 በተፃፈ የሽያጭ ውል ከነመልካም ስሙ በንብረቶቹ ላይ ካለት የኢትዮጵያ ልማት ባንክና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ዔዲዎች፣ የሆቴለ ሰራተኞች ክፍያ እና የሆቴለ የአገር ውስጥ ገቢ የግብር ዔዲዎችን ገዥዎች ሸፍነው ከእዲዎቹ ውጪ በብር 1,000.000.00 /አንድ ሚሉዮን ብር/ ከሳሾች ለተከሳሽ መሸጣቸውን፣ ውለ በተደረገ ዔለት ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ቀብድ መቀበላቸውን ቀሪውን ስመሃብቱ ሲዛወር ተከሳሽ ለመክፈል ግዳታ ውስጥ ገብተው ሆቴለን ከመገልገያዎቹ ዔቃዎች ጭምር መረከባቸውን፣ ተከሳሹ የሆቴለን ሥመሃብት ለማዛወር የሚረደትን በውለ የተጠቀሱትን ግዳታዎችን ለመፈፀም ፈቃደኛ ባለመሆን ቀሪ ክፍያም ሳይከፍለ መቅረታቸውንና ለዚህም ህዲር 23 ቀን 1998 ዓ.ም ተከሳሽ ግዳታቸውን ለመፈፀም ፈቃደኛ ባለመሆን ምክንያት ውለ ፈራሽ እንደሚሆንና ከሳሾች መብታቸውን በህግ አግባብ ለማስከበር የሚገደደ መሆኑን ገልፀው የመጨረሻ የጽሐፍ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን፣ ተከሳሹ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግዳታቸውን ባለመፈፀማቸው ውለ መፍረሱንና ጠበቃ ጥላሁን ደስታ ቀረቡ ክስ ማቅረባቸውን ዘርዝረው ተከሳሽ በውለ ምክንያት የተረከቡትን ሆቴል ከእነ መገልገያ ዔቃዎቹ ለከሳሾች እንዱያስረክቡ፣ በውለ የተመለከተውን የገደብ መቀጫ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እንዱከፍለ፣ በሆቴለ ድርጅት መልካም ስምና ዝና ለደረሰው ጉዲትና ለተገኘው ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ወደፉት ክስ የማቅረብ መብታቸው እንዱጠበቅና በክሱ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ አንደኛ አመልካች ላይ ክስ መስርተዋል። ክስና ማስረጃ ለአንደኛ አመልካች ደርሶም በ24/04/1998 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመከላከያ መልሱን አቅርበዋል። በመከላከያ መልሳቸውም የሽያጭ ውለ መደረጉ እውነት ሆኖ ተከሳሹ በውለ በገቡት ግዳታ መሰረት የልማት ባንኩን ዔዲ ከፍለው ንብረቱን ከልማት ባንክ መረከባቸውን፣ ለላልች ዔዲዎችም ከብር 800,000.00 /ስምንት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከፍለው ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ መቅረቱን፣ ላልች እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ያልቻለትም ጉዲዩን ለማስፈፀም የተሰጣቸውን ውክልና በከሳሾች በመሻሩ ምክንያት ሆኖ ከዚህ በኋላም ከሣሾች እንደውለ ለመፈፀም ምንም ዓይነት ጥረት አለማድረጋቸውንና ላልች ምክንያቶችን በመዘርዘር ለውለ አለመፈፀም ምክንያት ከሳሾች መሆናቸውን በመጥቀስ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበዋል። በዚህ ክሳቸውም በውለ መሰረት የባንክ ዔዲዎችንና ቅድሚያ ክፍያ ጨምሮ ብር 7,470,541.10(ሰባት መቶ ሺህ አራት መቶ ሰባ ሺህ አምስት መቶ አርባ አንድ ብር ከአስር ሳንቲም) ክፍያ ፈጽመው ድርጅቱንና ህንፃውን በመረከብ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሆነ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ስራ እንዱጀምር ማድረጋቸውን፣ ቀሪውን የሽያጭ ገንዘብ ስመሃብቱ ሲዛወር ለመክፈል በውለ መስማማታቸውንና የውለን ግዳታ የከሳሽ ተከሳሾች እንዱፈጽሙ ቢነገራቸውም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመዘርዘር በውለ ግዳታ የከሳሽ ተከሳሾች እንዱፈጽሙ ቢነገራቸውም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመዘርዘር በውለ ግዳታ መሰረት ተከሳሾች ለንግድ ድርጅቱና ለህንፃው ስመ ሀብት መዛወር አስፈላጊ የሆኑትን ማንኛውንም ፍርማሉቲዎች እንዱፈጽሙና በእጃቸው የሚገኘውን ማንኛውንም ሰነድች ለተከሳሽ ከሳሽ እንዱያስረክቡ፣ ውለ በግድ እንዱፈፀምና ወጪና ኪሣራም ይከፈላቸው ዘንድ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። የከሳሽ ተከሳሾችም ጥር 24 ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የተከሳሽ ከሳሽ ክስ ተቀባይነት የለውም የሚለባቸውን የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ምክንያቶችን ዘርዝረው ተከራክረዋል።
