No summary available.
ታህሳስ 28 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ሐጅራ አብሮ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሐሺም ሐጂ አሉዬ - ቀረቡ
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በምስ/ሐረ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው።
ተጠሪ በዚህ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአወዲይ ከተማ የሰሩትን ቤት ለአባታቸው ትተው ከሄደ በኋላ አባታቸው ሲሞቱ አመልካች ቤቱን ይዘው ያለ ስለሆነ እንዱለቁላቸው ጠይቀዋል። አመልካች ደግሞ ቤት የተሰራበትን ቦታ ባለቤታቸው ከአቶ ዮሴፍ ኡመር ከተባለ ሰው ወስደው በ1969 ዓ.ም ቤቱን የሰሩ በመሆኑ ከ38 አመት በኋላ ሉጠይቋቸው እንደማይችለ በመግለጽ ተከራክረዋል። ቤቱን ከረጅም ጊዜ በፉት የአመልካች ባለቤት ከአመልካች ጋር አብረው ሲኖሩ የሰሩት መሆኑን የግራ ቀኙ ምስክሮች አረጋግጠዋል በማለት ፍ/ቤቱ የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጏታል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኙን ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም ክርክር የተነሣበት ቤት በከሣሽ(ተጠሪ) ስም የተመዘገ በመሆኑ አመልካች ቤቱን ለተጠሪ ይልቀቁ ሲል ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሣኔ ላይ አመልካች ለክልለ ሰበር ሰሚ አቤቱታ አቅርበው አቤቱታቸው ተቀባይነት ሣያገኝ ቀርቷል።
አመልካችም ይህ ውሣኔ የሕግ ስህተት አለበት በማለት እንዱታረምላቸው አቤቱታ ለሰበር ችልት አቅርበዋል።
ይህ ችልትም ተጠሪ የይርጋ ጥያቄ አንስተዋል ወይ? ካነሱ በየፍ/ቤቶቹ ሣይታይ መታለፈ አግባብ ነው ወይ? ተጠሪስ ያቀረቡት ማስረጃ ባለቤትነትን ለማስረዲት ላቀርብ የሚችል ነው ወይ? የሚለትን ነጥቦች ለማጣራት አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። ተጠሪም ቀርበው ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተባለው ተጠሪ በአወዲይ ከተማ ቤት ሰርተው ለአባታቸው ሰጥተው መሄዲቸውን ገልፀው አባታቸው በ1978 ዓ.ም ሲሞቱ አመልካች ቤቱን ይዘው መቆየታቸውንና ቤቱንም ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላለሆኑ እንዱለቁላቸው ክስ መስርተዋል። አመልካችም ቤቱን ባለቤታቸው በ1969 ዓ.ም የሰሩት መሆኑን ገልፀው ቤቱን ለ38 አመታት ይዘው እይኖሩበት በመሆኑ ተጠሪ አሁን ሉጠይቋቸው እንደማይገባ ተከራክረዋል። አመልካች በዚህ ክርክራቸው በግልጽ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት አይግለፁ እንጂ ቤቱን ለ38 አመታት ይዘው እየኖሩበት በመሆኑ አሁን ክስ ላቀርብባቸው የማይችል መሆኑን መግለፃቸው ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት መከራክራቸውን ያመለክታል። አመልካች ቤቱን ለ38 አመታት ይዘው በመቆየታቸው የገለፁትን ፍሬ ነገር ተጠሪ አላስተባበለም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች ወደ ፍሬ ጉዲዩ ከመግባታቸው በፉት በአመልካች በኩል የቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ መርምረው ተገቢውን ውሣኔ ሉሰጡ ይገባ ነበር የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 244/1/ ይመለከቷል።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ቤቱን ለአባታቸው ትቼው ሄጃለሁ የሚለት በ1969 ዓ.ም ነው። አባታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት በ1978 ዓ.ም ነው። በመሆኑም ተጠሪ ቤቱን ለአባቴ ሰጥቼ ሄጃለሁ ካለበት ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ ክስ እስከተመሰረተበት እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ 27 ዓመት ያለፈው ነው። ተጠሪ ቤቱን ለአባታቸው በአደራ ሰጥተው ለመሄዲቸው በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር የለም። ነገር ግን ይህ ተረጋግጧል ቢባል እንኳን አባታቸው በ1978 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ አንስቶ ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ 17 አመታት አልፊል። በመሆኑም ተጠሪ ቤታቸው ያለአግባብ በልላ ሰው ተይዟል በማለት ክስ ማቅረብ የሚችለት እስከመቼ ነው? የሚለው ነጥብ መታየት ይኖርበታል።
በመሰረቱ ጉዲዩን በቀጥታ የሚመለከት በህግ ተለይቶ የተቀመጠ የይርጋ ድንጋጌ በላለ ጊዜ ተፈፃሚነት የሚኖረው የጠቅላላ ውል ህግ ድንጋጌ ነው። ምክንያቱም ምንም እንኳን ግንኙነቱ ከውል የመነጨ ባይሆንም ስለውልች በጠቅላላው የተነገሩት ድንጋጌዎች እንደሚፈጸሙባቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1677/1/ ያመለክታል። በዚህም መሰረት አንድ ሰው መብቱን መጠየቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ በ10 አመት ውስጥ ካልጠየቀ መብቱ በይርጋ ቀሪ መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 ይገልፃል።
በተያዘው ጉዲይም ተጠሪ ቤቱ ያለአግባብ በአመልካች ተይዟል ካለበት ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ 17 አመታት ያለፈ በመሆኑ የተጠሪ መብት በይርጋ ቀሪ ሆኗል። አመልካች ከስር ጀምሮ ቤቱን ለብዙ ዓመታት ይዘው እየተጠቀሙ የቆዩ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ እንደሚገባ ተከራክረው እያለ ፍ/ቤቶቹ ይህንን የአመልካችን የይርጋ ክርክር ሣያስተናግደ በማለፍ በፍሬ ጉዲዩ ላይ ውሣኔ መስጠታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን ያመለክታል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 39769 በ29/02/2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በ/ በ20/3/2000 የሰጠው ትእዛዝ በተጨማሪ በምስ/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 01899 በ08/07/98 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች ቤት ለመረከብ ያቀረቡት ጥያቄ /ክስ/ በይርጋ ቀሪ ሆኗል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል። ለመ/ቤት ይመለስ።