ከዚህም በኋላ የአሁኗ አራተኛ ተጠሪ የጣልቃ ገብነት አቤቱታ አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ ለሽያጭ መሰረት የሆነው ሆቴል ያልተከፊፈለ የውርስ ሀብት በመሆኑና በንብረቱ ላይ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ፣ ውለ በተንኯል የተደረገና የሦስትኛ ወገንን መብት የነካ በመሆኑ ፈራሽ ላሆን የሚገባው ህገ-ወጥ ውል ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። በዚህ የጣልቃገብ አቤቱታም አንደኛ አመልካችም ሆነ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጏ አለን ያለትን መልስ ሰጥተዋል። በልላ በኩል የአሁኑ ሁለተኛ አመልካች መጋቢት 13 ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ የጣልቃገብነት አቤቱታ ግንቦት 04 ቀን 1997 ዓ.ም የተደረገው የንግድ ድርጅትና የንግድ ድርጅቱ ህንፃ ሽያጭ ውል የተፈረመው የአበዲሪ ባንኮችንና የፊይናንስ ተቋማትን ፍላጏት ለማሟላትና ለማመቻቸት ሲባል ሆኖ ጣልቃገብ ሁለተኛ ገዥነት መዋዋለን፣ የአሁኑን አመልካች ዔዲም ጣልቃገብ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ባገኘው የብር 6,400,000.00 /ስድስት ሚሉዮን አራት መቶ ሺህ ብር/ መክፈለን፣የሆቴለን ህንፃ እና ጠቅላላ ድርጅቱንም ሐምል 01 ቀን 1997 ዓ.ም በተፈረመ የመያዣ ውል ለአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ በመያዣነት መስጠቱን፣ በጣልቃገብ ስም በወጣ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ስያሜም ሆቴለ ንግደ እየተመራና እየተካሄደ የሚገኝ መሆኑን፣ በገዥዎች በኩል የውል ግዳታ ተጥሷል በሚል የቀረበው ምክንያትም የማይገባ መሆኑን በመዘርዘር የሽያጭ ውለን ለማፍረስ የሚያበቃ የፍሬ ነገርም ሆነ የህግ ምክንያት የለም ከማለቱም በተጨማሪ ውለ ይፈርሳል ቢባል እንኳ ገዥዎች ወደ ነበሩበት ቦታ ለመመለስ የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን በመጥቀስ የውለ ቃል ተግባራዊ ይሆን ዘንድ እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቋል። በዚህ የጣልቃገብ አቤቱታም ከሣሾች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጏ ጣልቃገቡ የዲኝነት ሳይከፍለ የሚስተናገድበት ምክንያት አለመኖሩን፣ ጉዲዩም የአሁኑ አንደኛ አመልካች የተከሳሽ ከሣሽነት ክስ ሲያቀርቡ ሳይቀርብ ቀርቶ በኋላ መቅረቡ ሥነ-ሥርዓቱን የጠበቀ አለመሆኑን፣ አንድ ድርጅት በአንድ ቀን ለተለያዩ ግለሰቦች ሉሸጥ የማይችል መሆኑንና በጣልቃገብ በኩል የቀረበው የውል ሰነድም በስህተት የተፈረመ በመሆኑ በህግ ፉት ሉፀና እንደማይገባ በመግለጽ ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ቀደም ሲል ይዞት የነበረውን ጭብጥ በማሻሻል ተገቢ ነው ያለውን ጭብጥ ከያዘ በኋላ አግባብነት አላቸው ያላቸውን የውርስ እና የሽያጭ ህግ ድንጋጌዎችን በመጥቀስ የሽያጭ ውለ ህጋዊ የሚባልበት ምክንያት የለም በሚል ምክንያት የሽያጭ ውለን ፈራሽ ነው ብል ከደመደመ በኋላ የአሁኑ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ብር 513,012.20 /አምስት መቶ አስራ ሦስት ሺህ አስራ ሁለት ብር ከሃያ ሳንቲም/ ለአሁኑ አንደኛ አመልካች እንዱከፍለ አንደኛ አመልካችም የተረከቡትን የድርጅት ቤት ለሻጮች መልሰው እንዱያስረክቡ እና የአሁኑ ሁለተኛ አመልካች በሽያጭ ውለ ምክንያት ለሻጮች ከፈልኩ የሚለውን በተመለከተ ደግሞ ዲኝነት ከፍል የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀለት መሆኑን በመግለጽ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ይኸው ይግባኝ ሰሚው ችልት የህንፃው ሽያጭ ውል በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውለ ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ያልተደረገ በመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ሉያሟላ የሚችል አለመሆኑንና በዚህ ረገድ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
ስለ ፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1723 ድንጋጌ የሰጠውን ትርጓሜ በመጥቀስ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔን በውጤት ደረጃ የተቀበለው መሆኑን ገልጾ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ ሐምል 30 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረዋል። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተጠሪዎች ጠበቃ መጋቢት 25 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ አራተኛ ተጠሪም በተመሳሳይ ቀን ለብቻቸው በፃፈት ማመልከቻ መልሳቸውን አቅርበዋል። በተጠሪዎች መልስ ላይም የአመልካቾች ጠበቃ የመልስ መልሳቸውን አቅርበዋል። ከዚህም በኋላ ግራ ቀኙ በቃል እንዱከራከሩ ተደርጏ ህዲር 25 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት ክርክራቸው ተደምጧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍና የቃል ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ጥያቄ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍ/ቤት ተገቢነት ያለውን ጭብጥ በመያዝ አግባብነት ያለውን ዲኝነት ሰጥቷል ወይስ አልሰጠም? የሚለው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው የሆቴል ድርጅትና ህንፃው የሟች የአቶ ከበደ ዘለቀ እና የአሁኑ ሦስተኛ ተጠሪ የጋብቻ የጋራ ሀብት መሆኑን፣ ይህንኑ የሆቴል ድርጅት እና ህንፃ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች የጋራ ባለሃብት ነን በማለት ግንቦት 04 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ የሽያጭ ውል ለአመልካቾች የሸጡላቸው መሆኑን ነው። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ውለ መደረጉን አምነው ለፍ/ቤቱ ክስ መመስረት የቻለት አንደኛ አመልካች በሽያጭ ውለ የተቀመጠውን ግዳታቸውን ባለመወጣታቸው ተገቢውን ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ውለን በግላችን ስለሰረዝን ድርጅቱን አንደኛ አመልካች መልሰው ያስረክቡን በሚል ምክንያት መሆኑንም ተረድተናል። እንዱሁም አንደኛ አመልካች በስር ተከሳሽነታቸው የሰጡት መልስ የውለን መኖር አምነው በውለ ለተቀመጡት ግዳታዎች አለመፈፀም ምክንያት የሆኑት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች መሆናቸውን በመዘርዘር ውለ የሚሰረዝበት የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ምክንያት የለም ሲለ የሚከራከሩ መሆኑን ተገንዝበናል። የአሁኗ አራተኛ ተጠሪ ክርክር መሰረት ያደረገውም ለሽያጭ መሰረት የሆነው የሆቴል ድርጅት የሟች አባታቸው ያልተከፊፈለ የውርስ ንብረት ሆኖ እያለ ሽያጩ በሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች መከናወኑ መብቴን ስለሚነካ ውለ ሉፈርስ ይገባል በሚል ነው። የአሁኑ ሁለተኛ አመልካች ክርክር ደግሞ ለክርክሩ መሰረት የሆነው የሆቴል ድርጅት ከሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ከአንደኛ አመልካች ጋር በጋራ የገዛው የአበዲሪ ባንኮችንና የፊይናንስ ተቋማትን ፍላጏት ለማሟላትና ለማመቻቸት ሲባል መሆኑን፣ አንደኛ አመልካች በውለ መሰረት በገባው ግዳታም ለሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ዔዲ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ተበድሮ ብር 6,400,000.00 /ስድስት ሚሉዮን አራት መቶ ሺህ ብር መክፈለንና በራሱ የንግድ ስያሜም የንግድ ሥራውን እየሰራ እንደሚገኝ እንዱሁም ለፊይናንስ ተቋማትና ላልች የሻጭ ዔዲዎችን እና ሆቴለን በዘመናዊ ሁኔታ ለማደራጅት በድምሩ ብር 11,285,889.00 /አስራ አንድ ሚሉዮን ሁለት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር/ ወጪ ማድረጉን ገልጾ ውለ የሚሰረዝበት አግባብ የለም የሚል ነው።
እንግዱህ የግራ ቀኙ ክርክርና የዲኝነት ጥያቄ የሚያሳየው ግንቦት 04 ቀን 1997 ዓ.ም የተደረገው የሆቴል ድርጅት እና ህንፃ ሽያጭ ውል መኖሩ ታምኖ በውለ በተመለከተው አኳኋን ግዳታውን ያልተወጣው የትኛው ወገን ነው በሚል አመልካቾችና ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች የሚከራከሩ መሆኑን፣ አራተኛ ተጠሪ ደግሞ ሽያጩ ባልተከፊፈለ የውርስ ንብረት ላይ የተፈፀመ ስለሆነ ሉፈርስ ይገባል የሚለ መሆኑን ነው ከዚህ የክርክር ይዘት የምንገነዘበው ደግሞ በፍ/ቤቱ በጭብጥነት ተይዞ ውሣኔ ሉያገኝ የሚገባው ነጥብ ምን እንደሆነ ነው። ይህ ደግሞ ምላሽ የሚያገኘው የፍትሐብሕር ሙግቶች የሚመሩበትን የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ህግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ነው። በመሆኑም የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ህግ አንቀጽ 248 የሚያሳያው ጭብጥ የሚያዘው ከሣሽና ተከሳሽ በሥርዓቱ መሰረት የሚያቀርቡት የክስ ማመልከቻና የመከላከያ መልስ፣ ከአባሪ ሰነድችና በቁጥር 241 መሰረት ከተደረገው ምርመራ የተገኘውን የተከራካሪ ወገኖች ቃል መሰረት በማድርግ መሆኑን ነው።
በያዝነው ጉዲይም የተከራካሪ ወገኖች የክርክር ሂደት ሉያዝ እና በፍ/ቤት ሉወሰን የሚገባው ጭብጥ ምን እንደሆነ ያሳያል። ይኸውም የስር ከሣሶች ጥያቄ ግንቦት 04 ቀን 1997 የተደረገው የሽያጭ ውል ይፍረስልን ሳይሆን ውለ በግላችን ስለተሰረዘ ድርጅቱን ገዢ ያስረክበን የሚል ነው። ገዢዎች ውለ ሉሰረዝ አይገባም የሚለትን ምክንያት ዘርዝረዋል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ዲኝነት የሰጠው ውለ ፈራሽ ነው በሚል ምክንያት ነው።
በመሰረቱ ውል ማፍረስና ውል መሰረዝ በውል የተቋቋሙት ግዳታዎች ከሚቀሩባቸው መንገድች ውስጥ የሚካተቱ ቢሆንም ምክንያታቸውና ውጤታቸው የተለያዩ መሆኑን በዚህ ረገድ የተደነገጉት የውል ማፍረስ ከውል አመሰራረት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን ሲሆነ ውለ ከአመሰራረቱ በህጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባለማሟላቱ ግድፈት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው። በልላ በኩል የውል መሰረዝ ጉዲይ ከውል አመሰራረት ችግር የሚነሳ ሳይሆን ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዳታውን ካለመወጣት የሚመነጭ ነው። በልላ አገላለጽ ውል የሚሰረዘው ከመሰረቱ ግድፈት ስላለው አይደለም። ይልቁንም የውል መሰረዝ ምክንያት ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዳታን ከመፈፀምና ካለመፈፀም ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው። የውል መሰረዝ ሥርዓትም የራሱ የሆነ አካሄድ አለው። ይኸውም ውለን የመሰረዝ ፍላጏት ያለውን ወገን የውለ ግዳታ ባለመፈፀሙ የተነሳ ከህግ ወይም ከውለ ከራሱ ባገኘው መብት ተጠቅሞ ውለን ሉሰርዝ ይችላል።
ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆንበት አጋጣሚም ግዳታው ባለመፈፀሙ የተነሳ የደረሰውን ጉዲት ከማረጋገጥ ጋር ተያይዞ የሚታይ እንጂ ጥያቄ አቅራቢው ሁል ጊዜ ተቀባይነት የሚያገኝበት አይደለም። በመሆኑም የውል ይሰረዝልኝና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች በህጉ አግባብ የሚስተናገደ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1784 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። በተያዘው ጉዲይም የስር ከሳሾች ጥያቄ ውል ይሰረዝልኝንና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች በሚስተናገደበት የፍትሐብሕር ህግ ክፍል ምላሽ ማግኘት ሲገባ በህጉ አግባብ የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ ባልቀረበበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በራሱ ተነሳሽነት በፍ/ብ/ህ/ቁ 1723 ስር የተመለከተውን የፍርማሉቲ ጥያቄ በማንሳት ጉዲዩን መወሰኑ የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በመሰረቱ ፍ/ቤቱ በተከራካሪ ወገኖች የተጠየቀውን ዲኝነት በመተውና በተከራካሪ ወገኖች ያልተነሳለትን የፍርማሉቲ ጥያቄ በራሱ ጊዜ በማንሳት ውሣኔ እንዱሰጥ የሚያስችል የህግ አካሄድ የለም ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቤቱታ በቀረበበት ጉዲይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ የውል ይሰረዝልን፤
ሰርዘናል የክርክር ጭብጥ መሰረት አድርጏ የተሰጠ መሆን ያለመሆኑን በመመርመር ዲኝነት መስጠት ሲገባው የፍርማሉቲ ጥያቄን በማንሳት እና ምክንያቱን በመለወጥ ውጤቱን ማጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የክርክሩን ጭብጥ የውል ይሰረዝ፤ ሰርዘናል አኳያ አለመመልከቱን ከላይ ገልፀናል።
እንዱህ ከሆነ ይኸው ይግባኝ ሰሚው ችልት ከተገቢው ጭብጥ አኳያ እንዱመለከትና ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት በማድረግ ጉዲዩን መመለሱ ሥነ ሥርዓታዊ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም፡- 1ኛ/ የስር ከሣሽ የነበሩት የአሁኑ ሁለተኛ እና ሦስትኛ ተጠሪዎች ውለን ሰርዘናል ማለታቸው ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም?
2ኛ. የውለ መሰረዝ ጥያቄ በፍ/ቤት ሉወሰን የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
3ኛ. የአሁኗ አራተኛ ተጠሪ ውለን የመሰረዝ ጥያቄ ማቅረብ ይችላለ? ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ንብረት መብት አላቸው? መብት አላቸው ከተባለስ መብታቸው በምን መንገድ መከበር አለበት? በሚለትና ላልች አስፈላጊ ናቸው ባላቸው ከውል መሰረዝ ጥያቄ ጋር ሉያያዙ የሚችለትን ተጨማሪ ነጥቦችን በመመልከት ተገቢውን ውሣኔ ላሰጥበት የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ. 27497 ሐምል 26 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፍትሐብሕር ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔው የተሻረ መሆኑን አውቆ ከላይ ከተመለከቱት ጭብጦች አኳያ ጉዳዩን እንደገና በመመልከት ተገቢውን ይወስን ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343/1/ መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
No topics extracted.